Friday, 15 March 2013

13 አክራሪዎች ከ27 መሳሪያ ጋር ተያዙ


(አንድ አድርገን መጋቢት 6 2005 ዓ.ም)፡-በተለያዩ ሃይማኖቶች ውስጥ ወይም በአንድ ሃይማኖት ውስጥ የሚገኙትን የተለያዩ  የእምነት ቡድኖች እንዲህ ናቸው ብሎ ለመሰየም የሚያስችል ገላጭና ተስማሚ ቃል ወይም ስያሜ መምረጥ ሁልጊዜም ቢሆን አስቸጋሪ ሥራ ነው፡፡ ቃሎቹ ገላጭ ናቸው ሲባል አልፎ አልፎ አንድ ላይ ፈራጅ ሆነውም ይገኛሉ፡፡ 

ሁሉንም በአንድ አጠቃሎ መጥራት አደገኛ ነው ፤ የግበጹ ሼክ ሻኪር አል ሰይድ ከወደ አሜሪካ ባወጀው ጅሀድ ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሙስሞች እንዲነሱ  የተጠቀመበት ቃል አለ፡፡ “ ቤትህ ውስጥም ብትሆን ፤ከልጅህ ጋር ብትጫወት ፤ ቴሌቪዥን እያየህ ቢሆን ሙስሊም በመሆንህ ብቻ አሸባሪ ነህ ይሉሀል” ብሏል፡፡ መንግስት ሙስሊም የሆነውን ሁላ አሸባሪ በማለት ያሳድሀል”በማለት የወሃቢያ ፕሮፖጋንዳን ዘዴ ሰውን ለመቀስቀሻነት ሲጠቀም ተስተውሏል፡፡ ከዚህ ቃል ጋር ብዙ ተዛማጅነት ያላቸው ቃሎች ሰዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሲጠቀሙበት ይስተዋላል ፡፡ መሰረታውያን (Fundamentalist).. “ነውጠኞች” በውጊያ የሚያምኑ (Militant) ፤ ጽንፈኖች ወይም ጠርዘኞች (Extremists) ፤ ስር ነቀሎች (Radicals) ፤ አክራሪዎች (fanatics) ፤ የሃይማኖት ጦረኞች (Jihadist ) ፤ የእስላማዊ መንግስት አቀንቃኞች እስላማዊያን (Islamist) በመባል ይታወቃሉ፡፡  አክራሪ የሚለው መጠሪያ የተመረጠው ቡድን ለእምነቱ ፍጹም ቆርጦ የተነሳ ፤ እምነቱን ለድርድር የማያቀርቡ የሆኑ ነጥቦችን ብቻ መርጦ የሚያቀርብ በመሆኑ ነው፡፡ የአክራሪነት የመጨረሻው ግብ የሃይማኖቱን የበላይነት የሚያረጋግጥ ሃይማኖታዊ መንግስት Theocratic Government መመስረት ነው፡፡ ኢስላማዊያን የሚባለው አክራሪ ቡድንም ግቡ ይሄ ነው፡፡ የተለያየ ስም አንግተው ቢንቀሳቀሱም መዳረሻቸው ግን አንድና አንደ ብቻ ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ ውስጥ ብዙዎቹን እያደናገረ ያለው ሚዛናዊ እና አክራሪዎቹን (Moderate Vs extremist) ቡድኖችን የመለየት እና ያለመለየት ነገር ነው፡፡ ሚዛናዊ የምንላቸው ሰሞኑን በቴሌቪዥን የምናያቸው አክራሪነትን የሚቃወሙት ሙስሊሞች ናቸው ፤ አክራሪዎቹ ደግሞ እነዚያኛዎቹ ናቸው፡፡ አሁን በሀገራችን የሚታየው ግን በአክራሪ እና በሚዛናዊ ሙስሊም መካከል የሚደረግ ሃይማኖታዊ ትግል አይደለም፡፡ መዳረሻው የውስጥ ስርዓትን አስተካክሎ የሚቆምም አይደለም፡፡ የእኛ ጉዳይ በሳውዲ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ የሚካሄደው የወሀቢያ ሸፍጥ ነው፡፡       

WAHABISM IN ETHIOPIA AS "CULTURAL IMPERIALISM"የሚለው ጽሁፍ አንዱ አንቀጽ እንዲህ ይላል

WAHABIS CHALLENGE ETHIOPIAN MUSLIMS : In the Harar, Bale, and Dessie regions of Ethiopia, Arab Wahabi missionaries (and their Ethiopian disciples) are directly challenging the traditions and practices of the indigenous Muslim community.  As expressed to PAO by members of the IASC, Wahabi missionaries are able to use their money and &legitimacy as native speakers of the language of the Koran and their closeness to the holy cities of Mecca and Medina, to undermine Ethiopian Muslim customs and traditions and teach interpretations of the Koran that promote a far less tolerant view of other Muslims and non-Muslims alike. Because of the financial support these missionaries have, it is very difficult for Ethiopian Muslim leaders to counter their influence and many imams are not educated well enough to argue against these foreign interlocutors.
በአሁኑ ሰዓት መንግሥት በከፍተኛ ሁኔታ ብዙ የሰው ኃይል መድቦ ልዩ ክትትል እያደረገበት ያለው ጉዳይ አንዱ አክራሪነትና አመለካከቱን ነው፡፡ ፌደራል ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹን ሥራ ትቶ አይኑንና ጆሮውን እዚህ ነገር ላይ ብቻ ካደረግ ሰነባብቷል፡፡  ከስድስት ወር በፊት ከአዲስ አበባ 325 ኪሎ ሜትር በስተ ሰሜን በኩል የምትገኝው ከሚሴ ከተማ የተደራጁ አክራሪዎች  ከፖሊስ በጠራራ ጸሀይ መሳሪያ ሲቀሙ የነበረበት ሁኔታ ተፈጥሯል ፡፡ ወደ ደሴ የሚያልፉ መኪናዎችን መንገድ በመዝጋት እንቅስቃሴም ሲያደርጉ ተስተውሏል ፡፡ ይህን እንቅስቃሴ ለማስቆም መንግሥት ከአካባቢው ፖሊሶች በተጨማሪ ፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ማስፈር ችሎ ነበር ፡፡ በየጊዜው በግለሰብም ይሁን በቡድን የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በኃይል በመጠቀም  ለማስቆም ብዙ ጊዜ ጥረት ሲያደርግ ተስተውሏል፡፡


ከሶስት ቀናት በፊት ከአዲስ አበባ በደሴ መስመር በ283 ኪሎ ሜትር ላይ ርቃ የምትገኝው ወደ አጣዬ ከተማ ከእነዋሪ ከተማ በመሄድ ላይ ሳሉ 13 አክራሪዎች ከ27 መሳሪያ ጋር መያዛቸው ለማወቅ ተችሏል ፡፡እነዚህ 13 ሰዎች በአካባቢው ሰው ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ባደረገው  ፍተሻ ሊያዙ መቻላቸውን ከቦታው ያገኝነው የአይን እማኝ ሊያረጋግጥልን ችሏል ፡፡ በሰሜን ሸዋ መስመር በርካታ ቦታውች ላይ ከአጣዬ ኮምቦልቻ ፤ከደብረብርሀን ጅሁር ፤ ከጣርማ በር መሀል ሜዳ እና ከኮምቦልቻ አልውሃ ድረስ ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚጠቀሙባውን ማረፊያ ቤቶች ተከራይተው ለአባላቶቻቸው ማረፊያ እና የተለያዩ ጉዳዮችን ማስፈጸሚያ ስውር ቦታ አድርገው እንደሚጠቀሙባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓት መንግሥት የድምጽና የምስል ባለሙያዎችን በመላክ ሁኔታውን በምስል  የማስቀረት ስራ አከናውኗል ፡፡ ሰዎቹ ለተጨማሪ ምርመራ ከቦታው ዘወር እንዳደረጓቸውም ጭምር ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መረጃ ለመሰብሰብ ባደረግነው ጥረትም ባለፈው ዓመት ክረምት ላይ ብዙም ሙስሊሞች የማይገኙባት መራቢቴ ከተማም ትንሽ ቢሆኑም በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለማወቅ ችለናል፡፡ 


ከሁለት ዓመት በፊት በዶናልድ ያማማቶ ጊዜ በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን የእስልምና አክራሪነት አካሄድ በመከታተል WAHABISM IN ETHIOPIA AS "CULTURAL IMPERIALISM"የሚል ሰነድ ከአዲስ አበባው የአሜሪካ ኢምባሲ ወደ አሜሪካ የተላከውን ሰነድመመልከት ይቻላል፡፡ ሰነዱ አክራሪነት እየተካሄደባቸው ከሚገኙት ቦታዎች ውስጥ ደሴ ፤ ሀረር ፤ ጅማ ፤ አርሲ እና መሰል ቦታዎችን በአበይትነት ይጠቅሳል ፡፡ ቡድኖቹም ከውጭ የአረብ ሀገራት የብር ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ያወሳል ፡፡  አሁን ላይ ጆሯችን እየሰማ አይናችን እያየ ያለው ይህንኑ ይሆናል የተባለን እውነት ነው ፡፡ ከአጠገባችን የምንጎራበታቸው ሰዎች ኬንያ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን አቋርጠው ለአክራሪነት ትምህርት እየሄዱ ነው ፤ ኬኒያ ትምህርታቸውን ጨርሰው የመጡ አክራሪዎች በተመረጡ ቦታዎች አስምህሮታቸውን ለመጫን እየሰሩ ነው፡፡ መንግሥት በአሁኑ ሰዓት ማጣፊያ ያጣለትን ጉዳይ አክራሪነትንና አክራሪነት ብቻ ሆኗል ፡፡ ይህ አመለካከት በ97 ዓ.ም በጅማ ላይ ብዙ ቤተክርስቲያኖችን በእሳት ሲበላ  ፤ ብዙ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን በመሰዊያው ላይ የህይወት መስዋእትነትን ሲያስከፍል ፤ በርካቶችን ከቤት ከንብረታቸው ሲያፈናቅል ተመልክቶ ዝም ያለው መንግሥታችን አሁን ነገሩ በራሱ ላይ የመጣ የህልውና ጉዳይ ሲሆንበት የሚይዘውን ፤ የሚጨብጠውን ፤ ሚዲያ ላይ የሚቀርበውንና የማይቀርበውን ነገር መለየት ተስኖት ተመልክተናል፡፡ መንግሥት ከሳምንት  በፊት ‹‹ጀሀዳዊ ሀረካት›› የሚለውን ዶክመንተሪ ፊልም ለሕዝብ ማቅረብ ችሎ ነበር፡፡ ከፕሮግራሙ በኋላ በተነሱት ጥያቄዎች “በእኛ ጉዳይ” የቴሌቪዥን ፕሮግራም ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪንና የአቶ በረከት ስምኦንን ረዳት በማቅረብ ለተነሳው ጥያቄ መልስ ሰጥቶበታል፡፡  ከዚያ በኋላም በአዲስ አበባ  ቦሌ እና በአለም ባንክ አካባቢ እንቅስቃሴውን ይመራሉ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ቤታቸውን በጠራራ ጸሃይ በመግባት ያገኝውን የሲዲ ፤ የመጽሀፍ እና የድምጽ ዶክመንቶችን ሲሰበስብ እንደነበር ይታወቃል፡፡


ከወራት በፊት ስራ አመራር ኢኒስቲትዩት ‹‹አክራሪነት ፤ የእምነት ነጻነት …. በኢትዮጵያ›› በሚል አርዕስ በተካሄደ የአምስት ቀን አውደ ጥናት ላይ በቦታው ላይ ተገኝተን እንደተመለከትነው መንግሥት የመረጃ እጥረት እንደሌለበት ለማወቅ ችለናል ፡፡ ጉባኤው የእያንዳንዱን እምነት ታሪክ ፤ የሃይማኖት ተቋማትን ለማቋቋም የጠየቁ ተቋማት ብዛትን ፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈቀደላቸው 178 ሃይማኖቶችን እና አሁን እምነቶቹ ያሉበትን ሁኔታ የሚዳስስ ፤ በጅማ በአርሲ እና በሀረር በተለያዩ ቦታዎች ላይ የተፈጸሙ ድርጊቶችን ከነፈጻሚያቸውና አስፈጻማያቸው ጭምር ሌሎችም ዘርዘር ያሉ ጉዳዮች የቀረበበት ጉባኤ ነበር፡፡ ድርጊቶቹ የተፈጸሙት በአክራሪ ግለሰቦች ብቻ ሳይሆን ኢህአዲግን ወክለው ወንበሩን በያዙ ሰዎች ፤ በባለሀብቶች ፤ ጽንፈኝነትን ከሚከተሉ ሃይሎች ጋር መሆኑን መንግሥት እንደደረሰበት ነገር ግን ሁሉን ከመቅጣት ይልቅ የማስተማር ስትራቴጂ መጠቀሙን በጊዜው ተገልጿል ፡፡ በዚህ ላይም የፌደራል ጉዳዮች በኩል የተለያዩ መልዕክት ያላቸውን ጽሁፎች መበተኑን ጨምረው ገልጸዋል ፡፡ ጥፋት ለማድረግ ያሰበውን በትምህርት መመለስ መልካም ሆኖ ሳለ ደም ያፈሰሰውን በትምህርት ለመመለስ መጣር በሰው ነፍስ ከማፌዝ አይተናነስም ፡፡ 
አሁን በቴሌቪዥን አይናችንን ፤ በሬዲዮ ጆሯችንንና የሰለቸን ነገር አክራሪነትን በሚመለከት የሚደረግ ስብሰባ ነው፡፡ ኢቲቪ አሜሪካ ላይ የተደረገን የጅሀድ ጥሪ በዚያኑ ቀን ለዜና የማዋል ስራ ጀምሯል ፤ በቅርቡ ሙስሊሞች መሳሪያ እንዲያነሱ የተላለፈውን ጥሪ እኛም ተመልክተናል ፤ ስለዚህ ከአሁን በኋላ አክራሪነት አለ? የለም? የሚል ነጥብ ለመከራከሪያነት የሚበቃ አይመስለንም፡፡ የዚህ አመለካከት የመጀመሪያዎቹ ገፈት ቀማሾች እንማን እንደሆኑ የትላንት ወዲያው ታሪክ አስተምሮናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ ሙስሊም ማህበረሰቡን ጠርተው እንዲህ ብለው ነበር የተናገሩት “እውነቱን ለመናገር በአሁን ወቅት ኢትዮጵያ የምትጠቀመምበት ሕገ መንግስት ከየትኛውም የዓለም ክፍል በተሻለ ሁኔታ በሃይማት እኩልነት ላይ ተጠንቶ የጸደቀ ሕገ መንግስት ነው፡፡ ምንም አይነት የሃይማኖት ጥያቄ ቢሆን ምንም አይነት የእምነት ጥያቄ ቢሆን መፍታት የሚችል ሕገ- መንግስት ነው፡፡ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቻችለን ብንኖርም ፤ በሃይማኖቶች መካከል ግጭት ባይፈጠርም ፤ አንዳንዶቹ ሃይማኖቶች በዚህ ሃገር ውስጥ የመንግሥት የሆኑበት ፤ አንዳንዱ ደግሞ ተዋርዶ የኖረበት ሀገር ነው ፤ ሙስሊሙ ማህበረሰብ እስላም በመሆኑ ቀና ብሎ እንዲሄድ ያደረገው ሕገ መንግሥቱ ነው ፡፡ የእኛም የእናንተ መመሪያ እንደ አመራር ሕገ መንግስቱንና ሕገ መንግስቱን መጠበቅ ነው፡፡” በማለት ተናግረዋል፡፡ ችግሩ በስብሰባ ይፈታ ይመስል በቀን አስር አዳራሽ እየሰበሰቡ ስለ ሕገ-መንግሥት ማውራት መፍትሄ አያመጣም ፤ ችግሩ ከስብሰባ ያለፈ ነገር ያስፈልገዋል ፤ አማኙን እየሰበሰቡ መንግሥት መብቱ እንዳስጠበቀለት ለማስመሰልና የፖለቲካ ጥቅም ለማግኝት መደስኮር ጽንፈኞቹን መስመር አያስይዝም ፤ ሰው ቁስሌ ነው ብሎ የሚያስበውን ነገር በማንሳትና በማስጨብጨብ የችግሩን መፍትሄ መንገድ አያመላክትም ፡፡ ለማንኛውን እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ ፡፡
የዛሬ አመት የእሳቱን መነሻ የጭሱን መድረሻ ያላወቀው መንግሥት “አንዳንድ የኦርቶዶክስ አክራሪዎች” ሲል ነበር…..አሁንስ ?
ቸር ሰንብቱ

No comments:

Post a Comment