ቤተክህነቱ በደብሩ አለቃ የሚፈጸመውን ሙስናና የአስተዳደር በደል መቆጣጠር ተስኖታል
ደብሩ ሦስት ታላላቅ ሆቴሎች፣አንድ የእንግዳ ማረፊያ፣ ለሁለገብ አገልግሎት የተከራየ ባለሦስት ፎቅሕንጻ፣መኪኖች፣ወፍጮዎችና ሙዳዬ ምጽዋትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች ቢኖሩትም የተቋማቱአስተዳደር በቂ የትምህርት ዝግጅትና ልምድ በሌላቸው፣ እንዲሁም በጥቅም በተሳሰሩ ደጋፊዎቻቸውና ዘመድአዝማዶቻቸው እንዲመራ በማድረግ፣ የሕዝብና የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ እያባከኑ ነው ብለዋል፡፡የአቤቱታውአቅራቢዎች አስተዳዳሪው የደብሩን ገንዘብ ወጪ የሚያደርጉባቸውን ስልቶች ሲያስረዱም÷ ‹‹የደብሩንአስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ በበላይነት ለመምራት በካህናትና ምእመናን ጉባኤ የተሠየመው ሰበካ ጉባኤ ከፍተኛየገንዘብ ወጪ እንዲያደርግ ካስወሰኑ በኋላ ውሳኔው የሰፈረበት ቃለ ጉባኤ ተቀዶ እንዲጣል ያደርጋሉ፡፡የግዥም ሆነ የግንባታ ሥራዎች ያለጨረታ በራሳቸው ፈቃድ እንዲከናወን ያደርጋሉ፡፡ በአብዛኛው አዲስ አበባየሚገዙ ዕቃዎችን ያለፕሮፎርማ ራሳቸው ገዝተው ሲያበቁ ዕቃ ግዥ ሓላፊውን ወደ አዲስ አበባ ልከውእንደገዛ አስመስለው ይልኩታል፤››ይላሉ፡፡አስተዳዳሪው ቤተ አብርሃም የተሰኘውን ሆቴል አሠርተዋልበሚል “የልማት አርበኛ” ቢባሉም አሠሩት የሚባለው ሆቴል ከፍተኛ ሙስና የተፈጸመበትና ሪፖርትየተደረገው ገንዘብ በሥራ ላይ ከዋለው ገንዘብ በዕጥፍ እንደሚበልጥ ምንጮቹ ይናገራሉ፡፡ አያይዘውም ሆቴሉበሚገነባበት ጊዜ በሕዝቡና በካህናቱ በታማኝነቱ የተመረጠው ገንዘብ ያዥ÷ ያለምንም ምክንያት ከጅምሩሥራውን እንዲያቋርጥ ተደርጎ÷ በሌላ ሰው መተካቱንና እስከ አሁን ድረስ ግን ደሞዝ እንደሚከፈለውየሚያስረዱት ምንጮቹ፣ ቤተ አብርሃም እና ይምርሐ የተባሉት ሁለት ታላላቅ የደብሩ ሆቴሎችባለቤትነታቸው በውል እንደማይታወቅ ይናገራሉ፡፡ የሆቴሎቹ ፈቃድ በግለሰቦች ስም የተያዘ በመሆኑ ቤተክርስቲያኗ ባለመብትና ባለይዞታ ነች ብሎ በሕግ መከራከር እንደማይቻል ምንጮቹ ጠቁመው÷ የደብሩሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ ሲካሄድ ያለሰበካ ጉባኤው ዕውቅና መሆኑን÷ ገቢ የሚደረገውም በገንዘብ ያዥ ብቻበመሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጥቆማ÷ ደብሩ በብዙ ሚሊዮኖች የሚገመት ብር የሚያንቀሳቅስ ቢሆንም የሥራናየበጀት ዕቅድ የለውም፡፡ ገቢና ወጪው መደበኛ የሒሳብ አሠራር ተከትሎ ለሰበካ ጉባኤውም ኾነለሚመለከተው አካል ሪፖርት አይቀርብም፡፡የሒሳብ ቁጥጥር ካለመደረጉም በተጨማሪ የሒሳብ ሪፖርቱከተሠራው ሥራ ጋር ተገናዝቦ ስለማይቀርብ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና ምዝበራ እየተፈጸመ መሆኑ ያሳስበናልብለዋል፡፡የቦታው ነባር መንፈሳዊ ቅርሶችና ተቋማት እየፈረሱና እየተዳከሙ የጥገና ያለህ በሚሉበት፣የካህናቱኑሮ ባልተለወጠበት፣በደብሩ ከፍተኛ አቅም መታቀፍና መደገፍ የሚገባቸው አብነት ት/ቤቶች ወንበሮቻቸውእየታጠፉ መምህራኑና ተማሪዎቻቸው በተበተኑበት፣ ገዳማቱ ወደ መፈታት በደረሱበት ኹኔታ አስተዳዳሪውናዘመድ አዝማዶቻቸው ያለከልካይ ይፈጽሙታል የሚባለውን ምዝበራና ሙስና እንዲገታ ከሀገረ ስብከቱጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ቀድሞው ፓትርያሪክ ድረስ በተደጋጋሚ የቀረበው አቤቱታ ሰሚ እንዳላገኘ ካህናቱይስረዳሉ፡፡ አስተዳዳሪው ማንንም ሳያስፈቅዱ ለሁለት ወራት በአሜሪካ በቆዩበት ወቅት ለቦታው በሚመጥንሌላ ሰው እንዲተኩ በፓትርያርኩ ተሰጥቶ ነበር የተባለው ውሳኔም ባላወቁት ምክንያት ተፈጻሚ እንዳልኾነነው ካህናቱ የሚናገሩት፡፡በምትኩ በየጊዜው ተቃውሞ የሚያቀርቡ ካህናትና የሀገረ ስብከት ሠራተኞች ሳይቀርእንደሚታሰሩ፣ ያለምንም ምክንያት ደመወዛቸው እንደሚቆረጥ፣ ከሥራቸው እንደሚባረሩ፣ በዕድሜ የገፉሊቃውንትና መምህራን ለመንፈሳዊ ሥልጣናቸውና ክብራቸው ተቃራኒ በኾነ መልኩ በየሰበቡ እንደሚዋረዱናበተመልካቾች ፊት እንዲንበረከኩ ከመደረጋቸውም በላይ በተቃውሞ የተገኙ ካህናት ከአገልግሎትእንደሚባረሩ በግዴታ የፈረሙበት ሕግ በአስተዳዳሪው መውጣቱን አቤቱታ አቅራቢዎቹ በምሬት ይገልጻሉ፡፡በቤተ ክርስቲያኒቱ ቃለ ዐዋዲ ደንብ መሠረት የአስተዳዳሪውን አካሄድ ለመቆጣጠር ሥልጣን ያለው የደብሩሰበካ ጉባኤ ለይስሙላ የተቀመጠና አባላቱም በየጊዜው በአስተዳዳሪው ከሓላፊነታቸው እየተነሡ በሥነምግባር ጉድለታቸው በሕዝቡና በካህናቱ የታወቁ ግለሰቦችን እንደሚተኩበት ይናገራሉ፡፡
- የውቅር አብያተ መቅደሱ የቱሪስት ገቢ ተቆጣጣሪ የለውም፤ የቅርሶቹ ጉዳት ተባብሷል
- በደብሩ ገንዘብ የተሠሩት የቤተ አብርሃም እና ይምርሐነ ሆቴሎች ባለቤት አይታወቅም
ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ የተወሰደ
(አንድ አድርገን ህዳር 10 2004 ዓ.ም)፡-በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በሚገኘው የቅዱስ ላሊበላ ደብርየሚያገለግሉ ካህናት እና ምእመናን÷ በደብሩ አስተዳዳር በሚፈጸመው ሙስናና የአስተዳደር በደልመማረራቸውንና አቤቱታቸው ሰሚ አለማግኘቱን ለአዲስ አድማስ ገለጹ፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር የቱሪዝም ገቢየግል ሀብትን ለማደለብ እየዋለ መኾኑን የጠቆሙት ካህናቱ÷ በቅርሶች ላይ የሚደርሰው ጉዳት በከፍተኛደረጃ መባባሱን፣ሙሰኝነትንና የአሠራር ብልሹነትን የሚቃወሙና የሚያጋልጡ ካህናትና ሠራተኞች ለመባረርናለእስር መዳረጋቸውን ተናግረዋል፡፡
ላለፉት ስምንት ዓመታት “ካህናት - ነገሥታት” ተብለው በአገራችን ከሚታወቁት አራቱ የዛጉዌ ዘመን ስመጥር መሪዎች ዋነኛው በነበረው ቅዱስ ላሊበላ የተሠሩትና አገራችን በዩኔስኮ ካስመዘገበቻቸው ዓለም አቀፍቅርሶች ግንባር ቀደም በኾኑት ዐሥራ አንድ አብያተ መቅደስ በአስተዳዳሪነት የቆዩት መምህር አባ ገብረኢየሱስ መኰንን ”የደብሩን ካህናት ደመወዝና የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች ሸፍኖ በዓመት ከቱሪዝም ብቻበአነስተኛ ግምት የሚገኘው ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለምን እንዳዋሉት አይታወቅም” ይላሉ- አቤቱታ አቅራቢዎቹ፡፡
ደብሩ ሦስት ታላላቅ ሆቴሎች፣አንድ የእንግዳ ማረፊያ፣ ለሁለገብ አገልግሎት የተከራየ ባለሦስት ፎቅሕንጻ፣መኪኖች፣ወፍጮዎችና ሙዳዬ ምጽዋትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች ቢኖሩትም የተቋማቱአስተዳደር በቂ የትምህርት ዝግጅትና ልምድ በሌላቸው፣ እንዲሁም በጥቅም በተሳሰሩ ደጋፊዎቻቸውና ዘመድአዝማዶቻቸው እንዲመራ በማድረግ፣ የሕዝብና የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ እያባከኑ ነው ብለዋል፡፡የአቤቱታውአቅራቢዎች አስተዳዳሪው የደብሩን ገንዘብ ወጪ የሚያደርጉባቸውን ስልቶች ሲያስረዱም÷ ‹‹የደብሩንአስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ በበላይነት ለመምራት በካህናትና ምእመናን ጉባኤ የተሠየመው ሰበካ ጉባኤ ከፍተኛየገንዘብ ወጪ እንዲያደርግ ካስወሰኑ በኋላ ውሳኔው የሰፈረበት ቃለ ጉባኤ ተቀዶ እንዲጣል ያደርጋሉ፡፡የግዥም ሆነ የግንባታ ሥራዎች ያለጨረታ በራሳቸው ፈቃድ እንዲከናወን ያደርጋሉ፡፡ በአብዛኛው አዲስ አበባየሚገዙ ዕቃዎችን ያለፕሮፎርማ ራሳቸው ገዝተው ሲያበቁ ዕቃ ግዥ ሓላፊውን ወደ አዲስ አበባ ልከውእንደገዛ አስመስለው ይልኩታል፤››ይላሉ፡፡አስተዳዳሪው ቤተ አብርሃም የተሰኘውን ሆቴል አሠርተዋልበሚል “የልማት አርበኛ” ቢባሉም አሠሩት የሚባለው ሆቴል ከፍተኛ ሙስና የተፈጸመበትና ሪፖርትየተደረገው ገንዘብ በሥራ ላይ ከዋለው ገንዘብ በዕጥፍ እንደሚበልጥ ምንጮቹ ይናገራሉ፡፡ አያይዘውም ሆቴሉበሚገነባበት ጊዜ በሕዝቡና በካህናቱ በታማኝነቱ የተመረጠው ገንዘብ ያዥ÷ ያለምንም ምክንያት ከጅምሩሥራውን እንዲያቋርጥ ተደርጎ÷ በሌላ ሰው መተካቱንና እስከ አሁን ድረስ ግን ደሞዝ እንደሚከፈለውየሚያስረዱት ምንጮቹ፣ ቤተ አብርሃም እና ይምርሐ የተባሉት ሁለት ታላላቅ የደብሩ ሆቴሎችባለቤትነታቸው በውል እንደማይታወቅ ይናገራሉ፡፡ የሆቴሎቹ ፈቃድ በግለሰቦች ስም የተያዘ በመሆኑ ቤተክርስቲያኗ ባለመብትና ባለይዞታ ነች ብሎ በሕግ መከራከር እንደማይቻል ምንጮቹ ጠቁመው÷ የደብሩሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ ሲካሄድ ያለሰበካ ጉባኤው ዕውቅና መሆኑን÷ ገቢ የሚደረገውም በገንዘብ ያዥ ብቻበመሆኑ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቤቱታ አቅራቢዎቹ ጥቆማ÷ ደብሩ በብዙ ሚሊዮኖች የሚገመት ብር የሚያንቀሳቅስ ቢሆንም የሥራናየበጀት ዕቅድ የለውም፡፡ ገቢና ወጪው መደበኛ የሒሳብ አሠራር ተከትሎ ለሰበካ ጉባኤውም ኾነለሚመለከተው አካል ሪፖርት አይቀርብም፡፡የሒሳብ ቁጥጥር ካለመደረጉም በተጨማሪ የሒሳብ ሪፖርቱከተሠራው ሥራ ጋር ተገናዝቦ ስለማይቀርብ ከፍተኛ የገንዘብ ብክነትና ምዝበራ እየተፈጸመ መሆኑ ያሳስበናልብለዋል፡፡የቦታው ነባር መንፈሳዊ ቅርሶችና ተቋማት እየፈረሱና እየተዳከሙ የጥገና ያለህ በሚሉበት፣የካህናቱኑሮ ባልተለወጠበት፣በደብሩ ከፍተኛ አቅም መታቀፍና መደገፍ የሚገባቸው አብነት ት/ቤቶች ወንበሮቻቸውእየታጠፉ መምህራኑና ተማሪዎቻቸው በተበተኑበት፣ ገዳማቱ ወደ መፈታት በደረሱበት ኹኔታ አስተዳዳሪውናዘመድ አዝማዶቻቸው ያለከልካይ ይፈጽሙታል የሚባለውን ምዝበራና ሙስና እንዲገታ ከሀገረ ስብከቱጽ/ቤት ጀምሮ እስከ ቀድሞው ፓትርያሪክ ድረስ በተደጋጋሚ የቀረበው አቤቱታ ሰሚ እንዳላገኘ ካህናቱይስረዳሉ፡፡ አስተዳዳሪው ማንንም ሳያስፈቅዱ ለሁለት ወራት በአሜሪካ በቆዩበት ወቅት ለቦታው በሚመጥንሌላ ሰው እንዲተኩ በፓትርያርኩ ተሰጥቶ ነበር የተባለው ውሳኔም ባላወቁት ምክንያት ተፈጻሚ እንዳልኾነነው ካህናቱ የሚናገሩት፡፡በምትኩ በየጊዜው ተቃውሞ የሚያቀርቡ ካህናትና የሀገረ ስብከት ሠራተኞች ሳይቀርእንደሚታሰሩ፣ ያለምንም ምክንያት ደመወዛቸው እንደሚቆረጥ፣ ከሥራቸው እንደሚባረሩ፣ በዕድሜ የገፉሊቃውንትና መምህራን ለመንፈሳዊ ሥልጣናቸውና ክብራቸው ተቃራኒ በኾነ መልኩ በየሰበቡ እንደሚዋረዱናበተመልካቾች ፊት እንዲንበረከኩ ከመደረጋቸውም በላይ በተቃውሞ የተገኙ ካህናት ከአገልግሎትእንደሚባረሩ በግዴታ የፈረሙበት ሕግ በአስተዳዳሪው መውጣቱን አቤቱታ አቅራቢዎቹ በምሬት ይገልጻሉ፡፡በቤተ ክርስቲያኒቱ ቃለ ዐዋዲ ደንብ መሠረት የአስተዳዳሪውን አካሄድ ለመቆጣጠር ሥልጣን ያለው የደብሩሰበካ ጉባኤ ለይስሙላ የተቀመጠና አባላቱም በየጊዜው በአስተዳዳሪው ከሓላፊነታቸው እየተነሡ በሥነምግባር ጉድለታቸው በሕዝቡና በካህናቱ የታወቁ ግለሰቦችን እንደሚተኩበት ይናገራሉ፡፡
አስተዳዳሪው ችግሩን የሚያውቁትንና እንዲታረምም ማሳሰቢያና ምክር የሚሰጡትን የመንግሥትባለሥልጣናት በአንድ በኩል ‹‹በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አትግቡብኝ›› እያሉ እያናናቁ በሌላ በኩል ደግሞየዞንና የክልል ባለሥልጣናት ‹በእጃቸው እንደኾኑ›ና የከተማው አስተዳደር ሓላፊዎች ከእርሳቸው ጋራካልተስማሙ ሥልጣናቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ እንደሚያስፈራሯቸው በአቤቱታው ላይ ተመልክቷል፡፡አክለውም የጥንታዊው ቅዱስ ላሊበላ ደብር ጥገናና ክብካቤ ጉዳይ በቀጥታ ከሚመለከተው የባህልና ቱሪዝምጽ/ቤት ጋራ ተስማምተው መሥራት እንዳልቻሉ፣ ለሌሎችም የመንግሥት ሓላፊዎች ሳይቀር ማስቸገራቸውንለዝግጅት ክፍሉ ገልጸዋል፡፡ በአስረጅነትም የከተማውን የቱሪዝም ባለድርሻ አካላት ሳያማክሩ በራሳቸውፈቃድ የቱሪስት መግቢያ ክፍያን ከኻያ ዶላር ወደ ኀምሳ አምስት ዶላር እንዲጨምር መወሰናቸውንበማሳያነት ይጠቅሳሉ፡፡
ይህም አስተዳዳሪው ቀድሞም የባለድርሻ አካላቱን (አስጎብኚዎች፣ የጉዞና የጉብኝት ወኪሎች) በመዝለፍናበማዋረድ የሻከረው የሥራ ግንኙነታቸው የከፋ ተቃውሞ እንዲቀሰቀስበትና ከዘርፉ ቤተ ክርስቲያኒቱና አገሪቱማግኘት በሚገባቸው ጥቅም ላይ ዕንቅፋት ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ስለ መኾናቸው በበቂ ስለሚያስረዳበመንግሥትና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለደብሩ ተገቢውን መምህር በመመደብ አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስድአቤቱታ አቅራቢዎቹ ጠይቀዋል፡፡
የዝግጅት ክፍሉ ስለጉዳዩ የጠየቃቸውና ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከፍተኛሓላፊዎች አስተዳዳሪው የሚፈጥሩት ችግር ከቀድሞም ጀምሮ የሚታወቅ በመኾኑ መንበረ ፓትርያሪኩ ከሀገረስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋራ በመነጋገር በአጭር ጊዜ እልባት እንደሚሰጠው ያላቸውን አስተያየት ገልጸዋል፡፡
No comments:
Post a Comment