ከሱላማጢስ
በቅርቡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተጀመረውን ሥር ነቀል አስተዳደራዊ ለውጥ ተከትሎ ብቅ ብቅ ያሉ ውስጣቸው ተሃድሶ የሆኑ ጥቂት ሰባክያንና የአድባራት አስተዳዳሪዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ የተስፋፋውን የኑፋቄና የሙስናን በሽታ ከሥሩ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነቅሎ ለመጣል በሚደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የተነሳ ይኸው በሽታ የተቆራኛቸው እነ መላከ መንክራት ኃይሌ አብርሃ፣ አባ ሠረቀ እና ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ፣ ሊቀ ትጉሃን ዘካርስ፣ መላከ ብስራት መላክ አበባውን ጨምሮ በሙስናና በኑፋቄ የተጨማለቁ ግለሰቦች ለለውጡ እንቅፋት ለመሆን ዋና ተዋናዮች ናቸው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከትናንት በስትያ በፋንታ ገላው የመንበረ ፓትርያርክ ቅ/ማርያም ሰባኬ ወንጌል አስተባባሪነት የሚመራ ጥቂት የተሃድሶ አቀንቃኞች ሰባክያን ከእነ ኃይሌ አብርሃ ጋር በመቀናጀት እነ በጋሻው በአዲስ አበባ አድባራት እንዲሰብኩ ማድረግ አለብን፥ የለውጡን አቅጣጫ ለማስቀየስ ይህንን መጠቀም አለብን፥ ማኅበረ ቅዱሳንን በዚህ መልኩ ማናደድ አለብን የሚል ተራ አስተሳሰብና ሓላፊንት የጎደለው አስተሳሰብ በመያዝ መነጋገር መጀመራቸውን ምንጮች ጠቁመዋል።
በወንጌል እንደተጻፋ "እስከ መከር ድረስ ይቆዩ" ተብለው ለጊዜው በቤተክርስቲያናችን እንደ እባብ እራሳቸውን ቀብረው ያሉ ሰባክያን እና አስተዳዳሪዎች በይፋ በመውጣታቸው ማንነታቸው ይገለጣል እንጂ ምንም የሚፈጠር ነገር እንደማይኖር የታወቀ ነው ፡፡
በተያያዘ መረጃ፣ 96 / ዘጠና ስድስት ፐርሰንት/ የሆኑት የሀገረ ስብከቱን አስተዳደራዊ ለውጥ በታላቅ ደስታ የተቀበሉትና ለአፈጻጸሙ ዝግጅት ላይ የሚገኙት የአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎችና ካህናት፣ የአዲስ አበባ አድባራት፣ የሰንበት ት/ቤት አባላት እና ምእመናን የቤተክርስቲኒቷ አስተዳደራዊ ለውጥ ያለምንም እንከን ወደ ስራ መተርጎም አለበት ፤ ለውጡን የሚያደናቅፉት ሙሰኞችና ተሀድሶውያን ከቤተክርስቲያናችን እጃቸውን ያንሱ እስከ አሁን የዘረፉት ይበቃል ፤ በሕግም ይጠየቁልን…….. የሚል ጥያቄ ለቅዱስ ፓትርያርኩና ለቋሚ ሲኖዶስ ለማቅረብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በመደረግ ነው፡፡
ተጨማሪ መረጃ እናደርሳለን ፤ ይቆየን ፡፡
No comments:
Post a Comment