Wednesday, 26 September 2012
Thursday, 20 September 2012
እናቁም?
አንዳንዴ የትግላችን፣የጥረታችን፣የልፋታችን ውጤት መና የቀረ የሚመስልበት ጊዜ አለ፡፡ ውኃ አልቋጥር፣ ጠብ አልል ሲልብን፤ መንገዱ ሁሉ ረዥም፣ በሮቹ ሁሉ ዝግ፣ ጩኸቱ ሁሉ ሰሚ አልባ ሲመስለን፣ በመጨረሻ የምንወሰደው መፍትሔ ነገር ዓለሙን ሁሉ መተውና መሸነፍ ይሆናል፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ አበቃ›› ማለት እንጀምራለን፡፡ እንኳን እኛ ቀርቶ ሌሎች እንኳን እንዳይበረቱ ‹‹ባክህ እኛም ብለነው ብለነው አቅቶን ነው›› እያልን ተስፋ እናስቆርጣቸዋለን፡፡ግን ሰው መልፋት ያለበት፣ መትጋትስ ያለበት፣ መታገልስ ያለበት፣ መሮጥስ ያለበት እስከ የት ነው?ሰው ተስፋ መቁረጥ ያለበት የት ደረጃ ሲደርስ ነው? የመንገድ ማለቂያው የት ነው? ውጤቱን ዛሬ ያላየነው ነገር ሁሉ ውጤት አልባ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላልን? በታሰበው ጊዜ ያልተደረሰበት ነገር ሁሉ ሊደረስበት የማይችል ነገር ነው ማለት ነው? መንገዱስ ይሄ እኛ የያዝነው መንገድ ብቻ ነውን? በሌላ መንገድስ ሊሞከር አይቻልምን?መሆኑ ከማቆምና ከመቀጠል የትኛው ይመረጣል? ከማቆም ምን ይገኛል? ከተስፋ መቁረጥ በቀር፡፡ የሚጓዝ ሰው ጊዜው ይረዝም ይሆናል እንጂ አንድ ቀን የሚፈልገው ቦታ ይደርሳል፡፡ የቆመ ሰው ግን እንኳን ወደሚፈልግበት ለመሄድ ወደ ተነሣበት ቦታም ተመልሶ አይደርስም፡፡ የሚታገል ሰው አንድ ቀን ያሸንፋል፤ ያቆመ ሰው ግን ሳይማረክ እጁን ሰጥቷል፡፡ ደጋግሞ የሚያንኳኳ ሰው ከተኙት ሰዎች አንዱን መቀስቀሱ አይቀርም፤ ማንኳኳት ያቆመው ግን እንኳን ሊቀሰቅስ ራሱም ይተኛል፡፡ የሚሄድ መኪና ጋራጅ ይደርሳል፤ የቆመ መኪና ግን ባለበት ይወላልቃል፡፡ ለማሸነፍ ትልቁ መፍትሔ አቋምን መቀየር ሳይሆን መንገድን መቀየር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን መሞካከር ሳይሆን አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መሞከር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ማየት ሳይሆን አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማየት መቻል ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በውሳኔ ጊዜ መቁረጥ መቻል ነው፡፡ የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡ሁለት ዕንቁራሪቶች እየተጓዙ ነበር፡፡ አንዷ ወፍራም ሌላዋም ቀጭን ነበሩ፡፡ እንዳጋጣሚ በገረወይና የተሞላ ወተት አገኙና ሰፍ ብለው ገቡበት፡፡ እዚያም አስኪበቃቸው ጠጡና ሲጠግቡ መውጣት ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ውስጡ ያንዳልጥ ስለ ነበር ለመውጣት አልቻሉም፡፡ እግራቸውን ባንቀሳቀሱ ቁጥር ወተቱ እያንዳለጠ እዚያው ይጨምራቸዋል፡፡ ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ድረስ እጅግ ደከሙ፤ ነገር ግን ከድካም በቀር ያተረፉት ትርፍ አልነበረም፡፡በምን ቀን ነው እዚህ ወተት ውስጥ የገባነው? እያሉ ቀናቸውን የሚያማርሩበት ሰዓት ላይ ደረሱ፡፡
Friday, 14 September 2012
Thursday, 13 September 2012
"የዕርቀ ሰላም ሂደቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል" ቅ/ሲኖዶስ አስታወቀ
Posted by DejeS ZeTewahedo
- “የሃይማኖት መሪዎች ጊዜ ሳያልፍ አንድነታቸውን እንዲያጠነክሩ ጸሎቴ ነው” /ፕ/ር ኤፍሬም ይሥሐቅ/
- ከመጪው ግንቦት በፊት የሚፈጸም የፓትርያርክ ሹመት እንደማይኖር እየተነገረ ነው::
- ማኅበረ ቅዱሳን ስለዕርቀ ሰላሙ ያለውን አቋም በግልጽ ዐውጆ ሂደቱን እንዲያግዝ ተጠይቋል::
- “በአሐቲ ቤተ ክርስቲያን መርሕ የቤተ ክርስቲያን ፍጹም አንድነትና ሰላም እንዲጠበቅ እንሠራለን” /የነገረ መለኰት ምሩቃን ማኅበር/::
(ደጀ ሰላም፤ መስከረም 2/2004 ዓ.ም፤ September 12/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቅርቡ በመንግሥት በኩል ይኖራል ተብሎ የሚጠበቀው የአመራር ሽግግርና የሚተካው ርእሰ መንግሥት ከተለወጠው ዘመንና ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኅልፈት ጋራ ተያይዞ ከታየው የሕዝብ ጨዋነት፣ ይቅር ባይነትና ርኅራኄ አኳያ የሚመጥኑ ተፈላጊ ለውጦችን ለማምጣት የሚያስችል እንዲኾን እየተጠየቀ ባለበት በአሁኑ ወቅት በቤተ ክህነቱም በኩል ከቀጣዩ ርእሰ አበው ሹመት አስቀድሞ መከናወን ያለባቸው ተግባራት እንዳሉ እየተገለጸ ነው፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩና በፓትርያርኩ ኅልፈት ተገቢውን ሰው መተካትና የተፈጠረውን ክፍተት ማሟላት ሕገ መንግሥታዊ እና ሕገ ቤተ ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ በግዴታው አፈጻጸም ሂደት የሚታየው የመንግሥት ይኹን የቤተ ክህነት ባሕርይና ብቃት ለየራሱ ከጎሰኛነትና ጥቅመኛነት በላይ ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያንን በማስቀደም ሊጠናቀቅ እንደሚገባው ተመልክቷል፡፡
የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: እናቁም?
የዳንኤል እይታዎች Daniel Kibret's views: እናቁም?: አንዳንዴ የትግላችን፣የጥረታችን፣የልፋታችን ውጤት መና የቀረ የሚመስልበት ጊዜ አለ፡፡ ውኃ አልቋጥር፣ ጠብ አልል ሲልብን፤ መንገዱ ሁሉ ረዥም፣ በሮቹ ሁሉ ዝግ፣ ጩኸቱ ሁሉ ሰሚ አልባ ሲመስለን፣ በመጨረሻ የምንወሰ...
Monday, 10 September 2012
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል፣ የኢ/ኦ/ተ/ ቤተ ክርስቲያን አቃቤ መንበረ ፓትርያርክየአዲስ ዓመት መልእክት አስተላለፉ
(ደጀ ሰላም፤ ጳጉሜን 4/2004 ዓ.ም፤ September 9/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ አዲሱ የቤተ ክርስቲያናችን አቃቤ መንበር እና የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል አዲሱን ዓመት አስመልክተው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ብፁዕነታቸው ያስተላለፉት መልእክት ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ሰፍሯል። ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
Ø በሀገራችን ኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
Ø የሀገርን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣
Ø በደዌ ዳኛ በአልጋ ቁራባ ተይዛችሁ በየሆስፒታሉ የምትገኙ፣
Ø የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በማረሚአ ቤት ያላችሁ፣
Ø በተለያየ ምክንያት ከሀገራችሁ ከኢትዮጵያ ወጥታችሁ በዓለሙ ሁሉ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያት በሙሉ፤
የዘመናት ጌታ እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ማቴዎች 2005 ዓ.ም በሰለማም አደረሳችሁ፤ ለሚቀጥለውም ዘመን በቸርነቱ ጠብቆ በሰላምና በጤና እንዲያደርሳችሁ ቤተ ክርስቲአናችን ዘወትር ጸሎቷን ወደ ፈጣሪ ታቀርባለች።
“ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ስብሐተ ሐዲሰ”. “እግዚአብሔርን በአዲስ ምስጋና አመስግኑት” ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት (መዝ. 149 ቁ. 1)
ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ባለፈው ዓመት ስለተደረገልን መልካም ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን ማመስገን፣ በአዲሱ ዓመትም በአዲስመንፈስ አዲስ ሥራን ለመሥራት እንዲረዳን የልመና ጸሎት ማቅረብ ይገባናል።
የሰው ልጅ በዘመን ተወስኖ የሚኖር ሲሆን፣ እግዚአብሔር አምላካችን በዘመን፣ በዘመናት ሳይወሰን የነበረ፣ ያለና የሚኖር ዘለዓለማዊ አምላክ ነው፤ ዘመናትን መቁጠር የተጀመረውም እግዚአብሔር የሥነ ፍጥረታትን ሥራ ከጀመረበት አንሥቶ መሆኑን የሥነ ፍጥረት ታሪክ ያረጋግጣል። በስድስተኛውም ቀን የተፈጠረው ሰው ወደ ሥራ የገባው ከተፈጠረበት ጊዜ አንሥቶ መሆኑ ግልፅ ነው።
በመሆኑም የሰው ልጅ የኖረበት ዘመን ሁሉ የሥራና የታሪክ መን ሁኖ ይታያል። ከዚህ አንፃር ሁሉም ኅብረተ ሰብ መልካም ታሪክን ለማስመዝገብ በተሠለፈበት ዓላማ የሚጠበቅበትን ድርሻ ማበርከት ይኖርበታል።
በአዲስ ዓመት፣ በአዲስ ዕለት እግዚአብሔርን ለማመስገን አዲስ ምክንያትን ይሰጠናል፤ እግዚአብሔር በየቀኑ ለእኛ አዲስ ነገርን እያደረገልን ነው፤ ምሕረቱና ቸርነቱ በየማለዳው አዲስ ነው፤ እኛም ስለ ምሕሩ ቸርነቱ ምስጋናን ማቅረብ እንደሚገባን “እግዚአብሔርን በአዲስ ምስጋና አመስግኑት” ተብሎ ተጽፏል።
ሁል ጊዜ አዲስ ዓመት፣ አዲስ ዕለት ማለት የተለመደ ነው፤ ነገር ግን አዲስ ዓመትና አዲስ ዕለት ማለት የዓመቱ መለወጥ ሳይሆን ከላይ እንደተጠቀሰው አዲስ ዕቅድ በማውጣት አዲስ ሥራን መ ራት ሲቻል ነው፤ ማለትም በአምልኮተ እግዚአብሔር የጸና፣ በፍቅር በሰላም የተመሠረተ፣ ሁሉንም ያካተተ የመኖር እንቅስቃሴ ሲኖር ነው።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እስመ ለለአሐዱ ዘዘዚአሁ ጸጋሁ፤ የእያንዳንዱ ስጦታ ልዩ ልዩ ነው፣ መንፈስ ግን አንድ ነው፣ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው፣ ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፤ በሁሉ ላይ አድሮ ሁሉን የሚያደርግ አንድ እግዚአብሔር ነው” ብሎ ተናግሮአል (1ቆሮ. 12፡4-5)።
በዚሁ መሠረት እያንዳንዳችን የምንሠራው ሥራ ሁሉ በታደልነው ጸጋ እግዚአብሔር መሠረት ነው። ባለፈው ዘመን ልንሠራው የሚገባንን ሠርተን ከሆነበአዲሱም ዘመን የበለጠ መልካም ሥራን መሥራት እንችላለን። ልንሠራው የሚገባንን ሳንሠራ እንዲሁ ጊዜውን በቸልተኛነት አሳልፈነው ከሆነ ደግሞ የዘመኑ መለወጥ ብቻ ፋይዳ የለውም።
ለሀገር ልማት፣ ለወገን ዕድገት የሚሆን ሥራን ሠርቶ በታሪክ አስመዝግቦ ማለፉ ለትውልደ ትውልድ የማይረሳ ታሪክ ሁኖ ይኖራል።
ሌላው በአዲሱ ኣመት ሊዘነጋ የማይገባው ዓቢይ ነገር ቢኖር ለበዓሉ ክብር ሲባል ለቤተሰባችን ከምናደርግላቸው በረከት እንዳይለዩብን ያለንን ሁሉ በማብቃቃት በተለያየ ምክንያት ወላጆቻቸው ሙተውባቸው ሰብሳቢ ያጡ ሕጻናትን፣ ጠዋሪ የሌላቸው ሽማግሌዎች አሮጊቶችን፣ የሰው ፊት አይተው የሚኖሩትን፣ ለችግር የተጋለጡትን፣ ለደዌ የተዳረጉትን ወገኖች በሀሉም አቅጣጫ መርዳት፣ እንደሚገባ ሃይማኖታዊም፣ ወገናዊም፣ ሰብአዊም ግዴታ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ልዩ ልዩ ባህሎች፣ ትውፊቶች እንደሚታዩባት የሚታወቅ ነው፤ አንዱ ለሌላው ባህል ያለውን አክብሮት ባለመንፈግ፣ በማክበርና በመከባብ ነቀፌታ ካለበት አመለካከትና ጠባይ በመራቅና በመቻቻል መኖር፣ አሁንም ሀገራዊ፣ ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ግዴታ ከመሆኑ ጋር ለአንድነታችንና ለሰላማችን ታላቅ ዋስትና አለው።
“ኢይፈርሆ ለእኩይ እስመ አንተ ምስሌየ፣ አንተ ከእኔ ጋር ከሆንክ ክፉውን ሁሉ አልፈራም” ይላል ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት (መዝ. 22፤4)
የመኖር ዋስትናውን በሕገ እግዚአብሔር የሚመራ ሰው ማናቸውም ፈተና ቢያጋጥመው እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለሆነ የሚደርስበትን ፈተና ሁሉ መቋቋምና መከላከል አያዳግተውም።
ስለዚህ በእምነትም ሆነ በባህል ልዩነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን፣ ኢትዮጵያውያት ወገኖች ሁሉ በተፈጥሮ ወገናዊነት - ሰው በመሆን ወዘተ. አንድ ሲሆኑ፣ ከመለያየት ይለቅ አንድነትን፣ ከጭካኔ ርህራሄን፣ ከመራራቅም መቀራረብን አጎልብተው ስለሀገር ሰላምና ዕድገት በአዲሱ ዓመት በአንድነት መንፈስ እንዲሠሩ በዚህ አጋጣሚ መልእክታችን በአጽንኦት ለማስተላለፍ እንወዳለን።
ጠቅላይ ሚኒስትራችን ክቡር አቶ መለስ ዜናዊ ወስመ ጥምቀቱ “ገብረ ማርያም” ሀገረ ሕይወት መንግሥተ ሰማያት ያግባልን፣ በዘመናቸው ተጀምሮ የነበረው የልማት፣ የዕድገት እንቅስቃሴ በተጀመረው ሁኔታ እንዲቀጥል አደራችንን ለሁሉም እናስተላልፋለን፤ በብፁዕ ወቅዱስ ዶክት አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ የኢትዮጵያ ክርስቲያን ፓትርያርክ ተጀምሮ የነበረውም መንፈሳዊው እንቅስቃሴና ዕድገት በነበረው ሁኔታ እንዲቀጥል አደራ እንላለን፤ ነፍሳቸውን ከቅዱሳኑ ጋር ይደምርልን።
እግዚአብሔር አምላካችን አዲሱን ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ አንድነት ዘመን ያድርግልን፣ ሕሙማኑን ይፈውስልን፣ ሕጻናቱን ያሳድግልን፣ የታሠሩትን ያስፈታልን፣ ወገኖቻችን ኢትዮጵያውያንን፣ ኢትዮጵያውያትን ሁሉ በያሉበት በፍቅር አንድነት፣ በስምምነት አኑርልን፣ የተዘራውን፣ የተተከለውን ለበረከት ለፍሬ ያብቃልን፤ ለሀገራችንና ለመላው ዓለም ሰላሙን ይስጥልን፣ ከሀገራችን ድህነትን፣ ኋላቀርነትን ለማስወገድ እየተደረገ ያለውን ጥረት ለውጤት ያብቃልን፣ ርዕሰ ዐውደ ዓመቱን በቸርነቱ ይባርክልን፣ ቸሩ እግዚአብሔር አምላክ ሁላችንንም ይጠብቅ፣ ይቀድስ አሜን።
አባ ናትናኤል
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
አቃቤ መንበረ ፓትርያርክ፣ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ጳጉሜን 5 ቀን 2004 ዓ.ም
Wednesday, 5 September 2012
Tuesday, 4 September 2012
ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጀው የሁለት ሱባኤ የምሕላ ጸሎት
ማውጫ፦ ዜና Posted by DejeS ZeTewahedo
- ለአገራችን መልካም መሪ ለቤተ ክርስቲያናችንም ደገኛ አባት እንዲሰጥ ጸሎት ይደረጋል::
- የተቀጸል ጽጌና መስቀል ደመራ በዓላት አከባበር ዝግጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ማሳሰቢያ ተሰጥቷል::
- የአገር ሽማግሌዎች ቡድን በዕርቀ ሰላሙ ጉዳይ ከቅ/ሲኖዶስ ጋራ ይወያያል::
- ነገ ከሚጀመረው የማኅበረ ቅዱሳን ዐሥረኛ ጠቅላላ ጉባኤስ ምን እንጠብቅ?
በዋልድባ የመነኰሳቱ ስደት፣ እስርና ድብደባ ተባብሶ ቀጥሏል
Posted by DejeS ZeTewahedo
· የተሰደዱት መነኰሳትና መናንያን ቁጥር 13 ደርሷል::
· ሁለት መነኰሳት በማይ ገባ ወረዳ ታስረዋል::
· በጠ/ሚኒስትሩና በፓትርያርኩ አሟሟት “ውዥንብር ፈጥራችኋል” በሚል ተከሰዋል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 27/2004 ዓ.ም፤ September 2/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቤተ መንግሥቱም በቤተ ክህነቱም በተመሳሳይ ወቅት የደረሰብን ሐዘን አነጋጋሪ ከመኾን አልፎ ፍትሐ እግዚአብሔር የተፈጸመበት፣ የእግዚአብሔር መልእክትም የተላለፈበት እንደ ኾነ እየተነገረ ነው፡፡ እንደ አቶ ስየ ኣብርሃ ያሉ የተቃውሞ ፖለቲካ መሪዎች ሳይቀሩ በኹኔታው ላይ ቆም ብለን እንድናስብ እየመከሩ ናቸው፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ሱባኤ አወጀ
ማውጫ፦ ዜና Posted by DejeS ZeTewahedo
. ቅ/ሲኖዶሱ የአስታራቂ ኮሚቴውን ሪፖርት አዳምጧል::
. ሦስት የአስታራቂ ኮሚቴው አባላት አዲስ አበባ ናቸው::
. ቅ/ሲኖዶሱ አካሄዱን ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ቡድኖችን እንደማይታገሥ አስታውቋል::
. ከፓትርያርክ ምርጫ ይልቅ በመሠረታዊ መዋቅራዊ ችግሮቻችን ላይ መግባባት ለሚፈጥሩና ለተግባራዊ ለውጥ ለሚያነሣሱ ሚዲያዊ ሥራዎች ትኩረት እንዲሰጥ ተጠይቋል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 29/2004 ዓ.ም፤ September 4/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ቅዱስ ሲኖዶስ መጪው ዘመን ቤተ ክርስቲያናችን ሰላሟንና አንድነቷን የምታረጋግጥበት፣ ዐበይት ተቋማዊ ችግሮቿን በመፍታት ለአገራችንና ለመላው ዓለም ሐዋርያዊ አገልግሎቷን የምታጠናክርበት ይኾን ዘንድ ካህናትና ምእመናን በአንድነት ወደ እግዚአብሔር የሚያመለክቱበትና ከመስከረም 1-12/2005 ዓ.ምየሚቆይ የሱባኤ ጊዜ ማወጁ ታወቀ፡፡ የሱባኤ ጊዜ እንዲታወጅ የተወሰነው ቅዱስ ሲኖዶሱ ትናንት፣ ነሐሴ 28 ቀን 2004 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ሲሆን ዛሬ ማክሰኞ ባደረገው ስብሰባም ቀናቱን ይፋ አድርጓል። (ዝርዝሩን እንደደረሰልን ለማቅረብ እንሞክራለን።) ሱባኤውን የተመለከተ መግለጫ በተከታዮቹ ቀናት በቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊው በኩል እንደሚሰጥም ተመልክቶ ነበር፡፡ በመንፈሳዊው ትውፊታችን እንደቆየን ወደ አዲሱ ዘመን የምንሸጋገርባትና እንደ 13ኛ ወር የምትቆጠረው ጳጉሜን በበርካታ ክርስቲያኖች ዘንድ የፈቃድ ጾም የሚያዝባት ወቅት እንደኾነች ይታወቃል፡፡
Monday, 3 September 2012
ፓትርያርክ ጳውሎስና ያስፈጇቸው ሊቃነ ጳጳሳት
ገብረ ኪዳን
የፓትርያርክ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ ፣ ታዋቂው ደራሲና ሰባኪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “ለምጣዱ ሲባል አይጧን ” በሚል ርእስ ፣ አጭር ግን ጠንካራ መልእክት ለመላው ኢትዮጵያውያን አስተላልፎ ነበር ።
የጽሁፉም ዋና ጭብጥ አንድና ግልጽ ነው— ለቤተ ክርስትያኒቱ ክብር ሲባል ለተወሰኑ ቀናት ስለፓትርያርኩ ክፉ ስራና ደካማ ጎኖች የሚያትቱ ጽሁፎችምሆነ ውይይቶች አንዲዘገዩ “ የሚማጸን ነበር ። ለቤተ ክርስትያኗ ክብር ሲባል መራሄ ቤተ ክህነቱ አቡነ ጳውሎስ ከበቂ በላይ የሀዘን ( ይገባቸዋል ብዬ ባላምንም) ስርአት ተካሂዷል ። እነሆ አሁን በዘመናቸው ስለተከናወኑ አሰቃቂና አስጸያፊ ወንጀሎች እናውሳ።
ሟች ፓትርያርክ ጳውሎስ ይወቀሱበትና ይከሰሱበት የነበሩት ወንጀሎች ብዙ ናቸው። በሃይማኖት ጉዳይ አለቃ አያሌው በመፍቀሬ ካቶሊክነት ሲወቅሷቸው ፣ አቡነ አብርሃምና ሌሎች በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃነ ጳጳሳት ደግሞ ጥንተ አብሶን በተመለከተ ፓትርያርኩ በመመረቂያ ጽሁፋቸው ላይ በጻፉት ኢ – ኦርቶዶሳዊ ትምህርት አንቀው ይዘዋቸው ነበር። በገንዘብ አባካኝነትና በሙስና ሲወቀሱ የነበሩት ፓትርያርክ ጳውሎስ ፣ ህይወታቸው ሲያልፍ በዘመዶቻቸው አካውንት አስከፍተው ያስቀመጡት 22 ሚሊዮን ብር መገኘቱ በሙስና የሚቀርብባቸውን ወቀሳ እውነተኛነት ያመላክታል። ሌሎችም ብዙ መረጃና ማስረጃ የተገኘባቸው ክፉ ስራ ቢኖራቸውም እኔ ግን የትኩረት ነጥቤ የሳቸውን ስልጣን ከመጠበቅ ጋር በተያያዘ በምስጢር የተገደሉትን የሊቃነ ጳጳሳትና የሊቃውንተ ቤተ ክርስትያን ህይወት ይመለከታል።
ስንክሳርንና ግብረ ሕማማትን ወደ አማርኛ የተረጎሙት ሊቅ ዐረፉ
ማውጫ፦ From Contributors Posted by DejeS ZeTewahedo
(MKWebsite, ነሐሴ 28/2004 ዓ.ም/ August 3/2012/ በእንዳለ ደምስስ/ PDF):- ስንክሳርንና ግብረ ሕማማትን እንዲሁም ሌሎችን መጻሕፍት ከግእዝ ወደ አማርኛ የተረጎሙት ታላቁ የመጻሕፍት ሊቅ ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በተወለዱ በ90 ዓመታቸው ነሐሴ 1 ቀን 2004 ዓ.ም. በሞተ ስጋ ከዚህ ዓለም ተለዩ፡፡ ሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ በአርሲ ክፍለ ሀገር በጢዮ ወረዳ ልዩ ስሙ ጨቢ አቦ በተባለ አካባቢ ከአባታቸው መምህር ወልደ ኢየሱስ ዘነበ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ወለተ ሩፋኤል ብስራት ነሐሴ 16 ቀን 1915 ዓ. ም. ተወለዱ፡፡
ከአባታቸው ከመምህር ወልደ ኢየሱስ ዘነበ ንባብ፤ ውዳሴ ማርያም ንባብና ዜማ ፤መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ዲቁና በመማር ለስልጣነ ክህነት ከበቁ በኋላ በአካባቢያቸው በሚገኘው ዱግዳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በዲቁና ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
ደቂቀ ናቡቴ Dekike Nabute: ኑዛዜ
ደቂቀ ናቡቴ Dekike Nabute: ኑዛዜ: በዲ/ን ሕብረት የሽጥላ ራ ስን ለካህን ማሳየት ይገባል:: ኃጢአትን ለካህን መናገር አይገባም ለሚሉ :: ይህንን ልናስደምጣችሁ የፈለግንው መናፍቃን እና ፕሮቴስታንት ተሓድሶዎች ኃጢአትን ለካህን መና...
Sunday, 2 September 2012
የፓትርያርኩ ቀብር ላይ ትልቁ ስህተት
(አንድ አድርገን ነሐሴ 27 2004 ዓ.ም)፡-ፓትርያርኩ ቅዳሴውን አቋርጠው ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህዳሴውን አቋርጠው ከዚህኛ ዓለም ወደዚያኛው ዓለም ከሄዱ ቀናት ተቆጥረዋል ፤ ቤተመንግሰቱም ሆነ ቤተክህነቱ አስጨናቂ የሆነ የሀዘን ድባብ ወርሶታል ፤ የፓትርያርኩ አስከሬን ለ6 ቀናት አፈር ሳይቀምስ ሲቆይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ደግሞ ለ13 ቀናት ያህል ቆይቷል ፤ የፓትርያርኩን ሥርዓተ ፍትሐት ላይ የምስራቅ አብያተ ክርስትያናት ፤ የግብጽ ኦርቶዶክስ ፤ የአርመንና የህንድ ኦርቶዶክስም ጸሎተ ፍትሀት አድርገዋል ፤ ከእነዚህ አብያተክርስትያናት ጋር የኢትዮጵያ ኦርዶክስ ተዋህዶ እምነት የዶግማና የእመነት አንድነት ስላላት ጸሎተ ፍትሀት ማድረጋቸው በስርዓተ ቤተክርስትያናችን ተቀባይነት አለው፡፡
በዋልድባ የመነኰሳቱ ስደት፣ እስርና ድብደባ ተባብሶ ቀጥሏል
Posted by DejeS ZeTewahedo
· የተሰደዱት መነኰሳትና መናንያን ቁጥር 13 ደርሷል::
· ሁለት መነኰሳት በማይ ገባ ወረዳ ታስረዋል::
· በጠ/ሚኒስትሩና በፓትርያርኩ አሟሟት “ውዥንብር ፈጥራችኋል” በሚል ተከሰዋል::
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 27/2004 ዓ.ም፤ September 2/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በቤተ መንግሥቱም በቤተ ክህነቱም በተመሳሳይ ወቅት የደረሰብን ሐዘን አነጋጋሪ ከመኾን አልፎ ፍትሐ እግዚአብሔር የተፈጸመበት፣ የእግዚአብሔር መልእክትም የተላለፈበት እንደ ኾነ እየተነገረ ነው፡፡ እንደ አቶ ስየ ኣብርሃ ያሉ የተቃውሞ ፖለቲካ መሪዎች ሳይቀሩ በኹኔታው ላይ ቆም ብለን እንድናስብ እየመከሩ ናቸው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)