Wednesday, 25 July 2012





የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የፓትርያርክነት ማዕርግ የተቀዳጀችበት የነጻነት በዓል - በዓለ ሢመተ ፓትርያርክ - አከባበር የመንፈሳዊ ውርደትና የምዝበራ መንገድ ኾኗል




(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 16/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 23/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሙስና፣ ብኵንነት፣ ኑፋቄ እና ዐምባገነናዊ አሠራር የነቀዘው የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና 20 ዓመት በዓለ ሢመት ዛሬ ምሽት ለሁለተኛ ጊዜ በሼራተን አዲስ ይከበራል። የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና ራእይ ለትውልድ /Vision for Generation/ የተባለው አካል የጥቅም ትስስር የፈጠሩበት የሼራተኑ በዓለ ሢመት ዝግጅት በቅ/ሲኖዶስ ጽ/ቤት ይኹን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት አይታወቅም።


የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የአብያተ እምነት መሪዎች፣ አምባሳደሮችና ታዋቂ ግለሰቦችን ጨምሮ እስከ 1500 እንግዶች ይታደሙበታል በተባለው ይኸው ዝግጅት ከጥቅም ትስስር ባሻገር÷ በግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ስብሰባ እና ውሳኔዎች ክፉኛ የተጋለጠውን የአባ ጳውሎስን ማንነት ለማደስ የታሰበበት ‹የሕዝብ ግንኙነት› ሥራ እንደኾነ ተጠቁሟል። በበዓለ ሢመቱ አከባበር የቀደሙት ፓትርያርኮች መልካም ስምና ዝና በተለያዩ ስልቶች እየተንኳሰሰ በምትኩ በሙስና፣ ኑፋቄ እና ዐምባገነናዊ አሠራር የተበሳበሰው የአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና የሥራ ክንውን ብቻ “በወደር የለሽነት” /በእንግሊዝኛው የበዓለ ሢመት ኅትመት ላይ እንደተገለጸው - ‘unparalleled efforts/ እንደ ግለሰብ መሞገሱ ብዙዎችን አሳዝኗል።


በበዓለ ሢመቱ ቀን “አንተ የተወገዝኽ ፓትርያርክ ነኽ፤ ሃይማኖት የለኽም!!” ሲሉ አባ ጳውሎስን በመናፍቅነት ያወገዙት ባሕታዊ÷ “ማን ነው የላከኽ?” በሚል ለሳምንት ታስረው ሲደበደቡ ከሰነበቱ አንድ ሳምንት በኋላ ተፈተዋል። በዓለ ሢመቱን በማክበር ሰበብ በሚልዮን የሚቆጠር የአብያተ ክርስቲያን ገንዘብ ወደ ግለሰቦች ኪስ ገብቷል፤ ከመንበረ መንግሥት ቅ/ገብርኤል ገዳም ብቻ ግማሽ ሚልዮን ብር ተወስዷል፤ ምእመናኑና ሙሰኛው የገዳሙ አስተዳዳሪ ከመጪው የሐምሌ 19 ክብረ በዓል ገቢ ጋራ በተያያዘ ፍጥጫ ላይ ናቸው።

በችግር ፈጣሪነታቸውና ሙሰኛነታቸው በሰበካ ጉባኤው እና ምእመናኑ የተከሰሱት የግቢ ገብርኤል ገዳም አስተዳዳሪ ጉዳይ በቋሚ ሲኖዶስ እንዳይታይ የተከላከሉት አባ ጳውሎስ÷ የአድባራትንና ገዳማትን አለቆችን፣ ጸሐፊዎችንና ቁጥጥሮችን መቀያየርን እንደ ኢንቨስትመንት እንደሚመለከቱት ተነግሯል። ከባሕር ማዶ እየመጡ የአድባራትና ገዳማት እልቅና ከሚሾሙ መነኰሳት ነን ባይ ‹ቆሞሳት› እስከ ብር 200,000 እና ከዚያም በላይ የሚቀበሉት አባ ጳውሎስ÷ ለቤተ መዘክርና የሁለ ገብ ሕንፃ አገልግሎት ዕብነ መሠረት ለማስቀመጥ ሳይቀር እስከ ብር 100,000፣ በግለሰቦች ጸሎተ ፍትሐት ላይ ለመገኘት እስከ ብር 80,000 እንደሚከፈላቸው ተጠቁሟል። ኦዲት የማያውቃቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ የልማት ተቋማት የአባ ጳውሎስ ሙሰኛ አስተዳደር መናኸርያዎች መሆናቸው ሲነገር ለፓትርያርኩ የግል የሕክምና ክትትል የሚውለው ሳምንታዊ የጤና መጠበቂያ ወጪ እስከ ብር 60,000 ደርሷል።


በተያያዘ ዜና የሐምሌው ልዩ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ አባ ጳውሎስ ማደርያቸውን ቆልፈው “አልሰበስብም” በማለት ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ጥሪ የእምቢታ መልስ በመስጠታቸው ሳይካሄድ ቀርቷል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ “የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይፍረድ!!” በማለት ሐዘናቸውን ገልጸው ወደ የሀ/ስብከታቸው ተመልሰዋል። የሐምሌውን ጉባኤ መሰረዝ ብቻ ሳሆን የግንቦቱ ቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙት አባቶች ጋራ ስለሚደረገው የዕርቀ ሰላም ንግግር ውሳኔ ያሳለፈበት ቃለ ጉባኤ መጥፋቱ ተገልጧል፤ በበዓለ ሢመታቸው ቀን “የምንተጋገዝ፣ የምንተማመን፣ ይቅር የምንባባል እንኹን” በማለት የተናገሩት አባ ጳውሎስ÷ ቃለ ጉባኤውን ኾነ ብለው በመሰወር እና ለዕርቀ ሰላም ንግግሩ መቀጠል ጽኑ አቋም የያዙትን አባቶች በመገዳደር ግብዝነታቸውን አሳይተዋል፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ወደ የሀ/ስብከታቸው ከመመለሳቸው በፊት ቋሚ ሲኖዶሱ ጉዳዩን በቅርበት እንዲከታተለው አደራ ሰጥተዋል።
ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን፡፡


17 comments:

Anonymous said...
yeleboche degese!!!
Anonymous said...
Ahun enaneten man yamenal abatchen sim maeft ayeee kifu limad new lemehonu man lkebelachehu new min endezhi akatlachehu Abatachen Egziabher amelak rejem edmena tena yestelen telat diyabilosafer dingayyibela dejeselamoch leenanetem asteway libona yesteachehu
Anonymous said...
ወደ ሀገረ ስብከታቸው ከሚመለሱ ለምን ገዳም አይሄዱም
asbet dngl said...
የኢትዩጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ ምእመን በሙሉ መልዕክት አለኝ::ፓትርያርካችን የፈለጉት ሲያደርጉ ቆይተዋል አሁንም በማድረግ ላይ መሆናቸውን እያየንና እየሰማን ነው::በአንጻሩ ደግሞ የድንግል ልጅ ጌታ ታላቅ ሥራ ይሰራል:: ከኛ የሜጠበቅብን ግን አለ እሱም ጾለት ነው::እባካችሁ ከየቤታችን በመሆን እጃችንን ወደ ጌታችን እናንሳ ላልሰማ እናሰማ :: አመት ያልሞላው መልስ ይመጣልናል::ፀሐይና ጨረቃ በአዲስ አጥቤያ ይታያሉ::ይህን ከማየት አስደናቄይ ነገር ምን አለ??
የኢትዩጵያ አምላክ ይጠብቀን:: አሜን!
Gofa Geberal said...
aye lemewarde mechekole, ande medhanialem ejune yanesa elete ende chew mamutewe lemekerute, mechem seweyewe eko kene gebere abrochu, amlake yelem baye honual. Yegermal ye patriarche kehade, egzere yelem baye menafke, mechem aba Paulos yemekeberubete afre erasu yetregeme newe bewnete. Metene lenefesachew.
Gofa Geberal said...
aye lemewarde mechekole, ande medhanialem ejune yanesa elete ende chew mamutewe lemekerute, mechem seweyewe eko kene gebere abrochu, amlake yelem baye honual. Yegermal ye patriarche kehade, egzere yelem baye menafke, mechem aba Paulos yemekeberubete afre erasu yetregeme newe bewnete. Metene lenefesachew.
Anonymous said...
yikirta ande tiyakie alegn "abune paulos Egziabeher endale yawekalu?"teyekulegn,,,lelaw ahunis abezut bilen ho bilen beandinet yeminikawemibet letefatachew dinber "key"mesemer ale weys be banik yalewen bir cheresew betekirestiyanun bekumu shetew "churchless"eskiyaderigun tigistun yabizalin kifu kemenager yitebiken eyalin metegnat new yemiyawataw?????
Anonymous said...
I DON'T HAVE WORDS FOR ALL OF THIS CRIME I JUST WANT TO SAY THE TIME IS NEAR!!! THE GOD TIME IS NOT FAR JUST NEAR !!!. HE WILL PAY FOR EVERY ONE . DON'T WORY ABOUT MONEY JUST WORY ABOUT THE CHURCH . THE GOD OF OUR HOLY FATHERS SAVE OUR CHURCH IN OUR GENERATION.AMEN
Anonymous said...
ጌታ ሆይ ፍረድልን፡፡በእውነት ፍረድልን ፡፡፡፡፡፡፡፡፡ሰውየው አበዱ እኔ የፈራሁት አንድ ቀን በኢትዮጲያ ቲቪ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ካቶሊክን ተቀበለች ብለው እንዳያውጁ ነው፡፡በዚህ ዝምታችን ይሄ ቀን እሩቅ ላይሆን ይችላል፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
Anonymous said...
yalegebagne lemendenewe be email melake yaqomachehute?? ere ebakachehu jemeru because a number of people don't have access to ur web
Anonymous said...
Thank you very much Dejeselam for your reliable information. I hope soon later our God will remove this the so called Patriarch DIABILOS/POUL ES. please all orthodox christian try to exposed all the debir church leaders who have strong connection to this Diabilose Patriarch. if we believe the truth we don't have to hesitate to reveal the truth. God Bless you Dejeselam.
tersitewold said...
ante be ANONYMOUS yegebahew ወደ ሀገረ ስብከታቸው ከሚመለሱ ለምን ገዳም አይሄዱም

BELEH YEMETELEW MENGACHEWEN LEMAN TETEW NEW WEDEGEDAM YEMIHEDUT
BETASTEWEL: halafinet kelal aydelem endene ena endante aydelem yemiwesenew

tersiteweld negn kegermen
galela said...
edema laneseha nawe
masetawwale yesetote
Anonymous said...
Ewnet timeneminalech engi atibetesim yetesededut ewnetenga abatoch amlak gena bizu yadergal, semayawiw ketebedelut gon ayley Amen!
Anonymous said...
dear all..... Egziabher hulachin yitebk........ Yekedemewun ye abatochachenen zemen yamtaln.......amen
Anonymous said...
ኘሮቴስታንቱ/ራእይ ለትውልድ /Vision for Generation/... ምን አስጨንቆት ይሆን ለማያምንባት ቅድስት ቤተክርስቲያናችን የበላይ ጠባቂ የ2ዐ ዓመት በዓል አስመልክቶ በሸራተን አዲስ ወገቡን አጥብቆ ሽር ጉድ ሲል ያመሸው...ነው ወይስ... ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት እንዳሉት... ዓላማውን ለማሳካት መንገድ እየጠረገ??? ...

አባ ጳውሎስ ቤተክርስቲያንን የመናፍቅ ሊያደርጉ ደፋቀና አያሉ ነው
Anonymous said...
የበሰበሰ ዝናም አይፈራም አለ ያገሬ ሰው:: ለነገሩ አትፍረዱባቸው ከመቃብር በላይ የሚነበበውን ታሪካቸውን አስቀድመው ያውቁታልና ነው ይህ ሁሉ ድካም:: ምንም የሚነበብደህና ታሪክ እንደሌላቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ:: የሚጻፍላቸው ማባጣበጣቸው፣ ከሳቸው ጋ ማዕድ ተቀምጠው የነበሩ አባቶች የበላን አልተስማማንም ብለው መሞታቸው፣ ለመናፍቃኑ ጋሻ ጠበቃ መሆናቸው፣ ቤተ ክርስቲያንን የጋለሞታ መጫወቻ ማድረጋቸው፣ኧረ ስንቱ ተዘርዝሮ ያውቃል:: ታዲያ ሳይሞቱ ሳይሰሩ የሰሩ ቢመስላቸው፣ ያለ ተጋድሎ ሀውልት ቢቆምላቸው፣ ያለስራቸው እንደጻድቅ ቢቆጠርላቸው ምናለበት:: ድሃ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ እንደተባለው አይነት እኮ መሆኑ ነው:: ልጆች የቆባ ቅርፊት እያዘጋጁ እንደሚታኮሱት አይነት የእቃ እቃ ጨዋታ አይነት መሆኑ አይነት እኮ ነው በሽማግሌ ሲሆን ግን አይመጥንም ከልጆች ጨዋታ እንኳ ይወርዳል:: እዚህ አገር ፔን ስቴት ከበራቸው ያለውን የታዋቂውን የኮ ሌጃቸውን አሰልጣኝ ሃውልት ምን እንደተወሰነበት አልሰማችሁም:: የሳቸውም ሀውልት በሞቱ በሳልስቱ ይነቀልና ለልዋጭ ልዋጭ ይጣላል:: ታሪካቸውም ክህደታቸውን ዘራፊነታቸውን ደልቃቃነታቸውን ዘማዊነታቸውን ኧረ ስንቱን አሳፋሪ ስራዎቻቸውን ይዘክራል:: ማፈሪያ ናቸው ቢባል አይሻልም:: በቀረቻቸው ጥቂት ቀናት እርሱ ለንስሃ ያብቃቸው::

No comments:

Post a Comment