Friday, 17 August 2012

የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣ ““የገበያ ግርግር …” ይሆናል


“ቤተ ክርስቲያናችን አዲስ ፓትርያርክ ከመምረጧ አስቀድሞ አሁን ከገባችበት ዝብርቅርቅ ሁናቴ ለማገገም፣ ከሐዘኗም ለመጽናናት እና አሠራሯን በሥርዓተ አበው መሠረት ለማከናወን ጊዜ ያስፈልጋታል።”
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/ 2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ እነሆ አረፉ። በብዙ እሰጥ አገባዎች የተሞላው ዘመነ ፕትርክናቸው አሁን ሌላ እሰጥ አገባ ሊፈጥር እነሆ ተፈጠመ። ነገር ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ በመስቀለኛ መንገድ ላይ እንደቆመች ናት። ይህንን የፕትርክና ምርጫ በሰላማዊና ክርስቲያናዊ መንገድ ማካሔድ ከቻለች ብሩህ ዘመን፣ አልያም ደግሞ በግርግር እና በጥቅመኞች ፍላጎት በሚመራ አሠራር ከተከናወነም ሌላ የመከራ ዘመን ሊጠብቃት ይችላል።