Thursday 16 August 2012

የአቡነ ጳውሎስ ጳውሎስ ዜና ዕረፍት አጭር ሪፖርታዥ


  • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል፤ መኖሪያ ቤታቸውና ቤተ መጻሕፍት ወመዘክሩ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ታሽጓል፤
  • ጥቂት ብፁዓን አበው ወደ ባልቻ ሆስፒታል ሄደዋል፤ አስከሬናቸው በባልቻ ሆስፒታል ይገኛል፤ ጥቅመኛዋ እጅጋየሁ በየነ “አልሞቱም፤ አስከሬናቸው ይመርመርልኝ” እያለች በማወክ ላይ ትገኛለች::
     ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአድባራትና ገዳማት አለቆች በአስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲገቡ ጥሪ ተደርጓል::
  • የአቡነ ጳውሎስን ቀብር የሚያስፈጽም ኮሚቴ በመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ ጽ/ቤት ተቋቁሟል::
  • ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይሾማል፤ ከቋሚ ሲኖዶሱም ጋራ እየመከረ ይሠራል::(ሕገ ቤተ ክርስቲያን)
  • “ውሉደ ጳውሎስ” /እነ እጅጋየሁ በየነ/ በፓትርያርኩ ስም “ጳውሎስ ፋውንዴሽን”ለማቋቋም እየተሯሯጡ ነው፤ የሀብት ቅርምቱን ለማመቻቸት ይኾን?
  • በፓትርያርኩ በተለያዩ ዘመዶቻቸው ስም በአንድ የመንግሥታዊው ባንክ ቅርንጫፍ ሦስት አካውንቶች ውስጥ ከ22 ሚልዮን ብር በላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/READ THIS NEWS IN PDF) ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ፣ ነሐሴ 10 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ንጋት ላይ በዳጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡



(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 10/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 16/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ኻያኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን ከሐምሌ 5 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ወሩ መገባዳጃ ሲያከበሩ የቆዩት አምስተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ነሐሴ 8 ማምሻውን ወደ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ማረፋቸውን ምንጮቻችን እየገለጹ ነው። አቡነ ጳውሎስ በምንገኝበት የፍልሰታ ለማርያም ጾም የሰሞኑ ውሏቸው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ፓትርያርኩን ለሕልፈት ያበቃውን ሕመም ለይተው አልገለጹም፡፡

እግራቸው ከጉልበታቸው በታች በከፍተኛ ደረጃ መጎዳቱንና የጤናቸው ኹኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ የሚነገርላቸው ፓትርያርኩ÷ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንደሚስተዋለው የአባ ጳውሎስ መውጣትና መግባት ግራና ቀኝ በሚይዟቸው ሰዎች ድጋፍ እንደሚከናወን የተዘገበ ሲሆን ራሳቸውን ችለው መራመድ ይኹን ከመኪናቸው መውጣትና መውረድም እንደተሳናቸው ተመልክቷል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ለረጅም ጊዜ ሕመማቸውን ሲከታተሉ በቆዩበት የደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል ዶክተሮች ከፍተኛ ክትትል ላይ መኾናቸውንና አስጊ በሚባል ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ምንጮችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ደጀ ሰላም ዜናውን እየተከታተለች ማቅረቧን ትቀጥላለች።

ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡