የላስ ቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር እንደማይሠራ በድጋሚ አረጋገጠ
- የደብሩ ማኅበረ ካህናት የፈረሙበትን ደብዳቤ ተመልከቱ፤
(ደጀ ሰላም፤ ሰኔ 14/2004 ዓ.ም፤ ጁን 21/ 2012/ READ THISARTICLE IN PDF)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በምዕራብ አሜሪካ የካሊፎርኒያ ሀ/ስብከት ሥር የሚገኘው የላስ ቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ወቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን “ከብፁዕ አቡነ ፋኔኡል ጋር እንደማንሠራ እና የሸቱትንም ሾመት የማንቀበል መሆኑን” እንገልጻለን ባለበት መግለጫው አቡነ ፋኑኤል “ከዚህ በፊት ለአህጉረ ስብከቱ ተመድበው አባታዊ መመሪያ እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩት አባቶች በተለየ መልኩ በመጓዝ ካህናት እና ምዕመናንንን በማሳዘን ለመናፍቃን በር የሚከፍት የቤተ ክርስቲያን መዋቅር እና ሥርዓት ባልጠበቀ እና ባልተከተለ መንገድ መመሪያ በመስጠት እና በተግባርም በመፈፀም የግል ጥቅምን ብቻ በሚያስጠብቅ አካሄደ በመጓዛቸው በሚሠጡት የተሣሣተ እና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ አመራር ጋር አብሮ መጓዝ ተገቢ ባለመሆኑ ከዚህ በፊት ያለንን አቋም/ አቋማችንን እንገልጻለን” ብሏል።
ሊቀ ጳጳሱ መግለጫዎቻቸውን እና መመሪያዎቻቸውን ጸረ ተዋሕዶ በሆኑ ብሎጎች/ የጡመራ መድረኮች ላይ ማውጣታቸውን በጽኑዕ የነቀፈው መግለጫው “የብፁዕነታቸው ማንኛውም መልዕክት ያለ እሳቸው ፈቃድ ነው የወጣው እንዳይባል ምንም ዓይነት የጽሑፍ ማስተባበያ ያልሰጡ በመሆናቸው እና ይህንና ይህንን በመሳሰሉት የቤተ ክርስቲያን ችግሮች ምክንያት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ማምጣት ሳይሆን መለያየት ምክንያት ከመሆናቸው በተጨማሪ ለቤተ ክርስቲያን ክብር እና መቆርቆር እንደሌላቸው ከዚህ ተግባራቸው ተረድተናል። ስለዚህ … ቤተ ክርስቲያናችን አብራ የማትሠራ መሆኑን እና የፈፀሙትንም ተግባር የምንቃወመው መሆኑን ለሚመለከተው አካላት ሁሉ መግለፅ አስፈልጎናል። በአጠቃላይ የብፁዕነታቸው አካሄድ፦ 1. ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ቤት መሆኑን የዘነጋ፣ 2. የቀደሙ ቅዱሳን አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ያስቀመጡትን የቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቀስ በቀስ የሚሸረሽር በመሆኑ … ከብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ጋር አብሮ ለመሥራት የማንችል መሆኑን እና ለቤተ ክርስቲያናችን አስተዳዳሪ ለመላከ ኪዳን ቀሲስ ሳሙኤል ደጀኔ እና ለዲ. ስዩም ወ/አረጋዊ የተሠጠውን ሹመትም የማንቀበል መሆኑን እናስታውቃለን” ይላል።
የመግለጫውን ሙሉ ቃል ለማንበብ ይህንን ይጫኑ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን
11 comments:
ለሌሎች አራአያነት ያለዉ ሥራ ነዉ የሠራችሁት ሌሎችም የናንተኑ ፈለግ ቢከተሉ መልካም ነዉ። በተለይ ስም በመጥራት (ከመረቁ አዉጡልኝ ... አይነት) ላይ ያሉትም እንዲሁ ሊያደርጉ ይገባቸዋል። ደጋፊዎች አሉኝ እያሉ እዚያ አገር ቤት የሚያወሩትና የሚያስወሩትም ለዚሁ ይመስላል። አቡነ ፋኑኤልን ባዶአቸዉን የምናስቀርበት ጊዜ አሁን ነዉ።
አቡነ ፋኑኤል እና አቡነ ጳዉሎስ ከነ ግብር አበሮቻቸዉ የቤተ ክርስቲያናችንን እድገት ሳይሆን ዉድቀትዋን ለማየት የሚናፍቁ ናቸዉና በተለይ በዚህ በሰሜን አሜሪካ በቃችሁ ልንላቸው ይገባናል።
መቼም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያያቸዉ እንደማይፈልግ ስለሚያዉቁ ከዚህ በኅላ ወደ አገር ቤት ቤተ ክርስቲያንን ለማስተዳደር አይሄዱም: እዚያዉ እንደለመደባቸዉ የራሳቸዉን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክስቲያን ይዘዉ ቁጭ እንዲሉ ማድረግ ነዉ ::
ሁላችንም የነሡን ፈለግ በመከተል በየአብያተ ክርስቲያኑ ያሉ መናፍቃንን ጥፋት እንከላከል።
Dn Seyoum Asfaw Teklearegay teblo Yistekakel
Dn seyoum w/agetay yemilew sihtet new