Sunday, 23 February 2014
Sunday, 16 February 2014
Saturday, 15 February 2014
ማኅበረ ቅዱሳን ከ 200 በላይ የአብነት መምህራን የምክክር ስብሰባ መታገድ ላይ ለአብነት መምህራኑ ገለጻ ሰጠ
ጉባኤው በ "አባ" ሰረቀብርሃን ምክንያት በመጨረሻው ሰአታት ላይ እንዲቋረጥ ተደርጓል። በጉባኤው ላይ የተጋበዙ የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ትልልቅ ባለስልጣናት ሃዘናቸውን ገልጸዋል። ለጉባኤው መሳካት ማህበሩ ብዙ ሺህ ብር ወጪ እንዳወጣበት አሳውቋል። ማህበሩ ለእዲህ ያሉ ችግሮች አዲስ እንዳልሆነና የሚጠበቅ እንደነበረም መ/ር ብርሃኑ አድማስ ተናግረዋል። "ይህ ጉባኤ በአይነቱ የተለየ ሰለሆነ፣ በቤተክህነቱም በዓመቱ መጀመሪያ ላይ አሳውቀን ተቀባይነትን ስላገኘ እንዲሁም ከተለያየ መስሪያ ቤቶች የተጋበዙ ታታላቅ ባለስልጣናትም ስለሚገኙ ነበር እክል አያጋጥመውም ብለን የተዘናጋነው። ሆኖም እግዚአብሄር ፈቅዶ ይህ ከሆነ መልካም ነው" መ/ር ብርሃኑ አድማስ።
በጉባኤው ላይ የተገኙት አባቶችም ሃዘናቸውን ትህትና በተሞላበት መንገድ ገልጸዋል። ቅዱስ ፓትሪያርኩንም ማነጋገር እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ሆኖም ግን ሁሉም አባቶች ብጹህ ፓትሪያርኩን ማነጋገር ባይችሉም ጥቂት የተመረጡ መምህራን ግን እንዲያነጋግሩ ተፈቅዶላቸዋል። ቅዱስ ፓትሪያርኩም "መመሪያ መመሪያ ነው!" የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው መምህራኑ ተናግረዋል።
ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጫን ማድመጥ ይችላሉ!
http://www.dtradio.org/index.php?option=com_content&%3Bview=article&%3Bid=136%3A-7-2006-february-14-2014-&%3Bcatid=1%3Aweekly-tansmission#.Uv6ECtKvl3w.facebook

Tuesday, 11 February 2014
Sunday, 9 February 2014
ከ2000 ዓመት በኋላ እንደ አዲስ እንመዘገባለን፣ እንደ አዲስም እንታወቃለን
ሰሞኑን የፌድራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖት ተቋማትን ለመመዝገብ የወጣ ረቂቅ መመሪያ› የሚል ወረቀት አስተያየት ይሰጥበት ዘንድ ለእምነት ተቋማት አሠራጭቷል፡፡ ይህ መመርያ የያዛቸውን ጉዳዮች እያንዳንዳቸውን እየነጠሉ መመልከት ያስፈልጋል፡፡ ይህንንም ወደፊት የምናደርገው ይሆናል፡፡ ለአሁኑ ግን መመሪያውን ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ነባራዊ፣ ሉዓላዊና መንፈሳዊ ጠባያት ጋር በማዛመድ ብቻ እንመለከተዋለን፡፡
1. መመሪያው የቤተ ክርስቲያኒቱን ልዩ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ ነው
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት 2000 ዓመታት በምድሪቱ ላይ የኖረች፣ የሰበከች ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ ክፉውንም ሆነ ደጉንም እኩል የቀመሰች፣ እንዲያውም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በመሆንዋ ብቻ ልዩ ጉዳት የደረሰባትም ናት፡፡ በጣልያን ወረራ ጊዜ የተሠውትን ጳጳሳትና መነኮሳት ማሰቡ ብቻ ለዚህ የቅርብ ምሳሌ ነው፡፡ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን በዘመናት ሂደት ውስጥ በሀገሪቱ ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሕይወት ውስጥ ልዩ የሆነና የማይተካ ሚና ተጫውታለች፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ተመሥርታ ሀገሪቱንም መሥርታለች፡፡
ይህንን ሁሉ ዘንግቶ በ2005 ዓም ላይ ቤተ ክርስቲያኒቱን እንደ አዲስ ተመዝገቢ፣ እንደ አዲስ ፈቃድ አውጭ፣ እንደ አዲስ ደንብና መመሪያሽን አምጭ ማለት እጅግ አሳዛኝም አስገራሚም ነገር ነው፡፡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም ራሱ ከፈለገ መረጃ ሰብስቦ መመዝገብና ማወቅ ነበረበት እንጂ ሰነድ አምጭ፣ ደንብ አስገቢ፣ ፈቃድ አውጭና ልወቅሽ ማለት አልነበረበትም፡፡

Friday, 7 February 2014
"እግዚኦ አርእየኒ እመከ = አቤቱ እናትህን አሳየኝ"
በቴዎድሮስ በለጠ
ምዕመናን ይጠይቃሉ " ስለ ድንግል ማርያም አስተምረን" ?
ጥያቄውን "ይመልስባቸዋል" እንዲህ ሲል "እኛ እዚህ ድረስ የመጣነው ጌታን ልንሰብክላችሁ እንጂ ስለ ማርያም ልናወራላችሁ አይደለም.... እስኪ ቅዱስ ጳውሎስን ተመልከቱ ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ ስለ ሶምሶንም ስለ ዮፍታሔም""""እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛል አለ እሱ ጊዜ ያለው ስለ ጌታ ብቻ ለመመስከር ነው...."
ይህ በአይሁድ ምኩራብ ፥ በተንባላት አውድ አልያም በመናፍቃን አዳራሽ የተነገረ እንዳይመስላችሁ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መድረክ ላይ በድፍረት የተፈጸመ እንጂ :: እውነትም ሥፍራው የምሕረት አደባባይ ነው አምላክ ለቁጣና ለመአት የቅጣት ሠይፉን የሚያዘገይበት ለትዕግስትና ለይቅርታ የፍቅር እጁን የሚዘረጋበት "አውደ ምሕረት"! .... እንግዲህ ምን እንላለን "እግዚኦ ተዘከራ ለአሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ሀለወት እምጽንፍ እስከ አጽናፈ ዓለም"
Monday, 3 February 2014
ንዋያተ ቅዱሳቱ የማን ናቸው?
ጥር 26 ቀን 2006 ዓ.ም.
ምንጭ፡- ሐመር መጽሔት 21ኛ ዓመት ቁጥር 8 2006 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የዜማ መሣሪያዎች ከቅዱስ ያሬድ ጀምሮ በርካታ ሊቃውንት ሲያገለግሉበት የነበረና የሰማያዊውን የዝማሬ ሥርዓት መነሻ ያደረገ፣ ሰማያዊውንም ዓለም የሚያሳስብ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃልም መነሻ ተደርጎ የተመረጠ፣ ኢትዮጵያዊ መልክ ኖሯቸውም የተዘጋጁ ናቸው፡፡
እነዚህ የዜማ መሣሪያዎች ቤተክርስቲያናችን ይዛ በምትጠቀምበት ቅርጽና ይዘት የሚገኙት በኢትዮጵያና ኢትጵያውያን እጅ ብቻ ነው፡፡ ይልቁንም ደግሞ የአንድ ቤተ ሃይማኖት ማለትም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት መጠቀሚያ ሆነው እያገለገሉ ያሉ ናቸው፡፡
ይህ በእንዲህ እያለ ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ሌሎች ቤተእምነቶች በከበሮ፣ በመቋሚያና ጸናጽሉ በራሳቸው ተጠቅመው በራሳቸው መንገድ የራሳቸውን እምነት ሲያራምዱበት እየታየ ነው፡፡ በመድረኮቻቸው ያንን ሲያደርጉ ታይተዋል፡፡ በቴሌቪዥን ፕሮግራም ሲያስተላልፉ ተስተውሏል፡፡
በተመሳሳይ ዜማው የዝማሬ ሥርዓቱ የበዓላት ሥርዓቱ ንዋየ ቅድሳቱ ሁሉ ደረጃ በደረጃ በተለያዩ ቤተእምነቶች ቁጥጥር ሥር ወድቋል፡፡ የበዓላት ቀናቱ ጭምር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ባሕረ ሐሳብ መሠረት የሚወጣ ቢሆንም እንደራሳቸው አደርገው በዓል ሲያደርጓቸው ልዩ ልዩ መርኀ ግብር ሲፈጸምባቸው ይታያል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆነው የመስቀል በዓል ነው፡፡ በዓለ መስቀል ኦርቶዶክሳውያንን ብቻ የሚመለከት በዓል ቢሆንም አሁን ግን በቤተክርስቲያኒቱ የበዓል ዐውድ ውስጥ ሌሎች ቤተእምነቶች የራሳቸውም እንደሆነ በሚያስመስል መንገድ ስለሚቀርቡ ግራ መጋባት እየፈጠረ ነው፡፡ ይሄ ነገር በዚሁ ከቀጠለ ቤተክርስቲያናችን የእኔ የምትለው የራሷ ነገር እየጠፋ ሊመጣ ይችላል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)