(አንድ አድርገን ሐምሌ 27 2004 ዓ.ም) ፡- ይህስ ለሚያምኑት ነው «ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግስትየማወቅ ስልጣን ተሰጥቷቹኋል» ጌታችን እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምሳሌ በሚያስተምርበት ጊዜደቀ መዛሙርት ለምን በምሳሌ እንደሚያስተምር በጠየቁት ጊዜ የሰጣቸው መልስ ከላይ ያለውን ይመስልነበር። ዛሬም የእግዚአብሔር መንግስት ስልጣን እና ስራ ሁሉን ቻይነት እና አድራጊነት ያልተረዱ ሁሉእግዚአብሔርን አሰራር የሚቃወሙበት ብዙ አጋጣሚ አለ። ይህ ደግሞ በጣም አስቸጋሪ ነው ምክኒያቱም ሰውየእግዚአብሔርን ስራ ተቃወመ ማለት አምላክነቱን እና መለኮታዊ የሆነውን ስልጣኑንም ተጋፋ ማለት ነው።በመሆኑንም እኛ ለምናምነው የእግዚአብሔር ኃይል ስለሆነው እና ሕዝቡንም ሁሉ ለመንግስቱ ተገዢስላደረገው ስራ ሁሌም ቢሆን በእምነት እና በድፍረት እንናገራለን።
ፍልሰታ ለማርያም «ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር» ፍልሰታ ማለት “ፈለሰ” ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆንከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ማዛወር የነበሩበትን ሀገር ለቆ ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ መፍለስ ማለት ነው፡፡ ጾመፍልሰታ ሲባልም የእመቤታችን ሥጋ ከጌቴሰማኒ ወደ ገነት መፍለስን በኋላም በገነት በዕፀ ሕይወት ሥርከነበረበት መነሣቱን ለማመልከት የሚነገር ነው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 64 ዓመት በዚህዓለም ኖራ በሞት ከተለየች በኋላ እንደ አንድ ልጅዋ ሞታ መነሣቷንና ዕርገቷን ያዩ ዘንድ ሐዋርያት ከነሐሴ 1እስከ 16 የጾሙት ጾም ነው፡፡
ጾመ ፍልሰታ ከሰባቱ ዐበይት አጽዋማት አንዱ ሆኖ በቀኖና እንዲጾም ከተወሰነበት ጊዜ ጀምሮ ምእመናንይጾሙታል፡፡ እመቤታችን በ5485 ዓ.ዓ ከአባቷ ከኢያቄም ከእናቷ ከሐና “እም ሊባኖስ ትወጽዕ መርዓት፡፡ከሊባኖስ ሙሽራ ትወጣለች” ተብሎ በተነገረው መሠረት ነሐሴ 7 ቀን ተጸነሰች፡፡ ግንቦት አንድ ቀን ሊባኖስበምትባል ወረዳ በብጽአት እንደተወለደች የቤተክርስቲያን ታሪክ በሰፊው ያስረዳል፡፡ በጾም በጸሎትበአስተብቁዖት የተገኘች ናት፡፡ ንጽሕት በመሆኗም ማኅደረ እግዚአብሔር ሆናለች፡፡ እመቤታችን ከእናትናከአባቷ ዘንድ ሦስት ዓመት፣ በቤተ መቅደስ 12 ዓመት፣ ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ 33 ዓመትከሦስት ወር፣ ከዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዘንድ 14 ዓመት ከዘጠኝ ወር ጠቅላላ ድምር 64 ዓመት ሲሆናት ጥር21 ቀን በ49 ዓመተ ምሕረት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች፡፡ ነቢያት አስቀድመው ስለ እመቤታችንእረፍትና ትንሳኤ በምሥጢር ተናግረዋል፡፡
ነቢዩ ዳዊት በመዝሙር መዝ 136:8 “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት” ብሎአል፡፡ፈጣሪዬ ሆይ ምእመናንን ወደምታሳርፍበት ወደ መንግሥተ ሰማያት የመቅደስህን ታቦት ድንግል ማርያምንይዘህ ተነሥ ሲል ነው፡፡ ይህም እመቤታችን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ መነሣቷን የሚያመለክት ነው፡፡ ታቦት ያላትምማደሪያው ስለሆነች ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን “ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ እነሆ ክረምት አለፈ ዝናቡምአልፎ ሄደ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፡፡ የዜማም ጊዜ ደረሰ የቀረ… ቃል በምድራችን ተሰማ፡፡ በለሱ ጐመራወይኖችም አበቡ መዓዛቸውንም ሰጡ፡፡ ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነይ” ሲል ስለ እመቤታችን በምሳሌተናግሮአል፡፡ መኃ 2:1ዐ-13 ወዳጁን ውበቱን ተነሺ ነይ እያለ የተጣራው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ተጠሪዋምእመቤታችን ናት፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ ማለት በስደት በአይሁድ የዘወትር ጠላትነት በልጅዋ መከራና ስቅላትስምዖን በቤተ መቅደስ እንደተናገረ ልቧ በሀዘን ሠይፍ የተከፈለበት በሀዘን ፍላጻ የተወጋበት የመከራ ክረምት/ወቅት/ አልፎ የክርስቶስ ሕማሙ ፣ ሞቱ፣ ቤዛነቱ ተፈጽሟል፡፡ ትንሣኤው በምድር ላይ ተገልጧል፣ ተሰብኳልማለት ነው፡፡ በምድራችን አበባ ታይቷል ማለት የሐዋርያት ድምፅ በምድር ሁሉ ደርሷል ማለት ነው፡፡ ነቢዩዳዊት ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ ብሎ ስለ ሐዋርያት የተናገረው በዓለምያለውን መከራ ስድት ሲገልጽ ነው፡፡ መዝ 18:4:: የዜማም ጊዜ ደረሰ ያለው የመከራን ጊዜ ነው፡፡ ሸለቆችምበእህል ተሸፈኑ በደስታ ይጮሃሉ፣ ይዘምራሉም ተብሏል፡፡ መዝ 14:13 የመከር ጊዜ ደረሰ የተባለው መከርየፍሬ ጊዜ በመሆኑ ክርስትና አፍርቷል ማለት ነው፡፡ በለሱ ጐመራ ማለት ደግሞ በጐ ምግባረ ፍሬ ሳያፈሩየነበሩ ሰዎች በጐ ምግባር መሥራት መጀመራቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ በመጨረሻም ወይኖች አብበዋል፣መዓዛቸውንም ሰጥተዋል እንደተባለ በመላው ዓለም አብያተ ክርስቲያናት በሃይማኖት ማበብ መዓዛምግባራቸውን ማቅረብ ከጀመሩ በኋላ እመቤታችን ዐረፈች፡፡
እመቤታችን ጥር 21 ቀን ዕረፍት በሆነበት ዕለት ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋ ለማሳረፍ ወደ ጌቴሰማኒ መካነዕረፍት /የመቃብር ቦታ/ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንዓት መንፈስ ተነሣሥተው ቀድሞ ልጅዋን በሦስተኛውቀን ከሙታን ተነሳ፡፡ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል፡፡እያሉ በማስተማር ሕዝቡን ፈጽመው ወስደውታል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷንም እንደ ልጅዋተነሣች ዐረገች እያሉ በማስተማር ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን: ኑ ተሰብሰቡና በእሳት እናቃጥላት ብለውተማክረው መጥተው ከመካከላቸው ታውፋኒያ የተባለው ጐበዝ አይሁዳዊ ተመርጦ ሄዶ የእመቤታችንን ሥጋየተሸከሙትን አልጋ ሽንኮር ያዘ፡፡ የአልጋውን ሽንኮር በያዘ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሠይፍ ሁለትእጁን ስለ ቆረጣቸው ከአልጋው ሽንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ ታውፋንያ በፈጸመው ድርጊት ተጸጽቶ ወደእመቤታችን ስለተማጸነ በኅቡዕ ተአምር የተቆረጡ እጆቹን እንደ ቀድሞ አድርጋ ፈውሳዋለች /ስንክሳር ዘጥር/፡፡የእግዚአብሔር መልአክ የእመቤታችን ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ተድላ ደስታ ወደ አለባት ገነት በመንፈስቅዱስ ተነጠቁ፡፡ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆችአዘዛቸው፡፡ እነርሱም ትወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አሏት፡፡ ያን ጊዜም ከዕፅ ሕይወት በታች ካለመቃብር የእመቤታችን የማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡ ጌታችንም ዘላለማዊ ወደሆነ መንግሥተ ሰማያት መላእክት እናሰማዕታት እየሰገዱላት አሳረጓት፡፡ ንጉሥ ዳዊት “በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋ ተሸፋፍና ንግሥቲቱ በቀኝህትቆማለች” እንዳለ፡፡ መዝ 44:9:: ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ተመልሶ ከሰማይ ወረደ፡፡ሐዋርያት ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው፡፡ እርሱም እንዳየ እንደሰማሥጋዋም በታላቅ ክብር ማረጉን ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ፡፡ የነሐሴም ወር በባተ /በገባ/ ቀንዮሐንስ እንዲህ አላቸው፡፡ የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት ኑ፤ ሁለት ሱባኤ በመጾም እንለምን አለ፡፡ በጾምበጸሎት ሱባኤ ያዙ፤ ጌታም የእመቤታችንን ሥጋ አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ፣ በውዳሴና በጽኑ ምሕላወስደው ቀድሞ በተዘጋጀው መካነ እረፍት በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡ የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዓት በተፈጸመጊዜ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ ቶማስ አልነበረምና ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣእመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጅዋ ትንሣኤ ተነሥታ ስታርግ ያገኛታል፡፡ ትንሣኤዋን ሌሎቹሐዋርያት አይተው ለእርሱ የቀረበት መስሎት ተበሳጭቶ “በመጀመሪያ የልጅሽን ትንሣኤ አሁን ደግሞ የአንቺንትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ” ብሎ ከማዘኑ የተነሣ ከደመናው ተወርውሮ ሊወድቅ ቃጣው፡፡ እመቤታችንም ከእርሱበቀር ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤዋን እንዳላዩ ነግራው አጽናንታው ሄዶም ለሐዋርያት የሆነውን ሁሉእንዲነግራቸው አዝዛው ምልክት ይሆነው ዘንድ ሰበኗን /መግነዟን/ ሰጥታው ዐረገች፡፡ ሐዋርያው ቶማስምኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት እርሱም “ሞት በጥር በነሐሴ መቃብርእንዴት ይሆናል?” አላቸው፡፡ “አንተ እንጂ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ አሁንም አታምንምን!” ብለው በቅዱስጴጥሮስ መሪነት ወደ እመቤታችን መካነ መቃብር ይዘውት ሄደው መቃብሩን ቢከፍቱ ሥጋዋን አጡት፡፡ደነገጡም፡፡ ቶማስም “አታምኑኝም ብዬ እንጂ እመቤታችን ተነሥታ ዐርጋለች” ብሎ የሆነውን ሁሉ ነገራቸው፡፡ለማረጋገጫ ምልክት እንዲሆን የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው፡፡ ሰበኗን /መግነዟን/ ለበረከት ቆራርጠውከተከፋፈሉ በኋላ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄደዋል፡፡ ሐዋርያትም ትንሣኤሽን ቶማስ አይቶ እኛ እንዴትይቀርብናል ብለው ከነሐሴ አንድ ቀን ጀምረው ሱባኤ ገቡ፡፡ በሱባኤው መጨረሻ በነሐሴ አሥራ ስድስት ቀንጌታችን ጸሎታቸውን ተቀብሎ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቅ /ረዳት/ ቄስ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስንገባሬ ሰናይ /ዋና/ ዲያቆን አድርጐ ቀድሶ ሁሉንም ከአቆረባቸው በኋላ የእመቤታችንን ዕርገቷን ለማየትአብቅቷቸዋል፡፡
ቤተክርስቲያናችንም ሥርዓት ሠርታ ከሰባቱ ዓበይት አጽዋማት ተርታ አስገብታ ይህን ታላቅ የበረከትናየምሥጢር መግለጫ ጾም እንድንጾም አድርጋናለች፡፡ ሐዋርያት ያዩትን ድንቅ ምሥጢር የእመቤታችንንትንሳኤና ዕርገት ለማየትና ከሐዋርያት አበው በረከት ለመሳተፍ ጌታችን “ልጆቼ” ይላቸው ለነበሩ ሐዋርያትአምሳል ሕፃናትና ወጣቶች፣ ሴቶችና ወንዶች፣ አረጋውያንም የጻመ ፍልሰታን መድረስ በናፍቆት እየጠበቁበየዓመቱ በጾም በጸሎት ያሳልፉታል፡፡ የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት መታሰቢያ /በጾመ ፍልሰታ/ ወቅትብዙዎች ከቤታቸው ተለይተው በመቃብር ቤት ዘግተው፣ አልጋና ምንጣፍ ትተው፣ በመሬት ላይ ተኝተው ዝግንጥሬ እፍኝ ውኃ እየቀመሱ በጾምና በጸሎት በመትጋት በታላቅ ተጋድሎ ይሰነብታሉ፡፡ በሰሙነ ፍልሰታምእመናን ለእመቤታችን ያላቸውን ጽኑና ጥልቅ ፍቅር የሚያሳዩበት ነው፡፡ ጌታችን ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊትበከርሰ መቃብር ቆይቶ ሙስና መቃብር ሳያገኘው፣ መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይል በሥልጣኑእሑድ በመንፈቀ ሌሊት እንደተነሣ ሁሉ እርሷም በተቀበረች በሦስተኛው ቀን ማኅደረ መለኮት ናትና ሙስናመቃብር ሳያገኛት መግነዝ ፍቱልኝ፣ መቃብር ክፈቱልኝ ሳትል የልጅዋ ሥልጣን ኃይል ሆኗት መነሣቷንትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ፤ እንደ ልጅዋ ትንሣኤ” ነው ተብሎ ሲከበርላት ይኖራል፡፡ በዚሁ በነሐሴ 16ቀን የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ፍልሰቱ ነው፡፡ ሥጋው ከፋርስ ሀገር ወደ ሀገሩ ወደ ልዳ በክብር የፈለሰበትነው፡፡ ፍልሰቴን ከፍልሰትሽ አድርጊልኝ፣ ብሎ ለምኗት ስለነበር ፍልሰቱ ከእመቤታችን ፍልሰት ጋር እንዳሰበውሆኖለታል፡፡ ስለዚህም እርሷን መውደዱ የሚያውቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይስላሉ፡፡ በስሙ ለሚማጸኑየድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ፡፡
ሌላው ታሪክ ድግሞ እናታችን ድንግል ማርያም ሞትን ድል አድርጋ ልክ እንደ ልጇ ተነስታ ባረገች ጊዜ ለቶማስየሰጠችውን ሰበን ሐዋሪያት ተከፋፍለው ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ጋራ ይዘው ወደየ አገረስብከታቸው በዓለም ወንጌልን ለመስበክ ዞረዋል በሄዱበት ስፍራ ሁሉ ከጌታችን መስቀል ጋራ የድንግልማርያምን ሰበንም ይዘው ዞረዋል። ዛሬም ይህን ምሳሌ በማድረግ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ከጌታችን ከኢየሱስክርስቶስ መስቀል ጋራ የሚይዙት ጨርቅ የዚህ ምሳሌ ነው። ድንግል ትንሳኤሽ እስከምናይ ድረስ……..ትንሳኤ ማለት ከሞት በኌላ በነፍስ ብቻ ሳይሆን በስጋምና በነፍስ ሕይወት ማግኘት ማለት ነው። ትንሳኤከትንታዊና ተስፋን ያዘለ እንደሆነ መጽሐፍ ቅሱስ ይነግረናል፡ «ሙታን ሕያዋን ይሆናሉ ሬሳቸውም ይነሳሉ»ት.ኢሳ 26፥19። ይህ የሚያሳየው የትንሳኤን እውነታ ነው። ምክኒያቱ እስካሁን ድረስ ትንሳኤን የማያምንሕዝብ እና ሰው ስላለ ነው። በአንድ ወቅት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዱቃውያን ትንሳኤ ሙታን የሚባል ነገርየለም ብለው ሲሞግቱት እንዲህ ማለቱን እንመለከታለን «….ኢየሱስም እንዲህ አላቸው መጽሐፍትን እናየእግዚአብሔርን ቃል አታስተውሉም እና ትስታላችሁ» ማቴ.21፥29። ይልቁንም ቅዱስ ዳዊት እንዳለውእንዲህም ያለ ነገር እናያለን «ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም አሴት አደረገች ሥጋየ ደግሞ በተስፋታድራለች ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና » መዝ.16፥19። የትንሳኤ ክብር እና የትንሳኤን እውነታ ያስረዳናል።እኛ የሰው ልጆች ትንሳኤ ሙታን መኖሩን ከተረዳን ዘንድ አሁን ደግሞ አንድ ማወቅ ያለብን እውነት አለ ይህምየጌታችን እናት ድንግል ማርያም ልክ እንደ ልጀዋ ማረጉዋን እና መነሳቱዋን ነው። ምክኒያቱም ነቢዩ ሳዊትበትንቢቱ እንዲህ ብሎዋል «ቅዱሱንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም» እንዳለው ድንግል እናታችንምሞት ድል ለማድረግ የልዋን ኃይል ኃይል አድርጋ ተነስታለች። በመሆኑም እኛ የተዋሕዶ አማኞች ይህንበማመን ሁሌም የድንግልን ትንሳኤ ለማየት እና ከበረከቱዋም ተሳታፊ ያደርገን ዘንድ እንደ ሐዋሪያት በአንድእና በመንፈስ በመሆን ሱባኤ እንይዛለን፡ በዚህ ወቅት አብዛኞቻችን ልባችንን ፍጹም አሳረፈን ወደ አምላካችንበማቅናት ስለ በደላችንም የምናለቅስበት እና የልቦናችንን ዓይንም ያበራልን ዘንድ የምንጸለይበት ወቅት ነው።የድንግል ማርያም ምልጃ እና በረከት ከሁላችንም ጋራ ይሁን። ለአባቶቻችን ለቅዱሳን ሐዋርያት ጸጋና ኃይልንየሰጠች እመቤታችን በረከትና ጸጋን ታድለን፡፡ አማላጅነቷ አይለየን አሜን፡፡ ወስብሐት ለእግዚአብሔር
By: Abel Kassahun