- አቶ ጁነዲን ሳዶ በእናታቸው ግቢ በአርሲ ሁሩታ አርብ ገበያ አካባቢ መስኪድ እያሰሩ ነበር

በተገኝው መረጃ መሰረት አቶ ጁነዲን በእናታቸው ቃል መሠረት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ መስጅድ ለማስገንባት፣በሚኒስትርነታቸው ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ለመስጅዱ ማስጨረሻ ከሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ ዕርዳታበመጠየቃቸው፣ የመስጅዱ የመጀመሪያ ደረጃ ምርቃት ሲደረግ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ተገኝተው500 ቅዱስ ቁርአንና 50 ሺሕ ብር ዕርዳታ መስጠታቸውን ራሳቸው አቶ ጁነዲን በጻፉት ደብዳቤ መንግስት ሊያረጋግጥ ችሏል፡፡
ከሳምንታት በፊት የአቶ ጁነዲን ባለቤት ከአንድ የአረብ ኢምባሲ በሚገቡበት ወቅት የፌደራል ፖሊስ ልዩ ኃይል ከመግቢያው በር ላይ ተበታትነው ይጠብቋው ነበር ፤ እኝህ ወ/ሮ ኢምባሲው ውስጥ ገብተው ሲወጡ በእጃቸው የተገኝው ነገር ቢኖር በርካታ የእስልምና እምነት መጽሐፍቶች ፤ በ50 ሺህ ብር እና መሰል ለሌላ አላማ የሚጠቀሙባቸው ሰነዶች ይዘው ሲወጡ በፌደራል ፖሊስ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፤ባለቤታቸው አምባሳደሩ የሰጡትን 50 ሺሕ ብር ለመቀበል ኤምባሲ ሄደው ተቀብለው ሲወጡ፣ ለሽብር ተግባርየሚውል ገንዘብ ተቀብለዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው እና ወደ እስር መውረዳቸውይታወሳል፡፡ አቶ ጁነዲን የሚስታቸውን መታሰር በማስመልከት የተቀበሉት ብር እናት አባቶቻው መንደር ለሚሰራው መስኪድ ማስጨረሻ መሆኑን በግልጽ ተናግረዋል ፤ ይህ ማለት አቶ ጁነዲንን እና መሰል በስልጣን ላይ የተቀመጡ መንግሥትና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነታቸውን መወጣት ያቃታቸው ባለስልጣናት በእንደዚህ አይነት ተግባር ላይ ለመሰማራታቸው አብይ ምሳሌ ሆኖ ተመልክተናል ፤ ይህ መስኪድ በእምነቱ ሰዎች ቢሰራ ማንም ምንም ላይመስለው ይችል ይሆናል ፤ ነገር ግን ህዝብን እንዲያገለግል በመንግስትና በህዝብ የተመረጠ ባለስልጣን አማካኝነት መሰራት መቻል ግን አግባብ አይደለም ፤ አሁንም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ስልጣናቸውን ተገን አድርገው ይህን መሰል ስራ የሚሰሩ ባለስልጣናት እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡
መንግስት አክራሪነትን እዋጋለሁ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የማይመለከታቸውን ማኅበራት ላይ እጁን ከሚጠቁምና የውሃ ወቀጣ ስራ ከሚሰራ ይልቅ ውስጡን ከእደነዚህ አይነት መሰሪ ሰዎች ቢያጸዳ መልካም ይመስለናል ፤የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ከመስከረም 21 ቀን እስከ መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ዓመታዊጉባዔው ላይ፣ በሟች እናታቸው መኖሪያ ላይ እያሠሩት ካለው መስጅድ ጋር በተያያዘ የተገመገሙት ሚኒስትርጁነዲን፣ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈጸማቸውንና ካሉበት ኃላፊነትና ሥልጣን አኳያ ተገቢ ያልሆነ ሥራመሥራታቸው በዋናነት እንደተገመገሙበት ታውቋል፤ በድርጅቱ ውሳኔ መሰረት ወደ ተራ አባል እንዲወርሱና እንዲያገለግሉ ተደርገዋል፡:
አቶ አሊ አብዶን የመሰለ የቀድሞ የአዲስ አበባ መስተዳደር ባለስልጣን ከተማ ከተማውን መስኪድ ሲሰሩ አቶ ጁነዲን ሳዶን የመሰሉ ባለስልጣናት ደግሞ ገጠር ገጠሩም መስኪድ በመስራት የረዥም ዓመት እቅዳቸውን ለማሳካት ሁሉም አማኝ በተቀመጠበት ወንበር የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ ሲያልፍ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡
ስድስት ኪሎ የሚገኝው የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ ሀሰን ባለቸው ሃላፊነት ምን ያህል የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ታሪክ እየበረዙ እንደሆነ ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን
ቸር ሰንብቱ
No comments:
Post a Comment