Monday, 19 November 2012

የቅዱስ ላልይበላ ደብር ካህናትና ምእመናን የመንግሥት ያለህ እያሉ ነው


     ቤተክህነቱ በደብሩ አለቃ የሚፈጸመውን ሙስናና የአስተዳደር በደል መቆጣጠር ተስኖታል
  • የውቅር አብያተ መቅደሱ የቱሪስት ገቢ ተቆጣጣሪ የለውም፤ የቅርሶቹ ጉዳት ተባብሷል
  • በደብሩ ገንዘብ የተሠሩት የቤተ አብርሃም እና ይምርሐነ ሆቴሎች ባለቤት አይታወቅም


አዲስ አድማስ ጋዜጣ የተወሰደ

(አንድ አድርገን ህዳር 10 2004 ዓ.ም)፡-በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የቅዱስ ላሊበላ ደብርየሚያገለግሉ ካህናት እና ምእመናን÷ በደብሩ አስተዳዳር በሚፈጸመው ሙስናና የአስተዳደር በደልመማረራቸውንና አቤቱታቸው ሰሚ አለማግኘቱን ለአዲስ አድማስ ገለጹ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር የቱሪዝም ገቢየግል ሀብትን ለማደለብ እየዋለ መኾኑን የጠቆሙት ካህናቱ÷ በቅርሶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በከፍተኛደረጃ መባባሱን፣ሙሰኝነትንና የአሠራር ብልሹነትን የሚቃወሙና የሚያጋልጡ ካህናትና ሠራተኞች ለመባረርናለእስር መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡