Thursday, 16 May 2013

የኤማሁስ መንገደኞች...ሉቃስ 24


በእታ ሰይፈ

ጸጥ ባለው አሸዋማ በረሃ ረጅሙን መንገድ ተያይዘውታል። ከመነሻቸው ጀምሮ እስከአሁን የመጡበትን ርቀት ባለማስተዋል
የልባቸውን ጭንቀት ያወጋሉ። ሰሞኑን በምድረ ኢየሩሳሌም ተደርጎ የማያውቅ ወደ ፊትም የማይደረግ ግፍ ተፈጽሟል፣ ፍርድ ተስተጓጉሏል። 

ሰዎቹ የጸሃዩን ግለት፣ የመንገዱን ርቀት፣ ረሃብና ድካሙን ረስተው ስለዚያ በግፍ ስለተገደለው ደግ ሰው ያወራሉ። አብሯቸው በቆየባቸው 3 አመታት ውስጥ ያዩትን የተለየ ፍቅር፣ ቸርነት፣ ትህትና፣ ደግነት፣ ተዓምራት እያሰቡ፡ ከአንደበቱ እንደ ማር እያዘነበ ያስተማራቸውን የጣፈጠ ቃል እያውጠነጠኑ ይነጋገራሉ። ፍቅሩ እንደ ልክፍት ተጠናውቷቸው ስለ እርሱ ከማሰ...ብ አልቦዘኑም። ስድሳውን ምዕራፍ እንደተጓዙ ያላስተዋሉት 3ኛ ሰው ተቀላቀላቸው። 

ድንገትም፦ 
"እንዲህ እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ እርስ በርስ የምትነጋገሯቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው?"ሲል ጠየቃቸው። 
በንግግሩ እጅጉን ተገርመው ከሁለቱ አንዱ ቀለዮጳ ፈጠን በማለት፦ 
"አንተ ደግሞ በኢየሩሳሌም ስትኖር በእነዚህ ቀናት የሆነውን አታውቅምን?" አለው። ሰውየውም ምንም እንዳልሰማ በመሆን፦ 
"ይህ ነገር ምንድር ነው?" አላቸው። 
"ከወዴት ሀገር የመጣ እንግዳ ይሆን?" ሲሉ አሰቡና በእግዚአብሔርና በህዝቡ ፊት በቃልና በስራ ብርቱ ስለነበረው በግፍ ስለተሰቀለው ስለ ናዝሬቱ ኢየሱስ አንድ በአንድ አወሩለት። 

አስቀድሞ እንደሚነሳ ቢነግራቸውም አሁን ግን ሞቶ ከተቀበረ 3 ቀን ሆነው። በእስራኤል ሁሉ የሞቱ ወሬ ተናፍሶ እነርሱም ተስፋ ቆርጠው ወደ መንደራቸው ኤማሁስ እየተጓዙ ነው። ግን ደግሞ የዛሬው የሴቶቹ ወሬ አጠራጥሯቸዋል። ቀጠል አድርገውም አሁን ደግሞ ያስገረመን አሉ፦ 
"ከእኛ መካከል ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የሄዱ ሴቶች ስጋውን ባጡት ጊዜ ተነስቷል በዚያ የለም አሉን" 
አሉ ግራ በተጋባ በሰከነ ድምጽ። የልባቸውን መዛል የተመለከው በጸጥታ ታሪኩን ያዳምጥ የነበረው ሰው፦ 
" እናንተ የማታስተውሉ፥ነብያትም የተናገሩትንም ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፡ ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን?"አላቸው። 
 ከሙሴና ከነብያት ጀምሮ ስለ እርሱ በመጽሃፍ የተነገረውን እየተረጎመላቸው ሳያስቡት ከመንደራቸው ደረሱ። ማንነቱን ያልተረዱት በቃሉ ብርታት የተማረኩት የሩቅ ተጓዥአብሯቸው ያድር ዘንድ ግድ አሉት። 
"ማታ ቀርቧልና፡ ቀኑም ሊመሽ ጀምሯልና እባክህ ከእና ጋር እደር?" አሉት በሚማጽን ንግግር።
 ሰውየው ቃላቸውን ተቀብሎ ከቤታቸው ገባና አብሯቸው በማዕድ ተቀመጠ። እንጀራንም በርኮ ሰጣቸው። ተከፍተው የማያዩ አይኖቻቸው ተከፈቱ፤ ሰውየውን አዩት፡ ያውቁታል። ረጅሙን መንገድ አብሯቸው የተጓዘው፣ንግግሩ ልባቸውን ያቀልጠው የነበረው፣ ከሞት የተነሳው እርሱ ኢየሱስ ነው። ሉቃስና ቀለዮጳ በደስታ ሰከሩ። ጊዜ ሳያባክኑ በፍጥነት ወደ ኢየሩሳሌም ሮጡ፤ ሁሉን በአንድ ቤት ውስጥ ተሰብስበው አገኛቸው።
"ተነስቷል! ተነስቷል! ጌታ በእውነት ተነስቷል" በደስታ ሲቃ ምስራቹን አበሰሯቸው።
 በመንገድ የተናገራቸውን፣ እንጀራም ሲሰጣቸው የሆነውን እየነገሯቸው ሳለ በብርሃን ጸዳል የተሞላ ድምጹ የሚያሳርፍ ሰው በመሃከላቸው ቆሞ 
"ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው፡፡ 
 በእርግጥ ኢየሱስ ነው። ምትሃት ያዩ መስሏቸው ፈሩ ደነገጡም፤ እርሱ ግን 
"እኔ ነኝ አትፍሩ አትደንግጡም፤ መንፈስ ስጋና ደም የለውም፡ እኔ እንደሆንኩ ታምኑ ዘንድ እጆቼንና እግሮቼን እዩ ዳስሱም" በማለት አረጋጋቸው።
 ኢየሱስን አዩት፥ ተነስቷል! ደስታቸው እጥፍ ሆኖ አይናቸውን ማመን ቸገራቸው። ልባቸውን ያወቀው አምላክ፡ እምነታቸው ሙሉ እንዳልሆነ ተመልክቶ 
"በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን?" አላቸው።
 የተጠበሰ ዓሣ ቁራጭና የማር ወለላ አቀረቡለት፤ እምነታቸው ይሞላ ዘንድ ዛሬም እንደቀድሞው በመሃከላቸው ተመገበ። አብሯቸው ሳለ በሙሴ ህግና በመዝሙራት መጻህፍት መከራን እንዲቀበልና እንዲነሳ የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ እንደሚገባው ያስተማራቸውን ያስታውሳቸው ጀመር... 

"ሰላም ለእናንተ ይሁን" ሉቃ 24:36...  
 እንኳን ለዳግማይ ትንሳኤ በሰላም 

አደረሳችሁ!!!..

Wednesday, 3 April 2013

የአዲርቃይ ፍርድ ቤት ‹‹ዋልድባ አይታረስ›› ያሉትን ወጣቶች በአሸባሪነት ከሰሰ


  • አዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስም በማለታቸው ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ
  • በዛሬማ የሚገኙ ነዋሪዎች በወጣቶቹ ላይ ምስክርነት አንሰጥም በማለታቸው እንግልትእየደረሰባቸው ነው
  • የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል ክሱ በአሸባሪነት መሆን አለበት በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል
  • የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከገዳሙ በረከት ለመቀበል የመጡት ማስፈራሪያ እና ፍተሻ (strip search) ተደረገባቸው
  • የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ሌላ አማራጮችን እንፈልግ ብሏል
  • የወልቃይት ነዋሪም እርሻውን እንዲቀጥል እስከሚመጣው ዓመት ምንም ነገር እንደማይኖርእየተነገረው ነው

Thursday, 28 March 2013

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት የመብት ጥያቄ በተሃድሶ መናፍቃን አጀንዳ ተጠለፈ



  • የደቀመዛሙርቱ አካዳሚክ፣ አስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ወደ ግለሰቦች ኃላፊነት ማስነሳት በሚል ቅድመ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡
  • “ተቃውሞውን አስተባብረሃል” በሚል ታስሮ የነበረው ደቀመዝሙር ከእስር ትናንት ተፈትቷል፡፡
  • የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጅ የሆኑ ተማሪዎች ተቃውሞውን ኦርቶዶክሳውያንን ከኮሌጆ ቁልፍ ቦታ በማስወገድ በመናፍቃን ለመተካት በኅቡዕ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡

(አንድ አድርገን መጋቢት 19 2005 ዓ.ም)፡- የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በኮሌጁ ስላለው የአስተዳደር ጉድለት ፣ የትምህርት ጥራት ማነስና የምግብ አቅርቦት ጥራት መጓደል ተቃውሟቸውን በትምህርት ማቆምና የረሃብ አድማ በማድረግ እየገለጹ ነው፡፡ በርካታ መገፋት ቤተክህነቱ  እያደረሰባቸው የሚገኙት የነገረ መለኮት ምሩቃንና ደቀ መዛሙርት ያቀረቡት ተቃውሞ የቤተክህነቱን አስተዳደረዊና መንፈሳዊ ድቀት ርቀት እንደ ማሳያ ተደርጎ ተወስዶአል፡፡

፩ የቅዱሳን አባቶች ህይወት

ከዝክረ ቅዱሳን ዘተዋህዶ ቁ.፪
ትርጉም  በሃዜብ በርሄ

"እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንኩት እርሱንም እሻለሁ በህይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኘውን አይ ዘንድ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።" መዝ 26:4

የቅድስና መሰረቱ ራስን መቆጣጠር መቻል፣የሚሰሩትንም ሆነ የሚናገሩትን ማስተዋልና ጠንቅቆ ማወቅ፣ ጎጂ ከሆኑ ልማዶች ራስን መቆጠብ፣ የሌሎችን ጉድለትና ስህተት ከማጉላት ይልቅ ፍቅረ እግዚአብሔርን እያሰቡ ከመልካም ምግባራቸው መማር መቻል፣ እኔ ከሁሉ ያነስኩ ነኝ ብሎ ማመንና ከምንም በላይ ደግሞ ከቤተ መቅደሱ አለመራቅ...ወዘተ ነው።ቅዱሳን አባቶች ፍቅራቸው ራስን አሳልፎ እስከመስጠት ነውና እውነተኛና ከቅን ልቡና የመነጨ ፍቅር መሆኑ አያጠያይቅም። ስለ ሃይማኖታቸው አንገታቸውን ለሰይፍ፣ ጀርባቸውን ለግርፋት፣ ፊታቸውን ለጽፋት ነፍሳቸውን ለሞት የሰጡና "ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ "ማቴ 5:6 የመጨረሻ ግባቸው የመንግስቱ ወራሾች መሆን ነው።

"ከዓለም ምንም አልፈልግም"


በአያሌው ዘኢየሱስ

ይህ ቃል አንድ ሰው የነፍሱን ነጻ መውጣት በሚሻበት ጊዜ ቅድሚያ ሰጥቶ ሊናገረው የሚገባው ቃል ነው።
ዓለም ያሏት ፈተናዎች ብቻ እንጂ ምንም የሚወደድ ነገር ስለሌላት ከእርሷ ምንም አልፈልግም።
ዓለም ለመስጠት በጣም ድሀ ስለሆነ ከእርሷ ምንም አልፈልግም። እኔ የምፈልገው ሁሉ በዓለም ካለ ዓለም ገነት ሆናለች ማለት ነው። በውስጧም ከቁሳዊ ነገሮች በስተቀር ምንም የለም። በእርግጥ እኔ የምፈልገው ሰማያዊ ነገሮችን ነው። ለመንፈሳዊ ህይወቴ እንዲጠቅመኝ።

Friday, 15 March 2013

13 አክራሪዎች ከ27 መሳሪያ ጋር ተያዙ


(አንድ አድርገን መጋቢት 6 2005 ዓ.ም)፡-በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ወይም በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ  የእምነት ቡድኖች እንዲህ ናቸው ብሎ ለመሰየም የሚያስችል ገላጭና ተስማሚ ቃል ወይም ስያሜ መምረጥ ሁልጊዜም ቢሆን አስቸጋሪ ሥራ ነው፡፡ ቃሎቹ ገላጭ ናቸው ሲባል አልፎ አልፎ አንድ ላይ ፈራጅ ሆነውም ይገኛሉ፡፡ 

Tuesday, 5 March 2013

ፍቅርና ሃይማኖት - ነፍስና ሥጋ በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ


(ምንጭ፡አዲስ ጉዳይ መጽሔት፣ ቅጽ 7፣ ቁጥር 153፣ የካቲት 2005)
 በአሁኑ ጊዜ ‹‹ፍቅር››ን የማይጠራው አለ ለማለት አይቻልም፡፡ አፍቃሪ -ተፈቃሪው፣ አጣይ-አፋቃሪው ፣ ሸምጋይ አስታራቂው፣ የሥነ ልቡና ባለሙያው፣ ጸሐፊ ደራሲው፣ አንባቢ ተርጓሚው፣ ሃይማኖት ሰባኪው፣ ልጅ አዋቂው፣ ከተሜ ገጠሬው ፣...ሁሉም ፍቅር ፍቅር ይላል፡፡ የሁሉም ፍቅር ግን አንድ ነው ለማለት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ‹‹ አምላክ›› የሚለውን ቃል የምንጠቀመው ሁሉ ‹‹ አምላክ›› በምንለው አካል እንደምንለያየው ማለት ነው፡፡ ለምን ቀናሽ? ለምን ገደልህ? ለምን ከሳህ?ለምን ታመምሽ? ለምን ተጣላህ?... ለሚሉት ድኅረ ፈተና ወመከራ ጥያቄዎች ብዙ ጊዜ መልሳቸው ‹‹ ስለ ምወደው! ስለምወዳት!›› የሚለውነው፡፡ ይኸ የገረማቸውም እረ ለመሆኑ ‹‹ፍቅር›› ራሱ ምንድን ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ በርግጥም ፍቅር ራሱ ምንድን ነው?

Tuesday, 26 February 2013

የ5ቱ እጩ ፓትርያርኮች አጭር የሕይወት ታሪክ


PDF http://bit.ly/YwKqd1:- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ አስመራጭ ኮሚቴ በመሠየም እጩ ፓትርያርኮችን ለመምረጥ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከካህናት፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ ከማኅበረ ቅዱሳን፤ እንዲሁም ከምእመናን ጥቆማ እንዲያካሔዱ ተደርጓል፡፡ በተካሔደው ጥቆማ መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማውን በግብአትነት በመጠቀም አምስት ሊቃነ ጳጳሳትን በእጩነት በማቅረብ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርቧል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ከየካቲት 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ውይይት በማካሔድ አምስቱም ሊቃነ ጳጳሳት በእጩነት እንዲቀርቡ አጽድቋል፡፡