“ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ” ለመመስረት ጥያቄ መቅረቡ ተሰማ
- መንግስት በጥያቄው ደንግጧል
- “ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ፡፡” የኢትዮጵያ ህገ መንገስት አንቀጽ 31
(አንድ አድርገን ሐምሌ 18 2004 ዓ.ም)፡- የሀገሬ ሰው “የባሰ አለና ሀገርህን አትልቀቅ” ይላል ፤ በአሁኑ ሰዓት እንዲህማ አይታሰብብ የምንለው ጉዳይ እንደ ትልቅ ጉዳይ ብቅ ብሏል ፤ ይህ ጥያቄ ውስጠ ወይራ ነው ፤ መንግስት የሚደሰኩርለትን ዲሞክራሲን መሰረት አድርጎ የውስጥን አላማ ለማሳካት የተነሳ ጥያቄ ፤ ካለመጠይቅ ደጃዝማችነት ይቀራል በማለት የተነሳ ወቅታዊ ጥያቄ ፤ ሙስሊሙን ነጻ አወጣለው በማለት የሙስሊምን የበላይነት ለማረጋገጥ ሲባል የዘመናት ጥያቄዎቻውን ለመመለስ ያመቻቸው ዘንድ የጠየቁት ጥያቄ ፤ ……
የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ተሰናባቹ የአሜሪካ የአዲስ አበባ አምባሳደር በጊዜው ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ስለሚደረገው ሰርጎ ገብ ውሀቢዝም እንቅስቃሴ ከዊኪሊክስ የተገኝ መረጃ ለዓለም ወጥቶ ነበር ፤ ይህን መረጃ ከአዲስ አበባ ወደ ዋሽንግተን ከመላኩ በፊት የኢህአዴግ መንግስት ጠንቅቆ እንደሚያውቀው በጊዜው በሚወጡ ማስረጃዎች ለማወቅ ተችሏል ፤ የአሜሪካ ኢምባሲ ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ወደፊት ወሀቢያ የእግር እሳት እንደሚሆንባት ጨምሮም ገልጾ ነበር ፤ የዛሬ ሁለት ዓመት በደሴ ፤ በአርሲ ፤ በሀረር ፤ በምስራቅ ሀረርጌ እና በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ወሀቢያን የሚያራምዱ ሰዎች የራሳቸው በሚሏቸው ሰዎች አማካኝነት ረብጣ የነዳጅ ብር እየከፈሏቸው አመለካከታቸውንና አይዲዎሎጂያቸውን ወደ ሙስሊሙ ማህበረሰብ የማውረድ ስራ ሲሰሩ እንደነበር ይታወቃል ፤ ( ከዊኪሊክስ የወጣ መረጃን ለማንበብ ይህን ይጫኑ Wahabism in Ethiopia as "CULTURAL IMPERIALISM")
ይህ አካሄድ መጨረሻው ኢስላማዊ መንግስት እስከ ማቋቋም ይደርሳል ፤ እኛ ይህን ለማለት የደፈርነው በጊዜው ከወጡ ሁለት መረጃዎች በመነሳት እንጂ መንግስት በኢቲቪ የሚደሰኩረውን ነገር መሰረት አድርገን አይደለም ፤ በመሰረቱ ኢቲቪ ላይ በአሁኑ ወቅት እያየን ያለነው ሁሉም እውነት አይደለም ሁሉም ደግሞ ውሸት አይደለም ፤ የፖለቲካ አካሄድ እንዳለ ሆነ በርካታ እውነታዎችም አብረውት እንዳሉት ለማየት ችለናል ፤ መንግስት ይህ ስር የሰደደ ለሀገርም ይሁን ለህዝብ የማይጠቅምን ፤ ሀገርን አደጋ ላይ የሚጥልን አመለካከት በጊዜው እንደ ተራ ነገር በመመልከት በ2003 ዓ.ም የካቲት ወር የሚመለከታቸውን የእስልምና የእምነቱን አባቶች በመጥራት በሀገሪቱ የሚካሄደውን ነገር እንደደረሰበት እና እጃቸውን እዚህ ላይ የሰደዱ ሰዎች እጃቸውን ከዚህ አመለካከት ላይ እንዲያነሱ ያለበለዚያ ግን ህጉ በሚፈቅደው መጠን እርምጃ እንደሚወስድ አበክሮ መናገሩ ይታወቃል ፤ ነገር ግን መንግስት የተናገረውን ወደ ተግባር ሲለውጠው መመልከት አልቻልንም ፤ ይህ አመለካከት ሲጀምር ግብር በሚከፈልበት ቦታ ላይ ሙስሊም ማህበረሰብ እንዳይሰግድ ያዛል ፤ ኢትዮጵያ የአረብ ሀገራት አባል እንድትሆን ጠንክሮ ይሰራል ፤ ሙስሊም ነጋዴ ግብር መክፈል ያለበት ለእስልምና መንግስት እንጂ ለማንም እንዳልሆነ አበክሮ ያሰብካል ፤ ሀገሪቱ በሸሪአ ህግ እንድትተዳደር ይደነግጋል ፤ ወሃቢያን ለማስፋፋት ፍቃደኛ ለሆነ ሰው ለአንድ ተራ ምዕመንም በወር ከ10 ሺህ ብር በላይ በካሽ እንደሚከፍለው መረጃዎች ያመለክታሉ ፤
መጀመሪያ የታሰበውና የተነሱበትን አላማ ማሳካት ያስችላቸው ዘንድ በአገሪቱ ላይ ሙስሊሞችን የሚወክል ፤ ሙስሊሞችን ነጻ ለማውጣት የሚታትር የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ፍቃድ መጠየቃቸው በአሁኑ ወቅት ተሰምቷል ፤ ይህ ጥያቄ መቅረብ ማንንም ሳይሆን የመንግስት ባለስልጣናትን ክፉኛ አስደንግጧቸዋል ፤ ሰዎቹ ይህን ጥያቄ ሊያነሱ የፈለጉበት ነጥብ ምንድነው ? ጥያቄው መነሳቱ ሳይሆን ትልቁ ጥያቄ ሊሆን የሚችለው አሁን የያዙት አመለካከት ምን ያህል ረዥም ርቀት ለመጓዝ ቆርጠው መነሳታቸው ጭምር ነው ፤ ይህ የፖለቲካ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንቡ ምን ሊሆን ይችላል ? አባላቶቻቸው እነማን ናቸው ? ምን አይነት አላማ ለማሳካት ነው በፖለቲካ ፓርቲነት መቋቋም ያስፈለጋቸው ? ይህ ሊመለስ የሚገባው ጥያቄ ነው ፡፡ ይህ ወሬ የተሰማው በአሁኑ ሰዓት ሀገሪቱ ያለችበትን የሃይማኖት ችግር እንዴት እዚህ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ፤ ከእምነት ተቋማት ምን አይነት ጥያቄዎች ለመንግስት አካላት እንዳቀረቡ ፤ ጥያቄዎች ከህገመንግስቱ አኳያ እንዴት እንደሚታዩከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በሚወያዩበት ወቅት የተነሳ ሃሳብ ነው ፤
በአሁኑ ሰዓት ተሀድሶያውያንን ለመጠራረግና ከቤተክርስቲያን ውስጥ ለማስወጣት ከፍተኛ ስራ ተሰርቷል ፤ በዚህ አጋጣሚ ብዙዎች ለምን እንዲወጡ ትገፏችዋላችሁ? ለምን ተምረው አይመለሱም ይላሉ? ሰዎቹ የእውቀት ችግር የለባቸውም ፤ “አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት አይሰማም” ነው ብሂሉ ፤ ይህ የውስጥ ችግር ሲሆን ይህን የመሰለ የውጭ ችግርን ለመከላከል ምን እየሰራን እንገኛለን ? እኛ እንደሚታየን ይህም የወደፊትየቤተክርስቲያን አደጋ ነው ፤ ዛሬ ዘሩን ለመዝራት ሲሞክሩ ብንመለከት ነገ ፍሬ አፍርቶ የምናጭድበት ጊዜ እንደማይመጣ እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፤ አይኖቻችንን ረዥም ርቀት እንዲያዩ እንፍቀድላቸው ፤
ይህን የመሰለ ፓርቲ ስያሜ የምናገኝው በግብጽ ፤ በሊቢያ ፤ በቱኒዚያ ባህሪን በሶሪያ እና መሰል የአረብ ሀገራት ነው ፤ በግብጽ 90 በመቶ የሚሆነው የእስልምና ተከታይ ሲሆን ቀሪው 10 በመቶ ደግሞ የክርስትና ተከታይ መሆኑ ይታወቃል ፤ ባህሬን ውስጥ ካላት 1.2 ሚሊየን ህዝብ ውስጥ 98 በመቶ የሚሆነው የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን የተቀሩት ደግሞ የተለያዩ እምነቶችን ይከተላሉ ፤ በተመሳሳይ ኳታር 1.7 ሚሊየን ከሚሆነው ህዝቧ አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ ነው ፤ በሶሪያ 89 በመቶ የሚሆነው ሙስሊም ሲሆን 11 በመቶ ግድም የሮማን ካቶሊክና ክርስትያኖች እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ ይህን ነገር ያነሳነው ያለምክንያት አይደለም ፤ እነዚህ ሀገራት ላይ ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲ ለማቋቋም ጥያቄ ቢነሳ ተገቢ ነው ብለን መቀበል እንችል ይሆናል ፤ መጀመሪያውኑ ህገ መንግስታቸው የሸሪያን ህግ መሰረት አድርገው ስለመሰረቱት የፓርቲውን ምስረታ ለመፍቀድ ብዙም አዳጋች አይሆንባቸውም የሚል ግምት አለን ፤ እንደ ኢትዮጵያ ባለች ከ45 በመቶ በላይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስትያኖች፤ 33 በመቶ ሙስሊም አማኞች ፤ 18 በመቶ አካባቢ ፕሮቴስታንቶች በሚኖሩበት ሃገር ላይ ይህን ጥያቄ ማቅረብ ማለት ምን ማለት ነው ?
የኢትዮጵያ ህገ መንግስት በአንቀጽ 11 “የመንግስትና የሃይማኖት መለያየት” በሚል በንኡስ አንቀጽ 1 ላይ “መንግስትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው” ይላል ፤ በንኡስ አንቀጽ 2 ላይ “መንግስታዊ ሃይማኖት አይኖርም” በማለት ያክላል ፤ በስተመጨረሻም በንኡስ አንቀጽ 3 ላይ “ መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ፤ ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም” በማለት በግልጽ ያስቀምጣል ፡፡ ይህን አንቀጽ እንደ አንቀጽ ከመቀመጡ በተጨማሪ መንግስት የእምነት ተቋማት እና ተከታዮቻቸው በዚህ አንቀጽ ላይ መብታቸው ምን ድረስ ነው ? ግዴታቸውስ ? የሚለውን ጉዳይ በአግባቡ የማስተማር እና የመተርጎም ስራ የሰራ አይመስለንም ፤ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 27 ንኡስ አንቀጽ 2 ላይ “ የሃይማት ተከታዮች ሃይማታቸውን ለማስፋፋትና ለማደራጀት የሚያስችሏቸውን የሃይማት የትምህርትና የአስተዳደር ተቋማትን ማቋቋም ይችላሉ” በማት ያስቀምጣል ፤ ይህ አንቀጽ እንደሚነግረን “የሃይማት የትምህርትና የአስተዳደር” ተቋማትን እንጂ የፖለቲካ ተቋም አይልም ፤ ህገ መንገስቱ አንቀጽ 31 ላይ “ ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ፡፡ ሆኖም አግባብ ያለውን ህግ በመጣስ ወይም ህገ መንግስታዊ ስርአቱን በህገወጥ መንገድ ለማፍረስ ተመሰረቱ ወይም የተጠቀሱትን ተግባራት የሚያራምዱ ድርጅቶች የተከለከሉ ይሆናሉ” በማለት ያስቀምጣል ፤ እዚህ አንቀጽ ላይ “ለማንኛውም ዓላማ በማህበር የመደራጀት መብት አለው ” ማለት ሁሉንም ስለሚያካትት ለምን ሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ፓርቲን ለመመስረት ጥያቄ አቀረቡ ማለት አይቻልም ፤ ለምን ቢባል ህገመንግስቱ ለማንኛውም አላማ በማህበር የመደራጀት መብትን ስለሚፈቅድ ፤ ሙሉ ህገ መንግስቱን ቢያነቡት አንድም ቦታ ሃይማኖትን መሰረት አድርጎ ስለሚቋቋም የፖለቲካ ፓርቲ የሚለው ነጥብ የለውም ፤ ይህ ለጥያቄያቸው ክፍተት የሰጣቸው ይመስለናል ፤ የህጎች ሁሉ የበላይ ደግሞ ህገመንግስቱ ነው፡፡
ስህተቶች የሚፈጠሩት አንድም ባለማወቅ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የተቀመጠውን ነገር በአግባቡ ከመተርጎም ጋር በተያያዘ ችግር ወይም ህጉን ክፍተት በመጠቀም የሚደረግ የህግ ትርጓሜ ሊሆን ይችላል ፤ ምንም ይሁን ምን ይህን ጥያቄ እንደ ተለያዩ የአረብ ሃገራት በሀገራችንም ፓርቲውን ለማቋቋም የሚፈልጉ ሰዎች ተነስተዋል ፤ በመሰረቱ ይህ አደጋው መጀመሪያ ለማን እንደሆነ ሳይታለም የተፈታ ጉዳይ ነው ፤ ጥያቄውን የተቀበለው አካል በመጀመሪያ ያስብበት ፤ እኛ ግን ሁለተኛ ተጎጂም መሆን ስለሌለብን የሚመለከቱንን ነገሮችን ብቻ አጽንኦት ሰጥተን ብንከታተላቸው መልካም ነው የሚል ሃሳብ አለን ፡፡ እኛ የሆነውንና የተደረገውን ለእናንተ ለአንባቢያን አድርሰናል ፤ ይህን ጥያቄ እርስዎ እንዴት ይመለከቱታል ? ሃሳብዎትን ያካፍሉን……
በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በዘር ፣ በቋንቋ ተጠራርቶ የሚመሰረት የፖለቲካ ፓርቲ ለሀገራችን አንዳች የሚያመጣው ሰላም አይኖርም፡
“ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም” …..
ቸር ሰንብቱ
ምን አይነት አካሔድ ነው እየሄዱ ያሉት? እነዚህ ሰዎች ለሃይማኖታቸው እንዴት እንደሚሆኑ እንዴት እንደሚሰሩ ደግሞም ኮኔክሽናቸው ከአረብ ጋር ሆነው ተቀናጅተው ለመስራት ሲነሱ ሳስብ ይገርመኛል:: እነዚህ ሰዎች እኮ የተሳሳተ መንገድ ቢሆኑም የሚዙት ጉዞ: ላመኑበት ነገር እስከሞት ድረስ መጓዛቸውም የሚያስደንቅ ነገር ነው:: መንግስት አለመቀበሉ መልካም ነው ቢሆንም እኛ ግን እውነተኛዋንና ርትዕት የሆነች ሃይማኖትን ይዘን አብረን ለመስራት አልቻልንም:: ከሃይማኖት ይልቅ ሆድ ገዛን:: ገዳማት ሲቃጠሉ: ገዳማት እንደ እርሻ ሲታረሱ: አብያተ ክርስቲያናት ሲፈርሱ: ንዋያተ ቅዱሳት ሲዘረፉ ይህ ሁሉ እየሆነ በፎቶ ብቻ ሳይሆን በቪዲዮም የተደገፈ ምስል እያየን አጃችን አጣጥፈን ዝም አልን መሪዎቻችንም ዝም አሉ ጭራሽ መንግስት ሃይማኖትን አልነካም እያሉ ይከራከሩ ጀመር:: እስኪ ልቦና ይስጠን አምላካችን እኛም ለሃይማኖታችን በአንድነት እንነሳ ሃይማኖታችንን እናስከብር:: ለወደፊቱ እነዚህ ሰዎች የጠየቁት ጥያቄ ቢፈቀድላቸው እኮ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን ለማጥፋት እንደሚነሱ አትጠራጠሩ::
እንንቃ በህብረት እንስራ ሃይማኖታችንን አናስከብር:: ለዚህም የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን አሜን::