ከታምራት ፍሰሃ
ፌስቡክ ገጽ ላይ የተወሰደ
እነሆ የጌታ ልደት ደረሰ ፡ የጭፈራ ጊዜም ደረሰ ፡ የዳንስና የእስክስታ የመጠጥና የዝሙት ጊዜም ደረሰ። ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የጌታዋን ልደት ድምጿን ከፍ አድርጋ ታውጃለች ፤ የዚህ አለም ገዢ ዲያቢሎስ ደግሞ ይህን ቅዱስ ጥሪ ማንም እንዳይሰማው ይህን አለም በልዩ ጩኸት በክሎታል ፤ ጭኸቱንም በሚዲያዎች በኩል ያደርጋል። “እንኳን ለጌታ ልደት አደረሳችሁ” ይሉናል። ቀጠል አድርገውም “እዚህ ክለብ ብትሄዱ ለገና ልዩ ዝግጅት ተዘጋጅቷል ፡ ጭፈራው ዘፈኑ ሌላ ነው ፡ መጠጡ ምግቡ ልዩ ነው ፡ ሆይታው ሞቅታው ልዩ ነው ፡ ኑ ና ጌታችሁን እያሳዘናችሁ የዲያቢሎስን ፈቃድ ፈፅሙ” ሲሉ በጥበብ እንሰማቸዋለን፤ በጌታችን ልደት ሰይጣን የሚከብርበት ፡ በክርስቲያኖች ልደት ዲያቢሎስ የሚደምቅበት ፡ በመድሃኒት ክርስቶስ መገለጥ ፡ የዚህ አለም ገዢ ሃሳዊው መሲህ የሚታይበት ይህ ዘመን እንደምን ክፉ ነው?