Monday, 3 February 2014

ኢትዮጵያ 46

በሳህሉ ወንድወሰን

ይህ ጽሁፍ አቶ ሳህሉ ወንድወሰን በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ያሰፈሩትን እንዳለ በመውሰድና ጥቂት ያልተካተቱትንም በመጨመር የተዘጋጀ ነው።

ኢትዮጵያ በመጽሃፍ ቅዱሳችን ውስጥ ምን ያክል ጊዜ መነሳቷንና የት የት ቦታ ላይ እንደተጠቀሰችም ማሳያ ነው። ለወንድማችን ቃለህይወትን ያሰማልን።
መልካም ንባብ!





ኦሪት ዘፍጥረት2፥13 የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።

ኦሪት ዘኍልቍ12፥1 ሙሴም ኢትዮጵያይቱን አግብቶአልና ባገባት በኢትዮጵያይቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በእርሱ ላይ ተናገሩ።

መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ19፥9 እርሱም፦ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊወጋህ መጥቶአል የሚል ወሬ በሰማ ጊዜ ደግሞ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥ እንዲህ ሲል፦

መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ12፥3 ከእርሱም ጋር ከግብጽ ለመጣው ሕዝብ ቍጥር አልነበረውም እነርሱም የልብያ ሰዎች፥ ሱካውያን፥ የኢትዮጵያ ሰዎችም ነበሩ።

  • 14፥9 ኢትዮጵያዊውም ዝሪ አንድ ሚሊዮን ሰዎችና ሦስት መቶ ሰረገሎች ይዞ ወጣባቸው ወደ መሪሳም መጣ።

  • 14፥12 እግዚአብሔርም በአሳና በይሁዳ ፊት ኢትዮጵያውያንን መታ ኢትዮጵያውያንም ሸሹ።

  • 4፥13 አሳም ከእርሱም ጋር ያለው ሕዝብ እስከ ጌራራ ድረስ አሳደዱአቸው ኢትዮጵያውያንም ፈጽመው እስኪጠፉ ድረስ ወደቁ፥ በእግዚአብሔርና በሠራዊቱ ፊት ተሰባብረዋልና እጅግም ብዙ ምርኮ ወሰዱ።

  • 16፥8 ኢትዮጵያውያንና የልብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረገሎችና ፈረሰኞች የነበሩአቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አልነበሩምን? በእግዚአብሔር ስለ ታመንህ በእጅህ አሳልፎ ሰጣቸው፥

  • 21፥16 እግዚአብሔርን የፍልስጥኤማውያንና በኢትዮጵያውያን አጠገብ የሚኖሩትን የዓረባውያንን መንፈስ በኢዮራም ላይ አስነሣ።

መጽሐፈ አስቴር1፥1 በአርጤክስስም ዘመን እንዲህ ሆነ ይህም አርጤክስስ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በመቶ ሀያ ሰባት አገሮች ላይ ነገሠ።

  • 3፥12 በመጀመሪያውም ወር ከወሩም በአሥራ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ወዳሉ መቶ ሀያ ሰባት አገሮች፥ በየአገሩ ወዳሉ ሹማምትና አለቆች ወደ አሕዛብም ሁሉ ገዢዎች እንደ ቋንቋቸው በንጉሡ በአርጤክስስ ቃል ሐማ እንዳዘዘ ተጻፈ፥ በንጉሡም ቀለበት ታተመ።

  • 8፥9 በዚያን ጊዜም ኒሳን በተባለው በመጀመሪያው ወር ከወሩም በሀያ ሦስተኛው ቀን የንጉሡ ጸሐፊዎች ተጠሩ መርዶክዮስም ስለ አይሁድ እንዳዘዘው ሁሉ ከህንድ ጀምሮ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ በመቶ ሀያ ሰባቱ አገሮች ላሉ ሹማምትና አለቆች አዛውንትም ለእያንዳንዱም አገር እንደ ጽሕፈቱ ለእያንዳንዱም ሕዝብ እንደ ቋንቋው ለአይሁድም እንደ ጽሕፈታቸውና እንደ ቋንቋቸው ተጻፈ።

መጽሐፈ ኢዮብ28፥19 የኢትዮጵያ ቶጳዝዮን አይተካከላትም፥ በጥሩም ወርቅ አትገመትም።

መዝሙረ ዳዊት68፥31 መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

  • 72፥9 በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።

  • 74፥14 አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውንሰጠሃቸው።

  • 87፥4 የሚያውቁኝን ረዓብንና ባቢሎንን አስባቸዋለሁ እነሆ፥ ፍልስጥኤማውያን ጢሮስም የኢትዮጵያም
ሕዝብ፥ እነዚህ በዚያ ተወለዱ።

ትንቢተ ኢሳይያስ11፥11 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብጽ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደ ገና እጁን ይገልጣል። 
  • 18፥1 በኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ ላለች፥ ክንፍ ያላቸው መርከቦች ላሉባት፥
  • 20፥3 እግዚአብሔርም አለ፦ ባሪያዬ ኢሳይያስ በግብጽና በኢትዮጵያ ላይ ሦስት ዓመት ለምል ለተአምራት ሊሆን ራቁቱንና ባዶ እግሩን እንደ ሄደ፥
  • 20፥4 እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብጽንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን፥ ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ ገላቸውንም ገልጦ፥ ለግብጽ ጕስቍልና ይነዳቸዋል።
  • 20፥5 እነርሱም ከተስፋቸው ከኢትዮጵያ ከትምክሕታቸውም ከግብጽ የተነሣ ይፈራሉ ያፍሩማል
  • 37፥9 እርሱም፦ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቲርሐቅ ሊዋጋህ መጥቶአል የሚል ወሬ ሰማ። በሰማም ጊዜ ወደ ሕዝቅያስ መልእክተኞችን ላከ፥
  • 43፥3 እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።
  • 45፥14 እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል። የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ። በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።ትንቢተ ኤርምያስ
  • 13፥23 በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጕርጕርነትን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን? በዚያን ጊዜ ክፋትን የለመዳችሁ እናንተ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ።
  • 38፥7 በንጉሡም ቤት የነበረው ጃንደረባ ኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ ኤርምያስን በጕድጓዱ ውስጥ እንዳኖሩት ሰማ። ንጉሡም በብንያም በር ተቀምጦ ነበር።
  • 38፥10 ንጉሡም ኢትዮጵያዊውን አቤሜሌክም። ከአንተ ጋር ሠላሳ ሰዎች ከዚህ ውሰድ፥ ነቢዩም ኤርምያስ ሳይሞት ከጕድጓድ አውጣው ብሎ አዘዘው።
  • 38፥12 ኢትዮጵያዊውም አቤሜሌክ ኤርምያስን፦ ይህን አሮጌ ጨርቅና እላቂውን ልብስ በብብትህ ከገመዱ በታች አድርግ አለው ኤርምያስም እንዲሁ አደረገ።
  • 39፥16 ሂድ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው። የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል።
  • 46፥9 ፈረሶች ሆይ፥ ውጡ ሰረገሎችም ሆይ፥ ንጐዱ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፋጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።ትንቢተ ሕዝቅኤል
  • 29፥10 ስለዚህ፥ እነሆ፥ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ፥ የግብጽንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ።
  • 30፥4 ሰይፍ በግብጽ ላይ ይመጣል፥ ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል የተገደሉትም በግብጽ ውስጥ ይወድቃሉ፥ ብዛትዋንም ይወስዳሉ፥ መሠረትዋም ይፈርሳል።
  • 30፥5 ኢትዮጵያና ፉጥ ሉድም የተደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነርሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ።
  • 30፥9 በዚያ ቀን መልእክተኞች ተዘልለው የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን ለማስፈራት ከፊቴ በመርከብ ይወጣሉ እንደ ግብጽም ቀን ሁከት ይሆንባቸዋል እነሆ፥ ይመጣልና።
  • 38፥5 ፋርስንና ኢትዮጵያን ፉጥንም ከእነርሱ ጋር ጋሻና የራስ ቍርን የለበሱትን ሁሉ፥ትንቢተ ዳንኤል
  • 11፥43 በወርቅና በብርም መዝገብ ላይ፥ በከበረችም በግብጽ ዕቃ ሁሉ ላይ ይሠለጥናል የልብያና የኢትዮጵያ ሰዎችም ይከተሉታል።

ትንቢተ አሞጽ9፥7 የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር፦ እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን?

ትንቢተ ናሆም3፥9 ኢትዮጵያና ግብጽ የማይቈጠር ኃይልዋ ነበሩ ፉጥና ልብያ ረዳቶችዋ ነበሩ።

ትንቢተ ዕንባቆም3፥7 የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።

ትንቢተ ሶፎንያስ2፥12 እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።

  • 3፥10 ከኢትዮጵያ ወንዞች ማዶ የሚማልዱኝ፥ የተበተኑት ሴቶች ልጆቼ፥ ቍርባኔን ያመጡልኛል። 

የሐዋርያት ሥራ8፥27 ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤

    No comments:

    Post a Comment