- አዲርቃይ ፍርድ ቤት ገዳማችን አይታረስም በማለታቸው ወጣቶችን በአሸባሪነት ከሰሰ
- በዛሬማ የሚገኙ ነዋሪዎች በወጣቶቹ ላይ ምስክርነት አንሰጥም በማለታቸው እንግልትእየደረሰባቸው ነው
- የሰሜን ጎንደር ጸጥታ ክፍል ክሱ በአሸባሪነት መሆን አለበት በማለት ትዕዛዝ አስተላልፏል
- የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከገዳሙ በረከት ለመቀበል የመጡት ማስፈራሪያ እና ፍተሻ (strip search) ተደረገባቸው
- የጣሊያኑ ኮንስትራክሽን ሌላ አማራጮችን እንፈልግ ብሏል
- የወልቃይት ነዋሪም እርሻውን እንዲቀጥል እስከሚመጣው ዓመት ምንም ነገር እንደማይኖርእየተነገረው ነው
(From Save Waldeba):- የዛሬ ዓመት አካባቢ ይሆናል የዛሬማ ወጣቶች ከመንግሥት ጋር ገዳማችንአይታረስም፣ የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም በማለት ከመንግሥት ታጣቂዎች ጋር ግብግብ የተፈጠረው፥በወቅቱ የክልሉ ባለሥልጣናት በቦታው ተገኝተው ከዛሬማ ነዋሪዎች ጋር ስብሰባ አድርገው የዛሬማን ነዋሪ ውሳኔእንዲሰጥ እያስፈራሩ ባሉበት ወቅት ነበር ጥቂት ወጣቶች የአባቶቻችንን ድንበር አናስነካም፣ ገዳማችንንም ፈቅደንአናሳርስም በማለታቸው ጥቂቶቹን በወቅቱ ወደ እስር ቤት ሲከቷቸው የተቀሩት አምልጠው ጫካ ገብተውገዳማችንን ማንም ሊነካውም፣ ሊደፍረው፣ ሊረግጠውም አይገባም በማለት ጥሪያቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋልየአካባቢውንም ገበሬ ማኅበራት፣ የሃገር ሽማግሌዎችን በማነጋገር እንዴት ዓይናችን እያየ ገዳማችንን የማንምአማቄላውያን (አረማውያን) መፈንጫ ይሆናል፣ ይሄ ቦታ እኮ የቅዱሳን ማረፊያ፣ የግዑሳን መጠጊያ ለእኛለተዳደፍነው እረፍት፣ በረከት፣ ቅድስና ለማግኘት የምንሄድበት እንጂ እንዴት እነዜህ አረማውያን ዛሬእንደፈለጉት ያደርጉታል በማለት ተቃውሟቸውን በከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ከሃገረ ስብከቱ ሃላፊዎችቢያቀርቡም የተወሰኑ የመንግሥት ሃላፊዎች በሃገር ሽማግሌዎች ምከሯቸው እና ወደ ቤታቸው እና ቤተሰባቸውይመለሱ በማለት አግባብተው ወደ ሃገራቸው እና ቤተሰባቸው ከተቀላቀሉ የሦስት ወይም ሁለት ወርአይበልጣቸውም ነበር።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያስገነባቸው ያሰባቸው የስኳር ፋብሪካዎች ወጣቶቹም ወደ ሃገራቸው እና ወደቤተሰቦቻቸው እንደተመለሱ ብዙም ሳይቆይ የአዲርቃይ ከተማ አቃቤ ሕግ ቢሮ ደብዳቤ ከሰሜን ጎንደርየጸጥታው ቢሮ ይደርሰዋል በደብዳቤውም ላይ “ከዚህ በፊት ታስረስው እና በምሕረት የተመለሱት ወጣቶችበሙሉ በአሸባሪነት፣ በመንግሥት ላይ በመነሳት፣ እና ከግንቦት 7 ታጣቂዎች ጋር በመተባበር” በአስቸኳይእንዲከሰሱ እና የፍርዱንም ሄደት እንደሚከታተሉት ጠቅሰው ደብዳቤ ይጽፋሉ። ደብዳቤ የደረሳቸው የአቃቢሕጉ ቢሮ ሰራተኞች ወደ ዛሬማ በመሄደ ከከተማው የመንግሥት ተወካዮች እና የጸጥታው ሃላፊዎች ጋርመመካከር ይጀምራሉ፥ የዛሬማ ከተማ መስተዳደር እና የጸጥታው ሃላፊዎች እንዴት ብለን ነው በአሸባሪነትየምንከሳቸው? በምን መረጃ ነው ብለው ሲጠይቁ ሰዎችን አስመስክሩባቸው በማለት የአቃቢ ሕጉ ሰራተኞችቢጠይቁም ጥቂት የአካባቢው ነዋሪዎች ተጠርተው የምስክርነት ቃላቸውን እነሱ በሚፈልጉት መልኩ ቢመሰክሩወሮታውን መንግሥት እንደሚሰጣቸው ቢያብሏቸውም “እኛ በልጆቻችን ላይ የሃሰት ምስክር ልንሆን አንችልም፣የምናውቀው ነገር ቢኖር ገዳማችንን አትንኩ ማለታቸውን ነው በማለት እንቢታቸውን ገልጸዋል” የአካባቢውነዋሪዎችም ‹‹እስከ ዛሬ ድረስ ሰዎችን እንዲህ እየደረጉ ነው ለካ በሃሰት እየከሰሱ ያሉት›› እነኝህ ወጣቶችያደረጉት ነገር ቢኖር ገዳማችን አትንኩ ከማለት በስተቀር፡፡ እንኳን አሸባሪ ሊሆኑ ጭራሽ እንዴት እንዲህ ዓይነትክስ ሊመሰርትባቸው ይችላል? በማለት ቅሬታቸውን ደጋግመው በማሰማት የአካባቢው የጸጥታ ቢሮ እናየአዲርቃይ የአቃቢ ሕግ ሰራተኞች ተመካክረው ወጣቶቹን በአሸባሪነት ቀርቶ በሌላ ክስ ሊመሰርቱባቸውተስማምተው እንደነበር ለማውቅ ተችሏል፡፡
መጋቢት ፲፮ ቀን ፳፻፭ ዓ.ም. በአዲርቃይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የዛሬማ ወጣቶችለቤተክርስቲያናቸው፣ ለገዳመ ዋልድባ፣ እንዲሁም ለቅርስ እና ለሃገራቸው ሃብት በመቆርቆራቸው የተነሳ እንደ ወንጀለኛ ተከሰው በፍርድ ቤት ቀርበው የአዲርቃይ ከፍተኛ ፍርድ ቤት
፩ኛ/ ወጣት ደስታው በ ብር 3000.00 ብር እንዲቀጣ
፪ኛ/ ወጣት ደፋሩ ታከለ በ ብር 2000.00
፫ኛ/ ወጣት ማሙሽ አሰፋ በብር 800.00
፬ኛ/ ወጣት ስሙን ያላገኘነው በብር1800.00 ብር እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡
የአካባቢው ማኅበረሰብ በወጣቶቹ ላይ የተወሰነውንም ውሳኔ በጥብቅ ተቃውመውታል።
በተያየዘ ዜና ከተለያየ የጎንደር ከተማ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ ወደ 70 የሚጠጉ ተማሪዎች በየዓመቱእንደሚያደርጉት ወደዋልድባ ገዳም በመሄድ ከገዳሙ በረከት ለመቀበል፣ በዮርዳኖስ ጸበል ለመጠመቅ፣እንዲሁም ከመጋቢት መድኅኒዓለም ዋዜማ ጀምሮ በበዓሉ በረከት ተካፋይ ለመሆን ጉዞ እንደሚያደርጉይታወቃል፥ ዘንድሮም እንደ አምናው እነዚህን ተማሪዎች ታጣቂዎች ከመንገድ አስወጥተው ምን ልታደርጉመጣችሁ በማለት ብዙ ማንገላታታቸውንም የደረሰን መረጃ ያሳያል፣ ተማሪዎቹንም የተጠየቁት ጥያቄዎች
- ከአካባቢው ሃገረ ስብከት ደብዳቤ ይዛችኃል ወይ?
- እናንተ ባለፈው ጎንደር ላይ አመጽ ልታስነሱ ስትሞክሩ የነበራችሁ ናቸሁ፥
- ዘራችሁ ምንድነው? አማሮች ከሆናችሁ ወደ ትግራይ ክልል መግባት አትችሉም፥
- የግንቦት 7 ቡድን ናችሁ፣ ደፈጣ ለማድረግ ነው የመጣችሁት ፤ ጸረ ልማት እና ጸረ ሰላምናችሁ
በሚል ክስ ወደ በረሃ ወስደው አንድ ቀን ሙሉ ልብሳቸውን ሲበረብሩ፣ ሻንጣቸውን ሲፈትሹ ውለው እጅግ ብዙእንግልት እና ድብደባም ደርሶባቸው በመጨረሻ ከአንድ ቀን ሙሉ እንግልት በኃላ ወደሚፈልጉበት እንዲሄዱፈቅደውላቸዋል፤ ተማሪዎቹም እኛ ከገዳማችን በረከት ለመቀበል የማንንም ፈቃድ አንጠይቅም፣ የሃገረ ስብከትተወካዮችም ሂዱ ወይም አትሂዱ ሊሉን የሚችሉበት ስልጣን የላቸውም እንደ ክርስቲያን ቤተክርስቲያንንለመሳም እና በረከት ለመቀበል ፈቃድ ልንጠይቅ አይገባም በማለት ቁጣቸውን ቢገልጹም ታጣቂዎቹ ብዙማስፈራራት እና እንግልት አንዳደረሱባቸው ለመረዳት ችለናል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ እስከ ዛሬ ድረስ በገዳሙ ክልል ሊገነባ የታሰበውን ግድብ (እስከ ዛሬ ድረስ ብዙ ውዝግብያስነሳው ግድብ) የኮንስትራክሽኑ ሃላፊ የሆነው የጣሊያን ኩባንያ ለመጭው ሁለት ወራት ስራውን በደንብ ጥናትእንዲያደርግ እና መልሱን ለባለሥልጣናቱ እንደሚያሳውቅ አስታወቀ። ባለፉት 13 ወራት በ4 የተለያዩኩባንያዎች ግንባታውን ለመሥራት ጥረት ሲያደረጉ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን የሰው ሕይወት ከመጥፋትበስተቀር፣ ምንም አይነት ስራ መስራት ባለመቻላቸው ተስፋ መቁረጥ የሚታይባቸው የጣሊያን ኩባንያባለሥልጣናት ተጨማሪ የሆኑ ቦታዎችን ተመልክተው የቦታ ለውጥ ለማድረግም ጥያቄ እንደሚያቀርቡይገመታል። የጣሊያኑ ኩባንያ ከህንዱ ኪባንያ ተቀብሎ ስራዎችን ለመሥራት ያደረገው የ4 ወራት ጥረት ምንምመስራት ባለመቻላቸው ከመንግሥት ባለሥልጣናት ነቀፋ ቢደርስባቸውም ቀን ከሌሊት ቢሰሩም በመድኅኒዓለምጥበቃ ግድቡ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ መስራት ባለመቻሉ ተስፋ መቁረጥ፣ እልህ፣ እና በቀል የሚታይባቸውየስኳር ፋብሪካ ኮርፖሬሽን ዳይሬክተር አቶ አባይ ጸሐዬ ተጨማሪ ወይም ተለዋጭ ሃሳቦችን ከጣሊያኑ ኩባንያእንደሚቀበሉ አስታውቀዋል።
የወልቃይት ገበሬ ማኅበራት እና በፕሮጀክቱ ምክንያት ከአካባቢው ትፈናቀላላችሁ ተብለው በስጋት ላይ ነበሩትአርሶ አደሮችም ለጊዜው ኑሮአቸውን መቀጠል እንደሚችሉ እና እርሻም ማረስ እንደሚችሉ የክልሉባለሥልጣናት ሲናገሩ ሰንብተዋል፥ የክልሉ ነዋሪም እምነቱን በእግዚአብሔር አድርጎ የእለት ተእለት ኑሮውንቀጥሏል ፤ ነገ ምን ሊመጣ እንደሚችል ስለማይታወቅ ሁልጊዜም ባጣዳፊ ትነሳለህ ቢባል እንኳ ዝግጁ ሆኖ የነገንስለማያውቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል። እርሻውንም ለማረስ ምንም አማራጭ ያጡት የወልቃይት ገበሬዎች “ነገተነሱ ብንባል ደግሞ፥ ለከርሞ ቤተሰባችንን የምናበላው የለንም” እንዴት እንሁን? በማለት ምሬታቸውንአሰምተዋል አንዳንዶችም እጃቸውን ወደ ሰማይ በመዘርጋት “አንተ ታውቃለሃ” በማለት አቤቱታቸውንለአምላካቸው አቅርበዋል።
እኛም ለቤተክርስቲያናችን ፍጹም ሰላምን፣ በክፋት እና በድፍረት በአባቶቻችን ላይ ግፍ እና በደል ለሚያደርሱት ልቦንእንዲሰጥልን እንመኛልን።
የጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ በረከት ይደርብን፥ እግዚአብሔር አምላካችን ተዋሕዶሃይማኖታችንን፣ ቅድስት ሃገራችንን፣ ሕዝባችንን በረደኤት ይጠብቅልን
No comments:
Post a Comment