(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 5/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 15/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ የውይይት መሥመሩን ያመቻቸው በውግዘት በተለያዩት አባቶች መካከል ዕርቀ ሰላም ወርዶ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አንድነት ይጠበቅ ዘንድ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው “የሰላምና አንድነት ጉባኤ” ነው፡፡ በሁለቱ አባቶች የስልክ ውይይት÷ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ጋራ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፤ ከአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አብረው መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡
Monday, 15 October 2012
ከተሀድሶያውያን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት አባ ናትናኤል በወንጀል ተከሰሱ
(አንድ አድርገን ጥቅምት 5 2005 ዓ.ም)፡- ባለፈው ዓመት የሀዋሳን ህዝብ ሲያስለቅሱት የነበሩት ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን አስተዳዳሪ ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ተደርገው ከቤተክህነት ተሾሙው እንደነበር በጊዜው ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል ፤ነገር ግን ህዝቡ እኝን አባት አስተዳዳሪ አድርገን አንቀበልም ብሎ እሳቸው በእግራቸው ቢመጡም በኮንትራት ታክሲ ከቤተክርስቲያን አባሯቸው ነበር ፤ በፊት በተሐድሶ እና ከፕሮቴስታንት አራማጆች (ተስፋኪዳነምህረት ማህበር እና ከመሰሎቻቸው ) ጋር በመሆን የእግዚአብሔርን አውደ ምህረት እንዲፈነጩበት ካደረጉ ሰዎች መካከል ግንባር ቀደሙን የሚይዙ ሰው ናቸው ፡፡ በጊዜው ገንዘብ አይናቸውን አሳውሯቸው ፤ ለአውደምህረት የማይመጥኑ ፤ ትምህርቱ የሌላቸው ሰዎችን በመጋበዝ ህዝቡን እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ካደረኩ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)