Tuesday 23 October 2012

‹ሲኖዶስ ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም›


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለቀጣይ ዘመናት የሚመራውን አባት የመምረጡ ታላቅ ሥራ ቅዱስ ሲኖዶሱን ከገጠሙት የዘመናችን ተግዳሮቶች ዋናው ነው፡፡ ይህንን ተልዕኮ ከተግዳሮቶቹ ሁሉ ዋናው የሚያደርጉት አራት ምክንያቶች ናቸው፡፡
የመጀመርያው በአራተኛውና በአምስተኛው ፓትርያርኮች መካከል በተደረገው ሽግግር በተፈጠሩ ወቅታዊና ቀኖናዊ ጉዳዮች ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱ በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ ሁለት ‹ሲኖዶሶችን› ያስተናገደችበት ዘመን ላይ የሚደረግ ምርጫ መሆኑ ነው፡፡ በሀገር ቤትና በውጭ ባሉት አባቶች መካከል እየተከናወነ ባለው የዕርቀ ሰላም ሂደት ውስጥ ዛሬም በሕይወት ያሉት የአራተኛው ፓትርያርክ ዕጣ ፈንታ ቀጣዩን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰላማዊና መንፈሳዊ ብሎም ቀኖናዊ ጉዞ የሚወስነው ይሆናል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድም አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበር ትመልሳለች፣ ያለበለዚያም አራተኛውን በጸሎት ወስና በእንደራሴ ትቀጥላለች፣ ያለበለዚያም ስድስተኛውን ትመርጣለች፡፡ 
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ኅብረተሰቡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ በንቃትና በቅርበት በሚከታተልበት ጊዜ የሚከናወን ሂደት መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የተደረጉት የፓትርያርክ ምርጫዎች የሕዝብን በቂ ክትትል ለማግኘት ዕድል አልነበራቸውም፡፡ በአንድ በኩል የመገናኛ አውታሮች እንደልባቸው ያለመሆን፣ በሌላም በኩል ሕዝባችን አስቀድሶ ከመሄድ ባለፈ የቤተ ክህነቱን ጉዳይ ለቤተ ክህነት ሰዎች ብቻ የተወበት ዘመን ስለነበር ምርጫዎቹ የሕዝብን በቂ ትኩረት አላገኙም ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የስብከተ ወንጌል መስፋፋቱና የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ የሚዘግቡ ሚዲያዎች መብዛት የፓትርያርክ ምርጫው ጉዳይ ትኩረት እንዲኖረው አድርጓል፡፡ በመረጃ መረብ እንኳን ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሚዘግቡ 26 ብሎጎችና ከስድስት በላይ ድረ ገጾች አሉ፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጀመረ


የሊቀ ማእምራን አበባው ይግዛው የቀብር ሥነ ሥርዐት ተፈጸመ:: 

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 12/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 22/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የ2005 ዓ.ም ጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ትናንት ተሲዓት በኋላ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡ በፍትሕ መንፈሳዊ አምስተኛው አንቀጽ ቁጥር 164 በታዘዘው መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም የሚጀምረው ምልአተ ጉባኤው ከአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በሥራ ላይ በሚቆይባቸው ቀናት የዕርቀ ሰላሙ ሂደት አስቸኳይ ፍጻሜ ስለሚያገኝበት ኹኔታ፣ በፓትርያርክ አመራረጥ ሕግ ረቂቅ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ካለፈው ምልአተ ጉባኤ በተላለፉ አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ 31ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለስድስት ቀናት በቆየበትና በአጠቃላይ ጉባኤው ታሪክ የተለየ ገጽታ በታየበት የስብሰባ ዝግጅት የተመከረባቸው የመዋቅር፣ የአደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ ውሳኔ ሐሳቦች ላይም እንደሚመክር ተመልክቷል፡፡ ምልአተ ጉባኤ እንዲያጸድቀውና የሥራ መመሪያ አድርጎ እንዲያስተላልፈው አጠቃላይ ጉባኤው የውሳኔ ሐሳቡንና የአቋም መግለጫውን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ያቀረበበት ቃለ ጉባኤ 33 ነጥቦችን እንደያዘ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአጠቃላይ ጉባኤው የውሳኔ ሐሳብና የአቋም መግለጫ ትኩረት የሰጣቸው ነጥቦች፦

ላያቸው ተዋህዶ ፤ ውስጣቸው ተሐድሶ የሆኑ መጻህፍት



(አንድ አድርገን ጥቅምት 13 2005 ዓ.ም)፡- ባሳለፍነው ዓመት በወርሀ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አንድ ወሳኝ ውሳኔ መወሰኑን ይታወቃል ፤ በውሳኔውም በርካቶች የተወገዙበት ቀሪዎቹ ደግሞ መዝገባቸው በይደር እንደቆየ የምናስታውሰው ነው ፤ በጊዜው  በፕሮቴስታንቶች እየተደገፉ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ በኅቡእና በገሃድ ተደራጅተው ለማፍረስና ለማፋለስ እየተንቀሳቀሱ  ድርጅቶች ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች በመለየት ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ የመሰሉት ሰዎችና ላያቸው ማር የተቀቡ ውስጣቸው ግን ነጣቂ የሆኑ ተቋማት ተለይተው መለየታቸው ይታወቃል፡፡