Wednesday 25 July 2012


ተቋምን በተቋም


Egyptian Coptic activists declare creation of Christian Brotherhood

The Christian Brotherhood has branches in 16 governorates in Egypt as well as three branches in Europe and one in Australia. (Reuters)

A group of Coptic activists in Egypt announced the establishment of the Christian Brotherhood to counter the growing influence of the Muslim Brotherhood especially after their candidate Mohammed Mursi won the presidential elections.


ውድ የእንደማመጥ አንባቢያን


ይህቺ ድረ ገጽ የተጀመረችበት ዋና አላማ ኢትዮጵያ ውስጥ ደጀ ሰላም እና አንድ አድርገን በፓትርያርኩ ግብረ አበሮች እና በመንግስት አማካኝነት እንዳይነበቡ በመደረጋቸው የተፈጠረውን የመረጃ ክፍተት ለመሙላት ነው። 
በእርግጥ ተራዋ ደርሶ እርሷም መዘጋቷ አይቀርም ሆኖም ግን እስከዛው ድረስ ስለቤተክርስትያን አጥብቀው ማወቅ መስማት ለሚፈልጉ ወንድም እና እህቶች በሚስጥር መልእክት  (PRIVATE MESSAGE) በመለዋወት መንፈሳዊ እና ታሪካዊ ግዴታችንን እንወጣ። 


ማሳሰቢያ
እባክዎን በፌስቡክ ገጽዎ ወይም ግሩፕ ላይ(share) እንዳያደርጉ
ሰላመ እግዚአብሄር ከሁላችን ጋር ይሁን አምላከ ቅዱሳን ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን 




የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክነት ማዕርግ የተቀዳጀችበት የነጻነት በዓል - በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ - አከባበር የመንፈሳዊ ውርደትና የምዝበራ መንገድ ኾኗል




(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 16/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 23/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሙስና፣ ብኵንነት፣ ኑፋቄ እና ዐምባገነናዊ አሠራር የነቀዘው የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና 20 ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ ምሽት ለሁለተኛ ጊዜ በሼራተን አዲስ ይከበራል። የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና ራእይ ለትውልድ /Vision for Generation/ የተባለው አካል የጥቅም ትስስር የፈጠሩበት የሼራተኑ በዓለ ሢመት ዝግጅት በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይኹን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት አይታወቅም።


የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአብያተ እምነት መሪዎች፣ አምባሳደሮችና ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ እስከ 1500 እንግዶች ይታደሙበታል በተባለው ይኸው ዝግጅት ከጥቅም ትስስር ባሻገር÷ በግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ እና ውሳኔዎች ክፉኛ የተጋለጠውን የአባ ጳውሎስን ማንነት ለማደስ የታሰበበት ‹የሕዝብ ግንኙነት› ሥራ እንደኾነ ተጠቁሟል። በበዓለ ሢመቱ አከባበር የቀደሙት ፓትርያርኮች መልካም ስምና ዝና በተለያዩ ስልቶች እየተንኳሰሰ በምትኩ በሙስና፣ ኑፋቄ እና ዐምባገነናዊ አሠራር የተበሳበሰው የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና የሥራ ክንውን ብቻ “በወደር የለሽነት” /በእንግሊዝኛው የበዓለ ሢመት ኅትመት ላይ እንደተገለጸው - ‘unparalleled efforts/ እንደ ግለሰብ መሞገሱ ብዙዎችን አሳዝኗል።


“ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ” ለመመስረት ጥያቄ መቅረቡ ተሰማ


  •   መንግስት በጥያቄው ደንግጧ
  •    “ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ፡፡” የኢትዮጵያ ህገ መንገስት አንቀጽ 31

(አንድ አድርገን ሐምሌ 18 2004 ዓ.ም)፡- የሀገሬ ሰው “የባሰ አለና ሀገርህን አትልቀቅ” ይላል ፤  በአሁኑ ሰዓት  እንዲህማ አይታሰብብ የምንለው ጉዳይ እንደ ትልቅ ጉዳይ ብቅ ብሏል ፤ ይህ ጥያቄ ውስጠ ወይራ ነው ፤ መንግስት የሚደሰኩርለትን ዲሞክራሲን መሰረት አድርጎ የውስጥን አላማ ለማሳካት የተነሳ ጥያቄ ፤ ካለመጠይቅ ደጃዝማችነት ይቀራል በማለት የተነሳ ወቅታዊ ጥያቄ ፤ ሙስሊሙን ነጻ አወጣለው በማለት የሙስሊምን የበላይነት ለማረጋገጥ ሲባል የዘመናት ጥያቄዎቻውን ለመመለስ ያመቻቸው ዘንድ የጠየቁት ጥያቄ ፤ ……


መወቀር - በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ


ክርስትና ሰዉነት ለክርስቶስ ማደሪያ መቅደስነት የተሠራበት የድኅነት መንገድ ነው፡፡ሰው በነፍሱ ወይም ከትንሣኤ በኋላ ባለው ሕይወቱ ብቻ ሳይሆን በዚህ ምድር በሚኖርበት ጊዜም ሰዉነቱ የክርስቶስ ማደሪያ መቅደስ፣ኅሊናዉ ቃሉ የተቀረጸበት ጽላት፣ ልቡናዉም  የበጎ ነገር ሁሉ ማደሪያ ታቦት እንዲሆን የተዘጋጀ ነዉ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ‹‹ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?...  ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? በዋጋ ተገዝታችኋልና ለራሳችሁ አይደላችሁም፤ ስለዚህ በሥጋችሁ እግዚአብሔርን አክብሩ›› /1ኛ ቆሮ 6፤ 13- 19/ ሲል እንደገለጸልን ሰዉነታችን ለእኛ ፍላጎት ማከማቻነት የተዘጋጀ ቁምሳጥን ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም የተሰጠን ቅዱስ ንዋይ ነው፡፡ ሐዋርያዉ እንደገለጸዉ ገንዘብነቱም ለእግዚአብሔር ነዉ፡፡  አገልግሎቱም እግዚአብሔርን ማክበር ነው፡፡