Thursday 28 March 2013

፩ የቅዱሳን አባቶች ህይወት

ከዝክረ ቅዱሳን ዘተዋህዶ ቁ.፪
ትርጉም  በሃዜብ በርሄ

"እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንኩት እርሱንም እሻለሁ በህይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኘውን አይ ዘንድ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።" መዝ 26:4

የቅድስና መሰረቱ ራስን መቆጣጠር መቻል፣የሚሰሩትንም ሆነ የሚናገሩትን ማስተዋልና ጠንቅቆ ማወቅ፣ ጎጂ ከሆኑ ልማዶች ራስን መቆጠብ፣ የሌሎችን ጉድለትና ስህተት ከማጉላት ይልቅ ፍቅረ እግዚአብሔርን እያሰቡ ከመልካም ምግባራቸው መማር መቻል፣ እኔ ከሁሉ ያነስኩ ነኝ ብሎ ማመንና ከምንም በላይ ደግሞ ከቤተ መቅደሱ አለመራቅ...ወዘተ ነው።ቅዱሳን አባቶች ፍቅራቸው ራስን አሳልፎ እስከመስጠት ነውና እውነተኛና ከቅን ልቡና የመነጨ ፍቅር መሆኑ አያጠያይቅም። ስለ ሃይማኖታቸው አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ጀርባቸውን ለግርፋት፣ ፊታቸውን ለጽፋት ነፍሳቸውን ለሞት የሰጡና "ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ "ማቴ 5:6 የመጨረሻ ግባቸው የመንግስቱ ወራሾች መሆን ነው።


ቅዱሳን ሰዎች ሰው ሲሆኑ እንደ መላእክት የሚኖሩ፣ በምድር ሳሉ ምድራዊ አሽንክታብን የናቁ፣ እነርሱ የእግዚአብሔር መሆናቸውን ከማመን በስተቀር በምድር ላይ የኔ ነው የሚሉት ምንም ነገር የሌላቸው፣ በመንፈስ ከመላእክት ጋር የሚዘምሩ፣ ከቅዱሳን ጋር የሚያመሰግኑ ጸጋ እግዚአብሔርን የተላበሱና ሰማያዊ ኅብስት እየተመገቡ የሚኖሩ ናቸው። ህይወታቸውን በሙሉ በተጋድሎ ያሳለፉ ቅዱሳንን ታሪክ ማንበብ ራሳችንን ለመልካም ስራ እንድናዘጋጀው ይረዳናል። ህገ እግዚአብሔርን ስለ መጠበቃቸው፣ ስለ ጽናታቸውና ትዕግስታቸው፡ተግተን ባነበብንና በተገነዘብን ቁጥር የራሳችንን ህይወት እንድንመረምርና በመልካም ምግባር የዳበርን ከሰይጣናዊና እንስሳዊ አስተሳሰብ የራቅን፣ ከእኩይ ተግባር የተቀጠብን እንድንሆን ይረዳናል።ፍጹም ቅንነትና ርህራሄ የሞላበት ህይወታቸው እውነተኛ ክርስቲያናዊ ፍቅር ምን እንደሆነ ያሳየናል። ፍጹም ፍቅር፦ ትዕዛዘ እግዚአብሔርን ያስፈጽመናል፤ ሰላምና መረጋጋትን፣አንድነትን፣ልግስናን፣ የበደሉንን ይቅር ማለትን፣ የባልንጀራችንን በደል መሸፈንን ያስተምረናል።

2, ቅዱሳን ሰማእታት
የሰማዕትነት መሰረቱ ምንኩስና ሲሆን የምንኩስና የትውልድ ስፍራ ደግሞ የግብጽ ቤተ ክርስቲያን ነች። ገዳማዊ አኗኗር ለመንፈሳዊነትና ለሰማዕትነት አመቺ ሆኖ ያገኘው በምድረ-በዳ (ገዳም) ለዘጠና አመታት የኖረው የመጀመሪያውና አንጋፋው መናኝ አባታችን ቅዱስ ጳውሊ ነው።
፠ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፣ ሀሴትንም አድርጉ፣ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነብያት እንዲሁ አሳደዋቸዋልና።" በማለት ጌታችን ደቀ መዛሙርቱ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ችግር አስቀድሞ ገልጾላቸዋል።ማቴ ፭:፲፪"...ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፤ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ሁሉ ያገኛታል። "ማቴ፲:፴፱
በ፪፻፳፰ ዓ/ም ሰማዕቱ ቅዱስ ሂፖሊጦስ st.Hippolytus "ሰማዕታት ይህን ዓለም በጸጋ ይተዋሉ ፣ ኃጥያታቸውም ይሰረይላቸዋል ፣ እንደ ሰለስቱ ቅዱሳን ወጣቶች ሰማያዊ አክሊል ይሸለማሉ። በጥንታዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሰማዕትነት ከፍተኛ ቦታ ነበረው።" በማለት ገልል።
ከ፪፻፶፮-፪፻፶፰ ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ ንጉስ ዳኬዎስ Emperor Decius የክርስትናን ሃይማኖት ለማስወገድ አዋጅ አወጣ። በዚህ አዋጅ መሰረት የተቀረጸ በድን ጣዖት ላመለከ የሞት ቅጣት ይፈረድበት ነበር። ብዙ ግብጻውያን ክርስቲያኖች ራሳቸውን በመሰዋዕትነት አሳለፉ።የተቀሩትም ወደ ምድረበዳ ተሰደዱ። በዚህ ጊዜ ነበር ታላቁና የመጀመሪያው ግብጻዊ መናኝ አባ ጳውሊ የበረሃ ኑሮውን የተያያዘው። ንጉስ ዳኬዎስ ከበርበሮች ጋር ሲዋጋ ሞተ። በእርሱ ምትክ ንጉስ ቫሌሪያን Valerian (፪፻፶፫-፪፻፷) ህጉን በማደስ ጣዖት እንመልኩ አወጀ። ከቫሌሪያን ሽንፈት በኋላ ለአርባ ዓመታት ቤተ ክርስትያን በሰላም ቆየች።
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ በንጉስ አርያኖስ Arrianus ዘመን የተቆረቆረችው አንቴኖፖሊስ ወይም አንሴና Antenoepolis or Ansea በግብጽ አሉ ከሚባሉ የክርስቲያን መናኸሪያ አንዷ ነበረች።
ከጥንቱ ዘመን ሰማዕታትም በግብጽ ለሃይማኖታቸው ሲሉ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ከሰጡት ክርስቲያኖች ውስጥ የአብዛኛዎቹ ደም የፈሰሰበት ቦታ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ቅጣት ከተወሰነባቸው በኋላ ከከተማዋ በስተምዕራብ በሚገኘው ኮረብታማ ቦታ ላይ በመወሰድ የሞት ቅጣት ተቀብለዋል። በዚሁ የብዙ ክርስትያኖች ደም በፈፈሰበት ምዕራባዊ ክፍል የሚገኘው
ውሃ ጉድጓድም ቦታውን ታሪካዊ ካሰኙት ነጥቦች አንዱ ነው።
ምንኩስና የምድራውያን ወይም የሰብአውያን መላእክት ህይወት እንደሆነ ይነገራል። ራስን ከዓለማዊ ፍላጎትና ከምድር አሽንክታብ ቆጥቦና ለይቶ በቅድስና ለመኖር ዋነኛ መሣሪያው ምንኩስና ነው። ይህም ለሰማዕትነትና ለብትህውና ጥርጊያ መንገድ ያዘጋጃል። አንድ ሰው መነኮሰ ማለት ዓለማዊ ወይም ሥጋዊ ዓይኑን ጋርዶና ዓይነልቡናውን ከፍቶ ለእግዚአብሔር በማደር በተመስጦና በመንፈሳዊ ተጋድሎ ኖረ ማለት ነው። የዚህ ውጤት ደግሞ መንፈሳዊ ፍሬ ማፍራት ይሆናል።
መንፈሳዊ ፍሬ ማለት፦ ፍቅር፣ ደስታ ፣ሰላም ፣ ቅንነት፣ ትዕግስት፣ ቸርነትና ትህትናን ገንዘብ ማድረግ ነው። ይህ የሚገኘው ደግሞ ራስን በውስጥም በአፍአም ለእግዚአብሔር ማስገዛት ሲችሉ ነው።

ታሪክ ጸሃፊው ላክታንቲየስ Lactantius "ሰማዕትነት ኢ-ክርስቲያኖችን ለማስተማሪያ
ወደ እግዚአብሔር ቤት እንዲመጡ፣ ለአገልግሎትም እንዲተጉ የሚያበረታታ ታላቅ መሳሪያ ነው። ሰማዕትነት ሰማዕታት ለፈጣሪያቸው ያላቸውን ታላቅ ፍቅርና ክብር እስከ ሞት ድረስ የሚያሳዩበት ብቸኛ መንገድ ነው። እነርሱን በማየት ብዙ ከሐድያን ወደ ክርስትናው ዓለም ይመለሱ ነበር።" ብሏል። ህይወታቸውን ለእውነተኛዋ ወንጌል አሳልፈው የሰጡ ሰዎች የክብር ቦታቸው ከቀዳማውያን ክርስቲያን አባቶቻችን ጋር ነው።
በቅብጥ ስንክሳር ላይ ከተጠቀሱት ፫፻፹፩ ሰማዕታት ውስጥ ግማሽ የሚሆኑት ከ፪፻፺፮-፫፻፭ ዓ/ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ መከራን የተቀበሉ ናቸው። ከእነርሱም ውስጥ ከደሀ ሸማኔ አንስቶ እስከ ተራ ወታደር፣ ጀኔራል፣ ሀብታም፣ ነጋዴና ንጉሳዊ ቤተሰብ ይገኙባቸዋል። አንዳንዶች ሰማዕታት ለተጋድሎ ከመነሳታቸው በፊት ሰማያዊ ጥሪ ይደረግላቸዋል። ለምሳሌ ቅዱስ ኢሶዶር St.Isidore የተባለ ሰማዕት በቅዱ ሚካኤል አማካኝነት ነበር ለሰማዕትነት የተጠራው። ቅዱስ ሚናስ ተአምር ሰሪው St.Mina the miraculous ደግሞ እግዚአብሔር በዙፋኑ በሰማዕታት ታጅቦ ሳለ በራዕይ ተገለጠለት። የአንጾኪያው ጀነራል የቅዱስ ፋሲለደስ St. Basilides Stratelates of Antioch ልጆች የሆኑት ቅዱስ አፓተር St.Apater እና ቅዱስ ኢሬን St.Eirene በመላዕክት ተጠርተው ወደ ግብጽ በመሄድና በእስር ቤት ለረጅም ጊዜ በመቆየት ነበር ሰማዕታት የሆኑት። እነዚህ ሁለት ቅኡሳን በቅብጥ አባድርና ኢራ SS.Abadir & Ira'i በመባል ይታወቃሉ። ቅዱስ ቴዎድሮስ እስትሬሪለትስ St.Theodore Stratelates ከሰማዕትነቱ በፊት ድራጎን ገድሏል።

ቅዱሳን ሰማዕታት ከእለተ ሞታቸው በፊት በያሉበት ሀገር ነገስታት ፊት ይቀርባሉ eror's Goverror of Upper Egypt እጅ የእነ
ቅዱስ ጁልየስ ዘ-አክፋ፣ አባድርና ኢራ SS Julius of Aqfas, Apater & Eirene እና ሌሎችም ሰማዕታት ህይወት አልፏል። ቅዱሳኑ ይህ ነው  የማይባል ሥቃይ ቢደርስባቸውም በጸሎታቸው ጸንተው ይቋቋሙታል። ከዚያም አልፈው ይህን በደል ለሚፈጸምባቸው ሰዎች የኃጥያትን ስርየት ይለምናሉ። ቅዱሳን መላእክት አብረዋቸው ሆነው ህመማቸውን በማስታገስና ቁስላቸውን በመፈወስ ይረዷቸዋል። ተጋድሎአቸውን በትጋት እንዲፈጽም ያጽናኗቸዋል። ቅዱስ አቢስክሪዮስ St.Abiskhirun ይህ በተደጋጋሚ ተደርጎለታል።

ህጻኑ
ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅዱስ ኢየሉጣ SS.Cyriacus & Julitta ለጣዖት እንዲሰግዱ ሲጠየቁ ቅ/ኢየሉጣ " ለጣዖት መስገድ አግባብ መሆን አለመሆኑን ከሶስት አመቱ ህጻን ጠይቃችሁ ተረዱ" ብላ መለሰች። ህጻኑም በተጠየቀ ጊዜ ጣዖት ሀሰተኛ አምላክ መሆኑን ተናገረ። ቅ/ኢየሉጣ በዚህ ምክንያት ስለሚደርስባቸው ቅጣት ፍርሃት ቢያድርባትም፤ በህጻኑ ቂርቆስ አበረታችነት ሁሉንም በመቋቋሟ፤ የቀለጠ መዳብ ላይ ቢጣሉም እንኳ ለእነርሱ የተሰማቸው መንፈስ ቅዱስ ያለበት የመጽናኛ የመታደሻ ቦታ ላይ እንደ ተቀመጡ ነበር እንጂ ቃጠሎው አልተሰማቸውም።እነርሱ የተጣሉበት እሳት ፍንጣሪ ንጉሱ ላይ ቢያርፍበት አጥንቱ ድረስ ገብቶ አቃጥሎታል።ይህ ንጉስ በህጻኑ ቂርቆስ አማካኝነት ፈውስ ቢደረግለትም በክርስቶስ ግን አላመነም፣ ልቡ እንደ ፈርዖን ልብ ደንድኖ ቀረ። አስደናቂው ተአምር ግን እነዚህ ቅዱሳን ከሞት በኋላ ዳግም በመነሳት በህይወት መገኘታቸው ነው። ቅዱስ አይሲዶር St.Isidore አምስት ጊዜ ተገድሎ ከሞት ተነስቷል፣ የልዳው ቅዱስ ጊዮርጊስም ሶስት ጊዜ ሞቶ ተነስቷል።
የእነዚህ ቅዱሳን ከሞት በኋላ መነሳት ለብዙ ሃይማኖት የለሾች ድህነት ምክንያት ሆኗቸዋል። ለዚህም ነው የታሪክ ሰዎች ሲጽፉ "ሰማዕትነት የኢ-አማንያን ትምህርት ቤት ነው" የሚሉት።በህጻኑቂርቆስና በእናቱ ኢየሉጣ ምክንያት አስራ አንድ ሺህ ሰዎች ክርስቲያን ሆነዋል።የንጉስ ድዮቅልጥያኖስ ሚስት በቅዱስ  ጊዮርጊስ አማካኝነት ከኢ-አማኒነት ከተመለሱት ሶስት ሺህ ክርስቲያኖች አንዷ ስትሆን ሁለተኛው አብሮ አስፈራጅ የነበረውና በጭካኔው ወደር የሌለው  አርያኖስ ነው።

 "ሰማዕትነት በሥጋ  መሞት/ መጎዳት ብቻ አይደለም። ነገር ግን ድንግልና፥ የመንፈስ ድኅነት፣ የዓለምን አሸንክታብ መናቅ፣ የተቸገረን መርዳት፣ ያዘነን ማጽናናት፣ ቅንነት፣ የዋህነት፣ ስለ ጽድቅ መራብና መጠማት፣ የልብ ንጽህና፣ የተጣሉትን ማስታረቅ፣ ጠላትን መውደድ" ነው። ተብሎ በአንቀጸ ብጹዓን እንደተጻፈው "ክርስቲያኖች ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች በአንክሮ ከፈጸሙ በጽድቅ መሰላል ወደ እግዚአብሔር ሊደርሱ ይችላሉ" ብለዋል። ማቴ ፭፥፫-፱
በአራተኛው መ/ክ/ዘ መጀመሪያ ላይ በንጉስ አርያኖስ Arrianus ዘመን የተቆረቆረችው አንቴኖፖሊስ ወይም አንሴና Antenoepolise or Ansena በግብጽ አሉ ከሚባሉት የክርስቲያን መናኸሪያ አንዷ ነበረች። ከጥንቱ ዘመን ሰማዕታትም በግብጽ ለሃይማኖታቸው ሲሉ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ከሰጡት ክርስቲያኖች ውስጥ የአብዛኛዎቹ ደም የፈሰሰበት ቦታ ነው። ብዙ ክርስቲያኖች ቅጣት ከተወሰነባቸው በኋላ ከከተማዋ በስተ ምዕራብ በሚገኘው ኮረብታማ ቦታ ላይ በመወሰድ የሞት ቅጣት ተቀብለዋል። በዚሁ የብዙ ክርስትያኖች ደም በፈሰሰበት ምዕራባዊ ክፍል የሚገኘው የውኃ ጉድጓድም ቦታውን ታሪካዊ ካሰኙት ነጥቦች አንዱ ነው። ከዚሁ ከክርስቲያን ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ ምክንያት የቅብጥ የዘመን አቆጣጠር ወይም ባህረ ሐሳብ ዘመነ ሰማዕታት በመባል ይታወቃል። የተጀመረውም በ፪፻፹፬ ዓ/ም ድዮቅልጥያኖስ Diocletian በሮም በነገሠበት አስከፊ ዘመን ነበር። ከ፪፻፹፬-፫፻፭ ዓ/ም ድዮቅልጥያኖስ ህዝባዊ ጦርነትን ያቆመበትና ኃያል መንግሥት መሆኑን ያሳየበት ዘመን ሲሆን በ፪፻፺፰ ዓ/ም በቤተ ክርስቲያን ላይ ጦርነት አወጀ። ከ፫፻፫-፫፻፲፪ ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ ክርስቲያኖችን ከሥልጣን በማውረድና ወታደሮችን ከሥራ በማባረር በየካቲት ወር ፫፲፳፮ ዓ/ም እያንዳንዱ ሰው ለጣኦት እንዲሰዋ የሚል በጽሁፍ የተደገፈ አዋጅ በሀገሪቱ ሁሉ አወጀ። መከራው ቢበዛባቸውም ለጣኦት ከመስገድ ይልቅ በዚያው ልክ የሰማዕታት ቁጥር እየጨመረ በመሄዱ ቁጥራቸው በአኅዝ ለመወሰን ከማይቻልበት ደረጃ ላይ ደረሰ። አብዛኛው ግብጻዊ ክርስቲያን በመሆኑ ጭፍጨፋው የሁሉንም ቤት አንኳኳ። አውሳብዮስ የተባለው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሀፊ "በሺህ የሚቆጠሩ ቅብጦች ሞቱ፣ በአንድ ቀን ብቻ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወንዶች፣ ሴቶችና ህጻናት አንገታቸው ይቆረጥ፣ ወደ እሳትም ይጣል ነበር" ብሎ ጽፏል።

No comments:

Post a Comment