(አንድ አድርገን ሰኔ 25 ፤2004 ዓ.ም)፡-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ ስለ አክራሪነት ሰፊ ማብራሪያ ከሰጡ ወዲያ መንግስት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከቀን ቀን እየጨመረ እየመጣ ነው ፤ መንግስት በአዲስ ራዕይ መጽሄት አማካኝነት ሀሳቡን በደንብ አድርጎ ገልጾልናል ፤ ይህን ሀሳብ በህዝቡ ዘንድ ለማስረጽ ይረዳው ዘንድ ዛሬ ሰኞ ማታ ከ2፡00 ሰዓት ዜና በኋላ ‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› የሚል ዶክመንተሪ ፊልም በኢቲቪ እንደሚለቀቅ ሰሞኑን የተመለከትናቸው ማስታወቂያዎች ይናገራሉ ፤ ይህ ወቅታዊውን ነገር መሰረት ተደርጎ የተዘጋጀ ቢሆንም አሁንም እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ነገር በክርስትያኑ እና በሙስሊም አማኞች አማካኝነት ተፈጥሯል ብለን አናምንም ፤ ይህን ሁኔታ እዚህ ደረጃ ያደረሰው መንግስት ራሱ ነው ፤ ሙስሊም ወንድሞቻችን “መጅሊስ ይውረድ” ብለው ጥያቄ በመጠየቅ ይህን ጥያቄ ጫፍ የሚያደርስ ኮሚቴ አቋቁመው ለጥያቄያቸው ተገቢ መልስ መንግስት መስጠት ሲሳነው ነገሩን ወደ አክራሪነት በማዞር ከወቅታዊ ነገር ጋር ተገቢ ያልሆነ ትንታኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ ፤ በዚህ ወቅት 90 በመቶ ንግግራቸው ወሀቢያና ሰለፊያ ሲሆኑ አንድ ቦታ ላይ ብቻ ተገቢ ያልሆነ አብሮ ሊሄድ የማይችል ምሳሌ በመስጠት የንግግራቸው ማጣፈጫ አድርገው ተጠቀሙብን ፤ ከዚያ የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር የሚቃወሙ ድምጾች ከየቦታው መሰማት ጀመሩ ፤ “የአቶ መለስን አቋም እቃወማለሁ” በማለት ሰዎች ውስጣቸውን ተነፈሱ ፤
በዚህ ጊዜ መንግስት ነገሩን ለማክረር እና የዘመናት አላማውን ለማሳካት ይመቸው ዘንድ ሌሎች ያልተፃፉ ነገሮችን እየመዘዘ ማውጣት ተያያዘው “አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት” ፤ በበዓላት ወቅት መንገዶች ላይ የሚጻፉ ጥቅሶች ፤ ህገ መንግስቱን የሚጋፋ የወጣቶችን እንቅስቃሴ በማለት እና ሌሎችን አላማውን የሚሸፍኑለትን አጀንዳዎች በማጠየም አነሳቸው ፤ ጉዳዩን ወደ ሌላ ምዕራፍ እንዲሻገር የሚፈልገውና ጠንክሮ የሚሰራው መንግስት ባሳለፍነው ወር ላይ “አዲስ ራዕይ” መጽሄት ላይ ከለፍተኛ አባሎቹ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በጣም በማጋነን አላማውን ያሳካ ዘንድ ከ40 ገጽ በላይ የሚጠጋ ጽሁፍ የሃይማትን ክብር በሚያጎድፍ መልኩ በመጻፍ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጽሁፉን አደረሰ ፤ የድርጅት አባሎቻቸውም በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜ ወስደው መከሩበት አሁንም እየመከሩበት ይገኛሉ ፤ ባለን መረጃ መሰረት አክራሪነትን በተመለከተ መጽሄቷ ላይ የሰፈረውን ጽሁፍ በመገምገም እና የኢህአዴግ አባላት አቋም ለማስያዝ ብዙ ቦታዎች ላይ መወያየታቸው መረጃዎች ደርሰውናል ፤
እስኪ እኛን አክራሪ ለማለት የሚያበቃ ወይም ከአክራሪዎች ጋር ደምሮ ለማሰብ የሚያስችል ፤ ይህን ፊልም ለማዘጋጀት የሚያደርስ በቂ ምክንያት መንግስት ይኖረዋል ብለው ያምናሉ ? ባሳለፍነው የጥምቀት በዓል ላይ “አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት” የሚል ጽሁፍ በስህተትና ካለማወቅ ሰዎች ቢለብሱ እንኳን(መልበሳቸውን ማስረጃ የለንም) ከሃይማኖት አባቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቀረብ ብሎ በመነጋገር ጽሁፉ ህገ መንግስቱንና የሌሎችን የእምነት ነጻነት ይጋፋል ፤ ስለዚህ ለወደፊት ይህን አታድርጉ ማለት አይቻልምን ? ለዚህ ፊልም መዘጋጀት መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ይህን የመሰለ አቋም የያዘበት ምክንያት ይህ ከመሰሎት ተሳስተዋል ፤ በ1984 ዓ.ም በራሳቸው አባል የተጻፈ መጽሀፍ ላይ እንደሰፈረው ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ላይ የማፈራረስ አላማ እንዳላቸው ጠቅሶ በግልጽ ፅፎልናል ፤ ይች ቤተክርስትያን የአንድነት ጉዞዋ ለእነርሱ እንቅፋት ነው ብለው ያስባሉ ፤ ስለዚህ ይህን የቤተክርስትያን የአንድነት ጉዞን ከቻሉ ለመቁረጥ ካልሆነ ደግሞ ለማላላት ዘወትር ተግተው ይሰራሉ ፤ ባሳለፍናቸው 21 ዓመታት ውስጥ በታምራት ላይኔ አማካኝነት ቤተክርስትያኒቱ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ እና ስደተኛው ሲኖዶስ ተብላ እንድትጠራ ሁለት እንድትሆን የራሳቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል ፤ ተሳክቶላቸዋልም ፤ “ኢህአዴግ እያለሁ ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ውጪ መንገድ ያለ አይመስለኝም ነበር” ብለው በቅርቡ ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የበፊት የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገብሩ አስራት ነበሩ ፤ አሳቸው ከድርጅት ተባረው ሌላ መንገድ መኖሩን ተመለከቱ ፤ አሁንም ግን የትግል አጋሮቻቸው ሌላ መንገድ አለ ብለው ለአፍታ አስበው አያውቁም ፤
ከዚህ በተጨማሪ ከ97 ወዲህ ሰዎች ለማህበራዊ ፤ ለፖለቲካዊ እና ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች ማህበር መስርተው ሲንቀሳቀሱ መመልከት ለኢህአዴጋውያን የራስ ህመም ሳይሆን የራስ እጢ ይፈጥርባቸዋል ፤ ስለዚህ በሆነው ባልሆነም ምክንያት እነዚህን ማህበራት ስማቸው ከመቃብር በታች ለማድረግ ዘወትር ያለመሰልቸት ይተጋሉ፡ ስለዚህ አሁን እየሰሩ ያሉት ነገር ይህን ነው ፤ ዛሬ የምታዩት የኢቲቪ ፊልም የነገ ህልማቸውን ለማሳካት የሚራመዱት የመጀመሪያ እርምጃ አድርገው ይውሰዱት ፤ ለዚህ ጽሁፋችን ማስረጃችንን ከቀናት በኋላ ብሎጋችን ላይ ይጠብቁ ፤(ጦላይ ማሰልጠኛ ውስጥ በአክራሪነት ላይ ለአባላት ምን አይነት ስልጠና እየሰጡ እንደሆነ እንነግሮታለን)
በአሁኑ ወቅት ‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› የሚል ፊልም የሚያዘጋጁበት ምክንያት “አዲስ ራዕይ” ላይ በተቀመጠው ሃሳብ ይመስለናል ፤ “አዲስ ራዕይ” መጽሄት ገጽ 37 ላይ እንዲህ ይላል “ጅምላ ፍረጃ ማስወገዳችን አንድ ነገር ሆኖ በየደረጃው የሰከነ ውይይት እንዲካሄድ ማድረግ ይገባል፡፡ በሚዲያ የተጀመረው ውይይትም ህዝቡ በአጠቃላይ ስዕሉንና በዝርዝር ክስተቶች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲዘነዘብ ማድረግ ያስፈልጋል ፤ ለዘብተኛ አቋም ያላቸው ጽንፈኞቹም የሚዲያ አክሰስ አግኝተው ሀሳባቸውን ቢገልጹ ህዝቡ ተጨማሪ መረጃ ያገኛል፡፡ የተሻለ ግልጽነት ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች በተለያዩ አማራጮች ሰፊው ህዝብ እውነታው ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዝ ማድረግ አለባቸው፡፡ ከወሃቢያ ይሁን ከማህበረ ቅዱሳን ወይም ከሌላው እምነት ውስጥ ጽንፈኝነት አይመለከተኝም የሚል በግላጭ ወጥቶ እንዲያወግዝ እድል ሊኖረው ይገባል ፡፡ በዚህ አግባብም ልናደፋፍረው እና ጽንፈኛው ተነጥሎ እንዲጋለጥ የሚያደርግ አካሄድ ሊኖረን ይገባል፡፡” በማለት ያስቀምጣል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይህ ወቅታዊ መሳይ ፊልም የተዘጋጀው ይህን መሰረት በማድረግ ነው ፤ እንደ መንግስት ሀሳብ ህዝቡ ዘንድ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር በማሰብ ይህን ፊልም አዘጋጅቷል ፤ ህዝቡ ግን ከዚህ በፊት የተሰሩትን “አኬልዳማን” እና መሰል የኢቲቪ ዶክመንተሪዎችን በግልጽ ስለሚያውቃቸው ይህን አይቶ እንደ እውነት ይቀበለዋ ማለት የቀን ቅዥት ነው ፤
በአኬልዳማ ዶክመንተሪ ፊልም ተከሳሾችን አሸባሪ ለማለት በ1984 ዓ.ም በወለጋ አካባቢ እና ሀረር በደኖ አካባቢ በንጹሀን ላይ የተፈጸመን የግፍ ግድያ በ2004 ዓ.ም ለ”አኬልዳማ” ዶክመንተሪ ፊልም እንደ ግብአት በመጠቀም ተከሳሾቹን “ይህን ሲሰሩ ነበር” ብሎ ያቀረበው የወረደ ስራ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቀዋል ፤ በጣም አሳፋሪው ነገር በአሁኑ ሰዓት በህይወት የሌሉ ሰዎች ምስል በአኬልዳማ ፊልም ላይ መካተቱ እና እንደ ማስረጃ በመጠቀም የተሰራው ስራ ከሙያው ስነ ምግባር ውጪ ከመሆኑም በተጨማሪ ኢቲቪ ያለፍቃድ የሞቱትን ሰዎች ምስል በማውጣቱ ቤተሰቦቻቸውን ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል ፡፡
ድሮ ድሮ ህዝባችን የዋህ ከመሆኑ የተነሳ ነገሮችን ፊልም ሰርቶ ለማሳመን ቀላል ነበር ፤ ህዝባችን እኮ “ሰው ለሰው” ድራማን አይቶ ተዋናዩ ደራሲው በሰጠው ገጸ-ባህሪ አማካኝነት ተዋናዩን የሚጠላ ነው ፤ አሁን ግን “ኢቲቪን ማመን ዘግቶ ነው” የሚባል አባባል ውስጥ ውስጡን ማንሸራሸር ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል ፤ የኢቲቪ ዋናው ችግሩ ለማን እንደሚያዘጋጅ አለማወቁ ነው ፤ እነሱ የሚያወሩልን ኢትዮጵያ እና እኛ የምናውቃት ኢትዮጵያ እየተራራቁብን ተቸግረናል ፤ህዝቡ የሚያውቀው አክራሪነት እና እነሱ የሚያወሩት አክራሪነት አራንባ እና ቆቦ እየሆነብን ነው ፤ ህዝቡ ቀድሞት 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ገብቷል ኢቲቪ ግን በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተደረገን ነገር ከአሁኑ ጊዜ ጋር በማነጻጸር መልሶ መላልሶ እያቀረበልን ይገኛል ፤ እኛ አይናችን እንመን ወይንስ ኢቲቪን እንመን? በአይናችን ያየነውን እና የምንኖርበትን ኑሮ ኢቲቪ እንዴት እንደሚያቀርበው ለናንተ መናገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብናል ፤
ለመጀመሪያ ጊዜ የክርስትያን አክራሪዎችን አላማ ዛሬ በቴሌቪዥን ለማየት ተዘጋጅተናል ፤ ይህ ፊልም ላይ ፓስተር ዳዊትን ስናየው ተገርመናል ፤ ይህ ሰው እኮ በ1988 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ያማልዳሉ ብላ የምታምናቸውን ጻድቃን ሰማዕታትንና ቅዱሳን መላእክትን በአዳራሾቻቸው አፉን ከፍቶ የተሳደበ ሰው ነው ፤ ፓስተር ዳዊትን አስተያየት እንዲሰጥ መደረጉ ራሱ አስገራሚ ነገር ነው ፤ መጀመሪያ በጊዜው የተሳደበው ስድብን ይቅርታ አስብሉት ከዚያ ድንገት ሲናገር ሰሚ ሊያገኝ ይችላል፡፡ ስለዚህ ዛሬ ላይ የሚተላለፈው ፊልም ተመልከቱ እና የራስዎን አስተያየት ይጻፉልን … ባለን መረጃ መሰረት እኛ ይህን ብለናል …ተመልክተን ስናበቃ ደግሞ ሚዛን ላይ እናስቀምጠዋለን ……
“እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን” ብለን ውስጣችንን ፍርሃትን አናለማምደውም ፤
የነገ ሰው ይበለን…..
ሀገራችን ክርስትናንም (34ዓ.ም) እስልምናንም (6ኛው መቶ ከ/ዘ) ከአለም ህዝብ ቀድማ የተቀበለች ሀገር ነች፡፡ ክርስትናን ሀይማኖት ከእስራኤል ፣ እስልምና ሀይማኖት ከአረቡ አለም ይምጣ እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለቱም ሀይማኖት ከመምጣቱ በፊት ነበረ፣ ሀይማኖቱን ከመቀበሉ በፊትም በጋራ የኖረ ነው ከተቀበለ በኻላም አብሮ የኖረ ህዝብ ነው ወደፊትም በጋራ ይኖራል፡፡ እስልምና እና ክርስትና ሀይማኖት ኢትዮጵያ ውስጥ አልተፈጠሩም ስለዚህ ሁለቱም ሀይማኖቶች መጤ ናቸው፡፡ ዋናው ቁም ነገር አትዮጵያዊ ለመባል መስፈርቱ ሀይማኖት ሳይሆን በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ወይንም ከኢትዮጵያን እናት/አባት መወለድ ስለሆነ ሀገራችን ለየትኛውም እምነት ተከታይ ሀገር ናት ማንም ሊሰጠን/ ሊወስድብን አይችልም መብትም የለውም፡፡
በሀገራችን ታሪክ በሁሉም ሀይማኖት ዘንድ ጥሩ ሀይማኖተኛ ሰዎች እንደነበሩ ኣሁንም እንዳሉ ቢታወቅም ኣንዳንድ በማወቅም ባለመወቅም ስህተት የሰሩ ኣሁንም የሚሰሩ ይኖራሉ፡፡ በነዚህ በተሰሳቱ ሰዎች እይታ ሀይማኖቱንም የምንፈርጅ ከሆንን ትልቅ ስህተት እየሰራን እንደሆነ መገንዘብ ኣለብን፡፡ ከዚህ ይልቅ የሚጠቅመው ለሀገራችንም ሆነ ለሀይማኖታችን ጥሩ እናስባለን የምንል ሰዎች በመቀራረብ እና በመወያየት የተሰሳቱትን ማስተካከል ነው እንጅ በመወነጃጀል ለራሳችንም ለሀይማኖታችንም ለሀገራችንም ጥሩ ነገር ልናተርፍ አንችልም፡፡ የተሻለው ነገር ሁሉም ሀይማኖቱን በነጻነት እና በእኩልነት ያከብር ዘንድ በጋራ መስራት እና መተባበር ሁሉንም ይጠቅማል፡፡ እናት ሀገራችንንም አያቶቻችን በጋራ ጠብቀው እንዳስረከቡን እኛም ለልጆቻችን የበለፀገች እና አንድነቱአ እንደተጠበቀ ለማውረስ እና በታሪክም ተጠያቂ እንዳንሆን ድርሻችንን እንወጣ፡፡”የእሳት ልጅ አመድ ከመሆን እግዚአብሔር ይሰውረን፡፡”
“ሀገራችን የጋራ ሀይማኖታችን የግላችን ናት”፡፡
ፍቅር ያሸንፋል
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ
አብዲሳ
የሚተረጉሙ ሰውን እያሳሳቱ ነው፡፡ የክርስቲያን ደሴት የተባለችው የኢትዮጵያ አጎራባች ሀገሮች ሱዳን፣ግብፅ፣የመን፣ሶማሊያ፣ጅቡቲ በአብዛኛው የሙስሊም ሀይማኖት ተከታይ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ግን በብዛት የክርስትና ሀይማኖት ተከታይ ህዝብ መኖሪያ (>60%) ስለሆነች የክርስቲያን ደሴት ተባለች እንጅ ሌሎች ሀይማኖቶች የሉም ወይንም እውቅና አለመስጠት አይደለም፡፡
ሀገራችን ክርስትናንም (34ዓ.ም) እስልምናንም (6ኛው መቶ ከ/ዘ) ከአለም ህዝብ ቀድማ የተቀበለች ሀገር ነች፡፡ ክርስትናን ሀይማኖት ከእስራኤል ፣ እስልምና ሀይማኖት ከአረቡ አለም ይምጣ እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለቱም ሀይማኖት ከመምጣቱ በፊት ነበረ፣ ሀይማኖቱን ከመቀበሉ በፊትም በጋራ የኖረ ነው ከተቀበለ በኻላም አብሮ የኖረ ህዝብ ነው ወደፊትም በጋራ ይኖራል፡፡ እስልምና እና ክርስትና ሀይማኖት ኢትዮጵያ ውስጥ አልተፈጠሩም ስለዚህ ሁለቱም ሀይማኖቶች መጤ ናቸው፡፡ ዋናው ቁም ነገር አትዮጵያዊ ለመባል መስፈርቱ ሀይማኖት ሳይሆን በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ወይንም ከኢትዮጵያን እናት/አባት መወለድ ስለሆነ ሀገራችን ለየትኛውም እምነት ተከታይ ሀገር ናት ማንም ሊሰጠን/ ሊወስድብን አይችልም መብትም የለውም፡፡
በሀገራችን ታሪክ በሁሉም ሀይማኖት ዘንድ ጥሩ ሀይማኖተኛ ሰዎች እንደነበሩ ኣሁንም እንዳሉ ቢታወቅም ኣንዳንድ በማወቅም ባለመወቅም ስህተት የሰሩ ኣሁንም የሚሰሩ ይኖራሉ፡፡ በነዚህ በተሰሳቱ ሰዎች እይታ ሀይማኖቱንም የምንፈርጅ ከሆንን ትልቅ ስህተት እየሰራን እንደሆነ መገንዘብ ኣለብን፡፡ ከዚህ ይልቅ የሚጠቅመው ለሀገራችንም ሆነ ለሀይማኖታችን ጥሩ እናስባለን የምንል ሰዎች በመቀራረብ እና በመወያየት የተሰሳቱትን ማስተካከል ነው እንጅ በመወነጃጀል ለራሳችንም ለሀይማኖታችንም ለሀገራችንም ጥሩ ነገር ልናተርፍ አንችልም፡፡ የተሻለው ነገር ሁሉም ሀይማኖቱን በነጻነት እና በእኩልነት ያከብር ዘንድ በጋራ መስራት እና መተባበር ሁሉንም ይጠቅማል፡፡ እናት ሀገራችንንም አያቶቻችን በጋራ ጠብቀው እንዳስረከቡን እኛም ለልጆቻችን የበለፀገች እና አንድነቱአ እንደተጠበቀ ለማውረስ እና በታሪክም ተጠያቂ እንዳንሆን ድርሻችንን እንወጣ፡፡”የእሳት ልጅ አመድ ከመሆን እግዚአብሔር ይሰውረን፡፡”
“ሀገራችን የጋራ ሀይማኖታችን የግላችን ናት”፡፡
ፍቅር ያሸንፋል
እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ
አብዲሳ
The guy who comment the first line u said" gin enante manachu" if u don't know who they "ANDADRGEN" are why u are READING their article and trying to post ur veeeeeery unfair comment.
Even u don't who Mahebere Kidusan is, and what the members doing ' They are the TRUE SONS AND DAUGHTERS OF ETHIOPIAN ERTHODOX TEWAHEDO.and same WITH ANDADRGEN
It looks you are one of the members of Anti Tewahedo or Tplf
By the way, "kanegagereh... se'nefena me'kegna temeselaleh."