Sunday 28 October 2012

የፓትርያርክ ምርጫ ሕግን በሚመለከት ቅዱስ ሲኖዶሱ በኅዳር ወር መጨረሻ ልዩ ስብሰባ ይጠራል


አርእስተ ጉዳይ፡- 
  • READ THIS ARTICLE IN PDF
  • የግብጹ ፓትርያርክ ምርጫ ልኡክ ዛሬ ማምሻውን ወደ ካይሮ ያመራል፤ በምርጫው ይሳተፋል፤
  • የጠ/ቤ/ክህነቱ ‹የጨለማ ቡድን› የተቋማዊ ለውጡን አመራር ለመቀልበስ ያደረገው ሙከራ ከሸፈ፤
  • በወኅኒ ቤት የሚገኙ መነኰሳት ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ኾኗል፤ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብቻ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የተፈረደባቸው ከ70 ያላነሱ ‹መነኰሳት› ይገኛሉ፤
  • ገዳማት የመነኮሳታቸውን ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎቻቸውን ለአህጉረ ስብከትያሳውቃሉ፤ መነኰሳት መታወቂያ እንዲኖራቸውና ከቦታ ወደ ቦታም ያለደብዳቤ እንዳይንቀሳቀሱ ይደረጋል፤
  • ከአብነት ት/ቤቶች ጋራ የተያያዘው የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በልዩ ትኩረት ክትትል ይካሄድበታል፤ የአብነት ትምህርት መለኪያ ተበጅቶለትና በየቋንቋው መምህራን ተመድበው መምህራን በየጊዜው የሚስመርቋቸው ደቀ መዛሙርት በምደባ በየአህጉረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እንዲመደቡ ይደረጋል፤
  • ምልአተ ጉባኤው በድሬዳዋ ሀ/ስብከትና በድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያጣራው ልኡክ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው እንዲያመራ አዘዘ፤ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ስም በማጥፋት የኮሚቴውን ተልእኮ የሚያደናቅፉ ሕገ ወጥ ቡድኖችን እያደራጁ ነው፤
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፤

የቅ/ሲኖዶስ የሰሞኑ ውሎ ሪፖርታዥ

  • በግብጹ የፓትርያርክ ምርጫ ቤተ ክርስቲያናችን በአምስት ብፁዓን አባቶች ትወከላለች
  • የጠ/ቤ/ክህነቱ የመዋቅር ማሻሻያ እንዲጠና ቅዱስ ሲኖዶስ ትእዛዝ ሰጠ::
  • የውጭ ግንኙነት መምሪያ በክፍለ አህጉር ዴስኮች ይደራጃል፤ የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ የሚዳስስ መጽሔት በእንግሊዝኛ ቋንቋ  ይጀምራል::
  • “አዲስ አበባ በአራት አህጉረ ስብከት መከፈሉ አስተዳደራዊ ችግሮችን በዘላቂነት ይቀርፋል፡፡” /የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/
  • ሢመተ ፓትርያርክ በምርጫ ወይስ በዕጣ? ከግብጽ ምን እንማራለን?

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 16/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 26/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ጥቅምት 25 ቀን 2005 (እ.አ.አ ኖምበር 4 ቀን 2012) በሚካሄደው የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 118 ፓትርያርክ ምርጫ ላይ የሚገኙ አምስት ብፁዓን አባቶችን በልኡክነት መሠየሙን የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ አስታወቀ፡፡