Friday, 13 July 2012


የኦርቶዶክሳውያንና የጨለማው ቡድን ትንቅንቅ ከቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ስብሰባ ማግስት እስከ በዓለ ሢመት

  •   ፓትሪያሪኩ በአራት የቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነባቸው አጀንዳ ቃለጉባኤ በብዙ ጫናዎች ባለፈው ሳምንት ፈረመዋል፡፡
  •  ቋሚ ሲኖዶስ ፓትሪያሪኩ በአጀንዳዎቹ ላይ ካለመፈረማቸው ጋር ተያይዞ የቅዱሰ ሲኖዶስ የበላይነት አምነው ስላልተቀበሉና ለውሳኔዎቹ ተገዥ ስላልሆኑ  ከቅዱስነታቸው ጋር መሰብስብ እንደማይችሉ በመግለጽ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ አልተሰበሰቡም፡፡
  •  “ጉባኤ አርድእት ዘተዋህዶ”  አባላት እርስ በእርሳቸው ተከፋፍለዋል፡፡ ቡድኑም በጠቅላይ ቤተክህነት እንዳይሰባሰብ ታግድዋል፡፡ የጠቅላይ ቤተክህነት የሥራ ኅላፊዎችና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቃውሞ እንዲሁም የመንግስት ማስጠንቀቂያን ተከትሎ ቡድኑ ፓትሪያሪኩ አግደወታል፡፡
  •  እገዳው በጠቅላይ ቤተክህነቱ ጠቅላላ አገልግሎቱ ደብዳቤ እንደሚጸና እየተጠበቀ ነው
  •  በዓለ ሢመት ጠንካራና ተጽእኖ ፈጣሪ አባቶች እንደማይገኙ በማሰብ የጨለማው ሲኖዶስ አባላት የጠነሰሱትን ሴራ ለማክሸፍ ብጹአን ሊቃነጳጳሳት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡
  •  ምንደኛው ኃ/ጊየርጊስ ጥላሁን በጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥአስኪያጅ አቶ ተስፋየ ውብሸት ብርቱ ትግል አቡነ ጳውሎስ መኪናው እንዲነጠቅ አድርገዋል፡፡
  • ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተመስርቷል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ለመስራች ጉባኤው የምግብ ወጭ 35,000 ብር ስፖንሰር አድርጓል፡፡ 
  •  “የመለስ አባት ነው ትሉኛላችሁ፤ አዎ የመለስ አባት ነኝ” አቡነ ጳውሎስ       
  •  ማኅበረቅዱሳን በመላው ዓለም ፳ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ እያከበረ ነው



አባ ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ

አባ ሙሴ ጸሊም በትውልዱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን አስቀድሞ በውንብድና ኑሮ ሕይወቱን ይገፋ ነበር፡፡ ሰዎች ከገድሉ የተነሳ ያደንቁታል፡፡እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበርና እርሱ በሥጋው ጠንካራ ፤ በሥራውም ኃይለኛ ነበር፡፡
አባ ሙሴ ጸሊምም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ፤ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ፡፡ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር ፡፡

አባ ሙሴ ጸሊም  ኢትዮጵያዊ

በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኮሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ፤ ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው፡፡  ያንጊዜም ተነሳ ሰይፉንም ታጥቆ ወደአስቄጥስ ገዳም ሄደ ፤ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው ፤ አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ አለው ፡፡ አባ ኤስድሮስም ወደአባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው፡፡ እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲህም አለው ታግሰህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ
የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ አመነኮሰው ከብዙዎች ገድለኞች ቅዱሳን ይልቅ ብዙ እና ጽኑዕ ገድልን መጋደል ጀመረ፡፡፡፡በኋላም በገዳመ አስቄጥስ የገዳሙ አበምኔት የነበረው የአባ ኤስድሮስ ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ በአባ መቃርዮስ ምክር ወደ ጴጥራ ሂዶ በተባሕትዎ መኖር ቀጠለ፡፡ ከገድሉ ብዛት የተነሳ አረጋውያን መነኮሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውሃ መቅጃዎቹን ወስዶ ውሃ ሞልቶ በየቤታቸው ደጃፍ ያኖር ነበር፡፡ ውሃው ከእነርሱ ሩቅ ነበርና እንዲህም እያደረገ በመጋደል ለብዙ ዘመናት ኖረ ፡፡
አባ ሙሴ ጸሊም በበአቱ እያለ የፈቲው ፆር ያሠቃየው ነበር፡፡ ፈተናውን ተቋቁሞ በበአቱ መቀመጥ ስላልቻለ ወደ ገዳሙ አበምኔት ወደ አባ ኤስድሮስ ዘንድ ሄደና ‹በበኣቴ መቀመጥ አልቻልኩም› አለው፡፡ አባ ኤስድሮስም ወደ በኣቱ ተመልሶ በዚያው እንዲጸና መከረው፡፡ ሙሴ ግን ‹ፈጽሞ አልችልም› አለ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ኤስድሮስ ሙሴን ይዞት ከገዳሙ ቅጥር ውጭ አወጣው ከዚያም ወደ ምዕራብ አዞረውና ‹ተመልከት› አለው፡፡ በዚያ አቅጣጫ የአጋንንት መንጋ ለወረራ ሲዘጋጁና ሲንጫጩ አሳየው፡፡ ቀጥሎ ደግሞ ወደ ምሥራቅ እንዲመለከት አደረገውና እልፍ አእላፍ መላእክት ብርሃን ተጐናጽፈው አሳየው፡፡ ከዚያም ‹እነዚህ የብርሃን መላእክት ቅዱሳንን ለመርዳት ከእግዚአብሔር የሚላኩ ናቸው እነዚህ ርኩሳን አጋንንት ደግሞ ቅዱሳንን ለመፈተን የሚዘምቱ ናቸው፡፡ የብርሃን መላእክት ኃይል ከአጋንንት ኃይል ይበልጣሉና ጸንተህ ተጋደል› ሲል መከረው አባ ሙሴም ወደ በኣቱ ተመለሰ፡፡
አባ ሙሴ በገዳመ አስቄጥስ እያለ ከገዳማውያን አንዱ ጥፋት ሠራና ማኅበሩ ለፍርድ  ተሰበሰበ፡፡ አባ ሙሴ ግን በጉባኤው ላይ አልነበረም፡፡ ስለዚህ ካህኑ ተልኰ ‹ና. ሁላችንም አንተን እየጠበቅን ነው› አለው፡፡ አባ ሙሴም በሚያፈስስ ከረጢት አሸዋ ሞልቶ ያንንም በጀርባው ተሸክሞ ከኋላው እያፈሰሰ ወደ ጉባኤው አመራ፡፡ ጉባኤተኞቹ ተገርመው ለምን እንደዚህ እንዳደረገ ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹የእኔ ኃጢአቶች በኋላየ እንደዚህ አሸዋ በዝተው ይፈሳሉ፤ ነገር ግን ላያቸው አልቻልኩም ዛሬ ግን በሌላው ላይ ለመፍረድ መጥቻለሁ፡፡› አላቸው፡፡ ይህን ሲሰሙ ዝም አሉ፡፡ ያን ወንድምም በይቅርታ አለፉት፡፡
በሌላ ጊዜ በገዳመ አስቄጥስ ያሉ መነኰሳት ተሰበሰቡና የአባ ሙሴን ትዕግሥት ለመፈተን ሲሉ “ይህ ጥቁር መነኩሴ ለምን እዚህ መጣ “ ብለው ተናገሩት፡፡ እርሱም ዝም አለ፡፡ ጉባኤው ሲበተን “አባ ክፉ ስንናገርህ ምንም ሐዘን አልተሰማህም ነበርን ?” ሲሉ ጠየቁት፡፡ “ተሰምቶኛል፣ ነገር ግን እንዳልናገረው አንደበቴን ተቆጣጠርኩት” አላቸው፡፡
በአንድ ወቅት በገዳመ አስቄጥስ ጾም ታወጀ፡፡ በዚያ ሳምንት አባ ሙሴን ለማየት ከግብጽ ወንድሞች መጡ፡፡ አባ ሙሴም በእንግድነት ተቀበላቸውና ምግብ ያበስልላቸው ጀመር፡፡ የእሳቱን ጢስ የተመለከቱ ጐረቤቶቹ “አባ ሙሴ ትእዛዝ አፍርሶ ምግብ ያበስላል” ብለው ለገዳሙ ሓላፊዎች ተናገሩ፡፡ ሓላፊዎቹም ‹አሁን ተውት ሲመጣ እኛው ራሳችን እናናግረዋለን› አሏቸው፡፡ ሓላፊዎቹም አባ ሙሴን ጠርተው ለምን ምግብን እንዳበሰለ ተረዱ፡፡ በቀዳሚት ሰንበት ማኅበሩ ሁሉ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲመጣ በአደባባይ ‹አባ ሙሴ ሆይ የሰውን ትእዛዝ አልጠበቅኽም፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ (እንግዳ ሆኜ መጥቼ ተቀብላችሁኛል የሚለውን) ግን ጠብቀሃል› ብለው አመሰገኑት፡፡
አንድ ጊዜ የአካባቢው ገዥ ስለ አባ ሙሴ ዝና ሰምቶ ያየው ዘንድ ወደ ገዳመ አስቄጥስ መጣ፡፡ ይህን የሰማው አባ ሙሴ ሸሽቶ ወደ ጫካ ገባ፡፡ በመንገድም ላይ የገዥው መልእክተኞች አገኙትና ‹እባክህ አባ ሙሴ የት እንዳለ በኣቱን አሳየን› አሉት፡፡ ‹ከርሱ ምን ትሻላችሁ፤ እርሱ ኮ ቂላቂል ነው› አላቸው፡፡ ይህን የሰማው የአካባቢው ገዥ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መጣና የሆነውን ሁሉ ለአገልጋዮች ነገራቸው፡፡ ‹ብዙ ሰዎች ስለ አባ ሙሴ ሲያወሩ ሰምቼ ለማግኘት መጥቼ ነበር፤ በመንገድ ላይ ያገኘነው አንድ አረጋዊ ሰው ግን የአባ ሙሴ በኣት የት እንደሆነ ስንጠይቀው ከርሱ ምን ትሻላችሁ እርሱ ኮ ቂላቂል ነው አለን› ብሎ ነገራቸው፡፡ አገልጋዮቹም በጣም ተናደዱና ‹ምን ዓይነት አረጋዊ ሰው ነው ስለ ቅዱሱ ይህን የሚናገር› ብለው ጠየቁት፡፡ ‹ትልቅ፣ ጠቆር ያለ፣ አሮጌ ልብስ የለበሰ ነው› አላቸው፡፡ አገልጋዮቹም ተገርመው ‹ይህማ ራሱ አባ ሙሴ ነው፤ ይህን ያለህ ሊያገኝህ ስላልፈለገ ነው› አሉት፡፡ የአካባቢው ገዥም ከአባ ሙሴ ሁኔታ ከንቱ ውዳሴን ስለ መሸሽ ትልቅ ትምህርት ተምሮ ተመለሰ፡፡
አባ ሙሴ በኣት ሠርቶ ወደ ጴጥራ ሲሄድ በአካባቢው ውኃ ስላልነበረ ተጨንቆ ነበር፡፡ አንድ ድምፅ ‹ሂድ ስለምንም ነገር አትጨነቅ› አለው፡፡ ስለዚህም በዚያ መኖር ጀመረ፡፡ አንድ ቀን በጴጥራ እያለ አበው ሊጐበኙት መጡ፡፡ የነበረችው ውኃ ጥቂት ነበረችና በርሷ ምግባቸውን አበሰለ፡፡ የሚያጠጣቸው ግን አላገኘም፡፡ ስለዚህ ወደ ውጭ እየወጣ ውኃ ይሰጠው ዘንድ እግዚአብሔርን ይለምን ነበር፡፡ በመጨረሻ ዝናብ ዘነበና የውኃ ማጠራቀሚያዎቹን ሁሉ ሞላቸው፡፡ እነዚያ አባቶችም ‹ትወጣና ትገባ የነበረው ለምን እንደሆነ እባክህ ንገረን› አሉት፡፡ ‹እናንተ በእንግድነት ስትመጡ ውኃ አልነበረኝም፣ ስለዚህ ያንተን አገልጋዮች ወደ እኔ ልከሃቸዋል፣ ነገር ግን ውኃ የለኝም፣ ስለዚህ እባክህ ውኃ ስጠኝ እያልኩ እግዚአብሔርን ለመለመን ነበር› አላቸው፡፡

 አንድ ወንድም አባ ሙሴን ‹አንድን አገልጋይ ባጠፋው ጥፋት የተነሣ ጌታው መታው፡፡ አገልጋዩ ምን ማለት አለበት?› ብሎ ጠየቀው፡፡ አባ ሙሴም ‹አገልጋዩ ብፁዕ ከሆነ፣ አጥፍቻለሁና ይቅር በለኝ ማለት አለበት፡፡› አለው፡፡ ‹ሌላ አይጠበቅበትምን?› ሲል ያ ወንድም ጠየቀው፡፡ ‹አይጠበቅበትም፣ ለጊዜው ለጥፋቱ ሓላፊነቱን ወስዶ አጥፍቻለሁ ካለ ጌታው ይቅር ይለዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ዓለማው በባልጀራ ላይ ላለመፍረድ ነው፡፡ በእውነቱ ጌታችን የግብጽን በኩራት ሁሉ ሲመታ ሰው ያልሞተበት አንድም ቤት አልነበረም› አለና መለሰለት፡፡ ያም ወንድም ‹ምን ማለት ነው?› አለው፡፡ ‹ሁላችንም የየራሳችንን ጥፋቶች ካየን የባልንጀራችንን ለማየት ዕድል አንሰጥም፡፡ በራሱ ቤት ሰው የሞተበት በጐረቤቱ ልቅሶ ለማልቀስ አይሄድም፡፡ ለባልንጀራ መሞት ማለት ለራስ ጥፋት ትኩረት በመስጠት፣ የሌላውን ጥፋት ከቁም ነገር አለመቁጠር ነው፡፡ ማንንም አትጉዳ፣ በማንም ላይ ክፉ አታስብ፣ ክፉ የሚሠራውን ሰው አትናቀው፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ በሚሠራ ሰው ላይ አትተማመን፣ በባልንጀራው ላይ ክፉ ከሚሠራ ሰው ጋር አትደሰት፣ ለባልንጀራ መዋቲ መሆን ማለት ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ አትማረር፣ ነገር ግን ‹ሁሉንም እግዚአብሔር ያውቃል፡፡› በል፡፡ ከሚያማ ሰው ጋር አትተባበር፣ በሐሜቱም አትደሰት፣ ወንድሙን የሚያማውን ሰውም አትጸየፈው፡፡ አትፍረድ ማለት ትርጉሙ ይህ ነው፡፡ በማንም ላይ የጥላቻ ሓሳብ አይኑርህ፣ ጥላቻ ልብህን እንዲያሸንፈውም አትፍቀድለት፡፡ ባልንጀራውን የሚጠላውን አትጥላው፣ ሰላም ማግኘት ማለት ይህ ነው፡፡
አንድ ጊዜ በገዳመ አስቄጥስ ወንድሞች አብረውት እያሉ አባ ሙሴ ‹ተመልከቱ በርበሮች ገዳማችንን ሊያጠፉ እየመጡ ነው፡፡ ተነሡና ሽሹ› አላቸው፡፡ እነርሱ ግን ‹አባ አንተስ አትሸሽምን?› ሲሉ ጠየቁት፡፡ አባ ሙሴም ‹እኔማ ይህችን ቀን ለብዙ ዘመናት ስጠብቃት ኖሬአለሁ፡፡ ጌታ በወንጌል ‹ሰይፍን የሚያነሡ በሰይፍ ይጠፋሉ› ያለው ቃል (ማቴ. 25.52) ይፈጸማል፡፡› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹እኛም አንሸሽም፣ አብረን እንሞታለን እንጂ› አሉት፡፡ አባ ሙሴም ‹ያ ለእኔ ረብ የለውም፤ ሁሉም ሰው ለየራሱ ይወስን› ብሉ መለሰላቸው፡፡ በዚያ ለነበሩት ሰባት ወንድሞች ‹በርበሮች ወደ ገዳሙ ደጅ እየደረሱ ነው› ብሎ ነገራቸው፡፡ ወዲያውም በርበሮቹ ደርሰው ገዳማውያኑን በሰይፍ መቷቸው፡፡ ከሰባቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ ሸሸና በተቆለለው ሰሌን ውስጥ ተደበቀ፤ ወዲያውም ሰባት አክሊላት ሲወርዱላቸው ተመለከተ፡፡
የአባ ሙሴ ጸሊም በረከት ይደርብን አሜን
ዋቢ   ስንክሳር ሠኔ 24
በበረሓው ጉያ ውስጥ

የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር እንደማይሠራ በድጋሚ አረጋገጠ


  • የደብሩ ማኅበረ ካህናት የፈረሙበትን ደብዳቤ ተመልከቱ

(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ መልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።

ሊቀ ጳጳሱ መግለጫዎቻቸውን እና መመሪያዎቻቸውን ጸረ ተዋሕዶ በሆኑ ብሎጎች/ የጡመራ መድረኮች ላይ ማውጣታቸውን በጽኑዕ የነቀፈው መግለጫው “የብፁዕነታቸው ማንኛውም መልዕክት ያለ እሳቸው ፈቃድ ነው የወጣው እንዳይባል ምንም ዓይነት የጽሑፍ ማስተባበያ ያልሰጡ በመሆናቸው እና ይህንና ይህንን በመሳሰሉት የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ምክንያት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ማምጣት ሳይሆን መለያየት ምክንያት ከመሆናቸው በተጨማሪ ለቤተ ክርስቲያን ክብር እና መቆርቆር እንደሌላቸው ከዚህ ተግባራቸው ተረድተናል። ስለዚህ … ቤተ ክርስቲያናችን አብራ የማትሠራ መሆኑን እና የፈፀሙትንም ተግባር የምንቃወመው መሆኑን ለሚመለከተው አካላት ሁሉ መግለፅ አስፈልጎናል። በአጠቃላይ የብፁዕነታቸው አካሄድ፦ 1. ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት መሆኑን የዘነጋ፣ 2. የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ያስቀመጡትን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቀስ በቀስ የሚሸረሽር በመሆኑ … ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጋር አብሮ ለመሥራት የማንችል መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ለመላከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ እና ለዲ. ስዩም ወ/አረጋዊ የተሠጠውን ሹመትም የማንቀበል መሆኑን እናስታውቃለን” ይላል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።


ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን

11 comments:

Anonymous said...
Endih New Enji Jegninet... Enat eko lijochuwan yemititebikibet gize new
Anonymous said...
Great Vegas,that how it should be done.Everyone should learn from vegas.
Anonymous said...
ይበል የሚያሰኝ ነዉ ቬጋሶች እንዲያ ነዉ እንጂ!

ለሌሎች አራአያነት ያለዉ ሥራ ነዉ የሠራችሁት ሌሎችም የናንተኑ ፈለግ ቢከተሉ መልካም ነዉ። በተለይ ስም በመጥራት (ከመረቁ አዉጡልኝ ... አይነት) ላይ ያሉትም እንዲሁ ሊያደርጉ ይገባቸዋል። ደጋፊዎች አሉኝ እያሉ እዚያ አገር ቤት የሚያወሩትና የሚያስወሩትም ለዚሁ ይመስላል። አቡነ ፋኑኤልን ባዶአቸዉን የምናስቀርበት ጊዜ አሁን ነዉ።
አቡነ ፋኑኤል እና አቡነ ጳዉሎስ ከነ ግብር አበሮቻቸዉ የቤተ ክርስቲያናችንን እድገት ሳይሆን ዉድቀትዋን ለማየት የሚናፍቁ ናቸዉና በተለይ በዚህ በሰሜን አሜሪካ በቃችሁ ልንላቸው ይገባናል።
መቼም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያያቸዉ እንደማይፈልግ ስለሚያዉቁ ከዚህ በኅላ ወደ አገር ቤት ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዳደር አይሄዱም: እዚያዉ እንደለመደባቸዉ የራሳቸዉን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክስቲያን ይዘዉ ቁጭ እንዲሉ ማድረግ ነዉ ::
Anonymous said...
Great job. All what they pointed out are acceptable.
Anonymous said...
I have been suggesting this for a long time. This is the only way to deal with Abune Paulos and his political and ethinic coronies. It is time believers fought back against, church gear clad so called fathers. It is enought they abuse poor church goers in Ethiopia, they shouldn;t be allowed to ran amock in a place we sought refugee from thier brutality. God bless
Anonymous said...
ትክክለኛ የቤተክርስቲያን ልጆች ውሳኔ። እግዚአብሔር አምላክ ቤተክርስቲያናችን ይጠብቅ።
ሁላችንም የነሡን ፈለግ በመከተል በየአብያተ ክርስቲያኑ ያሉ መናፍቃንን ጥፋት እንከላከል።
Anonymous said...
Thank God! and thanks vegas here you go the real orthodox followers and keep it up.we expect more jobs like this clearing the unclean. the God of our fathers be with you.God for the sake of your mother and our holly fathers please protect our church.amen
Anonymous said...
እናታችንን የመጠበቅ ግዴታ አለብን ጐበዝ ቨጋስ ጠንካራ ክርስትያን ያለበት ብዙ ፈተና ያሳለፉ ወንድሞችና እህቶች ያሉበት ነው አሁንም ከነዚህ በተክርስትያንን ከምጠሉ ጋር ህብርት ያለው ማንም ይሁን ማን በጥንቃቄ እንድታዩት አደራ እናንተ ውስጥ እርም የሆነውን ቤቱ ያስቀመጠ አለና
Anonymous said...
ደጀ ሰላሞች እናመሰግናለን ቬጋሶች እግዚአብሔር ይስጣችሁ ስለሃይማኖት በሰው ፊት እውነትን መመስከር ማለት ጌታችን በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ ማቴ 10፥ 32 ያለውን ምስክርነት ያገኛል በሃይማኖት ዲፕሎማሲያዊ መልስ የለም ባይሆን ከመረቁ ማለት ለቤተክርስቲያን አይደለም ለዓለምም ያሳፍራል አባ ጳውሎስ አባ መላኩ ወይም አባ ፋኑኤል እና መሰሎቻቸው የቤተክርስቲያንን ጥፋት የሚመኙ ብቻ ሳይሆን የቤተከረሰቲያናችንን ጥፋት የሚያፋጥኑ ናቸው እኛ ዝም ካልን ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ተዋህዶን ከኢትዮጵያ ምድር ልናጣት ተስማምተናል ማለት ነው ከናንተ መካከል ነውር የሆነውን ወደ ቤታቸው ያስገቡ አሉ ያሉ አስተያየት ሰጪ የሚያውቁትን ለመመስከር እርስዎስ ምን ያዘዎት እገሌ ወደ ቤትህ ያስገባሀውን ነውር ያውጣ ለምን አይሉም ለማንኛውም ለስልጣን ለጥቅምና ለተለያዩ ተራና አላፊ ነገሮች ስንል ቤተክርስቲያንን አሳልፈን ለምንሰጥና ለምንተባበር ወዮልን
Anonymous said...
Thanks Dejeselam....
Dn Seyoum Asfaw Teklearegay teblo Yistekakel
Dn seyoum w/agetay yemilew sihtet new
Anonymous said...
ደጀ ሰላሞች እናመሰግናለን ቬጋሶች እግዚአብሔር ይስጣችሁ ስለሃይማኖት በሰው ፊት እውነትን መመስከር ማለት ጌታችን በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ ማቴ 10፥ 32 ያለውን ምስክርነት ያገኛል በሃይማኖት ዲፕሎማሲያዊ መልስ የለም ባይሆን ከመረቁ ማለት ለቤተክርስቲያን አይደለም ለዓለምም ያሳፍራል አባ ጳውሎስ አባ መላኩ ወይም አባ ፋኑኤል እና መሰሎቻቸው የቤተክርስቲያንን ጥፋት የሚመኙ ብቻ ሳይሆን የቤተከረሰቲያናችንን ጥፋት የሚያፋጥኑ ናቸው እኛ ዝም ካልን ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ተዋህዶን ከኢትዮጵያ ምድር ልናጣት ተስማምተናል ማለት ነው ከናንተ መካከል ነውር የሆነውን ወደ ቤታቸው ያስገቡ አሉ ያሉ አስተያየት ሰጪ የሚያውቁትን ለመመስከር እርስዎስ ምን ያዘዎት እገሌ ወደ ቤትህ ያስገባሀውን ነውር ያውጣ ለምን አይሉም ለማንኛውም ለስልጣን ለጥቅምና ለተለያዩ ተራና አላፊ ነገሮች ስንል ቤተክርስቲያንን አሳልፈን ለምንሰጥና ለምንተባበር ወዮልን