Thursday 28 March 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት የመብት ጥያቄ በተሃድሶ መናፍቃን አጀንዳ ተጠለፈ



  • የደቀመዛሙርቱ አካዳሚክ፣ አስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ወደ ግለሰቦች ኃላፊነት ማስነሳት በሚል ቅድመ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡
  • “ተቃውሞውን አስተባብረሃል” በሚል ታስሮ የነበረው ደቀመዝሙር ከእስር ትናንት ተፈትቷል፡፡
  • የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጅ የሆኑ ተማሪዎች ተቃውሞውን ኦርቶዶክሳውያንን ከኮሌጆ ቁልፍ ቦታ በማስወገድ በመናፍቃን ለመተካት በኅቡዕ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

(አንድ አድርገን መጋቢት 19 2005 ዓ.ም)፡- የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በኮሌጁ ስላለው የአስተዳደር ጉድለት ፣ የትምህርት ጥራት ማነስና የምግብ አቅርቦት ጥራት መጓደል ተቃውሟቸውን በትምህርት ማቆምና የረሃብ አድማ በማድረግ እየገለጹ ነው፡፡ በርካታ መገፋት ቤተክህነቱ  እያደረሰባቸው የሚገኙት የነገረ መለኮት ምሩቃንና ደቀ መዛሙርት ያቀረቡት ተቃውሞ የቤተክህነቱን አስተዳደረዊና መንፈሳዊ ድቀት ርቀት እንደ ማሳያ ተደርጎ ተወስዶአል፡፡

፩ የቅዱሳን አባቶች ህይወት

ከዝክረ ቅዱሳን ዘተዋህዶ ቁ.፪
ትርጉም  በሃዜብ በርሄ

"እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንኩት እርሱንም እሻለሁ በህይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኘውን አይ ዘንድ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።" መዝ 26:4

የቅድስና መሰረቱ ራስን መቆጣጠር መቻል፣የሚሰሩትንም ሆነ የሚናገሩትን ማስተዋልና ጠንቅቆ ማወቅ፣ ጎጂ ከሆኑ ልማዶች ራስን መቆጠብ፣ የሌሎችን ጉድለትና ስህተት ከማጉላት ይልቅ ፍቅረ እግዚአብሔርን እያሰቡ ከመልካም ምግባራቸው መማር መቻል፣ እኔ ከሁሉ ያነስኩ ነኝ ብሎ ማመንና ከምንም በላይ ደግሞ ከቤተ መቅደሱ አለመራቅ...ወዘተ ነው።ቅዱሳን አባቶች ፍቅራቸው ራስን አሳልፎ እስከመስጠት ነውና እውነተኛና ከቅን ልቡና የመነጨ ፍቅር መሆኑ አያጠያይቅም። ስለ ሃይማኖታቸው አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ጀርባቸውን ለግርፋት፣ ፊታቸውን ለጽፋት ነፍሳቸውን ለሞት የሰጡና "ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ "ማቴ 5:6 የመጨረሻ ግባቸው የመንግስቱ ወራሾች መሆን ነው።

"ከዓለም ምንም አልፈልግም"


በአያሌው ዘኢየሱስ

ይህ ቃል አንድ ሰው የነፍሱን ነጻ መውጣት በሚሻበት ጊዜ ቅድሚያ ሰጥቶ ሊናገረው የሚገባው ቃል ነው።
ዓለም ያሏት ፈተናዎች ብቻ እንጂ ምንም የሚወደድ ነገር ስለሌላት ከእርሷ ምንም አልፈልግም።
ዓለም ለመስጠት በጣም ድሀ ስለሆነ ከእርሷ ምንም አልፈልግም። እኔ የምፈልገው ሁሉ በዓለም ካለ ዓለም ገነት ሆናለች ማለት ነው። በውስጧም ከቁሳዊ ነገሮች በስተቀር ምንም የለም። በእርግጥ እኔ የምፈልገው ሰማያዊ ነገሮችን ነው። ለመንፈሳዊ ህይወቴ እንዲጠቅመኝ።