Monday 31 March 2014

ማኅበረ ቅዱሳንን ለምን ጠሉት??


READ IN PDF
አባ ሰላማ በማለት በቅዱሳን ስም እየተጠራ ቅዱሳን መላእክትን፣ እመቤታችንን እና ጻድቃንን የሚዘልፈው “አባ ሰላማ” የተሰኘው የተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ፤ በማያፍር አንደበቱ ማኅበረ ቅዱሳንን በመሳደብ ላይ ይገኛል:: ማኅበረ ቅዱስንም “የቅዱሳኑ የስድብ በረከት ለእኔም ይድረሰኝ” በማለት ይመስለናል ለብሎጉ ምን ዓይነት መልስ ሰጥቶ አያውቅም::

“አባ ሰላማ” ብሎግ በ1992 ዓ/ም ከቤተ ክርስቲያ ተወግዘው የተለዩት የተሐድሶ መናፍቃን በድሬዳዋዎቹ ቡድን እንደሚመራ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::

ማህበረ ቅዱሳን


ከታምራት ፍሰሃ
በአገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ት/ት ተቋም ተማሪወችን አሰባስቦ ስላስተማረ ፡ ብዛት ያላቸውን በግእዝ የተፃፉ መፃህፍትን ተርጉሞ ፡ ለወጣቱ የሚጠቅሙና የሚያንፁ መፃህፍትን አሳትሞ ስላቀረበ ፡ እጅግ የበዙ ገዳማትን አድባራትን ስለረዳ ፡ የአብነት ተማሪወችና አስተማሪወች ራሳቸውን እንዲችሉ እጅግ ብዙ ፕሮጄክቶችን ቀርፆ በተግባር ስላዋለ ፡ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትን ስላሳነፀ ፡ ብዙ ሺህ ኢአማንያንን በፈቃዳቸው አስተምሮ እንዲጠመቁ ስላስተባበረ ፡ የካህናት ማሰልጠኛወች በየቦታው እንዲቋቋሙ ስላስተባበረ ፡ አፅራረ ቤተክርስቲያንን ነቅቶ ስለጠበቀ ፡ የመናፍቃንን ክፉ አላማ ለሁሉ ዘወትር ግልፅ ስላደረገ ፡ ቤተክርስቲያንን ከተሃድሶወች ስለተከላከለ ፡ የክርስቶስን ወንጌል በየገጠሪቷ ክፍል እየዞረ ስላስተላለፈ ፡ ወጣቶች በነፃ ያለምንም ክፍያ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ አርአያ ስለሆነና ስላስቻለ ፡ በጣም ርቀው የነበሩ ክርስቲያኖችን አቅርቦ ለቤተክርስቲያን በሙያቸው እንዲያገለግሉ ስላስተባበረ ፦አክራሪ ከተባለ እንግዲህ እኔም አክራሪ ልባል እወዳለሁ!!!

ከሙስና መራቅ ፡ ሃገርን መውደድ ፡ ቤተክርስቲያንን ማወቅ ፡ ክርስቶስን ማምለክ አክራሪ ካስባለ እኔም አክራሪ ተብየ እንድከሰስ እወዳለሁ!!!

ቦንብ ሳልወረውር ቦንብ የሚወረዉሩትን አስቀድሜ አይቼ ወገኖቼን እንዳያጠፉ ማሳሰቢያ መስጠቴ አክራሪ ካስባለኝ ፡ እንዲህ ያለ አክራሪነቴን እወደዋለሁ!!!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትክክል ናት ፡ ክርስቶስም መሰረቷ ነው ፡ ድንግል ማርያምም ክብሯ ናት ማለት አክራሪ ካስባለ ፡ አክራሪ ተብሎ መሞት ክብር ነው!!!

ክርስቶስን በካደ ትውልድ መካከል ፡ በዲያቢሎስ በምትደምቅ አለም ለመዋብ በሚቋምጥ ሰው መካከል እውነት እውሽት መስላ መወቀሷ ፡ ውሽትና ክፋትም ከሚሰሯት ጋር መከበሯ የሚጠበቅ ነው፡፡

ዲያቢሎስ የተጣባት ክርስቶስ የራቃት ህሊና ፦ የገደላትን እየሾመች የሞተላትን መጥላቷ የሚጠበቅ ነው፡፡

ነገር ግን ፦ እኛ ከዚህ ህብረት አለመሆናችን ይታወቅ ዘንድ : አንድም እውነት ስለሆነው ስለጌታችን ስለክርስቶስ ምስክርነት ከእውነት ጎን እንቆማለን፡፡

ማቴ 5፡11 “ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።”

የማን መጨረሻ? የማኅበረ ቅዱሳን? ወይስ… የኢህአዴግ የመጨረሻ መጀመሪያ?

  • አቶ መለስ ዜናዊና አቦይ ጸሀዬ ከደርግ በተሰነዘረባቸው ጥቃት ገዳማውያን አባቶች የመነኮሳትን ልብስ በማልበስ ከሞት አድነዋቸዋል፡፡(ደርሶ ጡት ነካሽ ቢሆኑም)
  • ‹‹ቤተ ክርስቲያኗ ተከታዮቿን፣ ለነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲገዙ ከማስተማር በዘለለ የብሔራዊንቃት(ማንነት) ማስተማርያም ነበረች፡፡ ዶ/ር አረጋዊ
  • ‹‹መንግሥት ያግዘኛል ብዬ ነው እዚህ መንበር ላይ የተቀመጥኩት፤ ባያግዘኝ ሥልጣኑን አልቀበልም ነበር››አቡነ ማትያስ
  • ፓትርያርኩ የመዘንጋት፣ ለውሳኔ የመቸገር፣ ዕንቅልፍ የማብዛትና መሰል ችግሮች ሥራቸውንእያስተጓጎሉባቸው እንደኾነ ይነገራል፤ ራሳቸውም ‹‹ሲጨንቀኝ እተኛለኹ፤ ስተኛ ደግሞ እረሳዋለሁ››በማለት ችግሩን አምነው ተቀብለዋል፡፡
  • ‹‹የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን ይመለከታል›› በሚል ርእስ ለደኅንነቱ ዋና መሥ/ቤት የተላከ ደብዳቤ…(ያንቡት)
  • ‹‹እናቋርጣለን፤ ነገር ግን ‹እናንተ የጸጥታ ስጋት አለ› ብላችሁ በደብዳቤ ሓላፊነቱን ውሰዱ፡፡ እኛምለካህናቱ ለምእመናኑ ሁኔታውን ዘርዝረን እንገልጻለን›› አቡነ እስጢፋኖስ መዋቅራዊ ጥናቱ ይቁም በማለት ለመጣ የመንግሥት ካድሬ ሰጡት መልስ…