Sunday 18 May 2014

ዜና ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ: መዝሙር አለቀሰ

ዜና ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ: መዝሙር አለቀሰ

መዝሙር አለቀሰ

መዝሙር አለቀሰ
የያሬድ ዝማሬ፣ የአዘማመር ስልቱ
የበገናው ቃና፣ማሲንቆ ቅኝቱ
የከበሮው ውበት የዋሽንት ፍሰቱ፡


ነበር ተፈጥሯቸው ስብሐት ሊዘሩ
ሥርዓት ሊያከብሩ
መንፈስን አድሰው ውበት ሊደምሩ
ምህላ ሊያደርሱ ኑዛዜ ሊያወሩ
ስንዱዋ እመቤት ቤተ ክርስቲያን ቅድስት
እንዳላስተማረች ሁሉን በሥርዓት


ዛሬማ አፍ የፈታ ሁሉ እያንጎራጎረ፣
ቀኖና ትውፊቱን እየሸረሸረ
የመዝሙር ሥርዓቱ ስልቱ ተቀየረ
መዝሙር ዜማ ሳይሆን ጩኸት ሆኖ ቀረ
ለነፍስ ሐሴት ትቶ ለሥጋ አደረ


ሳኦልም ከደዌው እንዳልተፈወሰ
ወኅኒውም በመዝሙር እንዳልፈራረሰ
መዝሙር ቅዱሳንን እንዳላወደሰ
ዜማን ሐዘን ገባው መዝሙር አለቀሰ


ንጉሥ ገብረ መስቀል ጦር ከእግር ሰክቶ
በፍጹም ተመስጦ አለምን ረስቶ
እንዳልነበር ሁሉ ጸጋችን ምግባችን
መዝሙር አንገት ደፋ ከመላእክት በላይ አዋቂዎች ሆነን


ሳይጠፋ መዝሙሩ እስከ ሥርዓቱ
ፈር እየለቀቀ ዘማሪ ነኝ አለ ሁሉም በየቤቱ
በጠፋበት ሁሉ ተሰጥኦው መክሊቱ
መዝሙር አለቀሰ ተገፍቶ መብቱ
ተጥሶ ሥርዓቱ።
ምንጭ
ገድለ ቅዱሳን Gedle Kidusan Acts of Kidusan