Monday 19 November 2012

የቅዱስ ላልይበላ ደብር ካህናትና ምእመናን የመንግሥት ያለህ እያሉ ነው


     ቤተክህነቱ በደብሩ አለቃ የሚፈጸመውን ሙስናና የአስተዳደር በደል መቆጣጠር ተስኖታል
  • የውቅር አብያተ መቅደሱ የቱሪስት ገቢ ተቆጣጣሪ የለውም፤ የቅርሶቹ ጉዳት ተባብሷል
  • በደብሩ ገንዘብ የተሠሩት የቤተ አብርሃም እና ይምርሐነ ሆቴሎች ባለቤት አይታወቅም


አዲስ አድማስ ጋዜጣ የተወሰደ

(አንድ አድርገን ህዳር 10 2004 ዓ.ም)፡-በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የቅዱስ ላሊበላ ደብርየሚያገለግሉ ካህናት እና ምእመናን÷ በደብሩ አስተዳዳር በሚፈጸመው ሙስናና የአስተዳደር በደልመማረራቸውንና አቤቱታቸው ሰሚ አለማግኘቱን ለአዲስ አድማስ ገለጹ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር የቱሪዝም ገቢየግል ሀብትን ለማደለብ እየዋለ መኾኑን የጠቆሙት ካህናቱ÷ በቅርሶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በከፍተኛደረጃ መባባሱን፣ሙሰኝነትንና የአሠራር ብልሹነትን የሚቃወሙና የሚያጋልጡ ካህናትና ሠራተኞች ለመባረርናለእስር መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

Friday 9 November 2012

እምሊባኖስ ትወፅእ መርዓት




 ኦ ድንግል አኮ በፍተወተ ደነስ ዘተጸነስኪ ፡፡ ድንግል ዘርዕ ዘይወጽእ እምስካበ ተዓዳዌ ሕግ ይከውን ለቅጥቃጤ ወለሙስና ባለው ፈቃድ የተፀነሽ አይደለሽም፡፡ አላ በሩካቤ ዘበህግ እምሐና ወኢያቄኒም ተወለድኪ ክቡር አውስቦ በኵለሄ ወለምስካቦሙኒ አልቦቱ ስዕበት ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፡፡ አንድም እስመ ናሁ በኃጢአት ተፀነስኩ፡፡ ወበአመፃ ወለደተኒ እ...ምየ እንዲል፡፡ በልተው ጠጥተው በሚያደርጉት ፈቲው ጽነት የተፀነስሽ አይደለም፡፡ ብዝኁ ወተባዝኁ ባለው ፈቃድ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ፡፡ ታሪክ የእመቤታችን ቅድመ አያቶቿ ቴክታ በጥሪቃ ይባላሉ፤ ይህ ቀራቸው የማይባሉ ባለጸጎች ነበሩ ፤ ብእላቸውም የወርቅ ፤ የብር የፈረስ ፤ የበቅሎ የሴት የባርያ የወንድ ባርያ ነው፡፡ ከወርቁ ብዛት የተነሳ እንደ አምባር እንደ ቀለበት እያሠሩ ከበሬው ከላሙ ቀንድ ያደርጉት ነበር፡፡ ይህን ያህል አቅርንተ ወርቅ ይህን ያህል አቅርንተ ብሩር ተብሎ ይቆጠር ነበር እንጂ የቀረው አይቆጠርም ነበር፡፡


በጋሻው ደሳለኝና አሰግድ ሣህሉ


(ደጀ ሰላም ጥቅምት 30/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 9/2012, READ THE NEWS IN PDF)፦ሃይማኖት ጉዳይ በተነሣባቸው ጥያቄ ምእመኑ ዓይናችሁን ላፈር ያላቸው ብዙ ሰዎች ቢኖሩም በተለይ በበጋሻውና በባልንጀሮቹ ላይ ጠበቅ ያለ አጀንዳ እንደተከፈተባቸው ለረዥም ጊዜ ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል። ጉዳዩ በቅዱስነታቸው እረፍት እና በመከካሉ በመጣው ጊዜ ክፍተት ተረሣ ቢመስልም “ይደር” ተባለ እንጂ “ይዘጋ” ስላልተባለ እነሆ ርዕሳችን አድርገነዋል። በድጋሚ። ከበጋሻው እንጀምር።

Thursday 8 November 2012

ለአዲስ አበባ አራት አህጉረ ስብከት ሥ/አስኪያጆች ተሾሙ



(ደጀ ሰላም ጥቅምት 29/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 8/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው ኮሚቴ በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የገነገነውን ሙስናና ሌሎችም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ያቀረበውን ጥናት የመረመረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሀገረ ስብከቱ በአራት አህጉረ ስብከት ተከፍሎ እንዲደራጅ መወሰኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ስለ አከፋፈሉ እና አደረጃጀቱ መነሻ “አቤት ባዩ በዛ፤ ጩኽት በዝቷልና” በማለት የምልአተ ጉባኤውን ውሳኔ ለጋዜጠኞች ያስረዱት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል÷ ሁሉም አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በየአካባቢያቸው እንዲስተናገዱ በፓትርያርኩ ጊዜ በአባቶችና ሊቃውንት ተጠንቶ ቀጠሮ ተይዞበት የቆየ ጉዳይ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ቀሲስ በላይ መኰንን ከሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲንነት ተነሡ


(ደጀ ሰላም ጥቅምት 29/2005 ዓ.ም፤ ኖቬምበር 8/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ባለፉት የዜና ዘገባዎቻችን ስንጠቅሳቸው የነበሩትና በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲን የነበሩት ቀሲስ በላይ መኰንን ከዚህ ሓላፊነታቸው መነሣታቸው ታውቋል፡፡ የደጀ ሰላም ምንጮች እንደሚገልጹት ከሆነ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ሰሞኑን በሚደረገው የከፍተኛ ሓላፊዎች ሽግሽግ ቀሲስ በላይ መኰንን የሕግ አገልግሎት መምሪያ ሓላፊው አማካሪ ኾነው መመደባቸውን እየተነገረ ነው፡፡ በርካታ ዋና ዲኖች በፍጥነት በሚቀያየሩበትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሳይሆን የመቅጫ ቦታ ተደርጎ በሚታሰበው መንፈሳዊ ኮሌጅ ለስድስት ወራት የቆዩት ቀሲስ በላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ውሳኔ ከሓላፊነታቸው መነሣታቸው የታወቀው “በእድሳትና ለዲግሪ መርሐ ግብር መጀመር ይደረጋል በተባለው ዝግጅት” ሰበብ የመንፈሳዊ ኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደት ከሁለት ወራት በላይ በተስተጓጎለበት፣ ይህንንም ተከትሎ የደቀ መዛሙርቱ (በተለይም የሰሚናር ኮርሰኞቹ) አቤቱታ ጎልቶ በሚሰማበት ኹኔታ ውስጥ ነው፡፡

Tuesday 6 November 2012

የኃይለማርያም አጣብቂኝ በመንፈሳዊ ሕይወትና በፖለቲካዊ ማንነት ውስጥ




ከአዲስ ጉዳይ መጽሄትቅጽ 6 ቁጥር 136 ጥቅምት 2005 ዓ.ም


  • እኔ ችግር ያለብኝ እናቴ አልዳነችም› ማለታቸው ላይ ነው ፤ እንደዚህ ማለታቸው ሌሎቹም ሁሉ እንዳልዳኑና እሳቸው ብቻ እንደዳኑ የሚያረጋግጥ ሃሳብ ነው፡፡” ፕሮፌሰር መስፍን
  • አቶ ኃ/ማርያም ለቀድሞ ጠ/ሚኒስትር ዘላለማዊ  ክብር እመኛለሁ” ማለታቸውን እንደተጸጸቱበት ተናግረዋል፡፡
  • “እናቴ አልዳነችም”  ብለው መናገራቸው ራሱ በጣም የሚያሳዝንና  ሞኝነት ጭምር ነው፡፡ ይህ እኮ ሁላችንም ማለትም ኦርቶዶክስም ፤ ሙስሙና ካቶሊኩ በሙሉ አለመዳናችንን የገለጹበት ቀላል አሽሙር ይመስለኛል” ዶ/ር ያእቆብ
  • “አቶ ኃይለማርያም የአቶ መለስን ራዕይ ለማስጠበቅና በሃይማኖተኛነት መካከል እየዋለሉ የሀገሪቱን ሕገ መንግስት ሊጥሱ ይችላሉ” ዶ/ር ያእቆብ
  • ዛሬ ስለ ሃይማኖት መጠቃቀስ የጀመሩት የአገር መሪ ነገ ደግሞ  ስልጣናቸውን ተጠቅመው እግዚአብሔርን ማገልገል በሚል ሰበብ  ሃይማኖታቸውን ለማስፋፋት ምን ያዳግታቸዋል?

(አንድ አድርገን ጥቅምት 27 2005 ዓ.ም)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን ከተረከቡ ወዲህ ህዝብ ስለ እኚህ አዲሱ መሪ ስብዕና የተለያዩ አስተያየቶችንና ቅድመ ግምቶችን ሲያንጸባርቅ ቆይቷል ፡፡ መገናኛ ብዙሃኑ በተለይም የህትመት ሚዲያው እንዲሁም ድህረ ገጹ በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የፖለቲካ ብቃትና የፊት ለፊት ተግዳሮቶች ዙሪያ ያላቸውን አስተያየት በመረጃና ትንተና ላይ ተመርኩዘው ለንባብ አብቅተዋል ፡፡ ሰውየው ወደ ስልጣን ከወጡ ብዙም ጊዜ አላለፈምና አሁንም አዲስ ተብለው ቢጠሩ አይገርምም ፤ አዲስ ነገር ደግሞ ሁሌም በውስጡ የሚነገር ወሬ አያጣውም ፡፡ አዲስ ጉዳይ እስከ አሁን ስለ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለንባብ ካበቃቻቸው ጉዳዮች ውስጥ የዛሬውን ርዕሰ ጉዳይ ለዳሰሳ መርጦት አያውቅም፡፡ ይህም የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉት ሃይማኖት የግል በመሆኑና ይህም እምነታቸው በፖለቲካ ህይወታቸው ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ለንግግር የሚያበቃ ጉዳይ እስካልፈጠረ ድረስ ነገሩ እንደ አንድ ጉዳይ አንስቶ ማራገብ ፋይዳ የለውም ተገቢም አይደለም በሚል እምነት ነው፡፡

Saturday 3 November 2012

በሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ትምህርት ከተቋረጠ ከሁለት ወራት በላይ ኾኖታል

የስድሳ ዓመት ዕድሜ ባስቆጠረ ሥርዐተ ትምህርት ወደ ኮሌጅ ደረጃ አድጓል የተባለው ተቋሙ “የዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመር ዝግጅት አጠናቀናል” ብሏል፤

ደቀ መዛሙርቱ በበኩላቸው “ሥርዐተ ትምህርቱ አልተለወጠም፤ ኮሌጁም አላደገም፤ ቦታው አልሚ አላገኘም” እያሉ ነው፤
ደቀ መዛሙርቱ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ውሳኔ በጉጉት እየተጠባበቁ ነው
የኮሌጁ ዋና ዲን ቀሲስ በላይ መኰንን ለፕሮቴስታንቱ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሺፈራው ተክለ ማርያም÷ “ዘመነ ማቴዎስ የተጠሩበት[ን] ሐዋርያዊ አገልግሎት የበለጠ የሚፈጽሙበትና የሚያስፈጽሙበት ዘመን እንዲኾንልዎ ምኞቴን ስገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው፤” በማለት በኮሌጁ የፕሮቶኮል ደብዳቤ የመልካም ምኞት መግለጫ ጽፈውላቸዋል፤ /ሰነዱን ይመልከቱ/፡፡

Friday 2 November 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ መግለጫም በማውጣት ተጠናቀቀ


  • ምልአተ ጉባኤው የዕርቀ ሰላሙንአምስት የመነጋገሪያ ነጥቦች ለይቷል፤
  • ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ደቡብ እና ምዕራብ አዲስ አበባን፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል ሰሜንና ምሥራቅ አዲስ አበባ አህጉረ ስብከትን ይመራሉ፤
  • “የመነኰሳት መተዳደሪያ ደንብ” ይወጣል፤ የገዳማት ተወካዮች በመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ዓመታዊ ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉና ሪፖርት እንዲያቀርቡ ይደረጋል፤
  • ለአኵስም ጽዮን ማርያም አዲስ ንቡረእድ ይሾማል፤
  • ለካህናት ማሠልጠኛ፣ ለገዳማት፣ ለአብነት ት/ቤቶች (ብር 10 ሚልዮን+) እና ለሌሎችም የልማት ዕቅዶች ማስፈጸሚያ ከብር 128 ሚልዮን በላይ በጀት ተመድቧል፤
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 21/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 31/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ላለፉት ዐሥር ቀናት በሥራ ላይ የቆየው የጥቅምት 2005 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ፣ ጥቅምት 21 ቀን 2005 ዓ.ም ላይ መግለጫ ተጠናቀቀ፡፡ በ“ልዩ ልዩ ጉዳዮች” አጀንዳዎች ሥር በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሰውና የበጀት ምደባን ጨምሮ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቀደም ሲል ውሳኔ ያሳለፈባቸውን የመነጋገሪያ ነጥቦች ዳግመኛ በጥልቀት ሲመለከት የቆየው ምልአተ ጉባኤው÷ ከኅዳር 26 - 30 ቀን 2005 ዓ.ም በዳላስ ቴክሳስ ለሚካሄደው የዕርቀ ሰላም ውይይት የቅዱስ ሲኖዶሱ ልኡክ መነጋገሪያ (መደራደሪያ?) የሚያደርጋቸውን አምስት ነጥቦች መለየቱን ለመረዳት ተችሏል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶሱን አቋም የሚገልጡ ናቸው የተባሉት አምስቱ ነጥቦች “የሰላምና አንድነት ጉባኤው” ላቀረባቸው ሰባት ጥያቄዎች በተሰጡ መልሶች ላይ በመመሥረት የተዘጋጁ መኾናቸውን የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች አስረድተዋል፡፡

ዜና ሕይወቱ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ


ከደቂቀ ናቡቴ ድረ-ገጽ ላይ የተወሰደ

ልደቱ 

የወርቃማው ዘመን ወርቃማ ደራሲ፣ መናኝ፣ ጻድቅ፣ ሊቅ፣ የሕዝብ መምህር እና የሥነ ምሕንድስና ባለሙያ የሆነው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የተወለደው በ1357 ዓመተ ምሕረት በወሎ ክፍለ ሀገር በዛሬው ቦረና በጥንቱ ወለቃ ወረዳ ሸግላ በተባለ ቦታ ነው፡፡ አባቱ ሕዝበ ጽዮን እናቱ እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ስለ አባቱ ሕዝበ ጽዮን ሁለት የተለያዩ ታሪኮች ይተረካሉ፡፡ የሰኔ ድርሳነ ዑራኤል ምንባብ አባቱ በመጀመሪያ የትግራይ በማስከተል የሰግላ /ጋሥጫ/ አገር ገዢ እንደነበር ይወሳል፡፡ ገድሉ ደግሞ /ጠቢብ ወማእምረ መጻሕፍት ወአቡሁኒ መፍቀሬ እግዚአብሔር አምኁልቈ ካህናተ ደብተራ ዘውሳጤ ዓጸደ ቤተ ንጉሥ/ አባቱም የእግዚአብሔር ወዳጅና በቤተ መንግሥት በነበረችው ድንኳን /ሥዕል ቤት/ ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ነበረ ይላል፡፡ እንደ ገድሉ ገጸ ምንባብ ትርጉም ሕዝበ ጽዮን ከንጉሡ ሥዕል ቤት በቅዳሴ ወይም በማሕሌት ከሚያገለግሉ ካህናት አንዱ ነው፡፡ /. . . ወእሙኒ እም ሥዩማነ ወለቃ/ እናቱም ከወለቃ ሹማምንት ወገን ነች ይላታል፡፡ ይኸውም የጥንቱ ወለቃ /የዛሬው ደቡብ ወሎ፣ ቦረና ከላላ/ ከነበሩ መኳንንት ወገን መሆኗን ያመለክታል፡፡      የአባ ጊዮርጊስ ወላጆች ልጅ ሳይወልዱ ለረጅም ዓመታት ቆይተዋል፡፡ የልጅ ፍላጎታቸው እንዲሠምር ለሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተሳሉ፡፡ ስእለታቸውም ሥምሮ በመልአኩ ቀዱስ ዑራኤል አብሣሪነት ወንድ ልጅ ወለዱ፡፡ ልጃቸውን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመማጸን ስለወለዱ ስሙን ጊዮርጊስ ብለው ጠሩት፡፡ ወላጆቹ የታላቁን ሰማዕት ስም ለልጃቸው ያወጡት ወደ ፊት በዓላውያን ነገሥታት ፊት ምስክር፣ አፅራረ አምነትን አሳፋሪ፣ ካህናትንና ምእመናት በየዘመናቱ ከሚነፍሱ የኑፋቄና የክህደት ነፋሳት በወንጌል ብርሃን ነፃ የሚያወጣ ሲሉ ይህን ስም እንዳወጡለት ድርሳነ ዑራኤል እንዲህ ይተርካል፡፡ ‹‹ዘይከውን መምህረ ኵሉ ዓለም ወበጸሎቱ ዘያድኅን አሞተ ሲኦል ፍቁረ ድንግል ማርያም ወላዲቱ ለአማኑኤል፡፡ ወመገሥጾሙ ለነገሥት፡፡ ወፀሮሙ ለዐላውያን ሃይማኖት በሰይፈ ቃሎሙ ለሐዋርያት ዘያጠፍኦሙ እም ብሔረ ኢትዮጵያ፤ ወለካህናተ ጽድቅ ዘይመርሆሙ እምጽልመተ ኑፋቄ መንገለ ብርሃን ቃለ ወንጌሉ ለክርስቶስ በትምህርተ ሕጎሙ ለሐዋርያት›› ይላል፡፡
ትምህርት :-አባ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ ደረጃ መንፈሳዊ ትምህርቱን ከወላጅ አባቱ ሕዝበ ጽዮን እንደተማረ ይገመታል፡፡ አባቱ የመጀመሪያ ደረጃ ተምህርቱን ካስተማሩት በኋላ መዐርገ ዲቁና እንዲቀበል ማድረጋቸውን  ገድሉ ይነግረናል፡፡ ወሶበ ልህቀ ሕቀ ወሰዶ ኀበ ጳጳስ ወሴሞ ዲያቆነ፡፡ ባደገም ጊዜ ከጳጳስ ዘንድ ወሰደው ጳጳሱም በዲቁና አሾመው ይላል ገድሉ፡፡ ዲቁና መቀበሉን እንዲ መዓርገ ዲቁና የሰጡትን ጳጳስ ስም አይገልጽም፡፡ ዳሩ ግን መዓርገ ዲቁናን በ1341 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እስከ ዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ አካባቢ ከነበሩት ብፁዕ አቡነ ሰላማ መተርጉም እንደተቀበለ ይገመታል፡፡