Monday, 25 February 2013

የማኅበረ ቅዱሳን አባሎች የፓትርያርክ ምርጫ ላይ ድምጽ እንዳይኖራቸው ለማድረግ ዘመቻ ተጀምሯል

  • የማህበረ ቅዱሳን አባል የሆነ ከሀገረ ስብከት ተወክሎ ድምጽ እንዳይሰጥ ትዕዛዝ ተላፏል፡፡
  •  ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ያለምንም ተቀናቃኝ የካቲት ሃያ አራት 6ተኛፓትርያርክ ሆነው ይሾማሉ፡

(አንድ አድርገን የካቲት 19 2005 ዓ.ም)፡- የስድስተኛው ፓትርያርክ አስመራጭ ኮሚቴ ባቀረባቸው አምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ዙሪያ ቅዱስ ሲኖዶስ ተወያይቶ እጩዎቹን በማጽደቅ ትላንት ጥር 18 2005 ዓ.ም ይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል ፤ ይህ ይፋዊ መግለጫ 2791 በላይ ጥቆማዎች እንደደረሱት ገልጿል ፡፡ ለእጩነት የተጠቆሙት አባቶች በጠቅላላ 36 ሲሆኑ 15ቱ በአግባቡ ባለመጠቆማቸው እነርሱን ጥሎ አስራ ዘጠኙ ላይ በተቀመጠው የመመዘኛ መስፈርት መሰረት አምስቱን አሳልፎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኮሚቴው ያከናወነውን ስራ አባ አስጢፋኖስ እንዲህ በማለት ገልጸዋል “የአስመራጭ ኮሚቴው ከአምስት ያልበለጡ ከሶስት ያላነሱ እጩ ፓትርያርኮችን የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለማቅረብ ሰፊ ውይይት አድርጓል ፤ በተደረገው ውይይትም አሁን በአገልግሎት ላይ ካሉ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት መካከል 19 ሊቃነ ጳጳሳትን በቀጣይነት ለማጣራት አሳልፏል ፤ እጩዎቹን ለመለየት የተከተለው መመዘኛም እድሜና ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ነው፡፡”በማለት ገልጸዋል፡፡ አስመራጭ ኮሚቴው ባደረገው ማጣራትም አምስቱን እጩ ፓትርያርኮችን ለይቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቧል ተብሏል ፡፡ እነርሱም 1ኛ ብጹዕ አቡነ ማቲያስ ፤ 2ተኛ ብጹዕ አቡነ ኤልሳ ፤ 3ተኛ ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ፤ 4ተኛ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል እና 5ተኛ ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ  መሆናቸው ታውቋል፡፡ የአምስቱ እጩ ፓትርያርኮች ስም የቀረበለት ቅዱስ ሲኖዶስም ማጽደቁን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ “ለመንጋው የሚሆን እረኛ እግዚአብሔር እንዲሰጠን ምዕመናን ፋጣሪያቸው በጸሎት እንዲጠይቁ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል”ብለዋል፡፡ 

ሽማግሌዎች ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን አነጋገሩ፤ አስመራጩ መግለጫ ሰጠ


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 18/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 25/2013/ PDF) ቅዳሜ የካቲት 16/2005 ዓ.ም ቀርበው በአብዛኛው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ይሁንታ አግኝተዋል የተባሉት አስምት ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው ሐሙስ ለሚካሄደው የፓትርያርክ ምርጫ ያለፉ መሆናቸውን አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል።


ከፍተኛ ታቃውሞና የከረረ ተግሳጽ የደረሰባቸውን አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌምን ጨምሮ ሌሎቹ አራት አባቶች የተካተቱበት የአስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማ ለቅ/ሲኖዶስ ቢቀርብም ተጨማሪም ተቀናሽም ሳይደረግበት መጽደቁ ዛሬ ይፋ ሆኗል። በዚህም መሠረት ሐሙስ በሚደረገው ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር የሚያገኘው ተወዳዳሪ ስድስተኛ ፓትርያርክ ተብሎ ይሾማል ማለት ነው።

Sunday, 24 February 2013

የዕጩዎች ምርጫው እንደፈለጉት ያልሆነላቸው ጳጳሳት ሙግት ገጥመዋል


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2013/PDF)፦ የስድስተኛው  ፓትርያርክ  አስመራጭ   ኮሚቴ  በዛሬው   ዕለት  የዕጩዎቹን  ዝርዝር  ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበበት ወቅት ምርጫው በፈቀዱት መልክ አልሔደላቸውም የተባሉ ጳጳሳት ሙግት ገጥመው መዋላቸውን የደጀ ሰላም ምንጮች ገለፁ።


“ፓትርያሪክ እንድሆን የመንግስት ባለሥልጣን አላግባባሁም” (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)


‹ካህናትና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብለው ብቻ ማሰብ፣ ይገባቸዋል›› - (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)


(አዲስአድማስ ጋዜጣ፤ የካቲት 17/2005 ዓ.ም

ፌብሩዋሪ 24/2013/ PDF)፦ የምርጫው ሂደት በይፋ ከተጀመረ አንሥቶና ከዚያም በፊት ቀጣዩ ፓትርያሪክ እንደሚኾኑ ብዙ ከተነገረላቸው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል አንዱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በፓትርያሪክነት ምርጫው ከሚሳተፉ ከ800 በላይ መራጮች የምርጫ ድጋፍ ለማሰባሰብ በሥልጠና ስም በርካታ ገንዘብ ማውጣታቸውን፤ በሕንፃ ኪራይ፣ በሥራ ምደባ፣ በውጭ ተልእኮና በሹመት አሰጣጥ ለብዙዎች ቃል መግባታቸውን፤ ከዚህም አልፎ ቀጣዩ ፓትርያሪክ እርሳቸው እንደሚኾኑ ራሳቸውን ለመንግሥት አካላት ስለ ማስተዋወቀቸው በአንዳንድ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡

Wednesday, 20 February 2013

ሰበር ዜና - አቡነ ሳሙኤል በካህናትና ምእመናንን ጥቆማ (popular vote?) በከፍተኛ ብልጫ መሩ


የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ፣ ካህናትና ምእመናን ቀጣዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባት ሊኾን ይገባል ያሉትን እንዲጠቁሙ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት ከተበሰበሰቡት በሺሕዎች ከሚቆጠሩ ካህናትና ምእመናን ጥቆማዎች መካከል፣ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እጅግ ከፍተኛውን የጠቋሚዎች ቁጥር በማግኘት በከፍተኛ ብልጫ መምራታቸውን ለምርጫው ሂደት ቅርበት ያላቸው ምንጮቸ ገለጹ፡፡

ከየካቲት 1 - 8 ቀን 2005 ዓ.ም በተሰበሰበውና ከቅዳሜ የካቲት 9 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ በሚገኘው አግባብነት ያላቸው ጥቆማዎች ቆጠራ ከአንደኛው እስከ ሦስተኛ የወጡ አባቶች ማንነት ተለይቷል፡፡ በዚህም መሠረት ካህኑንና ምእመኑን በስፋት ለማሳተፍ በተሰበሰበው ጥቆማ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በእጅግ ከፍተኛ የጠቋሚዎች ቁጥር የመጀመሪያውን ደረጃ በመያዝ መምራታቸው ተረጋግጧል፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣በሦስተኛ ደረጃ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የከፍተኛ ጠቋሚዎችን ቁጥር ማግኘታቸው ተገልጧል፡፡

ኮሚቴው በጠቋሚዎቻቸው ብዛት አራተኛና አምስተኛ ደረጃ ያገኙትን የተቀሩትን ሁለት አባቶች ማንነት በነገው ዕለት በሚያካሂደው ቆጠራ እንደሚያውቃቸው ይጠበቃል፡፡ የጥቆማውን ውጤቶችና ምልከታዎች እንደ ግብአት (popular vote?) በመያዝ በምርጫ ሕጉ በሰፈረው ድንጋጌ በተጨማሪ መመዘኛዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ የሚያቀርባቸውን አምስት አባቶች የካቲት 14 ቀን እንደሚያቀርብ መገለጹ ይታወሳል፡፡ አሁን ሾልኮ የተሰማው የጥቆማ ደረጃ ውጤት፣ የተጠቀሱትን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከአምስቱ ዕጩዎች ለመካተት ያበቃቸው እንደኾነ ቆይተን የምናየው ይኾናል፡፡

የዜናው ዝርዝር ይቀጥላል፡፡

የውጪውን ጠላት ለመመከት በቅድሚያ የውስጥ ችግሮቻችንን ማስወገድ ይኖርብናል


ቤተ ክርስቲያን አልተከፈለችም” በሚለው መጣጥፍ መነሻነት የተዘጋጀ ….


(ከመልዐከ ብሥራት፣ ቨርጂኒያ/PDF)፦ ጌታቸው ኃይሌ ናቸው ለዚህ ጽሑፌ መነሻ የሆኑኝ።በቅድሚያ ልባዊ ምሥጋናዬና አክብሮቴ ይድረሳቸው፡፡ በዚህ ጽሑፌ የምናገረው በእውነት ለቤተክርስቲያን ለሚጨነቁ ምዕመናንና አገልጋዮች ብቻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ላለፉት ሃያ አንድዓመታት በታላቅ ፈተና ውስጥ አልፋለች፡፡ አሁንም እያለፈች ነው፡፡ እግዚአብሔር አይበለውናምናልባት የከፋው ፈተና ያለው ከፊት ለፊታችን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የዚህም ሰበቡ ችግሮቻችንንበቅጡ ካለመረዳታችንና ከቸልተኝነታችን የመጣ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችንችግሮች በተለይ በውጪው ዓለም ምንና ምን ናቸው?

የውጪውን ጠላት ለመመከት በቅድሚያ የውስጥ ችግሮቻችንን ማስወገድ ይኖርብናል


ቤተ ክርስቲያን አልተከፈለችም” በሚለው መጣጥፍ መነሻነት የተዘጋጀ ….


(ከመልዐከ ብሥራት፣ ቨርጂኒያ/PDF)፦ ጌታቸው ኃይሌ ናቸው ለዚህ ጽሑፌ መነሻ የሆኑኝ።በቅድሚያ ልባዊ ምሥጋናዬና አክብሮቴ ይድረሳቸው፡፡ በዚህ ጽሑፌ የምናገረው በእውነት ለቤተክርስቲያን ለሚጨነቁ ምዕመናንና አገልጋዮች ብቻ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያናችን ላለፉት ሃያ አንድዓመታት በታላቅ ፈተና ውስጥ አልፋለች፡፡ አሁንም እያለፈች ነው፡፡ እግዚአብሔር አይበለውናምናልባት የከፋው ፈተና ያለው ከፊት ለፊታችን ሳይሆን አይቀርም፡፡ የዚህም ሰበቡ ችግሮቻችንንበቅጡ ካለመረዳታችንና ከቸልተኝነታችን የመጣ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ለመሆኑ የቤተ ክርስቲያናችንችግሮች በተለይ በውጪው ዓለም ምንና ምን ናቸው?

አስታራቂ ጉባኤው መግለጫ አወጣ


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 13/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 20/2013/ PDF)፦ በአባቶች መካከል የተፈጠረውን መለያየት ላማራቅና ዕርቅ ለማውረድ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የቆየው የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ አወጣ። የመግለጫው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በአገር ቤትና በውጭው ዓለም የሚገኙ አባቶችን በማስማማት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ያደረገውን ከፍተኛ ጥረት በዝርዝር ለመግለጽና የዕርቁ ሒደት ምን ይመስል እንደነበር በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም ለሚኖሩ መላው ኦርቶዶክሳውያን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምርን እንዲያውቁት ለመግለጽ ነው” ያለው መግለጫ ዝርዝር ሐሳቦችን አካቷል። ሙሉ ቃሉን ከዚህ በታች ተመልከቱ።

Tuesday, 19 February 2013

“ምርጫ ውስጥ ስካተት አትርሱኝ” አቡነ ጎርጎርዮስ


(አንድ አድርገን ህዳር 11 ቀን 2005 ዓ.ም)፡- “ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ፤ ክብር ፤ ባህል ፤ እምነት ፤ሥርዓት ፤ መንግሥትና ቋንቋ ያቋቋመች ፤ የማትናወጥ ከመሆኗ ጋር ፤ ከሔኖክ ፤ ከመልከ ጼዲቅ ፤ ከነቢያትና ከሐዋርያት የተላለፈውን ትምህርት ፤ ሥርዓት ፤ እምነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ስታስተላልፍ የኖረች ፤ በማስተላለፍ ላይ ያለች ፍኖተ ሕይወት ናት፡፡ ቅዱሳን አበውን ፤ ኃያላን ነገሥታትን ፤ ልዑላን መሳፍንትን ፤ ክቡራን መኳንንትን ፤ ዐይናሞች ሊቃውንትን በሥጋ ፤ በነፍስ ወልዳ ያሳደገች የሌላ የማትፈልግ ፤ የራሷንም የማትለቅ ዕጥፍ እናት ፤ ስንዱ እመቤት ናት፡፡” በማለት ስለ ቤተክርስቲያን የተናገሩት ታላቁ ሊቅ የቀለም ቀንድ አለቃ አያሌው ታምሩ ነበሩ ፡፡ እንዲህ የተባለላት ቤተክርስቲያን  ዛሬ ከእርቀ ሰላም የተከደነ አጀንዳ በኋላ ስድስተኛ ብላ ፓትርያርክ ለመሾም ወሳኝ ጊዜ ላይ ትገኛለች፡፡ 

የአቶ መለስ ዜናዊ ሃውልት ሲመረቅ አቡነ ጳውሎስ ያረፉበት ቦታ እንደታጠረ ነው




(አንድ አድርገን የካቲት 12 ፤ 2005 ዓ.ም)፡- የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር የአቶ መለስ ዜና ሀውልት ትላንትና የካቲት 11 2005 ዓ.ም ባለቤታቸው ወ/ሮ አዜብ ፤ ቤተሰቦቻቸው እና ጥቂት ባለስልጣኖች በተገኙበት ተመረቀ ፡፡ በምርቃቱ ጊዜ አንድም የሚዲያ ተቋም በቦታው አልተገኝም ፤ የዲዛይንና የኤሌክትሪካል ስራውን ጨምሮ ሙሉ በሙሉ ስራው የመከላከያና ኢንጂነሪንግ ኮንስትራክሽን ድርጅት አማካኝነት የተሰራ ሲሆን ስራውን  ለማጠናቀቅ ከስድስት ወር በላይ መፍጀቱ ታውቋል፡፡ የአቶ መለስ ዜናዊ አስከሬን ያረፈበት ቦታ በመንበረ ጸባኦት ቅድሥት ሥላሴ ካቴድራል ግቢ ውስጥ በስተግራ በኩል  በግምት ከ260 እስከ 300 ካሬ ቦታ የፈጀ ሲሆን አስከሬኑ ያረፈበት ቦታ ከ40 ካሬ እንደማይበልጥ በቦታው ተገኝተን ለማወቅ ችለናል፡፡ ይህ ሃውልት ሙሉ በሙሉ በጥቁር እምነበረድ የተሰራ ሲሆን በምሽት የተለየ ውበት የሚሰጡት በርካታ መብራቶች ተገጥመውለታል ፡፡  ሃውልቱ ላይ “የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ከ1947-2004 ዓ.ም”የሚል ጽሁፍ ብቻ በአማርኛ እና በእግሊዝኛ ተጽፎበታል፡፡ ሃውልቱ ላይ ፎቶም ሆነ ሌላ ጽሁፍ አይታይበትም፡፡ ቦታው ተገኝተን እንደጎበኝነው ሃውልቱ ለህዝብ እይታ ክፍት የሆነ ሲሆን ቦታው ላይ ባሉት በአራት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጥበቃ እየተደረገለት ይገኛል፡፡ በግቢ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሃውልቶች ፊታቸው ወደ ቤተክርስቲያኑ ያዙሩ ሲሆን የአቶ መለስ ሃውልቱ ግን  ፊቱን ወደ ውጭ በር አድርገው ሰርተውታል፡፡