Saturday 15 February 2014

ማኅበረ ቅዱሳን ከ 200 በላይ የአብነት መምህራን የምክክር ስብሰባ መታገድ ላይ ለአብነት መምህራኑ ገለጻ ሰጠ

ጉባኤው በ "አባ" ሰረቀብርሃን ምክንያት በመጨረሻው ሰአታት ላይ እንዲቋረጥ ተደርጓል። በጉባኤው ላይ የተጋበዙ የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ትልልቅ ባለስልጣናት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። ለጉባኤው መሳካት ማህበሩ ብዙ ሺህ ብር ወጪ እንዳወጣበት አሳውቋል። ማህበሩ ለእዲህ ያሉ ችግሮች አዲስ እንዳልሆነና የሚጠበቅ እንደነበረም መ/ር ብርሃኑ አድማስ ተናግረዋል። "ይህ ጉባኤ በአይነቱ የተለየ ሰለሆነ፣ በቤተክህነቱም በዓመቱ መጀመሪያ ላይ አሳውቀን ተቀባይነትን ስላገኘ እንዲሁም ከተለያየ መስሪያ ቤቶች የተጋበዙ ታታላቅ ባለስልጣናትም ስለሚገኙ ነበር እክል አያጋጥመውም ብለን የተዘናጋነው። ሆኖም እግዚአብሄር ፈቅዶ ይህ ከሆነ መልካም ነው" መ/ር ብርሃኑ አድማስ። 

በጉባኤው ላይ የተገኙት አባቶችም ሃዘናቸውን ትህትና በተሞላበት መንገድ ገልጸዋል። ቅዱስ ፓትሪያርኩንም ማነጋገር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ሆኖም ግን ሁሉም አባቶች ብጹህ ፓትሪያርኩን ማነጋገር ባይችሉም ጥቂት የተመረጡ መምህራን ግን እንዲያነጋግሩ ተፈቅዶላቸዋል። ቅዱስ ፓትሪያርኩም "መመሪያ መመሪያ ነው!" የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው መምህራኑ ተናግረዋል።

ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማድመጥ ይችላሉ!
http://www.dtradio.org/index.php?option=com_content&amp%3Bview=article&amp%3Bid=136%3A-7-2006-february-14-2014-&amp%3Bcatid=1%3Aweekly-tansmission#.Uv6ECtKvl3w.facebook