Thursday 25 October 2012

የዕርቀ ሰላሙ ውይይት በመጪው ኅዳር ወር ይቀጥላል


  • ቅዱስ ሲኖዶስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለአራት አህጉረ ስብከት እንዲከፈል ወሰነ
  • እስከ መጪው ግንቦት ወር የአራቱን አህጉረ ስብከት ጽ/ቤቶች የማጠናከር ሥራ እየተሠራ ይቆያል
  • የአራት ኪሎውን መንትዮች ሕንጻ ጨምሮ 283 ቤቶችንና ሕንጻዎችን ማስመለስ በሚቻልበት ኹኔታ ላይ ከከተማው ከንቲባ ጋራ ውይይት ተካሄደ
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 15/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 25/2012/ READ NEWS IN PDF)፦ አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰሜን አሜሪካ በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋራ የተመጀረው የዕርቀ ሰላም ውይይት በመጪው ኅዳር ወር መጨረሻ እንዲቀጥል ወሰነ፡፡ ከኅዳር 26 - 30 ቀን 2005 ዓ.ም በአሜሪካ ለሚቀጥለው ውይይት ምልአተ ጉባኤው ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን፣ ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስን፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማን በልኡክነት የሠየመ ሲኾን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በልኡካን ቡድኑ ጸሐፊነት ብቻ እንዲያገለግሉ ተወስኗል፡፡