ገብረ ኪዳን
የፓትርያርክ ጳውሎስን ሞት ተከትሎ ፣ ታዋቂው ደራሲና ሰባኪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት “ለምጣዱ ሲባል አይጧን ” በሚል ርእስ ፣ አጭር ግን ጠንካራ መልእክት ለመላው ኢትዮጵያውያን አስተላልፎ ነበር ።
የጽሁፉም ዋና ጭብጥ አንድና ግልጽ ነው— ለቤተ ክርስትያኒቱ ክብር ሲባል ለተወሰኑ ቀናት ስለፓትርያርኩ ክፉ ስራና ደካማ ጎኖች የሚያትቱ ጽሁፎችምሆነ ውይይቶች አንዲዘገዩ “ የሚማጸን ነበር ። ለቤተ ክርስትያኗ ክብር ሲባል መራሄ ቤተ ክህነቱ አቡነ ጳውሎስ ከበቂ በላይ የሀዘን ( ይገባቸዋል ብዬ ባላምንም) ስርአት ተካሂዷል ። እነሆ አሁን በዘመናቸው ስለተከናወኑ አሰቃቂና አስጸያፊ ወንጀሎች እናውሳ።
ሟች ፓትርያርክ ጳውሎስ ይወቀሱበትና ይከሰሱበት የነበሩት ወንጀሎች ብዙ ናቸው። በሃይማኖት ጉዳይ አለቃ አያሌው በመፍቀሬ ካቶሊክነት ሲወቅሷቸው ፣ አቡነ አብርሃምና ሌሎች በርካታ ኦርቶዶክሳውያን ሊቃነ ጳጳሳት ደግሞ ጥንተ አብሶን በተመለከተ ፓትርያርኩ በመመረቂያ ጽሁፋቸው ላይ በጻፉት ኢ – ኦርቶዶሳዊ ትምህርት አንቀው ይዘዋቸው ነበር። በገንዘብ አባካኝነትና በሙስና ሲወቀሱ የነበሩት ፓትርያርክ ጳውሎስ ፣ ህይወታቸው ሲያልፍ በዘመዶቻቸው አካውንት አስከፍተው ያስቀመጡት 22 ሚሊዮን ብር መገኘቱ በሙስና የሚቀርብባቸውን ወቀሳ እውነተኛነት ያመላክታል። ሌሎችም ብዙ መረጃና ማስረጃ የተገኘባቸው ክፉ ስራ ቢኖራቸውም እኔ ግን የትኩረት ነጥቤ የሳቸውን ስልጣን ከመጠበቅ ጋር በተያያዘ በምስጢር የተገደሉትን የሊቃነ ጳጳሳትና የሊቃውንተ ቤተ ክርስትያን ህይወት ይመለከታል።
የሊቃነ ጳጳሳቱ እልቂት በወፍ በረር እይታ
ፓትርያርክ ጳውሎስ በህይወት በነበሩ ዘመን ያካሂዱ የነበረውን ኢ ቤተክርስትያናዊ አካሄድ አምርረው የተቃወሙ ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንተ ቤተ ክርስትያናት በርካታ ነበሩ። በሚያስገርምና ሚስጥራዊ በሆነ ሁኔታ ግን እሳቸውን አምርረው የተቃወሙ ጳጳሳትና ሊቃውንት ህይወታቸው አልፏል። የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት አቡነ ሰላማ ፣ ፓትርያርክ ጳውሎስን ክፉኛ ተቃውመው የነበሩ ቆራጥ አባት ነበሩ። ከሳቸው( ከፓትርያርኩ) ጋር ጸብ በጀመሩ በጥቂት ግዜያት ውስጥ አቡነ ሰላማ አረፉ ተባለ ። አሟሟታቸው እንግዳ ነበር ። በ2001 ዓ.ም የፓትርያርኩን አምባገነናዊ አካሄድ ክፉኛ በመቃወም ፓትርያርኩ ስልጣናቸው እንዲቀነስና እንዲገደብ ታላቅ ትግል አድርገው የነበረው አቡነ መልኬጼዲቅም በጥቂት ግዜያት ውስጥ አረፉ ። የርክበ ካህናት ስብሰባ ላይም የሲኖዶሱ አካሄድ ውሃ ወቀጣ እየመሰለ እንደመጣና ፓትርያርኩ ለሰው ከሚያደሉና ከሚገዙ ለእግዚአብሔር ቢያደሉ የተሻለ እንደሆነ በመጥቀስ ፓትርያርኩን ክፉኛ የተናገሯቸው አቡነ በርናባስም አስገራሚ በሆነ ሁኔታ በድንገት መሞታቸው ታወጀ ።የነዚህን ሊቃነ ጳጳሳት ሞት ልዩ የሚያደርገው ጳጳሳቱ የሞቱት ከአቡነ ጳውሎስ ዛቻ በሁዋላ መሆኑ ሲሆን የሁሉም ሊቃነ ጳጳሳት ሞት ምክንያት የሆድ ህመምና የጉበት መመረዝ መሆናቸው ነው። ጉዳዩ የበለጠ አስገራሚ የሚሆነው ደግሞ ሁሉም የሞቱት ምግብ ተጋብዘው ከበሉ በሁዋላ ባደረባቸው ከባድ ህመም መሆኑ ነው። ዝርዝሩን ከመሰረቱ በማስረጃ እንመልከት
2001 አ.ም እና የፓትርያርክ ፓውሎስ ስልጣን መነቃነቅ
የ2001 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ፓትርያርክ ፓውሎስን በመረረና በከበደ ሁኔታ ነበር የወቀሳቸው። ሲኖዶሱም ፓትርያርኩን ከመውቀስ ባሻገር ስልጣናቸውን የሚገድብ ውሳኔ አሳለፈ። በግንቦት ወር 2001 ዓ.ም የወጣው አዲስ ነገር ጋዜጣ ሁኔታውን እንዲህ ሲል ነበር የዘገበው
በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባዔዎችም ሆነ በሌሎች አጋጣሚዎች በፓትርያርኩ ላይ “ይህን የመሰለ ግልጽና የተብራራ ወቀሳ ቀርቦአያውቅም” ያሉት ምንጮች እንደሚያስረዱት የውይይት ሐሳብ ያቀረቡት ሊቃነ ጳጳሳት በርካታ ጉዳዮችን ማንሣታቸውንገልጸዋል። ሐሳብ አቅራቢዎቹ በጉባዔው ላይ እንደተናገሩት ከሆነ የቀድሞውን ፓትርያርክ ጨምሮ አሜሪካ በሚገኙት እና አገርቤት ባለው ዋናወ ሲኖዶስ መካከል የተፈጠረው ችግር እንዳይፈታ እንቅፋት የሆኑት ፓትርያርኩ ናቸው ብለዋል።ፓትርያርኩ ያለቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ሊቃነ ጳጳሳትን ከአንዱ አገረ ስብከት ወደ ሌላው ያዛውራሉ፤ የቤተ ክህነቱን ውራ አስኪያጅ ስልጣንበመጋፋት በተለያዩ ሃላፊነቶች ላይ የሚገኙ ሰዎችን ሾመዋል፣ ሽረዋል፣ ቀጥረዋል፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሚዲያዎች ግልጽ አሠራርናኤዲቶርያል ፖሊሲ የሌላቸው የግል መጠቀሚያ አድርገዋቸዋል፣ አሠራሩ ከሚፈቅደው ውጪ ቨግል ትእዛዛቸው ገንዘብ ሠጪአድርገዋል የሚሉት ወቀሳዎች ለሲኖዶሱ ከቀረቡት በርካታ ሐሳቦች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።ሐሳብ አቅራቢዎቹ ቅ/ፓትርያርኩያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ ፈቃድ አሜሪካ ለሚገኘው “የሀገር ፍቅር ሬዲዮ” አዘጋጅ አንድ መቶ ሺህ ብር እንዲሰጥ ማድረጋቸውንከመጥቀሳቸውም በላይ በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያኒቱ በከፍተኛ የገንዘብ ችግር ውስጥ እንደምትገኝ ለጉባዔው አስረድተዋል።ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሏት ተከታዮች ብዛትና ግዴታ ያህል የሚጠበቅባትን እያበረከተች አለመሆኑን የገለጹት ሐሳብ አቅራቢዎቹመሠረታዊ የሠራር ለውጥ ልታካሂድ እንደሚገባት መጠየቃቸውም ታውቃል [i]
ሜይ 28 2009 ኢትዮ ሚዲያ ፎረም ባወጣው ዘገባ ላይ ደግሞ ፓትርያርኩ ከስልጣናቸው እንደተወገዱና በስልጣን ዘመናቸውም ስልጣናቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ስላስፈጇቸው ጳጳሳት እንዲህ ሲል ዘገበ
Week-long session was held by the Holy Synod from 14 to 29 May 2009, which passed the resolution to avoid Abune Paulos from his power.Reports from EOC also confirm that Abune Paulos has eliminated many of his opponents. Among the bishops removed by Aba Paulos include Abune Matias, Abune Yoseph, Abune Petros and Abune Elias. They all are dead in a mysterious way. Paulos’ bodyguards have also gunned down a priest inside a church in Addis Ababa.[ii]
የፓትርያርኩ ዛቻ
ፓትርያርክ ጳውሎስ ግን ቅዱስ ሲኖዶሱ የጣለባቸውን እግድና ማእቀብ በጸጋ አልተቀበሉትም። ለሲኖዶሱ አባላት ይልቁንም እሳቸውን አጥብቀው ለተሟገቷቸው ጳጳሳት የሰጧቸው መልስ ” ወዮላችሁ ጉዳችሁ ይፈላል ” የሚል ነበር ።
ቤተ ክርስቲያንን በሙስና (ኮራፕሽን) ዘፍቀዋል፣ ክብሯን አዋርደዋል፣ አንድነቷን አደጋ ላይ ጥለዋል፣ ሚዲያዎቿን ለግልጥቅማቸውና ጠላቶቻቸውን ለማዋረድ ተጠቅመውበታል ያላቸውን ፓትርያርኩን “ከቡራኬ ውጪ” በየትኛውም ዓይነትአስተዳደርና የሹመት ሥራዎች ውስጥ እንዳይገቡ አግዷቸዋል። በቤተ ክርስቲያኒቱ የቅርብ ዘመን የአባቶች ታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ በማያውቅ መልኩ በመንፈሳዊ አርበኝነት ፓትርያርኩንየተቋቋሟቸው ብፁዓን አባቶች እንደቀድሞው ለማስፈራራት፣ “ጉዳችሁን ነው የማፈላው” ያሉትን ፓትርያርክ ሳይፈሩ በመንቀሳቀስቤተ ክርስቲያኒቱ “አበቃላት፣ አከተመላት” የተባለው የተቀናቃኞቿን ጉራ የሚያከሽፍ ተግባር ፈጽመዋል። [iii]
የፓትርያርኩ “ጉዳችሁን ነው የማፈላው” ዛቻ ተከትለው የተፈጸሙ ወንጀሎች
የፓትርያርኩ ዛቻ ግን መሬት ወድቆ አልቀረም። የሲኖዶሱ አባላት ውሳኔውን በወሰኑ እለት ማታ በፓትርያርኩ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ በማቅረብ ውሳኔው እንዲወሰን ያደረጉ አባቶች ቤት ሌሊት ባልታወቁ ሰዎች ተሰበረ። ታፍነውም የተወሰዱ አሉ:: በግዜው የነበረውን ሁኔታ ደጀ ሰላም የተባለው ድረ ገጽ እንዲህ ዘግቦት ነበር።
ዛሬ ረቡዕ ከምሽቱ አራት ሰዓት ጀምሮ በአካባቢው ያለውን የመብራት መጥፋት ተገን ያደረጉ ሰዎች በብፁዓን አባቶች ላይ አደጋመጣሉ ተሰማ::የደጀ ሰላም ምንጮች እንደተናገሩት ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ 5 ሰዓት ባለፈው ጊዜ ማንነታቸው ለጊዜው ያልታወቀሰዎች የብፁዓን አባቶችን መኖሪያ በመደብደብ፣ በር ገንጥሎ በመግባት አደጋ ለማድረስ መሞከራቸው ሲታወቅ ይህ ዜናበተጠናቀረበት ወቅት አባቶች ላይ የደረሰው አደጋ ምን እንደሆነ፣ የተጎዱትስ አባቶች ምን እንደገጠማቸው አልታወቀም።ምንጮቻችን እንደተናገሩት ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ ሲጮሁና “አድኑኝ” ሲሉ ተሰምተዋልተብሏል።ፓትርያርኩን በመቃወሙ ዘርፍ ስብሰባዎችን ሲመሩ የሰነበቱት የብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መኖሪያ በር ከተሰበረ በሁዋላ ብፁዕነታቸውየመኝታ ቤታቸውን በር ቆልፈው ከአደጋው አምልጠዋል ተብሏል። ማንነታቸውን ለጊዜው ያላወቅነው አንድ አባት ግን ችግርሳይደርስባቸው አልቀረም። እኚሁ አባት “ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ናቸው፤ ታፍነው ሳይወሰዱ አልቀሩም” ሲሉ ምንጮቻችን ጥቆማሰጥተዋል። የዛሬው አደጋ ኢላማ የሆኑት አባቶች የፓትርያርኩ ተቃዋሚዎችና በዛሬው ስብሰባ ላይ ጠንካራ ሐሳብ የሰነዘሩትናቸው ተብሏል። [iv]
የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሕክምና ሞት
ከጥቂት ግዜያት በኋላም ፤ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ በጠንካራው አባ ጳውሎስን ሲቃወሙ የነበሩትና ይህንንም በማድረጋቸው በፓትርያርኩ ደጋፊዎች በሌሊት ቤታቸው የተደበደበው አቡነ መልኬጼዲቅ በድንገት መታመማቸው ተሰማ:: ህመማቸውም ከምግብ መመረዝ ጋር በተያያዘ የጉበት በሽታ እንደሆነ በሰፊው ተወራ:: ብዙም ሳይቆዩ ከተወሰኑ ወራት በኋላ ማረፋቸው ተሰማ::
የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው በጉበት ካንሰር በሽታ ሲታከሙ ቆይተው ዛሬ ሌሊትአርፈዋል። አስከሬናቸውም ዛሬ ወደ ታላቁ የምሑር ገዳም የተሸኘ ሲሆን ሥርዓተ ቀብራቸውም ነገ ማክሰኞይፈጸማል።ብፁዕነታቸው በታታሪነታቸው ከሚመሰገኑ አበው መካከል አንዱ ሲሆኑ ባለፈው ዓመት በቤተ ክህነቱ በተነሣውየሕገ-ቤተ ክርስቲያን ይከበር ጥያቄ ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም መኖሪያቸው ከተደበደበውና አደጋ ከተጣለባቸው ብፁዓን አባቶችመካከል አንደኛው መሆናቸው ይታወሳል። [v]
የአቡነ መልከጼዲቅን ማረፍ ተከትሎ አዲስ አበባ ላይ ሲወራ የነበረው ሊቀ ጳጳሱ በግፍ እንደተገደሉ ነው። ዜናውን መጀመርያ ይዛ በወጣችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ድረ ገጽ ደጀ ሰላም ላይም የተሰጡ አስተያየቶች ይህንኑ የሚያጠናክሩ ናቸው። “ anonnymus ሚስጥር አዋቂ “በሚል መጠርያ አስተያየት የሰጡ አንድ ግለሰብ በሳቸው ሞት ዙርያ investigative journalism ይካሄድ እስከማለት ደርሰው ነበር
ከጥቂት ግዜያት በኋላም ፤ በሲኖዶሱ ስብሰባ ላይ በጠንካራው አባ ጳውሎስን ሲቃወሙ የነበሩትና ይህንንም በማድረጋቸው በፓትርያርኩ ደጋፊዎች በሌሊት ቤታቸው የተደበደበው አቡነ መልኬጼዲቅ በድንገት መታመማቸው ተሰማ:: ህመማቸውም ከምግብ መመረዝ ጋር በተያያዘ የጉበት በሽታ እንደሆነ በሰፊው ተወራ:: ብዙም ሳይቆዩ ከተወሰኑ ወራት በኋላ ማረፋቸው ተሰማ::
የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው በጉበት ካንሰር በሽታ ሲታከሙ ቆይተው ዛሬ ሌሊትአርፈዋል። አስከሬናቸውም ዛሬ ወደ ታላቁ የምሑር ገዳም የተሸኘ ሲሆን ሥርዓተ ቀብራቸውም ነገ ማክሰኞይፈጸማል።ብፁዕነታቸው በታታሪነታቸው ከሚመሰገኑ አበው መካከል አንዱ ሲሆኑ ባለፈው ዓመት በቤተ ክህነቱ በተነሣውየሕገ-ቤተ ክርስቲያን ይከበር ጥያቄ ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም መኖሪያቸው ከተደበደበውና አደጋ ከተጣለባቸው ብፁዓን አባቶችመካከል አንደኛው መሆናቸው ይታወሳል። [v]
የአቡነ መልከጼዲቅን ማረፍ ተከትሎ አዲስ አበባ ላይ ሲወራ የነበረው ሊቀ ጳጳሱ በግፍ እንደተገደሉ ነው። ዜናውን መጀመርያ ይዛ በወጣችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ድረ ገጽ ደጀ ሰላም ላይም የተሰጡ አስተያየቶች ይህንኑ የሚያጠናክሩ ናቸው። “ anonnymus ሚስጥር አዋቂ “በሚል መጠርያ አስተያየት የሰጡ አንድ ግለሰብ በሳቸው ሞት ዙርያ investigative journalism ይካሄድ እስከማለት ደርሰው ነበር
Anonymous said…
ጁላይ 15,2009 የወጣው የደጀ ሰላም ዘገባ ይህ ነበረ።
“”(ሰበር ዜና፣ Breaking News) ብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ተጣለ”ከዚያን ግዚ ጀምሮ በርካታ አባቶች ችግር አየደረሰባችው ነው። ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በከባዱ ታመው ሀኪም ፍለጋ ውጭ ህደውታከሙ። የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው አባታችንም አቡነ ጳውሎስን ከሚቃወሙወገኖች መካከል አንዱ ነበሩ።ወዲያው በጉበትና ካንሰር በሽታ ታመሙ ተባለ።አዲስ አበባ ውሰጥ ውሰጡን የሚወራው አባታችንየሞቱት በደባ መሆኑን ነው።ከምግብ ጋር በተሰጠ መድሀኒት መታመምና መሞታቸው ይናፈሳል።ደጀ ሰላሞች ባካቸሁጦማራችሁሚስጥር ልታገኝ ስለምትችል investigative journalism ብታካሂዱ።
ሚስጥር አዋቂ
ያቡነ በርናባስ ፓትርያርኩን አጥበቀው መቃወምና ድንገተኛ እረፍታቸው
ከግንቦት 10-16 ,2003 ዓ.ም የተካሄደው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይም ባባ ጳውሎስ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። የግንቦቱን ተቃውሞ ልዩ የሚያደርገው ባባ ጳውሎስ ላይ የከረረ ትችትና ተቃውሞ ያቀረቡት ከዚህ በፊት ድምጻቸው ተሰምቶ የማያውቁት አቡነ በርናባስ ነበሩ። ብጹእነታቸው የሲዳሞ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ በፓትርያርኩ አላግባብ በተሾመው ጌታቸው ዶኒ ላይ የተደረሰበት ውሳኔ እንዳይረጋ አቡነ ጳውሎስ የጉባኤውን አመራር ውኃ ቅዳ ውኃ መልስ ያደረጉበትን አካሄድ ተቃውመዋል፤ ‹‹የሲኖዶሱ አካሄድ ውኃወቀጣ ሆኗል፤ ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር፣ ከግለሰብ ይልቅ ለቤተ ክርስቲያን መወገን አይሻልምወይ?››በማለት ፓትርያርኪን በግልጽ ነቅፈው ተሰብሳቢውንም እግዚአብሔርን እንጂ ፓትርያርኩን ሳይፈሩ አባ ጳውሎስ ያቀረቡትን ንድፈ ሀሳብ እንዲቃወም አስተባብረዋል። እጅግ የሚደንቀው ግን ይሄንኑ ተቃዎሞ ባካሄዱ ምሽት የበሉት ምግብ አልተስማማቸውም ተብሎ ታመሙ። በሚቀጥለው ቀን ስብሰባ ላይ እንዃን መገኘት አልቻሉም። ያስጀመሩትን አጅንዳ እንዃን መጨረሻውን ሳያዩ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
ብፁዕነታቸው በባሕር ዳር መንበረ ጵጵስናቸው ቅዳሜ ግንቦት 20፣ ከቀኑ 8፡00 ላይ ከደረሱ በኋላ ከምሽቱ 3፡00 ላይማረፋቸውን የስፍራው ምንጮች ተናግረዋል፡፡ ብፁዕነታቸው የሰነበተ ሕማም እንደሌለባቸው፣ ግንቦት 16 ቀን የነበረውን የቅዱስሲኖዶስ ስብሰባ የመጨረሻ ቀን ውሎ ‹‹ሆዴን አሞኛል›› በማለታቸው ሳይሳተፉ መቅረታቸው ተጠቁሟል፡፡ ረቡዕ ግንቦት 17ቀን ወደ ሕክምና የተወሰዱት ብፁዕነታቸው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሪፈራል ተጽፎላቸው የነበረ ቢሆንም ‹‹ግዴለም፤እዚያው ቤቴ ውሰዱኝ፤ ባሕርዳር ስደርስ እታከመዋለሁ›› በማለታቸው መንገድ መግባታቸውን እኒሁ ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ [vi]
የአቡነ ቄርሎስ ሽሽትና ምስጢራዊ ህክምና
“ለሕይወቴ ደህንነት አይሰማኝም”:- አቡነ ቄርሎስ
እየተካሄደ ያለውን የበቀል ዱላና ስራት አልበኝነት የተረዱት አቡነ ቄርሎስ የቤተ ክህነቱን ግቢ ለቀው ግለሰብ ቤት በመሰንበት ህይወታቸውን ለማዳን ቢችሉም እሳቸውም ፤ ከዚያን ግዜ በኋላ ጤነኛ ሆነው አልታዩም:: እንደ ብዙዎች ስጋት ከሆነ አደጋ ጣዮቹ ቤታቸውን በሌሊት በሰበሩበት ወቅት ቅዱስነታቸውንም አካላዊ ጉዳት ሳያደርሱባቸው( ምንም እንኳን እሳቸው ለመናገር ፈቃደኛ ባይሆኑም) እንዳልቀረ ይገመታል:: ለዚህም ማስረጃ የሚሆነው ክስተቱ በተፈጸመ በጥቂት ግዜያት ውስጥ ወደ ታይላንድ ለህክምና መሄዳቸው ነው:: በግዜው የነበረውን የሳቸውንም ጉዳይ ደጀ ሰላም እንዲህ ዘግባው ነበር
በማፊያ ቡድን አባሎችና ወረበሎች መኖሪያቸው የተሰባበረባቸውና በሕይወታቸው ላይ አደጋ የተቃጣባቸው አረጋዊው አባትብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለደህንነታቸው በመስጋት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢን ለቅቀው እንደወጡ የቅርብ ምንጮች ገለፁ።የቅዱስሲኖዶስ የበላይነት አልቀበልም ብለው በማስፈራራትና በሀይል ጭምር አጀንዳውን ጠምዝዘው ጊዜያዊ እፎይታ ካገኙት ፓትርያርክጋር በገቡት አለመግባባት የግል ቂም ተይዞባቸው አደጋ የተጣለባቸው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ሰሞኑን የጠቅላይ ቤተ ክህነትን ግቢለቅቀው የወጡ ሲሆን አንዳንዶች ወደ ሀገረ ስብከታቸው ወደ ወሎ መሄዳቸውን ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ እዚያው አዲስ አበባከሰዎች ዘንድ ማረፋቸውን ተናግረዋል።“ለሕይወቴ ደህንነት አይሰማኝም” እንዳሉ የተጠቆመው ብፁዕነታቸው ዕቃቸውንጠቅልለው ሲወጡ መታየታቸው ሲዘገብ ሌሎች አባቶችም ቢሆኑ በተመሳሳይ የደህንነት ስጋት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል። የደጀሰላም ምንጮች ጨምረው እንደተናገሩት የፓትርያርኩ ወዳጆች የተባሉት ሳይቀሩ በፍርሃት መያዛቸው ሲነገር ፓትርያርኩይቃወመኛል የሚሉት ላይ አደጋ ከማስጣል አይመለሱም የሚለው ጉዳይ እያደገ መምጣቱ ታውቋል። [vii]
የአቡነ ይስሀቅ ድንገተኛ ህመምናና ሞት
አቡነ ይስሀቅ ፓትርያርኩን ባደባባይ መውቀስ የማይወዱ እንደውም አንዳንዴ ከፓትርያርኩ ጎን በመሰለፍ ፓትርያርክ ጳውሎስን የሚደግፉ አባት እንደነበሩ የሚያውቛቸው ይናገራሉ:: ምንም እንዃን ፓትርያርኩን ባደባባይ መውቀስ ባይወዱም በግል ግን ፓትርያርኩን ከክፉ ስራቸው ይመለሱ ዘንድ በተደጋጋሚ ይገስጿቸው ነበር:: ይህ ያልተወደደላቸው የሚመስለው አቡነ ይስሀቅም በድንገት ታመው አረፉ ተባለ:: አሟሟታቸውም እንደተለመደው ነበር:: ምግብ ተጋበዙ ሆዴን ብለው ማቃሰት ጀመሩ:: ከጥቂት ግዜያት በኋላ አረፉ::ዘገባው እንዲህ ይላል
ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ ከዕረፍታቸው ጥቂት ደቂቃዎች በፊት በቅዳሴ ከተሳተፉበት መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያምገዳም ተመልሰው ፓትርያርኩን ጨምሮ በመንበረ ፓትርያርኩ የመመገቢያ አዳራሽ ወደተገኙት አባቶች ዛሬ የሚዘከረው የጻድቁአቡነ ተክለ ሃይማኖት ወርኃዊ በዓል መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ዝክር(ኅብስት) መላካቸው እና በጸሎታቸውም እንዲያስቧቸውመጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡ ከውሎው ቅዳሴው መልስ የቀመሱት እህል እንዳልተስማማቸው እና ሕመም እንደሚሰማቸው የተናገሩትብፁዕነታቸው ብዙም ሳይቆዩ ነው ሕይወታቸው ያለፈው፡፡[viii]
የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ ሚስጥራዊ አሟሟት
በሊቅነታቸው ወደር እንደሌላቸው የሚነገርላቸው መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ልክ እንደ አቡነ ይስሀቅ ፓትርያርክ ጳውሎስን ባደባባይ መናገር የማይወዱ ነገር ግን በግል አጥብቀው ፓትርያርኩን የሚኮንኑ እንደነበሩ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በተለይ ሁለቱን ሲኖዶስ አንድ ለማደረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ፓትርያርክ መርቆርዮስንም ክፉኛ በመተቸት ይታወቃሉ። ቢሆንም ግን ሁለቱን ሲኖዶሳት ለማስታረቅ ያቅማቸውን ደፋ ቀና ያሉ አባት ነበሩ። በቅዱስ ሲኖዶስ አባቶች በተደጋጋሚ እንደተገለጸው ፓትርያርክ ጳውሎስ እርቁ እንዲመጣ ፈቃደኛ አልነበሩም። በሚደንቅ ሁኔታ እርቁን በሚመለከት ሲኖዶሱ ያሳለፈውን በጎ ውሳኔ ቃለ ጉባአ እስከመደበቅ መድረሳቸው በሰፊው ተዘግቦ እንደነበር ይታወሳል። ለ እርቁ መሳካት ከልባቸው ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩት መጋቤ ብሉይም ሳያውቁት ጥላቻ ቀለበት ውስጥ ገቡ። ለ እርቁ ጉዳይ አሜሪካ ደርሰው እንደመጡ ህይወታቸው ድንገት አለፈ ተባለ።
በትላንትናው ዕለት ረፋድ ላይ ለእርቅ እና ድርድር ጉባኤ የሄዱበትን የአሜሪካ ተልእኮ አጠናቀው አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም ዓቀፍአየር ማረፊያ እንደ ደረሱ ራሳቸውን የማቃጠል እና ልባቸውን የመውጋት ስሜት እንደተሰማቸው አብረዋቸው ለተጓዙት የልኡካንቡድኑ አባላት የተናገሩት መጋቤ ብሉይ ሰይፈ፣ አስቸኳይ ሕክምና ሊያገኙ ይችሉ ከነበረበት ስፍራ ርቆ እና ከጊዜው ዘግይቶ አራትኪሎ አካባቢ ቀድሞ ‹‹ጉድሸፐርድ›› አሁን ‹‹አዲስ የሕፃናት እና እናቶች ሆስፒታል›› በሚባለው የሕክምና ተቋም ውስጥየመጀመርያ ደረጃ ምርመራ እየተደረገላቸው ሳለ ነበር ሕይወታቸው ያለፈው፡፡ ወዲያኑ አስከሬናቸው በቅዱስ ገብርኤል እናበዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታሎች ከፍተኛ ምርመራ ከተካሄደለት በኋላ ዛሬ ቀትር ላይ ሰበካቸው በሚገኝበት እና በአገልግሎት ብዙበደከሙበት በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እንዲያርፍ ተደርጓል፡[ix]
ማጠቃለያ
በፓትርያርክ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ቤተክርስትያኗ በርካታ ሊቃነ ጳጳሳቷንና ሊቃውንቷን አጥታለች:: የሊቃነ ጳጳሳቱም ሆነ የሊቃውንቱ አሟሟት ተመሳሳይ ነው -ወይ በመኪና አደጋ ወይ ደግሞ በድንገተኛ ህመም:: ያረፉት ጳጳሳት በሙሉ ማለት ይቻላል በህይወት እያሉ ፓትርያርክ ጳውሎስን የሚቃወሙ ነበሩ:: ፓትርያርኩን አምርረው በተቃወሙ በጥቂት ግዜያት ውስጥ ሁሉም አለፉ:: ብዙዎቹ ሊቃነ ጳጳሳት የህልፈታቸው ምክንያት ምግብ ተጋብዘው ከበሉ በኋላ ” ሆዴን ” እያሉ ነው:: ጥቂቶቹም እስካሁን ግልጽ ባልሆነ መኪና አደጋ አልፈዋል:: ፓትርያርክ ጳውሎስን የተቃወሙ ሊቃውንት በሚያስገርምና ድንገተኛ ሁኔታ ህይወታቸው አልፏል:: የጎንደሩ ሊቀ ሊቃውንት በፓትርያርኩ አዲስ አበባ ” ለመጽሀፍት ትርጓሜ” ተብለው ተጠርተው አዲስ አበባ በደረሱ በጥቂት ቀናት በድንገት አረፉ ተብሎ አስከሬናቸው ተጫነ:: ከህልፈታቸው በፊት እንደ ቤተክርስትያኗ ምሁርነታቸው ፓትርያርኩን አንደገሰጿቸው ይወሳል:: አለቃ አያሌው ታምሩም በፓትርያርኩ ሃምሳ ሶስት አመት ካገለገሉበት ቤተ ክህነት በግፍ ያለደሞዝና ጡረታ ተባረው በመጨረሻ አረፉ:: መጋቤብሉይም በድንገተኛ ህመም አረፉ ::
ሊቃነ ጳጳሳቱም ሆነ ሊቃውንቱ ህይወታቸው ከማለፉ አስቀድሞ ምእመኑን ተማጽነው ነበር:: አዲስ አበባ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያለው ቤታቸው ሲሰበርና አደጋ ሲደርስባቸው ” ደረሱልን” ብለው ነበር:: እነ አቡነ ቄርሎስም ” ለህይወታችን እየሰጋን ነው” በማለት በተደጋጋሚ ተናግረው ነበር:: አቡነ መልኬጼዲቅም ከማለፋቸው አስቀድመው ህልፈታቸውን ተገንዝበውት እንደነበር የቅርብ ሰዎቻቸው ይናገራሉ:: ሌሎችም አንደዛው::
በስተመጨረሻም የዚህ ሁሉ ውዝግብ ምንጭ የሆኑት አባ ጳውሎስ ሊቃነ ጳጳሳቱት ተከትለው ወደማይቀረው የፍርድ ቦታ ሄዱ:: ይሄሁሉ ጦርነት ለዚህ ነበር:: እሳቸውም ስልጣናቸውን ክብራቸውን ገንዘባቸውን ጥለውት ሄዱ:: ተከትሏቸው የሚሄድ አምስት ሳንቲም ንብረት የለም:: በዚህች ምድር ላይ እያሉ የሰሩት ስራ ግን ተከትሏቸው ይሄዳል:: በጥይት ያስገደሉት ባህታዊ ነብስ በተለያየ ሴራ ያስፈጇቸው ጳጳሳትና ሊቃውንት ነብስ ግን በሄዱበት እየሄደ የፍርድ ያለህ ይላል:: የከፈሏት ቤተ ክርስትያን ፣ የመዘበሯት የቤተ ክርስትያን ንብረት ፣ ቅስሙን የሰበሩት የክርስትያን ነብስ ግን አሳት ሆኖ ይፈጃቸዋል::
በግፍ የተገደሉትን ሊቃነ ጳጳሳት በተመለከተ በርካታ ምእመናን እጅ በርካታ መረጃ እንዳለ ሁሉም ያውቃል:: በመርዝ አንጀታቸው እየተቃጠለ ያለቁትን አባቶቻቸንን ቢያንስ ትውልድ ይዘክራቸው ዘንድ ቢያንስ ታሪካቸውን እንጻፍላቸው::
ወስብሀት ለ እግዚአብሔር
[i] አዲስ ነገር ጋዜጣ ግንቦት 2001 ዓ.ም እትም
[ii] http://www.ethioforum.org/?p=1081
[iii] http://www.dejeselam.org/2009/05/blog-post_27.html
[iv] http://www.dejeselam.org/2009/07/blog-post_16.html
[v] http://www.dejeselam.org/2010/06/blog-post_21.html#more
[vi] http://www.dejeselam.org/2011_05_01_archive.html
[vii] http://www.dejeselam.org/2009/07/blog-post_25.html
[viii] http://www.dejeselam.org/2011/03/1927-2003.html
[ix] http://www.dejeselam.org/2010/08/blog-post_
No comments:
Post a Comment