አንዳንዴ የትግላችን፣የጥረታችን፣የልፋታችን ውጤት መና የቀረ የሚመስልበት ጊዜ አለ፡፡ ውኃ አልቋጥር፣ ጠብ አልል ሲልብን፤ መንገዱ ሁሉ ረዥም፣ በሮቹ ሁሉ ዝግ፣ ጩኸቱ ሁሉ ሰሚ አልባ ሲመስለን፣ በመጨረሻ የምንወሰደው መፍትሔ ነገር ዓለሙን ሁሉ መተውና መሸነፍ ይሆናል፡፡ ‹‹ከዚህ በኋላ አበቃ›› ማለት እንጀምራለን፡፡ እንኳን እኛ ቀርቶ ሌሎች እንኳን እንዳይበረቱ ‹‹ባክህ እኛም ብለነው ብለነው አቅቶን ነው›› እያልን ተስፋ እናስቆርጣቸዋለን፡፡ግን ሰው መልፋት ያለበት፣ መትጋትስ ያለበት፣ መታገልስ ያለበት፣ መሮጥስ ያለበት እስከ የት ነው?ሰው ተስፋ መቁረጥ ያለበት የት ደረጃ ሲደርስ ነው? የመንገድ ማለቂያው የት ነው? ውጤቱን ዛሬ ያላየነው ነገር ሁሉ ውጤት አልባ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላልን? በታሰበው ጊዜ ያልተደረሰበት ነገር ሁሉ ሊደረስበት የማይችል ነገር ነው ማለት ነው? መንገዱስ ይሄ እኛ የያዝነው መንገድ ብቻ ነውን? በሌላ መንገድስ ሊሞከር አይቻልምን?መሆኑ ከማቆምና ከመቀጠል የትኛው ይመረጣል? ከማቆም ምን ይገኛል? ከተስፋ መቁረጥ በቀር፡፡ የሚጓዝ ሰው ጊዜው ይረዝም ይሆናል እንጂ አንድ ቀን የሚፈልገው ቦታ ይደርሳል፡፡ የቆመ ሰው ግን እንኳን ወደሚፈልግበት ለመሄድ ወደ ተነሣበት ቦታም ተመልሶ አይደርስም፡፡ የሚታገል ሰው አንድ ቀን ያሸንፋል፤ ያቆመ ሰው ግን ሳይማረክ እጁን ሰጥቷል፡፡ ደጋግሞ የሚያንኳኳ ሰው ከተኙት ሰዎች አንዱን መቀስቀሱ አይቀርም፤ ማንኳኳት ያቆመው ግን እንኳን ሊቀሰቅስ ራሱም ይተኛል፡፡ የሚሄድ መኪና ጋራጅ ይደርሳል፤ የቆመ መኪና ግን ባለበት ይወላልቃል፡፡ ለማሸነፍ ትልቁ መፍትሔ አቋምን መቀየር ሳይሆን መንገድን መቀየር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን መሞካከር ሳይሆን አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መሞከር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ማየት ሳይሆን አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማየት መቻል ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በውሳኔ ጊዜ መቁረጥ መቻል ነው፡፡ የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡ሁለት ዕንቁራሪቶች እየተጓዙ ነበር፡፡ አንዷ ወፍራም ሌላዋም ቀጭን ነበሩ፡፡ እንዳጋጣሚ በገረወይና የተሞላ ወተት አገኙና ሰፍ ብለው ገቡበት፡፡ እዚያም አስኪበቃቸው ጠጡና ሲጠግቡ መውጣት ፈለጉ፡፡ ነገር ግን ውስጡ ያንዳልጥ ስለ ነበር ለመውጣት አልቻሉም፡፡ እግራቸውን ባንቀሳቀሱ ቁጥር ወተቱ እያንዳለጠ እዚያው ይጨምራቸዋል፡፡ ከጠዋት እስከ እኩለ ቀን ድረስ እጅግ ደከሙ፤ ነገር ግን ከድካም በቀር ያተረፉት ትርፍ አልነበረም፡፡በምን ቀን ነው እዚህ ወተት ውስጥ የገባነው? እያሉ ቀናቸውን የሚያማርሩበት ሰዓት ላይ ደረሱ፡፡
የሚያማክሩት ሽማግሌ የሚጠይቁት ባለሞያ በአካባቢያቸው አልነበረም፡፡ ወደ ኋላ ተጉዘው የሰሟቸውንና ያዩዋቸውን ነገሮች ሁሉ አስታወሱ፡፡ ነገር ግን ለዚህ ነገር መፍትሔ የሚሆን ነገር ማስታወስ አልቻሉም፡፡ ወደ ሰማይ ቢጸልዩ እንኳን ጸሎታቸው የተሰማ አልመሰላቸውም፡፡ አንዳች ፈጣን መልስ አላገኙምና፡፡ በአካባቢው የሚያልፉ ሰዎችም ሆኑ ሌሎች ዕንቁራሪቶች ድምፃቸውን ሰምተው ከማለፍ በቀር ዘወር ብለው ሊያዋቸው አልቻሉም፡፡ አንዳንዶቹም ከገረወይናው ውስጥ የሚሰማው ዕንቁራሪቶች ድምፅ ከተለመደው ውጭ ነው ብለው ለማሰብ አልቻሉም፡፡ወፍራሟ ዕንቁራሪት ተስፋ ቆረጠች፡፡ ‹‹በቃን፤ ከድካም በቀር የተረፈን የለም፡፡ ለመውጣት መታገሉን ማቆም አለብን›› አለች፡፡ ቀጭኗ ግን ‹‹ የለም ከተስፋ መቁረጥ የምናገኘው ምንም ነገር የለም፡፡ ተቀምጦ ከመሞት እየታገሉ መሞት፤ ተሸንፎ ከመሞት እያሸነፉ መሞት፤ እጅ ሰጥቶ ከመሞት እጅን እያሠሩ መሞት፣ አልችልም ብሎ ከመሞት እችላለሁ ብሎ መሞት የተሻለ ነውና አታቁሚ›› አለቻት፡፡‹‹እስኪ ተመልከቺ ከጠዋት ጀምረን ለፋን፡፡ የጠጣነው ወተት እንኳን እስኪያልቅ ድረስ ለፋን፡፡ ከሰማይም ሆነ ከምድር የደረሰልን የለም፡፡ የእኛም ድካም ውጤት አላመጣም፡፡ አንዳንድ ጊዜ የምናደርገው ሁሉ ቀልድ ይመስለኛል፡፡ ተንቦጫረቅን ተንቦጫረቅን፤ ወይ የሚንቦጫረቁ ልጆች የሚያገኙትን ደስታ አላገኘን፤ አለበለዚያም ደግሞ ከዚህ ቦታ መውጣት አልቻልንም፡፡ ታድያ የልፋታችን ዋጋው ምንድን ነው? እዚህ ቦታ መልፋታችንን እንኳን ያወቀልን የለም፡፡››‹‹የሚረዳን ብናገኝ እንኳን የምንጠቀመው እኛ ለመውጣት የምንደርገውን ተጋድሎ ካላቋረጥን ብቻ ነው፡፡ ከልምድ መፍትሔውን የምናገኘው እኛ ጥረታችንን ካላቋረጥን ብቻ ነው፡፡ አንድ ቀን ይህንን ችግር ልናሸንፈው የምንችለው እኛ እየጣርን ከቀጠልን ብቻ ነው፡፡›› አለቻት ቀጭኗ ዕንቁራሪት፡፡ ‹‹ባለፈው ጊዜ አታስታውሽም ቅቤ ውስጥ የገቡት ሦስት ዕንቁራሪቶች ምን ሆኑ?›› ወፍራሟ ይህንን ስትጠይቅ ለመውጣት የምታደርገውን ጥረት እያቆመችው ነበር፡፡‹‹ለምን የተሸነፉትን ትጠቅሻቸዋለሽ? ከተሸነፉት መማር ያለብንኮ ለምን ተሸነፉ የሚለውን እንጂ የጥረት መጨረሻው መሸነፍ መሆኑን አይደለም፡፡ ሽንፈትኮ ትምህርት አያስፈልገውም፡፡ ሽንፈትኮ ልምድ አያስፈልገውም፡፡ ዕውቀት አያስፈልገውም፡፡ ሽንፈት እጅን አጣጥፎ መቀመጥ ብቻ ይበቃዋል፡፡ ለሽንፈት ምሳሌ መጥቀስ አያስፈል ግሽም፡፡ ሽንፈት ማለት በቀላሉ የሚደረስበት ነገር ነው፡፡ ሳትለፊ የምታገኚው ነገር ነው፡፡ ምሳሌ፣ አርአያ፣ ልምድ፣ ዕውቀት፣ ጥበብ፣ የሚያስፈልገው ድል ብቻ ነው፡፡ ስኬት ብቻ ነው፡፡ እርሱ በቀላሉ ስለማይገኝ ካገኙት ሰዎች ልምድና ጥበብ መቅሰም ያስፈልገዋል፡፡›› ቀጭኗ ዕንቁራሪት አሁንም በእግሮቿ ወተቱን መምታት አላቆመችም፡፡ እግሯ እየዛለ፤ ወገቧም እየከዳት ቢመጣም ግን ከወተቱ ላይ ተደግፋ ለመስፈንጠር በመታተር ላይ ነበረች፡፡‹‹እሺ ይሄው አንቺ እስካሁን በመልፋት ላይ ነሽ፤ ግን ምን አመጣሽ? ቢያንስ ከድካሜ እፎይ ያልኩት እኔ አልሻልም››‹‹ፈጽሞ አትሻይም›› አለቻት ቀጭኗ‹‹እንዴት››‹‹ቢያንስ እኔ ተስፋ አለኝ፤ አንቺ ግን የለሽም፡፡ እኔ በጥረት ውስጥ ደስታን አገኛለሁ፡፡ አንቺ ግን በኀዘን ውስጥ ነሽ፡፡ ጥረትኮ ባይሳካ እንኳን ደስታን ይሰጣል፡፡ ከቁዘማና ከድብርት ነፃ ያደርጋል፡፡ የሚጥር ስለነገ፤ ያቆመ ስለ ትናንት ያስባል፡፡ የሚጥር ስለ ኑሮ ያቆመ ግን ስለ ሞት ያስባል፡፡ በሩጫው ዓለም በመጀመርያዎቹ ዙሮች ቀዳሚውም መጨረሻውም እኩል ናቸው፡፡ አንዳንዴ እንዲያውም ተሸናፊው ከአሸናፊው የተሻለ መስሎ የሚታይበትም ጊዜ አለ፡፡ ግን ደወል ይደወላል፤ ያን ጊዜም አሸናፊውና ተሸናፊው ይለያል፡፡›› ‹‹በይ አንቺ እቴ አይሰለችሽም ቀጥይ፤ እኔ ግን በቃኝ፡፡ አንዳች ነገር ጠብ ላይል ምን አደከመኝ፡፡›› አለቻት ወፍራሟ ዕንቁራሪት፡፡‹‹ቢያንስ ቢያንስ ደክሞሽ ሳታስቢው መሞት እየቻልሽ እንዴት ዓይንሽ እያየ ሰጥመሽ ትሞቻለሽ›› አለቻት ቀጭኗ፡፡ወፍራሟ ግን አቆመች፡፡ ቀስ በቀስም ወደ ታች መስጠም ጀመረች፡፡ ቀጭኗ ዕንቁራሪት ልትረዳት ሞክራ ነበር፡፡ ነገር ግን ወፍራሟ ምንም ጥረት ስላላደረገች የርሷ ርዳታ ውጤት ሊያመጣ አልቻለም፡፡ የሌላ እገዛ ውጤት የሚያመጣው የራስ ጥረት ካለ ብቻ ነው፡፡ አፉን ያልከፈተን ሰው ማጉረስ፣ ላልተፈተነም ሰው ቦነስ መስጠት አይቻልም፡፡ወፍራሟ ዕንቁራሪት ቀስ በቀስ ወደ ወተቱ ዕቃ ሥር ገባችና ተሰናበተች፡፡ቀጭኗ ግን አሁንም ጥረቷን አላቋረጠችም፡፡ በእግሯ አንዳች ለመቆንጠጥ እየሞከረች ትታገላለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ የወፍራሟ ጓደኛዋ መፍትሔ ይሻላል? እያለች ታስባለች፡፡ ግን ደግሞ የዚያችን መሞትና ቢያንስ የርሷን መኖር ስታየው እንደዚህ ማሰቧንም ትቃወመዋለች፡፡ አንዳንድ ጊዜ ቆም ብላ ቀጥሎ ምን ሊመጣ እንደሚችል ታስባለች፡፡ ግን ምንም ነገር ታጣበታለች፡፡ ያን ጊዜ የምታደርገው ነገር ትክክል ይሁን ስሕተት ማረጋገጥ ትቸገራለች፡፡ በእርሷና በጓደኛዋ መካከል ያለውን ልዩነት የመሞቻ ጊዜ ልዩነት ይሆን? ብላም ታስባለች፡፡እንዲህ እያሰበች እግርዋንም እያወናጨፈች ሌሊቱን በድካም አሳለፈችው፡፡ እናም ነጋ፡፡ሲነጋም እንደዚሁ በእግሯ መወናጨፍን መስፈንጠርያ መፈለጉን ተያያዘችው፡፡ እኩለ ቀን ድረስ ግን ምንም አልነበረም፡፡እኩለ ቀን ላይ እግሮቿን ስታወናጭፍ አንዳች ደረቅ ነገር ነካች፡፡ ልቧ በደስታ ቀጥ ሊል ነበር፡፡ ከየት ተገኘ? አለች፡፡ እንዴት እስከ ዛሬ አላገኘሁትም?ለካስ ላለፉት ሰዓታት ወተቱን በእግሯ ስትመታው ወተቱ እይተናጠ፣ እየተናጠ፣ እየተናጠ ሄዷል፡፡ ከጊዜ በኋላም ወደ ቅቤነት ተቀይሯል፡፡ ያን ጊዜ እግሯ የሚረግጠው ነገር አገኘ፡፡ እርሱንም ተደግፋ ከገረወይናው ውስጥ ዘልላ ወጣች፡፡‹‹ይብላኝ ተስፋ ቆርጦ ለሚያቆም እንጂ፣ የጣረስ አንዳች መውጫ ነገር ያገኛል›› አለች ምድር ስትደርስ፡፡

ዳኒ ለዚህች ሀገር ዜጋ በተለይም ለመማር ልቡ ቅርብ ለሆነ ሰው እየሰጠህ ያለው ምክር፤ተሞክሮ፤ ግሳጼ እና ትምህርት መልካም ነው፡፡ ግለሰባዊ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ ግዴታህንም እየተወጣህ ነው ቀጥልበት፡፡
ገበታ
hoping.......I agree with u on not giving up but its a tough road to take. Believe me I've been there and still is.
thank you heartily you do for generation; God bless you
Almayehu from AA
i read always your writings it heals.
anduwa negn.
I do no how to thank you danie, nice man!!!
ተስፋ ያለመቁረጥን አንዱ በር የተዘጋ ሲመስል ሌላ በር መሻት እንደሚያስፈለግ አስተምረሕናል :: ህይዎት አልጋ በ አልጋ ሊሆን ከቶዉንም አይችልም:: ችግር በተፈጠረ ቁጥር ተስፋ ከመቁረጥ አማራጭ እየፈለጉ መራመድ እንጂ ተኝቶ መጠበቅ አያስፈልግም:: መሸሽም ሆነ ማፈግፈግ ሁለቱም ለዉድቀት ይጋብዛሉ:: ስለዚህ ሕይዎትን ተጋፍጦ ለማሸነፍ መጣር እንጂ ተስፋ አይቆረጥም :: አንድ የሃገሬ ገበሬ ወላጅ እናቱ ወደ ዘመድ ጋር ሄዶ መልዕክት እንዲያደርስ ያዙታል:: ሂድ የተባልበት ስፍራ የሁለት ቀን መንገድ ነው:: የአናቱን ትዕዛዝ ለማክበር ሰንቁን ሰነቆ ለመጉዋዝ የወጣው ብላቴና አመሻሽ ላይ ወደቤቱ ተመለሰ:: እናቱም በአግራሞት እያዩት እንዴት የሁለቱን ቀን መንገድ በአንድ ቀን ጨርሶ እንደተመለሰ ይጠይቁታል:: እናቴ ሆዴ የሁለቱን ቀን መንገድ ለመሄድ አሰብኩ አሰብኩና ደክሞኝ ሳልሄድ ቀረሁ ብሎአቸዉ አረፈ። ቻይናዎች እንደሚሉት አንድ ሺህ ኪሎሜትር ለመጉዋዝ በአንድ እርምጃ እንደሚጀመረው ሁሉ ተስፋን መሰነቅ ደግ ነው::
This article has a direct and timely message for me personally. It has come at a time when I am in a dilemma of quitting everything including my ten years of marriage. I am still struggling to internalize the following poem of Mother Teresa that I wish to share here as it might help others also.
Here it goes:
"People are often unreasonable,
illogical and self-centered;
Forgive them anyway.
If you are kind,
people may accuse you of selfish ulterior motives;
Be kind anyway.
If you are successful,
you will win some false friends and true enemies;
Succeed anyway.
If you are honest and frank,
people may cheat you;
Be honest anyway.
What you spend years building,
someone could destroy overnight;
Build anyway.
If you find serenity and happiness,
they may be jealous;
Be happy anyway.
The good you do today,
people will often forget tomorrow;
Do good anyway.
Give the world the best you have,
and it may never be enough;
Give the world the best you’ve got anyway.
You see, in the final analysis,
it is between you and God;
It was never between you and them anyway."
Huh!
I am not sure if I will overcome the serious contemplation of quitting I am currently harboring.
Please pray for me.
Help me God!
your reader simachew
from A.A
May GOD give u more!!!
አንደኛው “ተስፋ” ማስቆረጥ ነው።
ሁለተኛው አሁንም “ተስፋ” ማስቆረጥ ነው!
የአምናውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ያየ ገጣም እንዲህ አለ።
ተስፋ
ለለፋ
ትመጣለች ፊሽካ ሳትነፋ!
ወንድም ዓለም ዲያቆን ዳንኤል እርስዎ የሚያነቡት መጽሐፍት የት እንደሚታተሙ ማወቅ የዘወትር ጉጉቴ ነው!! ብሩህ አእምሮ ግሩም ተሰጥዎ አልዎት። ስለሀገርና ስለቤተክርስቲያን ስለሰው ልጅ ያልዎት አመለካከት ደስ ያሰኘኛል!
“ክፉ ዘመን አይምጣ ዘመድ እንዳላጣ” አሉ እቴጌ ጣይቱ። አዲሱ ዘመን ለእርዎ እና ለውድ ቤተሰብዎ ዘመነ ፍስሃ ዘመነ ሠላም ይሁንልዎ። አዲሱ ዓመት ለእናት ቤተክርስቲያን ለእናት ሀገራችን ለሁላችንም ዘመነ ሠላም ዘመነ ፍስሃ ይሁን፤ አሜን።
ተስፋ የቀረጥኩበትን ነገር ይህንን አስተያየት ጽፌ እነዳበቃሁ ለመጀመር ወሰንኩ………….በጥረት ውስጥ ደስታ አለና፡፡
ረጅም ዕድሜ ከጤና ጋር ያድልልኝ፡፡
ዘሪሁን ከሀላባ ቁሊቶ
Egziabher Yibarkih, Hulem Tsinatun Yistih,Ante ewnetegna memhir neh
የምትጽፋቸው ጽሁፎች እንደ አንዳች ነገር ውስጥን ይነካሉ በርታ ለእንደኔ አይነት አውቀተ ላነሳቸው ሰውች ዕውቀትን መጨመር ነው።
አይጠፋም::
Transformation has cost.like those frogs which were trying to feed on the milk in the bowl and hard to go out from it. As the Deputy PM said'' we can't stand up in the middle of the mountain due to fattig, we have to use all the strength we have to reach to the top which will be safe for us.''
Right now Ethiopia has started to establish 11 fertilizer factories with out which Ethiopia will be susceptible to foreign influence.Because most of our farmers are now using fertilizer without which the land won't be productive. The other factories which have equal importance with that of the fertilizer factories are the 10 sugar factories which are under construction now. These sugar factories will provide us ethanol which could be used as fuel, sugar,electric power,animal feed and so on. The other most important thing for Ethiopia is the hydro electric power dams under construction,and rail way construction. All these constructions can't be implimented without the full understanding of the people and what opportunity cost would the people pay. The first opportunity cost is inflation, we have two choices :
one to stop those mega projects,and die like the frog which gave up to come out of the bowl and sink.
The other choice is to persevere and finish those mega projects.When we say to persevere, we shouldn't forget that we could face hard times even worse than we are facing now,but not for very long time. Those problems could make us to lose hope,but we have to be encouraged by the light we are looking at the end of the tunnel. The political atmospher could even be challenging to pursue our goal,but we should move on in a positive direction atleast in finishing those mega projects. After all if we give up, we will die, so better to fight,fight and fight until death, this fight of ours is on poverty and ignorance.
Is there any shame worse than begging for food for more than half a century? Is there any shame worse than fighting each other for power while there is enough assignment for everyone to do? We have to not give up,but we should strive relentlessly to come out of this.Let us share the burden and do what we can do, to see a better future. May God be with us!
ትህትና ነኝ ከ አ.አ
ለማሸነፍ ትልቁ መፍትሔ አቋምን መቀየር ሳይሆን መንገድን መቀየር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን መሞካከር ሳይሆን አንድን ነገር በተለያዩ መንገዶች መሞከር ነው፡፡ የተለያዩ ነገሮችን ማየት ሳይሆን አንድን ነገር በተለየ መንገድ ለማየት መቻል ነው፡፡ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን፣ በውሳኔ ጊዜ መቁረጥ መቻል ነው፡፡ የምታገኘውን ሞት ከመመኘት የማታገኛትን ሕይወት በሚገባ ለመኖር ጣር፡፡
እነዚህ ሁለት ፓራግራፎች በጣም ነክተውኛል:: may God bless u