Thursday 13 September 2012


"የዕርቀ ሰላም ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል" ቅ/ሲኖዶስ አስታወቀ

  • “የሃይማኖት መሪዎች ጊዜ ሳያልፍ አንድነታቸውን እንዲያጠነክሩ ጸሎቴ ነው” /ፕ/ር ኤፍሬም ይሥሐቅ/
  • ከመጪው ግንቦት በፊት የሚፈጸም የፓትርያርክ ሹመት እንደማይኖር እየተነገረ ነው::
  • ማኅበረ ቅዱሳን ስለዕርቀ ሰላሙ ያለውን አቋም በግልጽ ዐውጆ ሂደቱን እንዲያግዝ ተጠይቋል::
  • “በአሐቲ ቤተ ክርስቲያን መርሕ የቤተ ክርስቲያን ፍጹም አንድነትና ሰላም እንዲጠበቅ እንሠራለን” /የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር/::
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 2/2004 ዓ.ም፤ September 12/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቅርቡ በመንግሥት በኩል ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀው የአመራር ሽግግርና የሚተካው ርእሰ መንግሥት ከተለወጠው ዘመንና ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኅልፈት ጋራ ተያይዞ ከታየው የሕዝብ ጨዋነት፣ ይቅር ባይነትና ርኅራኄ አኳያ የሚመጥኑ ተፈላጊ ለውጦችን ለማምጣት የሚያስችል እንዲኾን እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክህነቱም በኩል ከቀጣዩ ርእሰ አበው ሹመት አስቀድሞ መከናወን ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ እየተገለጸ ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በፓትርያርኩ ኅልፈት ተገቢውን ሰው መተካትና የተፈጠረውን ክፍተት ማሟላት ሕገ መንግሥታዊ እና ሕገ ቤተ ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ በግዴታው አፈጻጸም ሂደት የሚታየው የመንግሥት ይኹን የቤተ ክህነት ባሕርይና ብቃት ለየራሱ ከጎሰኛነትና ጥቅመኛነት በላይ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንን በማስቀደም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: እናቁም?

የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: እናቁም?: አንዳንዴ የትግላችን፣የጥረታችን፣የልፋታችን ውጤት መና የቀረ የሚመስልበት ጊዜ አለ፡፡ ውኃ አልቋጥር፣ ጠብ አልል ሲልብን፤ መንገዱ ሁሉ ረዥም፣ በሮቹ ሁሉ ዝግ፣ ጩኸቱ ሁሉ ሰሚ አልባ ሲመስለን፣ በመጨረሻ የምንወሰ...