Thursday 22 August 2013

በቄሣራውያን መዳፍ ሥር ያለ አስኬማ(ክፍል-1)

በታደሰ ወርቁ ከፌስ ቡክ ገጹ ላይ የተወሰደ


ይህ ጹሑፍ በእነ ተመስገን ደሳለኝ -ፋክት መጽሔት ላይ በሁለት ተከታታይ ክፍል የወጣ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛ ፓትርያርክ የነበሩት እና በአዛጋቢነታቸው የሚታወቁት ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ ጳውሎስ ቅጥ በአጣው አምባገነናዊነታቸው የተነሣ በቅጡ ሳይዘከሩና አስክሬናቸውም ያረፈበት ስፍራም ለመዓርጋቸውም ሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብር በማይመጥን መልክ በቆርቆሮ እንደታጠረ  እነሆ የሙት ዓመት መታሰቢያቸው ዋዜማ ላይ እንገኛለን፡፡                                                                                                ቅዱስነታቸው የሙት ዓመት መታሰቢያ ዋዜማ ላይ መሆናችንን ከተገነዘብን ሦስት መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሳታችን አይቀርም፡፡ የመጀመሪያው ተሰያሚው ፓትርያርክም ሆኑ ጳጳሳቱ ከአምስተኛው አወዛጋቢ ፓትርያርክና ከዘመነ ፕትርክናቸው ውድቀት ምን ተምረው ምን አደረጉ ? የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ  የቅዱስነታቸውን ሞት እንደ አንድ  ምቹ አጋጣሚ በመቁጠር በቀኖና ተጥሷል-አልተጣሰም ጭቅጭ የተነሣ የተከፈለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅራዊ አሐቲነት ለማከም ምንድ ተደርጉነው ውጤቱ እንዲህ የከፋው? የሚለው ነው፡፡  ሦስተኛው  ከአምስተኛው ፓትርያርክ ሞት በኃላ በእውንነታቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን  ወደ ቅድመ ግራኝ ክብሯና ልዕልናዋ  ይመልሷታል ተብለው ተስፋ  የተሰነቀባቸው የተቋማዊ ለውጥ  እንቕስቃሴዎች እና የፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊነት  ከየት ተነስተው በምን መልኩ ተደመደሙ  ? የሚለው ነው፡፡        
  ከእነዘህ ሦስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በመነሳት  ስንገመግምና አሁን እየሆነና እየተደረገ ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ተቀጥፋ ያልደረቀች  አበባን መስላለች፡፡ያውም አጥር ቅጥር የሌላትን፡፡የሚቀጥፏት ወጪዎቹና ወራጆቹ ጆቢራዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ወርቋን እንጂ የወርቁ መገኛ መሆኗን የዘነጉ ጳጳሳት መሆናቸው ደግሞ ነገሩን ግራ ያደርገዋል፡፡            
             ተቀጥፋ  እንዳትደርቅ  ተጨማሪ  አጥር ቅጥር ያበጃጁላታል ተብለው የተሾሙት  አበው ጳጳሳት አጥር ቅጥር መዝለላቸው ሳያንስ  ቀደምት አበው የሠሩትን  የእርቀ ሠላም ፣ዘመንን  የዋጀ ተቋማዊ  ለውጥና ሢመተ ፕትርክና  የሚመራበትን አጥር ቅጥር  አፍራሽ ኀይለ ግብር ሆነው ከመገለጣቸው በላይ ምን ግራ ያጋባል? ፡፡ 
ይህም ሆኖ አለመድረቋና በወርኃ ጽጌ እንደ አሉ አበባዎች ልምላሜ ሃይማኖትና መዐዛ ምግባር ከምዕመኑ አለመጥፋቱ እጅግ ይደንቃል፡፡ይህ የሆነው ግን    የሐዋርያት ውሳኔ በሆነው  በመጽሐፈ ዲድስቅልያለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ኤጴስ ቆጶስ ሆኖ  የሚሾመውየምዕመናን ጠባቂ፣ነውረ የሌለበት፣ንጹሕና ቸር፤ የዚህንም ዓለም ጭንቀት የማያስብ ፣፶ ዓመት የሞላው፣ የጉልማሳነትኀይልን ያለፈ፣ ነገር  የማይሠራ፣ በወንድሞች መካከል ሐሰትን  የማይናገር  ይሆን ዘንድ  እንደ ሚገባው በጌታችን ኢየሱስክርስቶስ ዘንድ ሰማን፡፡በሚለው አምላከዊ ድንጋጌ መሠረት የተሾሙ ወይም ሆነው የተገኙ ጳጳሳት  ሰላሉን  አይደለም፡፡ጌታ ሰለ ቃልኪዳኑ ሰለሚጠብቃትና የቀደምት አበውና እመት በረከተ ጥላ ከለላ ሰለሚሆናት ብቻ ነው፡፡/ዲድስቅልያ4 1 /                                                                                                                         
           ቀድሞም አብዛኛቹ  በዚህ ውሳኔ  መሠረት ባለመሾማቸው እና በኃላም መለካውያን-ፈጻሚ ፈቃድ ቄሣር ሆነው መገኘታቸው  ጵጵስናቸውን አስኬማ  መላእክት አለመሆኑን ከማጋለጡም  በላይ አስኬማ ቄሣር አድርገን እንድንወስድ አድርጉናል ፡፡                                                                                                                                    
የቤተ ክህነቱ የችግር ሰኮፍ ከነአቶ ስብሐት ነጋ ቢመዘዝም  እዚህ ጋ ብቻ ከአቶ ስብሐት ነጋ  አሳብ ጋር እንድስማማ እገደዳለው፡፡ይኸውም  እነርሱ መጥተው ተጣበቁብን  እንጂ እኛ መች  ሔድንባቸውከሚለው  ጋር፡፡ የአብዛኛዎቹ  ጳጳሳት  የነገር ማንጸሪያ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረት እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮ፣ቀኖናና ትውፊት ሳይሆን  ፈቃደ ቄሣር መሆኑ የአቶ ስብሐትን አሳብ ትክክል ያደርገዋል፡፡ሕገ ቤተ ክርስቲያን ምን ይላል? ከሚለው ይልቅ ቄሣራውያን ምን ይላሉ?የሚለው ቀልባቸውን በሚገዛ  ጳጳሳት በተወረረች ቤተ ክርስቲያን ሰለ እርቀ ሠላም፣ስለተቋማዊ  ለውጥና ሰለፓትርያርክ ምርጫ ውጤታማነት በራሱ ማሰብ አሰብኩ ፣አሰብኩናደከመኝ” እንዳለው ልጅ ነው ነገሩ ፡፡