Thursday, 5 July 2012


"የዋልድባን ልማት በግድም በውድም መቀበል ይኖርባችኋል" መንግስታችን


  • "እርሶ እኛን አይወክሉንም እና ልንሰማዎትም ሆነ ቡራኬዎትን አንቀበልም" ከመነኩሳት ወገን      ለብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
  • "በዋልድባ ገዳም ምንም ድርድር አናደርግምየአካባቢው ነዋሪ
  • በርካታ ወጣቶችም በመንግሥት ታጣቂዎች ታፍሰው ተወስደዋል
ባለፈው ቅዳሜ በዓዲርቃይ ከተማ ላይ በዋልድባ አካባቢ ሊሰራ በታቀደው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ ዙሪያ የአካቢው ነዋሪዎችን፣ የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤልሳዕ በተገኙበት፣ የመንግሥት ተወካዮች፣ የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች በተገኙበት እንዲሁም ከቤተክህነት ተወካዮች በተገኙበት የማስፈራራቱ እና በግድ የማሳመኑ ስራ እንደቀጠለ ነው። ሰሞኑን በደረሱን መረጃ መሰረት መንግስት ለልማቱ እፈልጋቸዋለው ከሚላቸው የዋልድባ ገዳም ክልል ውስጥ የሚፈርሱን መካናት የሚከተሉት ናቸው፡

  • ከአበረንታት
    • ማርገፅ ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን
    • ድል ሰቆቃ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
    • እጣኑ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም  ቤተክርስቲያን
    • ሙሉ ቤት ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን
  • ከአባ ነፃ
    • ዲዋር ግዛ ቅዱስ ተክለሃይማኖት  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ሸረፋ አቡነ አረጋዊ  ቤተክርስቲያን
    • አዲ ፈረጅ አብዮ እግዚ  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቤተክርስቲያን
    • ታች እጣኖ ቅዱስተ ማርያም  ቤተክርስቲያን
    • ላይ ኩርማ አቡነ አረጋዊ  ቤተክርስቲያን
    • ጎድጓድ ቅዱስ ጊዮርጊስ  ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ አቡነ ሳሙኤል  ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን
    • ቃሊማ ቅድስት ሥላሴ  ቤተክርስቲያን
    • ማይ ዓርቃይ ቅዱስ ሚካኤል  ቤተክርስቲያን እና ሌሎችም ስማቸው ያልተገለጸ አብያተ ክርስቲያናት እንደሚነሱ ዘገባው ደርሶናል።
ለዚህም ነው የገዳሙ መነኩሳት ይልቁንም በሰቋር ኪዳነ ምሕረት የሚገኙት መነኩሳይት (አነስትታላቅ ተጋድሎ እያደረጉ የሚገኙት፡፡ እንደ መነኩሳይቱ አነጋገር “በመጀመሪያ እኛን ገድላችሁ መሬቱን ማረስ ትችላላችሁ አለበለዚያ ግን እኛ በሕይወት ቆመን ቅዱሳን አባቶቻችን በደማቸው እና በአጥንታቸው ያስከበሩት ገዳም በኛ በልጆቻቸው በአረማውያን ሊወሰድ አይችልም” በማለት በታላቅ ተጋድሎ ላይ ይገኛሉ።  ". . .የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ. . ." መጽሐፈ ነገስት ቀዳማዊ ፳ ፥ ፫ የናቡቴ ቃል ዛሬም በእነዚህ መነኩሳይት አድሮ ለእያንዳንዱ ኦርቶዶክሳዊ ያስተጋባል የአባቶቻችን ርስት እንሰጥ ዘንድ ከእኛ ያርቅ በማለት።

እንደመረጃ ምንጫችን ከሆነ በስብሰባው ዕለት የሃገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በቦታው ተገኝተው ቡራኬ ለማድረግ ሲነሱ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል "እርሶ እኛን አይወክሉንም" በማለት ተሰብሰባዊ ገዳማውያኑ፣ የአካባቢው ነዋሪዎችን ጨምሮ በከፍተኛ ደረጃ በቦታቸው ያልተገኙትን አረጋዊ ሊቀ ጳጳስ ኮንነዋቸዋል፣ በተያያዘ ዜና በስብሰባው እለት የቤተክህነቱም ተወካዮች በቦታው ተገኝተው ገዳማውያኑን እና የአካባቢውን ነዋሪ ለማሳመን ከፍተኛ ጥረት ተደርጎ እንደነበር እና በመጨረሻ የመንግሥት ተወካዮች ቦታው እንደውም "የአማራ ክልል አይደለም" ይህንን በቀጥታ የሚመለከተው "የክልል ትግራይ" ነዋሪ ነው በማለት የስብሰባውን መንፈስ ወደ ዘር እና ጎሳ ሲለውጡት ተመልክተዋል። እነዚሁ የመንግሥት ተወካዮችም በግድም ይሁን በውድ ልማቱን መቀበል አለባችሁ የሃገራችን የሥራ አጥ ቁጥሩን በ50000 ይቀንሳል  በማለት ዲስኩራቸውን መስማት ለሰለቸው ተሰብሳቢ ሲያሰሙ ውለዋል።

በመጨረሻ በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ ተሰብሳቢው የማኅበረ መነኩሳቱ ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች “ከዚህ በኃላ ስብሰባ አትጥሩን አቋማችን የታወቀ እና አንድ ነው የአባቶቻችንን ርስት አትንኩብን፣ አጽመ ቅዱሳኑን አታፍልሱ፣ ካልጠፋ መሬት ለምን ወደ ገዳማን መጣችሁብን፣ እኛ ጉልበታችን መድኅኒዓለም ነው ያሻችሁን ማድረግ ትችላላችሁ መሬቱንም ስታርሱ እኛንም ገድላችሁ መሆን አለበት” በማለት ከፍተኛ የሆነ ሁካታ ተነስቶ በስብሰባው ከተሳተፉትም አንሰበሰብም በማለት በውጭ ቁጭ ብለው ከነበሩ በተለይ ወጣቶችን የመንግሥት ታጣቂዎች በርካታዎችን ጭነው ለእስር ዳርገዋቸዋል በርካቶችም ሸሸተው ወደ ጫካ እንደገቡ ከአካባቢው ምንጮቻችን ገልጸውልናል። ማኅበረ መነኩሳቱም ምሬት በተሞላበት መልኩ ነዋሪዎችን "መጥታችሁ ቅርሶቻችሁን ተረከቡን" ሲሉ መሰማታቸውንም እነዚሁ ምንጮቻችን ገልጸውናል።

መንግሥትም በማናለብኝነት አብያተ ክርስቲያኑን እንደሚያፈርስ ሲገልጽ፣ የቤተክህነቱም ተወካዮች ተባባሪ ሆነው ለአብያተ ክርስቲያኑ መፍረስ አይነተኛ ተሳትፎ ሲያደርጉ በሌላ በኩል የዋልድባ ገዳም ማኅበረ መነኩሳቱ፣ የአካባቢዊ ነዋሪ በተለይ ደባቅ፣ ዛሬማ፣ ዓዲርቃይ፣ እና አካባቢው ላይ ያሉ የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች ከመንግሥት ኃይሎች ጋር ከፍተኛ የሆነ መስዋዕትነት እየከፈሉ በሚገኙበት በዚህ ሰዓት እኛ እንደክርስቲያን አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል። በማንኛውም በጸሎትም  በገንዘብም በማንኛውም መንገድ ልንተባበራቸው እና ቅዱሱን ገዳማችንን የሊቃውንት መፍለቂያ እንዲሁም የበረካታ ዓይናማ መምህራንና የቤተክርስቲያን ሊቃውንት መገኛ የሆነውን ገዳም ልንታደግ ይገባል እንላለን። 

እግዚአብሔር ቤተክርስትያን ይጠብቅ
ከSave Waldba የተወሰደ

5 comments:

  1. ገዳማውያኑን አባቶች እግዚአብሔር ያታደጋቸው! ቤተ ክርስቲያናችን በአጠቃላይ መሪ የላት መሪዋ መድኃኔዓለም ነው የእሱ ሰራዊተ መላእክት አሉ እውነት ልንገራችሁ! አባ ጳውሎስና ግብረ በላዎቹ ቤተ ክርስቲያንችን ምንም አልቀረም እያጠፏት ነው ሐብቷን ንብረቷን እየዘረፉ እያዘረፉ ናቸው የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይፍረድባቸው! መለስ ዜናዊን ጀነራል ውንጌት አብረን ነው የተማርነው በጣም ክፉ አረመኔ እግዚአብሔርን የማያውቅ እግዚአብሔርን የሚሳደብ ነው ዓይነ ስውራንን እንዴት እንደሚያገላታ ጠቅላላ ተማሪዎችና አስተማሪዎችን የሚያዝኑበት ሰው ነው ከዲያብሎስ ጋር በእድሜ ነው እንጂ የሚበላለጡት ተግባራቸው አንድ ናቸው መለስ ሳይበልጥ አይቀርም እሱ ኢትዮጵያዊ ስላልሆነ ለኢትዮጵያውያን ግድ የለውም ጨካኝ ሰው ነው ወደ ልቡ ቢመለስና አማኝ ቢሆን መልካም ነው ወደ ፊት ብዙ የምለው ነገር አለኝ በመለስ እምነት ዙርያ በቅርብ ጓደኛዬ ስለነበር ምን እንደሚል አወራለሁ የኢትዮጵያ አምላክ ይፍረድበት ታያላችሁ በቅርብ ቀን እግዚአብሔር በቤተ መንግሥትም በቤተ ክህነትም ፍርድ ያመታል ... ይቀጥላል
    Reply
    Replies
    1. Please let us know about him(Meles) in this blog. We don't know our leader help us by writing something in this blog. Thanks.
  2. ተዉ ገዳማቱን መዳፈር ይቅርባችሁ
    በነሱ ፀሎት ነውና እዚህ መድሳችሁ
    እባካችሁ ገዳማቱን መዳፈር ይቅርባችሁ
    ሰለፊያ ስትሉን በአደባባይ ዝም አልናችሁ
    ለአምላካችን እርሱ ይየው አልናችሁ
    እርሱም የበቀል አምላክ ነውና መለሰው በአደባባይ
    ያውም አድርጎ ለዓለም እንዲታይ
    አሁን ተዉን አትንኩ ገዳማችንን ዋልድባን
    አትንኩብን አባቶቻችንን ቅዱሳን
    ለእኛም ለእናንተም ብሎም ለዓለም የሚፀልዩትን
    በረከታቸው ለሁላችን የሚደርስልንን
    እባካችሁ ዋልድባ እንኩዋን ፖለቲካ አይነገርበትም ወሬ
    መናኞቹ የሚኖሩ ናቸውና በመንፈስ ፍሬ
    አሁንም እንላለን አትንኩብን ገዳማችንን
    ለመኖራችሁ ምንም የላችሁም ተገን
    መጨረሻችሁ ይሆናል ማዘን
    ሳትባሉ ማኔ ቴቄል ፋሬስ
    የእውነት አምላክ በልባችሁ ይንገስ!!!
    Reply
  3. benatiwo tolo tsafu selzihe nfese bela aremene sewe yeaba paulose buchila, Egziabhere be Abebe Gelawe awredotale gena yeketililetale ayekerlete ke amilakachine eyemetabete endehone alaweke
    Reply
  4. ተዉ ገዳማቱን መዳፈር ይቅርባችሁ
    በነሱ ፀሎት ነውና እዚህ መድረሳችሁ
    እባካችሁ ገዳማቱን መዳፈር ይቅርባችሁ
    ሰለፊያ ስትሉን በአደባባይ ዝም አልናችሁ
    ለአምላካችን እርሱ ይየው አልናችሁ
    እርሱም የበቀል አምላክ ነውና መለሰው በአደባባይ
    ያውም አድርጎ ለዓለም እንዲታይ
    አሁን ተዉን አትንኩ ገዳማችንን ዋልድባን
    አትንኩብን አባቶቻችንን ቅዱሳን
    ለእኛም ለእናንተም ብሎም ለዓለም የሚፀልዩትን
    በረከታቸው ለሁላችን የሚደርስልንን
    እባካችሁ ዋልድባ እንኩዋን ፖለቲካ አይነገርበትም ወሬ
    መናኞቹ የሚኖሩ ናቸውና በመንፈስ ፍሬ
    አሁንም እንላለን አትንኩብን ገዳማችንን
    ለመኖራችሁ ምንም የላችሁም ተገን
    መጨረሻችሁ ይሆናል ማዘን
    ሳትባሉ ማኔ ቴቄል ፋሬስ
    የእውነት አምላክ በልባችሁ ይንገስ!!!

‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› የኢቲቪ ፊልም አንድምታው


 (አንድ አድርገን ሰኔ 25 ፤2004 ዓ.ም)፡-ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ ስለ አክራሪነት ሰፊ ማብራሪያ ከሰጡ ወዲያ መንግስት የሚያደርገው እንቅስቃሴ ከቀን ቀን እየጨመረ እየመጣ ነው ፤ መንግስት በአዲስ ራዕይ መጽሄት አማካኝነት ሀሳቡን በደንብ አድርጎ ገልጾልናል ፤  ይህን ሀሳብ በህዝቡ ዘንድ ለማስረጽ ይረዳው ዘንድ ዛሬ ሰኞ ማታ ከ2፡00 ሰዓት ዜና በኋላ ‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› የሚል ዶክመንተሪ ፊልም በኢቲቪ እንደሚለቀቅ ሰሞኑን የተመለከትናቸው ማስታወቂያዎች ይናገራሉ ፤ ይህ ወቅታዊውን ነገር መሰረት ተደርጎ የተዘጋጀ ቢሆንም አሁንም እዚህ ደረጃ የሚያደርስ ነገር በክርስትያኑ እና በሙስሊም አማኞች አማካኝነት ተፈጥሯል ብለን አናምንም ፤ ይህን ሁኔታ እዚህ ደረጃ ያደረሰው መንግስት ራሱ ነው ፤ ሙስሊም ወንድሞቻችን “መጅሊስ ይውረድ” ብለው ጥያቄ በመጠየቅ ይህን ጥያቄ ጫፍ የሚያደርስ ኮሚቴ አቋቁመው ለጥያቄያቸው ተገቢ መልስ መንግስት መስጠት ሲሳነው ነገሩን ወደ አክራሪነት በማዞር ከወቅታዊ ነገር ጋር ተገቢ ያልሆነ ትንታኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት አቀረቡ ፤ በዚህ ወቅት 90 በመቶ ንግግራቸው ወሀቢያና  ሰለፊያ ሲሆኑ አንድ ቦታ ላይ ብቻ ተገቢ ያልሆነ አብሮ ሊሄድ የማይችል ምሳሌ በመስጠት የንግግራቸው ማጣፈጫ አድርገው ተጠቀሙብን ፤ ከዚያ የጠቅላይ ሚንስትሩን ንግግር  የሚቃወሙ ድምጾች ከየቦታው መሰማት ጀመሩ ፤ “የአቶ መለስን አቋም እቃወማለሁ” በማለት ሰዎች ውስጣቸውን ተነፈሱ ፤
በዚህ ጊዜ መንግስት ነገሩን ለማክረር እና የዘመናት አላማውን ለማሳካት ይመቸው ዘንድ ሌሎች ያልተፃፉ ነገሮችን እየመዘዘ ማውጣት ተያያዘው “አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት” ፤ በበዓላት ወቅት መንገዶች ላይ የሚጻፉ ጥቅሶች ፤ ህገ መንግስቱን የሚጋፋ የወጣቶችን እንቅስቃሴ በማለት እና ሌሎችን አላማውን የሚሸፍኑለትን አጀንዳዎች በማጠየም አነሳቸው ፤ ጉዳዩን ወደ ሌላ ምዕራፍ እንዲሻገር የሚፈልገውና ጠንክሮ የሚሰራው መንግስት ባሳለፍነው ወር ላይ “አዲስ ራዕይ” መጽሄት ላይ ከለፍተኛ አባሎቹ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ በጣም በማጋነን አላማውን ያሳካ ዘንድ ከ40 ገጽ በላይ የሚጠጋ ጽሁፍ የሃይማትን ክብር በሚያጎድፍ መልኩ በመጻፍ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጽሁፉን አደረሰ ፤ የድርጅት አባሎቻቸውም በዚህ ጉዳይ ላይ ጊዜ ወስደው መከሩበት አሁንም እየመከሩበት ይገኛሉ ፤ ባለን መረጃ መሰረት አክራሪነትን በተመለከተ መጽሄቷ ላይ የሰፈረውን ጽሁፍ በመገምገም እና የኢህአዴግ አባላት አቋም ለማስያዝ ብዙ ቦታዎች ላይ መወያየታቸው መረጃዎች ደርሰውናል ፤


እስኪ እኛን አክራሪ ለማለት የሚያበቃ  ወይም ከአክራሪዎች ጋር ደምሮ ለማሰብ የሚያስችል ፤ ይህን ፊልም ለማዘጋጀት የሚያደርስ በቂ ምክንያት መንግስት ይኖረዋል ብለው ያምናሉ ? ባሳለፍነው የጥምቀት በዓል ላይ “አንድ ሀገር አንድ ሃይማኖት” የሚል ጽሁፍ በስህተትና ካለማወቅ ሰዎች ቢለብሱ እንኳን(መልበሳቸውን ማስረጃ የለንም) ከሃይማኖት አባቶችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ቀረብ ብሎ በመነጋገር ጽሁፉ ህገ መንግስቱንና የሌሎችን የእምነት ነጻነት ይጋፋል ፤ ስለዚህ ለወደፊት ይህን አታድርጉ ማለት አይቻልምን ? ለዚህ ፊልም መዘጋጀት መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ይህን የመሰለ አቋም የያዘበት ምክንያት ይህ ከመሰሎት ተሳስተዋል ፤ በ1984 ዓ.ም በራሳቸው አባል የተጻፈ መጽሀፍ ላይ እንደሰፈረው ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ላይ የማፈራረስ አላማ እንዳላቸው ጠቅሶ በግልጽ ፅፎልናል ፤ ይች ቤተክርስትያን የአንድነት ጉዞዋ ለእነርሱ እንቅፋት ነው ብለው ያስባሉ ፤ ስለዚህ ይህን የቤተክርስትያን የአንድነት ጉዞን ከቻሉ ለመቁረጥ ካልሆነ ደግሞ ለማላላት ዘወትር ተግተው ይሰራሉ ፤ ባሳለፍናቸው 21 ዓመታት ውስጥ በታምራት ላይኔ አማካኝነት ቤተክርስትያኒቱ የኢትዮጵያ ሲኖዶስ እና ስደተኛው ሲኖዶስ ተብላ እንድትጠራ ሁለት እንድትሆን የራሳቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል ፤ ተሳክቶላቸዋልም ፤ “ኢህአዴግ እያለሁ ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ውጪ መንገድ ያለ አይመስለኝም ነበር” ብለው በቅርቡ ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የበፊት የትግራይ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ገብሩ አስራት ነበሩ ፤ አሳቸው ከድርጅት ተባረው ሌላ መንገድ መኖሩን ተመለከቱ ፤ አሁንም ግን የትግል አጋሮቻቸው ሌላ መንገድ አለ ብለው ለአፍታ አስበው አያውቁም ፤ 


ከዚህ በተጨማሪ ከ97 ወዲህ ሰዎች ለማህበራዊ ፤ ለፖለቲካዊ እና ለሃይማኖታዊ ጉዳዮች ማህበር መስርተው ሲንቀሳቀሱ መመልከት ለኢህአዴጋውያን የራስ ህመም ሳይሆን የራስ እጢ ይፈጥርባቸዋል ፤ ስለዚህ በሆነው ባልሆነም ምክንያት እነዚህን ማህበራት ስማቸው ከመቃብር በታች ለማድረግ ዘወትር ያለመሰልቸት ይተጋሉ፡ ስለዚህ አሁን እየሰሩ ያሉት ነገር ይህን ነው ፤  ዛሬ የምታዩት የኢቲቪ ፊልም የነገ ህልማቸውን ለማሳካት የሚራመዱት የመጀመሪያ እርምጃ አድርገው ይውሰዱት ፤ ለዚህ ጽሁፋችን ማስረጃችንን ከቀናት በኋላ ብሎጋችን ላይ ይጠብቁ ፤(ጦላይ ማሰልጠኛ ውስጥ በአክራሪነት ላይ ለአባላት ምን አይነት ስልጠና  እየሰጡ እንደሆነ እንነግሮታለን)


በአሁኑ ወቅት ‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› የሚል ፊልም የሚያዘጋጁበት ምክንያት “አዲስ ራዕይ” ላይ በተቀመጠው ሃሳብ ይመስለናል ፤ “አዲስ ራዕይ” መጽሄት ገጽ 37 ላይ እንዲህ ይላል “ጅምላ ፍረጃ ማስወገዳችን አንድ ነገር ሆኖ በየደረጃው የሰከነ ውይይት እንዲካሄድ ማድረግ ይገባል፡፡ በሚዲያ የተጀመረው ውይይትም ህዝቡ በአጠቃላይ ስዕሉንና በዝርዝር ክስተቶች መካከል ያለውን ልዩነት እንዲዘነዘብ ማድረግ ያስፈልጋል ፤ ለዘብተኛ አቋም ያላቸው ጽንፈኞቹም የሚዲያ አክሰስ አግኝተው ሀሳባቸውን ቢገልጹ ህዝቡ ተጨማሪ መረጃ ያገኛል፡፡ የተሻለ ግልጽነት ያላቸው የእምነቱ ተከታዮች በተለያዩ አማራጮች ሰፊው ህዝብ እውነታው ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲይዝ ማድረግ አለባቸው፡፡ ከወሃቢያ ይሁን ከማህበረ ቅዱሳን ወይም ከሌላው እምነት ውስጥ ጽንፈኝነት አይመለከተኝም የሚል በግላጭ ወጥቶ እንዲያወግዝ እድል ሊኖረው ይገባል ፡፡ በዚህ አግባብም ልናደፋፍረው እና ጽንፈኛው ተነጥሎ እንዲጋለጥ የሚያደርግ አካሄድ ሊኖረን ይገባል፡፡” በማለት ያስቀምጣል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይህ ወቅታዊ መሳይ ፊልም የተዘጋጀው ይህን መሰረት በማድረግ ነው ፤ እንደ መንግስት ሀሳብ ህዝቡ ዘንድ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖር በማሰብ ይህን ፊልም አዘጋጅቷል ፤ ህዝቡ ግን ከዚህ በፊት የተሰሩትን “አኬልዳማን” እና መሰል የኢቲቪ ዶክመንተሪዎችን በግልጽ ስለሚያውቃቸው ይህን አይቶ እንደ እውነት ይቀበለዋ ማለት የቀን ቅዥት ነው ፤ 


በአኬልዳማ ዶክመንተሪ ፊልም ተከሳሾችን አሸባሪ ለማለት በ1984 ዓ.ም በወለጋ አካባቢ እና ሀረር በደኖ አካባቢ በንጹሀን ላይ የተፈጸመን የግፍ ግድያ በ2004 ዓ.ም ለ”አኬልዳማ” ዶክመንተሪ ፊልም እንደ ግብአት በመጠቀም ተከሳሾቹን “ይህን ሲሰሩ ነበር” ብሎ ያቀረበው  የወረደ ስራ ህዝቡ ጠንቅቆ ያውቀዋል ፤ በጣም አሳፋሪው ነገር በአሁኑ ሰዓት በህይወት የሌሉ ሰዎች ምስል በአኬልዳማ ፊልም ላይ መካተቱ እና እንደ ማስረጃ በመጠቀም የተሰራው ስራ ከሙያው ስነ ምግባር ውጪ ከመሆኑም በተጨማሪ ኢቲቪ ያለፍቃድ የሞቱትን ሰዎች ምስል በማውጣቱ ቤተሰቦቻቸውን ይቅርታ መጠየቅ ይገባዋል ፡፡


ድሮ ድሮ ህዝባችን የዋህ ከመሆኑ የተነሳ ነገሮችን ፊልም ሰርቶ ለማሳመን ቀላል ነበር ፤ ህዝባችን እኮ “ሰው ለሰው” ድራማን አይቶ ተዋናዩ ደራሲው በሰጠው ገጸ-ባህሪ አማካኝነት ተዋናዩን የሚጠላ ነው ፤ አሁን ግን “ኢቲቪን ማመን ዘግቶ ነው” የሚባል አባባል ውስጥ ውስጡን ማንሸራሸር ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል ፤ የኢቲቪ ዋናው ችግሩ ለማን እንደሚያዘጋጅ አለማወቁ ነው ፤ እነሱ የሚያወሩልን ኢትዮጵያ እና እኛ የምናውቃት ኢትዮጵያ እየተራራቁብን ተቸግረናል ፤ህዝቡ የሚያውቀው አክራሪነት እና እነሱ የሚያወሩት አክራሪነት አራንባ እና ቆቦ እየሆነብን ነው ፤ ህዝቡ ቀድሞት 21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ገብቷል ኢቲቪ ግን በ20ኛው ክፍለ ዘመን የተደረገን ነገር ከአሁኑ ጊዜ ጋር በማነጻጸር መልሶ መላልሶ እያቀረበልን ይገኛል ፤ እኛ አይናችን እንመን ወይንስ ኢቲቪን እንመን? በአይናችን ያየነውን እና የምንኖርበትን ኑሮ ኢቲቪ እንዴት እንደሚያቀርበው ለናንተ መናገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆንብናል ፤ 


ለመጀመሪያ ጊዜ የክርስትያን አክራሪዎችን አላማ ዛሬ በቴሌቪዥን ለማየት ተዘጋጅተናል ፤ ይህ ፊልም ላይ ፓስተር ዳዊትን ስናየው ተገርመናል ፤ ይህ ሰው እኮ በ1988 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ያማልዳሉ ብላ የምታምናቸውን ጻድቃን ሰማዕታትንና ቅዱሳን መላእክትን በአዳራሾቻቸው አፉን ከፍቶ የተሳደበ ሰው ነው ፤ ፓስተር ዳዊትን አስተያየት እንዲሰጥ መደረጉ ራሱ አስገራሚ ነገር ነው ፤ መጀመሪያ በጊዜው የተሳደበው ስድብን ይቅርታ አስብሉት ከዚያ ድንገት ሲናገር ሰሚ ሊያገኝ ይችላል፡፡ ስለዚህ ዛሬ ላይ የሚተላለፈው ፊልም ተመልከቱ እና የራስዎን አስተያየት ይጻፉልን … ባለን መረጃ መሰረት እኛ ይህን ብለናል …ተመልክተን ስናበቃ ደግሞ ሚዛን ላይ እናስቀምጠዋለን …… 


“እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን” ብለን ውስጣችንን ፍርሃትን አናለማምደውም ፤


የነገ ሰው ይበለን…..

  



17 comments:

  1. ኢትዮጵያ ሀገራችን የሙስሊሙም፣የክርስቲያኑም እና ሀይማኖት ለሌለውም እናት ሀገራችን ናት ማንም ሊሰጠን ወይንም ሊወስድብን አይችልም፡፡ ባለማስተዋል ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት ሲባል ሀገሪቱ የክርስቲያን ብቻ ሀገር ብለው ኢትዮጵያ ሀገራችን የሙስሊሙም፣የክርስቲያኑም እና ሀይማኖት ለሌለውም እናት ሀገራችን ናት ማንም ሊሰጠን ወይንም ሊወስድብን አይችልም፡፡ ባለማስተዋል ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ናት ሲባል ሀገሪቱ የክርስቲያን ብቻ ሀገር ብለው የሚተረጉሙ ሰውን እያሳሳቱ ነው፡፡ የክርስቲያን ደሴት የተባለችው የኢትዮጵያ አጎራባች ሀገሮች ሱዳን፣ግብፅ፣የመን፣ሶማሊያ፣ጅቡቲ በአብዛኛው የሙስሊም ሀይማኖት ተከታይ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ግን በብዛት የክርስትና ሀይማኖት ተከታይ ህዝብ መኖሪያ (>60%) ስለሆነች የክርስቲያን ደሴት ተባለች እንጅ ሌሎች ሀይማኖቶች የሉም ወይንም እውቅና አለመስጠት አይደለም፡፡
    ሀገራችን ክርስትናንም (34ዓ.ም) እስልምናንም (6ኛው መቶ ከ/ዘ) ከአለም ህዝብ ቀድማ የተቀበለች ሀገር ነች፡፡ ክርስትናን ሀይማኖት ከእስራኤል ፣ እስልምና ሀይማኖት ከአረቡ አለም ይምጣ እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለቱም ሀይማኖት ከመምጣቱ በፊት ነበረ፣ ሀይማኖቱን ከመቀበሉ በፊትም በጋራ የኖረ ነው ከተቀበለ በኻላም አብሮ የኖረ ህዝብ ነው ወደፊትም በጋራ ይኖራል፡፡ እስልምና እና ክርስትና ሀይማኖት ኢትዮጵያ ውስጥ አልተፈጠሩም ስለዚህ ሁለቱም ሀይማኖቶች መጤ ናቸው፡፡ ዋናው ቁም ነገር አትዮጵያዊ ለመባል መስፈርቱ ሀይማኖት ሳይሆን በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ወይንም ከኢትዮጵያን እናት/አባት መወለድ ስለሆነ ሀገራችን ለየትኛውም እምነት ተከታይ ሀገር ናት ማንም ሊሰጠን/ ሊወስድብን አይችልም መብትም የለውም፡፡
    በሀገራችን ታሪክ በሁሉም ሀይማኖት ዘንድ ጥሩ ሀይማኖተኛ ሰዎች እንደነበሩ ኣሁንም እንዳሉ ቢታወቅም ኣንዳንድ በማወቅም ባለመወቅም ስህተት የሰሩ ኣሁንም የሚሰሩ ይኖራሉ፡፡ በነዚህ በተሰሳቱ ሰዎች እይታ ሀይማኖቱንም የምንፈርጅ ከሆንን ትልቅ ስህተት እየሰራን እንደሆነ መገንዘብ ኣለብን፡፡ ከዚህ ይልቅ የሚጠቅመው ለሀገራችንም ሆነ ለሀይማኖታችን ጥሩ እናስባለን የምንል ሰዎች በመቀራረብ እና በመወያየት የተሰሳቱትን ማስተካከል ነው እንጅ በመወነጃጀል ለራሳችንም ለሀይማኖታችንም ለሀገራችንም ጥሩ ነገር ልናተርፍ አንችልም፡፡ የተሻለው ነገር ሁሉም ሀይማኖቱን በነጻነት እና በእኩልነት ያከብር ዘንድ በጋራ መስራት እና መተባበር ሁሉንም ይጠቅማል፡፡ እናት ሀገራችንንም አያቶቻችን በጋራ ጠብቀው እንዳስረከቡን እኛም ለልጆቻችን የበለፀገች እና አንድነቱአ እንደተጠበቀ ለማውረስ እና በታሪክም ተጠያቂ እንዳንሆን ድርሻችንን እንወጣ፡፡”የእሳት ልጅ አመድ ከመሆን እግዚአብሔር ይሰውረን፡፡”
    “ሀገራችን የጋራ ሀይማኖታችን የግላችን ናት”፡፡
    ፍቅር ያሸንፋል
    እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ
    አብዲሳ
    የሚተረጉሙ ሰውን እያሳሳቱ ነው፡፡ የክርስቲያን ደሴት የተባለችው የኢትዮጵያ አጎራባች ሀገሮች ሱዳን፣ግብፅ፣የመን፣ሶማሊያ፣ጅቡቲ በአብዛኛው የሙስሊም ሀይማኖት ተከታይ ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያ ግን በብዛት የክርስትና ሀይማኖት ተከታይ ህዝብ መኖሪያ (>60%) ስለሆነች የክርስቲያን ደሴት ተባለች እንጅ ሌሎች ሀይማኖቶች የሉም ወይንም እውቅና አለመስጠት አይደለም፡፡
    ሀገራችን ክርስትናንም (34ዓ.ም) እስልምናንም (6ኛው መቶ ከ/ዘ) ከአለም ህዝብ ቀድማ የተቀበለች ሀገር ነች፡፡ ክርስትናን ሀይማኖት ከእስራኤል ፣ እስልምና ሀይማኖት ከአረቡ አለም ይምጣ እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ ሁለቱም ሀይማኖት ከመምጣቱ በፊት ነበረ፣ ሀይማኖቱን ከመቀበሉ በፊትም በጋራ የኖረ ነው ከተቀበለ በኻላም አብሮ የኖረ ህዝብ ነው ወደፊትም በጋራ ይኖራል፡፡ እስልምና እና ክርስትና ሀይማኖት ኢትዮጵያ ውስጥ አልተፈጠሩም ስለዚህ ሁለቱም ሀይማኖቶች መጤ ናቸው፡፡ ዋናው ቁም ነገር አትዮጵያዊ ለመባል መስፈርቱ ሀይማኖት ሳይሆን በኢትዮጵያ ድንበር ውስጥ ወይንም ከኢትዮጵያን እናት/አባት መወለድ ስለሆነ ሀገራችን ለየትኛውም እምነት ተከታይ ሀገር ናት ማንም ሊሰጠን/ ሊወስድብን አይችልም መብትም የለውም፡፡
    በሀገራችን ታሪክ በሁሉም ሀይማኖት ዘንድ ጥሩ ሀይማኖተኛ ሰዎች እንደነበሩ ኣሁንም እንዳሉ ቢታወቅም ኣንዳንድ በማወቅም ባለመወቅም ስህተት የሰሩ ኣሁንም የሚሰሩ ይኖራሉ፡፡ በነዚህ በተሰሳቱ ሰዎች እይታ ሀይማኖቱንም የምንፈርጅ ከሆንን ትልቅ ስህተት እየሰራን እንደሆነ መገንዘብ ኣለብን፡፡ ከዚህ ይልቅ የሚጠቅመው ለሀገራችንም ሆነ ለሀይማኖታችን ጥሩ እናስባለን የምንል ሰዎች በመቀራረብ እና በመወያየት የተሰሳቱትን ማስተካከል ነው እንጅ በመወነጃጀል ለራሳችንም ለሀይማኖታችንም ለሀገራችንም ጥሩ ነገር ልናተርፍ አንችልም፡፡ የተሻለው ነገር ሁሉም ሀይማኖቱን በነጻነት እና በእኩልነት ያከብር ዘንድ በጋራ መስራት እና መተባበር ሁሉንም ይጠቅማል፡፡ እናት ሀገራችንንም አያቶቻችን በጋራ ጠብቀው እንዳስረከቡን እኛም ለልጆቻችን የበለፀገች እና አንድነቱአ እንደተጠበቀ ለማውረስ እና በታሪክም ተጠያቂ እንዳንሆን ድርሻችንን እንወጣ፡፡”የእሳት ልጅ አመድ ከመሆን እግዚአብሔር ይሰውረን፡፡”
    “ሀገራችን የጋራ ሀይማኖታችን የግላችን ናት”፡፡
    ፍቅር ያሸንፋል
    እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ሀገራችንን ይባርክ
    አብዲሳ
    Reply
  2. gin enante manachu? wikilinachu lbetekirstiyan wayis lpoltikgnoch? MK yejmerew 2 bila? arfachu sirachun bitisarus?
    Reply

    Replies


    1. hahahahaha.....minmalet newu? wanawu gudayi yemibalewun semto mamezazen inji wiklik minamin malet yemahyimoch hasab nowu wodaje.
  3. “እናውቃለን ብንናገር እናልቃለን” ብለን ውስጣችንን ፍርሃትን አናለማምደውም all true!!!!
    Reply
  4. Betam Yemiyasazin Gize new.
    Reply
  5. Mismarena kirstiyan simetute yetebkale
    Reply
  6. God bless u all Andadrgen

    The guy who comment the first line u said" gin enante manachu" if u don't know who they "ANDADRGEN" are why u are READING their article and trying to post ur veeeeeery unfair comment.

    Even u don't who Mahebere Kidusan is, and what the members doing ' They are the TRUE SONS AND DAUGHTERS OF ETHIOPIAN ERTHODOX TEWAHEDO.and same WITH ANDADRGEN

    It looks you are one of the members of Anti Tewahedo or Tplf
    Reply
  7. አንድ አድርገን የከሰረው ፖቲከኛ የማቅ ብሎግ ነው። ገና ለገና የእኛ ገመና ይገለጣል ብለችሁ ላላያችሁት ነገር ምላሽ መስጠታችሁ ያሳዝናል ማፈሪያዎች ናችሁ።
    Reply

    Replies


    1. Don't be angry! Ande-adregen is from ande-adregen. I always admire how this guys try to make a difference. Just do your part. You don't need to blame people if they are trying to do thier part.

      By the way, "kanegagereh... se'nefena me'kegna temeselaleh."
  8. mk leqeso jemere. lenante manem mehareb ayakerbem
    Reply
  9. Amlake kidusan yirdachehu yitebekachehu. betam tiru merejawochen binetekemibetem banitekemebetem selemitadersun, emebetachen asrat ageruan Ethiopian ena Hizbuan titebikelen selamun yadilen
    Reply
  10. Libeluat yasebuatin amora jigra yiluatal new negeru ,eski yihun, Andye fetari sirawn yiseral MK abalat yalefetena tsidq yelemna bertu tsinu begizewm yalegizewm endil metshafu
    Reply
  11. በጣም ጊዜ ወስጀ ይህን ፊልም አየሁት! አንድ ቃል ለሁለት በመክፈል ለፕሮፓጋንዳ የተሰራ በመሆኑ የመንግስትን ውሸት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ መሆኑ ደስ ብሎኛል።መንግስት ሙስሊም እና ክርስቲያኑን ለማጫረስ ብዙ ስራዎችን ሰርቶአል።የጅማ ጭፍጨፋ ተዋንያን ደግሞ ካድሬዎች ናቸው።ባይሆንማ ኖሮ በፉል ኤች ዲ ካሜራ በጥራት ባልተቀረጸ ነበር። ሙስሊሞች መጅልስ አይወክለንም ስላሉ አክራሪ ተባሉ!እናንተም ነገ ጳጳሱ አይወክሉንም ብትሉ ይኸው እጣ ያጋጥማኋል። እናንተ ክርስቲያኖች ሆይ?እባካችሁ መንግስት እድሜውን ለማራዘም እየተጠቀመበት ያለውን ሴራ በማጋለጥ በኩል የተቻላችሁን ተባበሩ።ከሙስሊሞች ጋር ለማጣላት የመጫወቻ ካርዶች ሁሉ እያለቁበት እና እየተነቁበት ነው። እንደሶሪያ መንግስት ህዝቦችን ለመጨፍጨፍ ቆርጦ ተነስቶአል።ሙስሊሞች ሰላማዊ አካሄዳቸው ስላልተመቸው እንጅ።ለሃገር ሰላም የሚያስብ እውነተኛ ዜጋ ሁሉ በሙስሊሙ መብት ላይ የሚደረገውን አፈና እስካልተቃወመ ድረስ ሁኔታወች የሁሉንም በር ማንኳኳታቸው አልቀረም።ሙስሊሞች በአወሊያ እና አንዋር ተወስነው መጅሊስ አይወክለንም/አወሊያ ኮሌጅ ለሙስሊሙ ይመለስ/መብቱን የሚጠይቅ በጅምላ አክራሪ እና አሸባሪ እየተባለ አይሸማቀቅ የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ አንስተዋል።መንግስት ወደ ሃይል እርምጃ ከገባ ደግሞ ጥያቄያቸው በትክክል ይቀየራል።መጅሊስ ይውረድ ይቀር እና መንግስት ይውረድ ይሆናል!!!ያኔ ማጣፊያው ያጥረዋል።በ 40 ሚሊዮን ሙስሊም ላይ መቀለድ መጨረሻው አያምርም።ሙስሊሞች የኢስላም መንግስት እናቋቁም የሚል ከንቱ ምኞት የላቸውም!!ይህን አይነት ነገር አስበውም አያውቁም።የመንግስት ካድሬዎች በየፓልቶክ ሩሙ ውስጥ እየገቡ የሚዘላብዱ መሆኑ ተደርሶበታል።እናም መንግስትን አትመኑት አብረን ተከባብረን እንደኖርን ወደፊትም በሰላም እና በመተማመን አንኑር ጥላቻ ለማንም አይጠቅምም ለመንግስት እንጅ!!!
    Reply
  12. what amazed me most is "pastor" Dawit cursing extremism in ETV. What is he? ETV and Dawit are ..........
    Reply
  13. Well explanetion is given by D/n birhanu admas& abayneh kassie. But it shame for etv, lenegeru mehal hager lay kebekele ebach minm antebkim, lemehonu yetgnaw ye ortodox teketay new mesgeid yakatelew,sew yaredew,dingay yeworewerew? Behulum zend akrarenet ale malet min malet new? EOTC sitsedeb zim tibel? Mels mestet yelebatm? Lenegeru wanawn tesadabe paster dawitn yehaymanot mere adirgachihu bemaqirebachihu mannetschun awqenal. ETV hoye minew human rights watch,Aministy international mengist lay yesela ticht siyanesu saywl sayadr aydel yemtchohut leziyawm be wishet,enante silepoleticachihu mels sitisetu silehymanot mels beset yakoral enji ayasafrm. Lengeru mela negeru wishet nehone sile ewnet benegrut aygebawm

በሞንታቦ ቤተክርስትያን በር ላይ የሚካሄድ ህገ ወጥ ንግድ ከ10ሺህ ብር በላይ የሚስቀጣ አዋጅ ሊወጣ ነው



  • አዋጁ ሚኒባስ ላይ ሞንታርቦ በመስቀል በየትኛው ቦታ ላይ የሚደረግ ማንኛውም ንግድ ከብሮድካስት ባለስልጣን ፍቃድ ያስፈልገዋል ይላል፡፡
  • አዋጁ በምክክር ላይ ስላለ ቤተክርስትያን በንብረቶቿ አማካኝነት የሚሰራን ማስታወቂያ እንዳይኖር በአዋጅ ውስጥ እንዲካተትላት መጠየቅ ትችላለች፡፡
  • አዋጁ ላይ ኦርቶዶክሳውያን ማንሳት የሚገባን ጥያቄ……..?????

(አንድ አድርገን ሰኔ 24 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- በተለይ በአዲስ አበባ ልደታ ቤተክርስትያን ፤ ምስካየ ኃዙናን መድሃኔዓለም ፤ 5ኪሎ ቅድስተ ማርያም ፤ ቦሌ መድሃኔዓለም ፤ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስትያን ፤ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትን ፤ አዲሱ ሚካኤል እና መሰል ብዙ ምዕመናን በበዓላት ወቅት የሚገኙባቸው አድባራትና አብያተክርስትያናት መንገድ ላይ ሚኒባስ ተከራይተው ሞንታርቧውን ሰቅለው የተለያየ ማስታወቂያ የሚነግሩ የቤተክርስትያኒቱ አስተምህሮ የሆኑትንና ያልሆኑትን አንድ ላይ በመቀላቀል መዝሙሮችንና ስብከቶችን በመሸጥ ስውር ዓላማቸውን የሚያሳኩ ሰዎችንና ማህበራትን መመልከት ከጀመርን ሰንበትበት ብለናል ፤ ከአውደ ምህረት ሲባረሩ በቀላሉ በሚኒባሶች የፈለጉበት የሃገሪቱ ከተማ በመዘዋወር በዓላትን በማስታከክ መዝሙርና ስብከቶቻቸውን  በመሸጥ የንግድ ተግባራቸውን ሲያጧጡፉም ተመልክተን ይህን የሚያስቆም ህግ ባለመኖሩ አይተን እንዳላየን አልፈናል ፤ በተጨማሪ እነዚህ ህገወጦች ከሞንታርቦ ስፒከሮቻቸው አማካኝነት የሚለቁት የድምጽ መጠን የሰው ጆሮ መስማት ከሚችለው በላይ ስለሆነ በጊዜው በየአብያተክርስትያናቱ የሚቀደሰውን ቅዳሴ ፤ የአውደ ምህረቶችን ስብከት እና መዝሙር ለመስማት የተቸገርንበትና ሃይ የሚል የጠፋበት ጊዜ ላይ መድረሳችን ይታወቃል ፤ እነዚህንና መሰል ስውር አላማ ይዘው በ500 መቶ ብር የቀን የሚኒባስ ኪራይ ምንፍቅናቸውን በአደባባይ የሚዘሩ ፤ ፍቅረ ነዋይ አይናቸውን የጋረዳቸው ሰዎችና ማህበራትን የሚመለከት አንድ አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት አማካኝነት ህግ ሊወጣለት መሆኑን በተባራሪ ወሬ ሰማን ፤ አዋጁንም ከአንድ የማስታወቂያ ባለሙያ ወዳጃችን ረቂቁን በመቀበል ማንበብ ችለን ነበር ፤በመሰረቱ አዋጁ በጠቅላላ ሀገሪቱ ላይ የሚደረጉትን የማስታወቂያ ስራች መስመር ለማስያዝ የወጣ ቢሆንም ይህ ጉዳይ ቤተክርስትያን ላይ ስለሚደረጉ ነገሮች በጥቂቱ ስለሚመለከት የእኛን ክፍል ብቻ በማንሳት የአዋጁን ሀሳብና ቅጣቱን ለእናንተው ለማቅረብ ወደድን፡፡


በቅርቡ መንግስት “የማስታወቂያ አዋጅ” ለማውጣት የሚመለከታቸውን አካላት በኢቲቪ እና በተለያዬ የኤፍ ኤም ጣቢያዎች በአዋጁ ዙሪያ ለመነጋገር ማስታወቂያ ሲያስነግር ሰምተን ነበር ፤ ይህን በሚመለከት ከሳምት በፊት ሪፖርተር ጋዜጣ የጻፈውን ጽሁፍም መመልከት ችለናል ፤ የሚመለከታቸውም አካላት ባሳለፍነው ሳምንት ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከብሮድካስት ኤጀንሲ ሃላፊዎች ጋር መነጋገገር መቻላቸውንና ጠቃሚ ነገሮች በውይይቱ ላይ መገኝታቸውን ኢቲቪ ዜና ላይ ተመልክተናል ፤ እኛም ይህ የማስታወቂያ አዋጅ በተወሰነ መልኩ በማስታወቂያ ችግር ቤተክርስትያናችን የምትገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታና እኛን ስለሚመለከተን ነገሮች ላይ ብቻ በመዳሰስ  አዋጁ ከመጽደቁ በፊት መጠየቅ የምንችላቸውን ጥያቄዎችን ለማንሳትና ለሚመለከተው አካል ለማቅረብ በማሰብ ይችን ሀሳብ አቅርበንላችኋል፡፡

አዋጁ 37 አንቀጾች ያሉት ሲሆን  ሲጀምር “ማስታወቂያ በስርዓት ካልተመራ የህብረተሰቡን መብትና ጥቅም እንዲሁም የሀገርን ገጽታ ሊጎዳ የሚችል በመሆኑ የማስታወቂያ ወኪሎች ፤ የማስታወቂያ አሰራጮች እና የማስታወቂያ አስነጋሪዎችን መብት እና ግዴታ በግልጽ መወሰን በማስፈለጉ…..” በማለት የአዋጁን አስፈላጊነት ይተነትናል ፤ ትክክል ነው የአንዲት ሀገር የማስታወቂያ ስርዓት በአግባቡ ካልተመራ  ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል ፤ በየጊዜው በቤተክርስትያን አካባቢዎች በዓልን መሰረት አድርገው የሚደረጉ የማስታወቂያ ስራዎችና ህገወጥ ንግዶች ምዕመኑ በዓሉን በሰከነ መንፈስ እንዳናከብር እያደረጉት ይገኛሉ ፡፡
እኛ እንደችግር የሚታየን በየጊዜው ዓመታዊ እና ወርሃዊ በዓል ላይ በየቤተክርስትያኑ ደጃፍ ላይ ሚኒባስ በመከራየት ፤ ማይክራፎን በመያዝ ጆሯችንን የሚያደነቁሩንን የማስታወቂያዎች ጉዳይ ነው ፤ ለበርካታ ጊዜያት የት ሄደን አቤት የምንልበትን ቦታ በማጣት ችለናቸው መቀመጣችን በአሁኑ ጊዜ ያለ እውነታ ነው ፤ ይህ የማስታወቂያ ህግ ከጸደቀ በኋላ ግን እነዚህን ሰዎች እኛ አይተን ዝም ብንላቸው ህጉ ዝም የሚላቸው አይመስለንም ፡፡እስኪ ረቂቁን አዋጅ እንመልከት፡፡

የረቂቅ አዋጁ አንቀጽ 2 ንኡስ አንቀጽ 11 ላይ ትርጓሜው ክፍል ላይ ይህን ሰፍሮ እናገኛለን “የውጭ ማታወቂያ ማለት በቢልቦርድ ፤ በኤሌክትሮኒክስ ስክሪን ወይም በተንቀሳቃሽ ምስል የሚሰራጭ ፤ በህንጻ ወይም በማናቸውም ስትራክቸር ወይም በትራንስፖርት ተሸከርካሪ ላይ የሚለጠፍ ፤ በተንጠልጣይ ነገር ፤ በፖስተር በስቲከር በብሮሸር ሊፍሌት ወይም በራሪ ወረቀት የሚሰራጭ ወይም በድምጽ ካሴት በድምጽ ማጉያ መሳሪያ የሚሰራጭ ወይም በሌላ መሰል ማሰራጫ መንገድ አማካኝነት የሚሰራጭ ማስታወቂያ ነው” ይላል፡፡ ይህ የውጭ ማስታወቂያ ትርጓሜ ላይ የእኛን አትኩሮት የሳበው ፤ በቀጥታ የሚመለከተንና ህገወጥ አካላትን አደብ የሚያስገዛልን  “በድምጽ ካሴት በድምጽ ማጉያ መሳሪያ የሚሰራጭ” የሚለው ይሆናል ፤

ይህን ጉዳይ በአንቀጽ 21 ላይ እንዲህ ብሎ ያስቀምጠዋል
21. ስለ ውጭ ማስታወቂያ
1.      ማንኛውም ሰው አግባብ ካለው የመንግስት አካል ፈቃድ ሳያገኝ እንደ አግባብነቱ ባለቤቱ ወይም ባለይዞታው ሳይስማማ
ሀ.  በማናቸውም ህንጻ ፤ ግድግዳ፤ አጥር ፤ የአውቶቡስ ፌርማታ ፤ ምሰሶ ፤ ቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት መስጫ አሳሪያ ወይም ሌሎች ነገሮች ላይ
ለ.   በማንኛውም መንገድ ፤ አውራ ጎዳና ፤ የባቡር ሃዲድ ወይም የህዝብ መጓጓዣ ላይ ወይም
ሐ.   በማናቸውም የህዝብ አገልግሎት በሚሰጥ ስፍራ ላይ
የውጭ ማስታወቂያ መለጠፍ ፤ መስቀል ፤ መትከል ወይም በሌላ መንገድ ማስተዋወቅ አይቻልም፡፡  በማለት ያስቀምጣል ፤

በመሰረቱ “ህግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም” ስለዚህ በበጎም ይሁን በሌላ መንገድ ቤተክርስቲያን አካባቢ ሚኒባስና ሞንታርቦ በመከራየት ፤ በማይክራፎን መዝሙሮችን ፤ ስብከቶችንና  ለመሸጥ የተሰማሩ ሰዎች ይህን አዋጅ ከጸደቀ በኋላ ቢያነቡት መልካም ነው የሚል ሃሳብ አለን፡፡ በቅን ልቦና ተነስቶ የጎዞ ማስታወቂያዎችን በየፈለጉት ቦታ መለጠፍም የማስታወቂያውን ባለቤት በህግ ስለሚያስጠይቅ መጠንቀቁ መልካም ነው ባዮች ነን ፤ በተጨማሪም የቤተክርስትያናት አስተዳዳሪዎች ፤ በተለያየ በስልጣን ተዋረድ ላይ የሚገኙ የቤተክርስትያን ኃላፊዎች ፤ መንፈሳዊ ማህበራት ፤ ይህን ተግባር ማስቆም ለሚፈልጉ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች ፤ የቤተክርስትያን የደጃፍ ላይ ህገወጥ ነጋዴዎች ጉዳይ የሚያሳስባቸው አካላት ይህን አዋጅ በማየት የቤተክርስትያንን ስርአት የፍቅረ ንዋይ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ብለው በድምጽ የሚረብሹ ሰዎችን ህግ ዘንድ ለማቅረብ ይችሉ ዘንድ አዋጁ ጸድቆ ሲወጣ  ቢያነቡትና የቤተክርስትያንን ስርዓት ለማስከበር ቢጥሩ መልካም ነው ፡፡

አዋጁ እንደሚያስቀምጠው በሚኒባስ እና በማይክራፎን በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ማስታወቂያ ለመስራት ከብሮድካስት መስሪያ ቤቱ ፍቃድ እንደሚያስፈልግ ያስቀምጣል ፤ ለእነዚህ አካላት ፍቃድ  ቢሰጥ እንኳን አንቀጽ 7 ንኡስ አንቀጽ 7 ላይ አግባብ ያለው የመንግስት አካል የሚወስነውን የድምጽ መጠን በማናቸውም አይነት የድምጽ ማጉያ መሳሪያ አማካኝነት መተላለፍ እንደሌለበት ያስቀምጣል ፤

ይህን ህግ በመተላለፍ ጥፋት የፈጸመ ማንኛውም አካል አንቀጽ 34 ንኡስ አንቀጽ 1 ላይ “ከ10 ሺህ ብር የማያንስ  ከ100ሺህ ብር የማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል” በማለት ያስቀምጣል፡፡ ሀገሪቱ ህግ የማውጣት ችግር የለባትም ፤ ዋናው ችግር የማስፈጸም ችግር ነው ፤  ይህ ህግ ሲወጣ የመጀመሪያ ተጠቃሚዎቹ የህገወጥ የሞንታርቦ ድምጽ ያስቸገራቸው ደብራት መሆናቸው እሙን ነው ፤ ስለሆነም ህጉን ይዞ መከልከልም ሆነ ማስከልከል ስለሚቻል እንደ ቀላል ጉዳይ መመልከት የለብንም፡፡ አነዚህን በመሰሉ ጉዳዮች ላይ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከአዲስ አበባ መስተዳደር ጽ/ቤት ጋር ከወራት በፊት መነጋገሩን ይታወቃል ፤ ሲጀመር ሀገረ ስብከቱ የዚህን አዋጅ መውጣት በጉጉት የሚጠባበቅ ቢሆንም ሌላ ክፍተቶች እንዳይፈጠሩ አዋጁን በመመልከት ከሚመለከተው አካል ጋር ቀርቦ የራሱን ሃሳብ መስጠት ቢችል መልካም ነው፡፡

አዋጁ ላይ ኦርቶዶክሳውያን ማንሳት የሚገባን ጥያቄ
የአዋጁ አንቀጽ 7 ንኡስ አንቀጽ 11 ላይ የሚከተሉት ማስታወቂያዎች ህግን ወይም መልካም ስነ ምግባርን የሚጻረር ይዘት ወይም አቀራረብ እንዳላቸው ሆነው ይቆጠራሉ በሚለው ስር “የመከላከያ ሰራዊት ወይም የፖሊስ የደንብ ልብስን ፤ ምልክትን ወይም ሽልማትን በመልበስ ወይም በማድረግ የሚቀርብ የንግድ ማስታወቂያ” እንደማይፈቀድ ያስቀምጣል ፤ ይህ አንቀፅ መንግስት ለፖሊስ እና ለመከላከያ አባላት ልብሶችና ኒሻኖች ምን ያህል እንደተጠቆረቆረ ያሳየናል ፤ እንደ ሀገር ስናየው መልካም ነው ፤ መንግስት ለራሱ ተቋማት ይህን ያህል የሚጠነቀቅ ከሆነ እኛም የቤተክርስትያናችን ንዋየ ቅዱሳትን ፤ የአባቶችን ቆብና ልብስ ፤ ከበሮ ፤ ጸናጸል ፤  እና መሰል የቤተክርስትያኒቱ መገልገያ መሳርያዎች የማስታወቂያ ስራ ግብአት እንዳይሆኑ መጠየቅና አዋጁ ላይ ማካተት አለብን የሚል አቋም አለን ፤ እኛ እንደ ግለሰብ አንዲት ደብዳቤ ላይ ሃሳባችንን ገልጸን ለብሮድካስት ኢጀንሲውና ይህን ለሚመለከተው የህዝብ ተወካዮች አባላት ቋሚ ኮሚቴ ጥያቄያችንን ማቅረብ እንችላለን ፤ ቤተክህነቱም  ቤተክርስትያኒቱን ወክሎ ጥያቄ ቢያቀርብ መልካም ነው የሚል ሃሳብ አለን ፤ እርስዎ ምን ይላሉ…? ይህ ጉዳይ ያሳስበናል የምትሉ ሰዎች ካላችሁ ለመጽደቅ ቀናት የቀረው አዋጅን ብሮድካስት መስሪያ ቤት ድረስ በግልም ይሁን በቡድን በመሄድ አዋጁን ማግኝት እንደምትችሉ ለመግለጽ እንወዳለን ፤ ሀገሪቱ የምታወጣውን ማንኛውንም ህጎች ላይ በማየት ሃሳቦትን የመስጠት መብት ስላለዎት ረቂቅ አዋጁን ለማግኝት ሀሳብ አይግባዎ ፤

ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ስርዓት መሰረት ተዘጋጅተዋል ተብለው በማስታወቂያ ለምዕመኑ የሚሰራጩት የመጽሀፍት ፤ የመዝሙር እና የስብከት ስራዎች በማስታወቂያ አማካኝነት ከመሰራጨታቸው በፊት ቤተክርስቲያኒቱ የሚሰራጩትን የህትመት ውጤቶች መፍቀድ አለባት ፤ ይህን ጉዳይ በሀሳብ መልክ በማንሳት አዋጁ ላይ ይካተት ዘንድ ሃላፊነቱ የቤተክህነቱ ቢሆንም እኛም ከቻልን የአቅማችንን ማድረግ ይገባናል ፤  “ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል” ይላል የሀገሬ ሰው፡፡

ቸር ሰንብቱ

‹‹ብዙ ሃይማት አንዲት ሀገር›› ኢቲቪ የለቀቀው ውዥንብር

  •  982 ነጻ አስተያየት ወደ ኢቲቪ ከደወሉት አስተያየት ሰጪዎች ውስጥ 90 በመቶ ባዩት ነገር የተናደዱ እና የነበሳጩ ሆነው ነገኝተዋል
  • እውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መጤ ነችን?
(አንድ አድርገን ሰኔ 27 ፤ 2004 ዓ.ም)፡- የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ክብር ባህል እምነትና ስርዓት መንግስትና ቋንቋ ያቋቋመች የማትናወጥ ከመሆኗ ጋር ከሔኖክ ፤ ከኖህ ፤ ከመልከ ጼዴቅ ከነብያትና ከሀዋርያት ተላለፈውን ትምህርት ስርዓት ፤ እምነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ስታስተላልፍ የኖረች በማስተላለፍ ላይ ያለች ፎኖተ ህይወት መሆኗ የተረጋጠ ነው፡፡  ቅዱሳን አበውን ፤ ኃያላን ነገስታትን ፤ ልዑላን መሳፍንትን ፤ ክቡራን መኳንንትን ፤ ዐይናሞች ሊቃውንትን በስጋ በነፍስ ወልዳ ያሳደገች የሌላ የማትፈልግ የራሷ የማትለቅ ዕጥፍ እናት ፤ ስንዱ እመቤት ናት፡፡


“ማህበረ ቅዱሳን አክራሪና ጽንፈኛ ማህበር ነው” በማለት በጦላይ ጦር አካዳሚ ለአመራሮች ስልጠና ተሰጠ


  • ·        የምንሰማ እና የምናየው ነገሮች መልካም ባለመሆናቸው ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ “አንድ አድርገን” የመረጃ ምንጭ መሆኗን አቋርጣለች፡፡


(አንድ አድርገን ሰኔ 27 2004 ዓ.ም)፡- የመንግስት አካሄድ ከቀን ቀን እየከፋ እየመጣ ነው ፤ ነገሩ ከተነሳበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ የምንሰማው እና የምናየው ነገር ጥሩ አይደለም ፤ በየዓመቱ ከሰኔ እስከ መስከረም አጋማሽ በቀበሌ ፤ በክፍለ ከተማ ፤ በክልል በወረዳ ደረጃ ያሉ የኢህአዴግ አባላት ጦላይ ጦር ማሰልጠኛ ካምፕ  በመላክ ፖለቲካዊ ትምህርት እንደሚማሩ ይታወቃል ፤ ሀገሪቱ በተለያዩ ሀገራት ሰላም ማስከበር ብላ የምትልካቸው ከወታደር አንስቶ እስከ ጀኔራል ድረስ ያሉ ሰዎች ጦላይ ሳይደርሱ የፖለቲካ መርፌ ሳይወጉ ደቡብ ሱዳንም ሆነ ቡሩንዲ መሄድ አይቻልም ፤ ለተራ ወታደር ከሶስት እስከ ስድስት ወር የሚደርስ በተለያዩ ነገሮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ሲሰጥ በአመራር ደረጃ ያሉት ደግሞ እስከ ሁለት ወር የሚያቆይ ስልጠና እንደሚወስዱ ይታወቃል ፤ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ከ800 በላይ የኦህዴድ አባላትን ወደ አዲስ አበባ በማምጣት የተለያዩ ፖለቲካዊ የስልጣን ተዋረድ ላይ ያስቀመጣቸው ኢህአዴግ ለሁለት ወር ያህል ጦላይ ማሰልጠኛ ሄደው በቪዲዮ ኮንፍረንሲንግ ሲስተም  አማካኝነት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ የተለያዩ ሚንስትር ዴታዎች አማካኝነት ስልጠና ከወሰዱ በኋላ ለሁሉም አባላት አዲስ አበባ ውስጥ በኪራይ ቤቶች የሚገኙ ቤቶችን  ያለምንም ክፍያ እንደተሰጣቸው  ይታወቃል ፤ ኪራይ ቤት ለታጣላቸው ከተማዋ ውስጥ ያሉትን  ኮንዶሚኒየም ቤቶች መርጠው አባል እስከሆኑ ድረስ እንዲኖሩበት ተሰቷቸው ፤ በአሁኑም ሰዓት ድርጅቱን በማገልገል በገጸበረከት በተበረከተላቸው ቤቶች ውስጥ ኑሯቸውን እየኖሩ ይገኛሉ ፤ አሁን እኛን ይህ ጉዳይ ለመጻፍ ሳይሆን አነሳሳችን ጦላይ የጦር አካዳሚ ምን አይነት ስልጠና እንደሚሰጥ ? ፤ ምን አይነት አመራሮች ወደ ቦታ ሄደው እንደሚሰለጥኑ ?  ለምን አላማ እንደሚታጩ ? ቦታው ያለውን ገጽታ ለናንተው ለማስገንዘብ ያህል  ነው፡፡

በአሁኑ ሰዓት ጦላይ ጦር አካዳሚ ከቀበሌ አንስቶ እስከ ከተማ መስተዳድር ኃላፊዎች  ፤በክልላዊ መንግስት ደግሞ ከታችኛው ከወረዳ የስልጣን እርከን አንስቶ እስከ ክልላዊ መስሪያ ቤት ባለስልጣናት የሚገኙ የኢህአዴግ አባላትን  በመመልመል ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ ፤ የትግራይ ፤ የአማራ ፤ የደቡብ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስቶች የኢህአዴግ አባላት ገብተው የተማሩት ነገርና የተሰጣቸው መመሪያ ከዚህ በፊት በየዓመቱ ከሚሰለጥኑት ስልጠና የተለየ መሆኑን የደረሱን መረጃዎች ያስረዳሉ ፤ በስልጠናው ላይ ሰፊውን ጊዜ የወሰደው እና ራሳቸው ቋጥረውት አልፈታ ያላቸው ጉዳይ ቢኖር እነሱ እንደሚሉት የ”አክራሪነትና የጽንፈኝነት” አጀንዳ ነው ፤ በስልጠናው ላይ  ማህበረ ቅዱሳን የኦርቶዶክስ አክራሪ ማህበር እንደሆነ ፤ አመራሮቹ በያሉበት ቦታ ላይ ወደ ስራ ሲመለሱ አካሄዱን እንዲከታተሉትና እንዲዋጉት ፤ ከፍተኛ ክትትል በማድረግ በየደረጃ ያሉ አመራሮች እርምጃ እንዲወስዱበት ፤ ማህበሩ ጽንፈኛ አቋም እንዳለው ህገመንግስታዊ የእመነት ነጻነቶችን እንደሚጋፋ  ፤ ለሀገር አስጊ የሆነ ማህበር እንደሆነ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ያጠነጠኑ አጀንዳዎችን በማንሳት  አስረግጠው  ለኢህአዴግ አመራር ስልጠና ሰጥተዋል ፤ ይህ መረጃ የደረሰን በስልጠናው ላይ ከተካፈሉ በአካል ከምናውቃቸው አመራሮች  አማካኝነት ነው ፤  ይህ በስልጠና ደረጃ የተደረገ ተግባር መሆኑ ለየት ያደርገዋል ፤ ሌላ ሌላውን ትተነዋል፡፡

ከሳምንት በፊት “አዲስ ራእይ” ላይ ያለውን ሀሳብ ማስረዳት እንደሞከርነው መንግስት ግቡን ለመምታት ያመቸው ዘንድ በህዝቡ መሃል ይህን ጉዳይ ለማስረጽ እና ጊዜው ሲደርስ እርምጃ ሲወስድ ጠያቂ አካል እንዳይኖር ለማድረግ በኢቲቪ አማካኝነት የተሰራውን ፊልም አስመልክቶናል ፤ የ10 ሰዓት ቃለ መጠይቅ የ1፡30 ፊልም ወጥቶታል ፤ አዲስ ራእይ መጽሄትን መሰረት አድርጎ ቀጭን መመሪያ በመስጠት በኢቲቪ ጋዜጠኞች የተሰራው ፊልም  ከአዲስ ራእይ መጽሄት ቃል በቃል ከአንድ አንቀጽ በላይ በማንበብ ለፊልሙ እንደ ግብአት ተጠቅመውበታል ፤ (የተሰራውን ፊልም ጋዜጠኛው ያነበበውን የአዲስ ራእይ አንቀጽ ከቀናት በኋላ አነጻጽረን እናቀርብሎታለን)፡፡  

ስለዚህ ይህን ስራ እየተሰራ ያለው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስቶ እስከ ታችኛው አመራር ድረስ የእዝ ሰንሰለቱን ጠብቆ መሆኑን እነዚህ ነጥቦች አስረጅ ናቸው ፤ የሚቀጥለው እርምጃው ህዝቡን እስከ ታች ድረስ ወርዶ ማወያየት ይሆናል ፤ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኝት ያስችለው ዘንድ በስትራቴጂያዊ አካሄድ ስብሰባዎች ያካሄዳሉ ፤ እስከ አሁን ድረስ ህዝቡን ያሳተፈ ሳይሆን የኢህአዴግ አባላት የጠራ አቋም በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲይዙ ስብሰባዎችን በተለያዩ ቦታዎች ላይ አድርገዋል ፤ ቀጥሎም በእስልምናም ይሁን መልስ ተደርገው በኦርቶዶክሳዊያን የተዘጋጁ መጽሃፍቶችና ሲዲዎች ላይ ያተኩራል የሚል ወሬም ደርሶናል ፤ እያለ እያለ ግቡን እስኪመታ ድረስ የጀመረውን መንገድ ይቀጥላል ፡፡

የመንግስትን አካሄድ በመመልከት ከዚህ በፊት በንዝህላልነት ከቆምንባቸው ጊዜያት በተሻለ ሁኔታ የወደፊት የሚመጣውን ነገር ግምት ውስጥ በማስገባት ሁኔታዎችን ልንከታተላቸው ይገባናል ፤ አሁንም የተሰራውን ፊልም በደንብ ማህበረሰቡ እንዲመለከተው “በተመልካች ጥያቄ” በማለት ለቀጣይ ቅዳሜ ፊልሙን ደግመው ለማቅረብ ኢቲቪ ፕሮግራም ይዞልናል ፤ ህዝቡ የሰጠው አስተያየት አሁንም እየሰጠ ያለው ይቅርታ የሚያስጠይቅ ሆኖ ሳለ በህዝብ አስተያየት ብለው ፕሮግራሙን ለመድገም ማስታወቂያ እያስነገሩ ይገኛሉ ፤ የትኛው ህዝብ ነው ይደገም ያለው ?
የአሁኑን የጦላይ ስልጠናን ውጤት አሁን ላይ ላንመለከተው እንችላለን ከወራት በኋላ ግን ስለቤተክርስትያን ማንኛውም ምዕመን ጥያቄ ሲያነሳ የዛኔ ጦላይ የተረገዘው የሚወለድበት ጊዜ ይሆናል ፤  እንዴት ይህ ጉዳይ ከምን ተነስቶ እዚህ ደረጃ ደረሰ ብለው ሃሳብ አይግባዎት ፤ ነገ የሚደረግን ህገ-ወጥ ተግባርና የእጅ አዙር ተጽህኖን በማሰብ ራስዎን ለዚያ ጊዜ ያዘጋጁ ፤ ያለፍንበትን ያለንበትንና የምንሄድበትን መንገድ እናስተውል ፤ በግለሰብ ደረጃ አቋም ይኑረን ፡፡ ‹‹ተሰለፉ፥ ዝም ብላችሁ ቁሙ፥ የሚሆነውንም የእግዚአብሔርን መድኃኒት እዩ እግዚአብሔርም ከእናንተ ጋር ነውና አትፍሩ፥ አትደንግጡም፥›› መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 20 ፤17 ይላል ፡፡

ነገሮች ረገብ ሲሉ ቁጥጥሩም ላላ ሲል እንገናኛለን./……….

ቸር ሰንብቱ…..

Monday, 2 July 2012

ግራዉ ከራሴ በታች ፤ መኃ 2፤6 በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ ከፌስቡክ ገጽ ላይ የተወሰደ

እሥራኤልን ከግብጽ እየመራ የወጣው ሙሴ ሕዝቡን ከግብጽ ይዞ መውጣት ይቻለው ዘንድ የተዛዘው ታላቁ ትእዛዝ ፋሲካን በግብጽ ማክበር ነበር፡፡ ፋሲካ የሚባል በዓል ከዚያ በፊት ኖሮም ተከብሮም አያውቅም ነበርና በዝርዝር ማድረግ የሚገባቸዉ ሁሉ ተነገራቸዉ፡፡ ቀኑ በእነርሱ አቆጣጠር በአቢብ ወር በዐሥራ አራተኛዉ ቀን ይከበራል፡፡ ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት በግ ጠቦት ይመርጣሉ፡፡ በምድረ በዳ ሲመሽ ያርዱታል፡፡ ደሙን ወስደዉ የቤታቸዉን በር ሁለት ማቃኖችና ጉበኑን ይረጩታል፡፡ ሥጋውን በሌሊት በእሳት ጠብሰዉ ይበሉለታል፡፡ ጥሬውንና በውኃ የተቀቀለዉን አይበሉም፡፡ የተረፈውን ሌሊቱን በእሳት ያቃጥሉታል፡፡በፍጥነት ይበሉታል፡፡ ከዚያ በኋላ ለሰባት ቀን የቂጣ በዓሉን ያደርጋሉ፡፡ ቂጣዉም ምንም እርሾ ያልገባበት ይሆናል፤ …./ዘፍ 12፤ 1-36/፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ብዙ ዓይነት መሥዋዕት ሥርዓቶችና የበዓላት አከባበሮችን ተቀበሉ፡፡ በዚሁም መሠረት በየዕለቱ በጧት አንድ በማታ አንድ ነውር የሌለበት የበግ ጠቦት ይሠዋል፡፡ በየዕለቱም የእህል ቁርባን ይቀርባል፡፡በሰንበት፣ በወር መባቻና በሌሎች በዓላት ደግሞ የበጉ ቁጥር ይጨምራል፤ የፍየልና የከብት መሥዋዕቶችም ተጨምረዉ ይቀርባሉ፤ የእህሉም ቁርባን እንዲሁ፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ሕዝቡ በበደሉ ጊዜ እንደ ኃጢኣታቸዉና በደላቸዉ መጠን የተለያዩ መሥዋዕቶችን ያቀርቡ ነበር፡፡በዘመነ ኦሪት ይህ ሁሉ ነገር በሥርዓት ጸንቶ ከዓመት እስከ ዓመት በዚህ መንገድ ሲፈጸም ኖሯል፡፡

የአይሁድ ፋሲካ በእነርሱ የአቢብ ወር በወሩ በዐሥራ አራተኛዉ ቀን እንዲከበር የታዘዘ በዓል ነዉ፡፡ ይህም የሆነበት የራሱ ምክንያት እንዳለዉ ሊቃውንት አስረድተዋል፡፡ በመጀመሪያ ወሩን የዐመቱ መጀመሪያ ወር ይሁናችሁ ብሏቸዋል /ዘጸ 12፤2/፡፡ ይህንንም ይዘዉ ሊቃውንቱ መጀመሪያ ያለው ጥንተ ፍጥረት በዚህ ወር ቢገኝ ነዉ፤ ወይም ፍጥረትን የጀመረዉ (ጊዜንም ጭምር ማለት ነዉ) በዚህ ወቅት ነዉ ብለዉ ያስተምራሉ፡፡ በእኛ ቤተ ክርስቲያንም ይህ ትምህርት በትርጓሜ ሲሰጥ የኖረ ነዉ፡፡ በተለይም ጌታ ዓለሙን ለማዳን ሰዉ የሆነበት ጽንሰቱ መጋቢት 29 ቀን መሆኑንና በኋላም ጥንተ ስቅለቱን መጋቢት 27 አርብ አድርጎ ትንሣኤዉን እሑድ መጋቢት 29 ደግሞ ማድረጉ የዓለሙ ድኅነቱ የተፈጸመበት በዚህ ዕለት የሆነዉ ፍጥረቱን እም ኀበ አልቦ (ካለመኖር) ኀበ ቦ (ወደ መኖር) ያመጣዉ በዚህ ዕለት ስለሆነ ነዉ በማለት ያስተምራሉ፡፡ ከዚህም ተነሥተዉ ዓለም በዚህ ዕለት ተፈጥሮ በዚህ ዕለት ድኅነቱ እንደተፈጸመለት ሁሉ በኋላም በዳግም ምጽአት በዚሁ ዕለት መጋቢት 29 ቀን በዕለተ እሑድ በዘመነ ዮሐንስ ያሳልፈዋል ብለዉ ይጠብቃሉ፡፡ ነገር ግን በየትኛዉ ዓመት እንደሆነ እርሱ እንደ ተናገረዉ ማንም አያዉቅም ይሉናል፡፡ ለዚህ ነዉ በዘመነ ዮሐንስ የመጋቢት 29ን በእሑድ መዋል አንዳንድ አባቶች ሲፈሩት የሚኖሩት፡፡ ስለዚህ ጌታ ለሙሴና ለእሥራኤል በግብጽ እያሉ ይህ ወር የዐመቱ መጀመሪያ ይሁናችሁ ያለዉ የፍጥረት መጀመሪያ ወር እንደሆነዉ የእናንተም ከግብጽ የምትወጡበት የመጀመሪያ ወር ይሁን ሲል፣ በዚሁ አንጻርም ደግሞ ነፍሳትም በግብጽ ከተመሰለች ከሲኦል በዚሁ ወር እንደሚወጡ ሲነግራቸዉ ነዉ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ዐለሙ አልፎ ጻድቃን መንግሥተ ሰማያትን ኃጥኣንም ገሃነመ እሳትን የምትጀምሩበት ይህ ወር እንደሆነ ዕወቁ ሲል ነዉ ይላሉ ሊቃውንቱ፡፡አንባቢ ሆይ ርእሳችን የሆነዉ የ‹‹ግራን›› ነገር ከዚሁ ግራና ቀኝ ቁመት ጋር እያሰቡት ይታገሱ፡፡

የእኛ የትንሣኤ በዓልም በዚሁ ወር የሚከበርበት መሠረታዊ ምክንያትም ከዚሁ ጋር በተያያዘ ምክንያት ነዉ፡፡ ከላይ በሰፊዉ
ለማተት እንደተሞከረዉ ጌታ የፋሲካዉን በግ ብሉ ያላቸዉ በወሩ በአሥራ አራተኛዉ ቀን ነዉ፡፡ ይህም የእነርሱ የወር አቆጣጠር በጨረቃ ስለሆነ ዐሥራ ዐራተኛዉ ቀን ማለት ጨረቃ ከተወለደችበት ወይም መታየት ከጀመረችበት ቀስ በቀስ እያደገች መጥታ ሙሉ የምትሆንበት ጊዜ ስለሆነ ነዉ፡፡ በሌላ ቋንቋ በሙሉ ጨረቃ ወይም በሙሉ ብርሃን ይሁን ማለቱ ነዉ፡፡ ይህም የፋሲካዉ በግ ቅዱስ ዮሐንስ የዓለምን ኃጢኣት የሚያስወግደዉ ያለዉ የክርስቶስ ምሳሌ ስለሆነ እርሱ እዉነተኛዉና ሕጸጽ(ጉድለት) የሌለበት ብርሃን መሆኑን አሁንም በምሳሌ ሲነግረን ነዉ፡፡ የሐዲስ ኪዳኗ ቤተ ክርስቲያናችንም በመንፈቀ ሌሊት ከገጠር እስከ ከተማ ያላትን ብርሃን ሁሉ አብርታ ምእመናኑንም በእጃቸዉ ጧፍ አስይዛ ‹‹ ትንሣኤከ ለእለ አመነ፣ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ፤ ትንሣኤህን ላመንን ለእኛ ብርሃንህን ላክልን›› እያለች በመዘመር መቅደሱን የምትዞረዉ ለዚህ ነዉ፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ተጽፎ እንደምናገኘዉም መድኃኒታችን የተሰቀለዉ የአይሁድ የፋሲካ በዓል ሐሙስ ሆኖ አርቡን ነዉ፡፡ ያስታዉሱ፤ ጨረቃ ሙሉ ብርሃን በሆነችበት ዕለት ማለት ነዉ፡፡ በእርሱ ስቅለትም ይህችዉ ሙሉ ብርሃን የነበረች ጨረቃ ደም መሰለች፣ ሁልጊዜም ሙሉ የሆነችዉ ጸሐይም ጨለመች፣ ክዋክብትም ረገፉ፡፡ ሦስቱም በአንድነት አማናዊ ብርሃን እርሱ መሆኑን የእነርሱም ከእርሱ የተገኘ መሆኑን መሰከሩ፡፡ መድኃኒታችንም ድኅነታችን ፈጽሞ( ፍጹም አድርጎ) እሑድ ተነሣ፡፡ ስለዚህም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የትንሣኤ በዓላችን የአይሁድ ፋሲካ ከዋለ በኋላ በሚዉለዉ እሑድ ማለትም እሥራኤል ከግብጽ ነፍሳትም ከሲኦል በወጡበት ወር ጨረቃም ሙሉ ብርሃን ከሆነች በኋላ በምሥጢር አጊጦ ያለፈዉን እያስታወሰ ብቻ ሳይሆን መጪዉን ዋናዉን ትንሣኤ ሙታንንም እያሳሰበ ሲዘከር ሲከበር ይኖራል፡፡በጨረቃ አቆጣጠር ወራቱ የሚውሉበት ጊዜ ስለሚለዋወጥ በሠላሳ አምስት ቀናት( ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ ሠላሳ ባለዉ ጊዜ) ዉስጥ ሁልጊዜም ከአይሁድ ፋሲካ በዓል በኋላ ባለዉ እሑድ ጥንተ ታሪኩንና ምስጢሩን እንደጠበቀ ሲከበር ይኖራል ማለት ነዉ፡፡
ለትንሣኤያችን ምሳሌ ሆኖ የቆየዉ ይኸዉ የፋሲካዉ በዓል መሥዋዕቱን በተመለከተም የራሱ ሕጎች ነበሩት፡፡ ‹‹እግዚአብሔርም ሙሴንናአሮንን አለ። ይህ የፋሲካ ሕግ ነው ከእርሱ እንግዳ ሰው አይብላ። በብር የተገዛ ባሪያ ቢኖር ከተገረዘ በኋላ ከእርሱ ይብላ። መጻተኛና ሞያተኛግን ከእርሱ አይብሉ።በአንድ ቤትም ይበላ፤ ከሥጋውም አንዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታውጡ አጥንትም አትስበሩበት። የእስራኤልም ጉባኤ ሁሉያድርጉት።እንግዳ ሰውም በመካከላችሁ ቢቀመጥ ለእግዚአብሔርም ፋሲካን ሊያደርግ ቢወድድ፥ አስቀድሞ ወንድ ሁሉ ይገረዝ፥ ከዚያምወዲያ ይቅረብ፣ ያድርግ፣ እንደ አገር ልጅም ይሆናል፤ ያልተገረዘ ሁሉ ግን ከእርሱ አይብላ። ለአገር ልጅ በእናንተ መካከልም ለሚቀመጡእንግዶች አንድ ሥርዓት ይሆናል። የእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ አደረጉ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን እንዳዘዘ እንዲሁ አደረጉ››/ዘጸ 12፤ 43-50/ ተብሎ አንደተጻፈ ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ በሕግና በሥርዓት ይፈጽሙ ነበር፡፡

እነዚህ ሁሉ ግን ምሳሌዎች ነበሩ፡፡ እያዳንዱ ሰዉ ለኃጢኣትና ለበደል ከሚያቀርበዉ መሥዋዕት ጀምሮ ሁሉም ለሐዲስ ኪዳን አገልግሎታችንና መሥዋዕታችን ብዙ መልእክቶችን የተሸከሙ ነበሩ፡፡ ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በግልጥ አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ አይደለምና፥ በግልጥ በሥጋ የሚደረግ መገረዝም መገረዝ አይደለምና›› /ሮሜ 2፤28/ ሲል እንደ ገለጸዉ እነዚያ የመሥዋዕት ዓይነቶች ሁሉ ሌላ ትርጓሜ እንዳላቸዉ በቀላሉ መረዳት እንችላለን፡፡

የፋሲካዉ በግ ስለእኛ ስለሁላችን ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበዉ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና›› /1ኛ ቆሮ 5፤ 7/ ሲል እንደ ገለጸዉ ፋሲካችን እርሱ ነዉ፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም›› /ኢሳ 53፤7/ ሲል የተናገረለት፣ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ›› /ዮሐ 1፤ 29/ ሲል ያረጋገጠልን አማናዊዉ የፋሲካችን በግ እርሱ ነዉ፡፡የፋሲካዉን በግ ደሙን የቀቡት ሁሉ ሞት ወደ ቤታቸዉ አልገባም፡፡ እንዲሁ ከፋሲካችን ከክርስቶስ ሥጋና ደም በልተዉ በደመ ማኅተሙ የታተሙትን ሁሉ ሞት አያገኛቸዉም፡፡ እነርሱ የበራቸዉን ጉበንና መቃን በሚታይ ቦታ ላይ እንደቀቡት በእኛም በግንባራችን ላይ እርሱ ያስቀባዉና  የሚያነብበዉ ማኅተም አለ፡፡ነቢዩ ሕዝቅኤል ‹‹ እግዚአብሔርም፦ በከተማይቱ በኢየሩሳሌም መካከል እለፍ፥ በመካከልዋም ስለ ተሠራው ርኵሰት ሁሉ በሚያለቅሱና በሚተክዙ ሰዎች ግምባር ላይ ምልክት ጻፍ አለው። እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፤ ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ ›› /ሕዝ 9፤4-6/ ሲል እንደገለጸልን ምልክቱን እርሱ ያስቀረጸባቸዉ ብቻ ከዘላለም ሞት ይድናሉ።

በነቢዩ እንደተገለጸዉ ግን ፍርድ ከቤቱ መቅሰፍቱም በቤቱ ከተገኙ ሽማግሌዎች የጀመረዉ በቤቱ ከምንኖረውም ውስጥ ከሞት የማናመልጥ እንዳለን ያመለክታል፡፡ ይህ ደግሞ የሚከሰተዉ የፋሲካዉን በግ ባለመብላት ብቻ ሳይሆን ከላይ የተጠቀሱትን ሕጎቹን አክብሮ ባለ መብላት ምክንያት ነዉ፡፡ስለዚህ እንዲህ ያለዉ ነገር እንዳይገጥመን አስቀድመን ሕጎቹን አንድ በአንድ እንመልከታቸዉ፡፡

1.      ባዕድ አይብላዉ

ከላይ በሰፊዉ እንደተዘረዘረው ሦስት አካላት እንዳይበሉት ታዝዟል፡፡ መጻተኛና እንግዳ( ከእሥራኤል ወገን ያልሆነ) እንዲሁም በዘመኑ የነበሩ ባሮች ካልተገዘሩ ( አሁንም ባዕዳን የሆኑ) አይብሉ ተብሏል፡፡ ምክንያቱም የመንጻቱንም ሆነ ሌላዉን የቅድስና ሕግ አያውቁትም፡፡ ይህን ሳያውቁ ቢበሉት ደግሞ ‹‹ትእዛዝን የሚያቃልል በትእዛዝ ተይዞ ይጠፋል›› /ምሳ 13፤13/ ተብሎ እንደተጻፈ ጥፋትና መቅሰፍትን እንጂ ሥርየትና ሕይወትን አያገኙም፡፡ ይህም ልክ እንደ ይሁዳ ማለት ነዉ፡፡ ይሁዳ ራሱን ከአይሁድ የተንኮል ምክር አስተባብሮ ልቡናዉንና መንፈሱን ከሐዋርያት ኅብረት ሲያወጣ ባዕድ ሆነ፡፡ በዚሁ የባዕድ ልቡናዉ ሆኖ ከሥጋዉና ከደሙ ቢቀበልም ሳይጠቅመዉ ቀረ፡፡ በደኅንነት መሥዋዕቱም ጊዜ በግና ፍየል ለመሥዋዕት የሚቀርብበት ምክንያት ይህንኑ በምሳሌ ለማስረዳት ነበር፡፡ ምክንያቱም ጌታ የመሥዋዕት በግ ቢሆንም ተቀባዮቹ ወይም ቆራቢዎች ግን እንደ ይሁዳና ሐዋርያት የተገባቸዉና ያልተገባቸዉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ የጌታ ሥጋና ደም ለተገባቸዉ (ሐዋርያትን ለመሰሉት) የበግ መሥዋዕት ሲሆንላቸዉ ላልተገባቸዉ (ይሁዳን ለመሰሉት) ደግሞ የፍየል ይሆንባቸዋል ማለት ነዉ፡፡ ይህም ማለት ግን ጌታ በፍየል መሥዋዕቱ ተመስሏል ማለት አይደለም፤ አይመሰልምም፡፡ ነገር ግን በኦሪቱ ፍየል ለደኅንነት መሥዋዕት የሚቀርበዉ ላልተገባቸዉ ሰዎች የጌታ ሥጋና ደም እንሚለወጥባቸዉ ወይም እንደማይጠቀሙበት ለማጠየቅ (ለማስረዳት) ነዉ፡፡ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴዉ ‹‹ እሳት ማሕየዊ ለርቱዓነ ልብ ለእለ ይገብሩ ፈቃዶ፤ እሳት በላዒ ለዓማጽያን ለእለ ይክህዱ ስሞ ፤ ትእዛዙን ለሚፈጽሙ ቅኖች የሚያድን የሕይወት እሳት ነዉ፤ ስሙን ለሚክዱ ለዓማጽያን ደግሞ የሚያቃጥል የሚያፍገመግም እሳት ነዉ›› እንዳለ እንደሚበሉት ሰዎች ሕይወት ይለወጥላቸዋል ወይም ይለወጥባቸዋል፡፡ አሁን ‹‹ስሙን ለሚክዱ›› ሲል እግዚአብሔርን የማያምኑ ሰወች ሊቆርቡ ይመጣሉ ብሎ ሳይሆን ስሙን እየጠሩ እንደ ይሁዳ ልቡናቸዉ በፍቅረ ንዋይና በተንኮል ከተያዘ የማያምኑና አማጽያን የሚባሉትእነርሱ መሆናቸዉን ለማስረዳት ነዉ፡፡ ስለዚህ ባዕዳን አይብሉት የተባለዉ ሕጉን የማያከብሩ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር የማይኖሩ አይብሉት ለማለት ነዉ፡፡ ሊበሉት ከፈለጉ ግን ‹‹ወንዶቹ ይገረዙ፤ እንደ አገር ልጅም ይሆናሉ›› የተባለዉ ለዚህ ነዉ፡፡ ምክንያቱም ችግሩ ምድራዊ ዘራቸዉ ሳይሆን አለማመናቸዉ ነበርና፡፡ ስለዚህ አሁንም ፋሲካችንን ስናከብር እንደ ይሁዳ አካላችንን ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ሆኖ ሐሳባችንና ዓላማችን ግን ቤተ ክርስቲያንን መጠቀሚያ ሊያደረጓት ከሚሹ ከጠንቋዮች፣ ከክፉ ፖለቲከኞች፣ ሊለዉጧት ከተነሡ መናፍቃንና ተሐድሶዎች ወይም ይህን ከመሰለና ለቤተ ክርስቲያን ባዕድ ከሆነ ማንኛዉም ሐሳብ ጋር ያለን ከሆነ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ያሉ ሰዎች ፋሲካውን ሊቀበሉ አይገባቸዉም ይለናል፡፡ሊቁ አባ ሕርያቆስ ‹‹ በአማን ቁርባን ውእቱ ዘኢይክሉ ይጥዐሙ እምኔሁ ግሙናነ መንፈስ፤ መንፈሳቸዉን ያረከሱ ሰዎች ከእርሱ ሊቀበሉት የማይቻላቸዉ በእዉነት ቁርባን ነዉ›› /ቁ. 5/ እንዳለዉ ባዕዳን የተባሉት እነዚህ በአገልግሎትም ሆነዉ ነገር ግን በሐሳብና በውስጣቸዉ መንፈሳቸውን ያረከሱ ሰዎች ናቸዉ፡፡ መብላት ከፈለጉ ይገረዙ የተባለዉም የሥጋ ሸለፈትን ማስወገድ ምሳሌነቱ የኃጢኣት ሸለፈትን ማለትም መንፈሳቸዉን ያረከሰዉን ነገር በንስሐ ቆርጠዉ ጥለዉ ይምጡ ማለት ነዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ይቻላል፤ ቢቀበሉትም ሕይወት ይሆናል፡፡ በኦሪቱ ‹‹ እንደ አገር ልጅም ይሆናል›› ማለትም ለሰማያዊት ሀገር ለገነት ለመንግሥተ ሰማያትም የተገባ ይሆናል ማለት ነዉና ጽድቁን ገንዘብ ያደርጋል፡፡   

2.     በአንድ ቤትም ይበላ

ሌላዉ ስለፋሲካዉ የተሰጠዉ ትእዛዝ በአንድ ቤት የመበላቱ ጉዳይ ነዉ፡፡ በዚያ ጊዜ በግብጽ እያሉ እንኳ ከአንዱ ቤት ወጥቶ እንዲሔድ አልተፈቀደም፡፡ ይህም ከላይ እንደገለጽነዉ ሥጋዉና ደሙ በአንድ ቤት በቤተ ክርስቲያን ብቻ ልንቀበለዉ እንደሚገባ የተሠጠ ትዕዛዝ በመሆኑ ነዉ፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው። እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፤ ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ።›› / መዝ 68፤ 5-6/ ሲል እንደገለጸው ምድረበዳዉ የሌሎች ነዉ፡፡ እኛ እንደተጻፈው እግዚአብሔር በቤቱ እንዲያሳድረን የእርሱንም ሥጋና ደም (የፋሲካዉን በግ) እንዲመግበን አስቀድሞ ነግሮናልና ሌላ ቦታ እንበላዉ ዘንድ ክብሩንም ከአማናዊነት ወደ ምሳሌነት እናወርደዉ ዘንድ አንገዳደረዉም፡፡ ይህ ፋሲካ የሚበላባት ቤቱም ቤተ ክርስቲያን አንዲት ብቻ ናት፡፡ የተረፈው ሥጋ እንኳ ከቤት ወጥቶ ወደ ምድረ በዳ አይጣል የተባለዉ የክርስቶስ ሥጋና ደም ከቤተ ክርስቲያን ዉጭ ሌላ ቦታ ሊጣልም ሊበላም ስለማይገባ ነዉ፡፡ አባ ጄርም ይህን በተረጎመበት ድርሳኑ የኖኅ መርከብ ዉስጥ የገቡት ብቻ ከጥፋት ዉኃ እንደዳኑ ፤ዳግመኛም በረዓብ ቤት የነበሩ ብቻ ከኢያሪኮ ጥፋት እንዳመለጡ በአንዲት ቤተ ክርስቲን ተሰባስበዉ ሥጋዉንና ደሙን የበሉ ብቻ ይድናሉ ይላል፡፡

3.     አጥንቱ መሰበር የለበትም

ስለ መሥዋዕቱ ከተሰጠዉ ትእዛዝ አንዱ አጥንቱ አይሰበር የሚለዉ ነዉ፡፡ ይህም ስለ እኛ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበዉ በግ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርፋቱና እየተገፋ በወደቀ ጊዜ፣በችንካሩም ሆነ ለንጊኖስ በጦር በወጋዉ ጊዜ ከአጥንቱ አንድም እንኳ አንደማይሰበር አስቀድሞ የተነገረ ምሳሌያዊ ትንቢት ነዉ፡፡ ይህንንም ወንጌላዊ ዮሐንስ ‹‹ ጭፍሮችም መጥተው የፊተኛውን ጭን ከእርሱም ጋር የተሰቀለውን የሌላውን ጭን ሰበሩ፤ ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤ ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ።… ይህ የሆነ። ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነዉ›› /ዮሐ 19፤ 32-36/ በማለት አረጋግጦልናል፡፡

በግብጽ የነበሩት ሕዝቡም ሙሴ እንደነገራቸዉ አድርገው ለእግዚአብሔር እንደታዘዙ ሁሉ እኛም እንዲሁ ለእግዚአብሔር በሐዋርያትና በተከታዮቻቸዉ እንደ ሰማነዉ አድርገን ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባናል፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም የምትፈጽመው ሥርዓተ አምልኮ በሙሉ እንዲህ የታዘዘውንና የተተረጎመውን (ጌታ አማነዊ ያደረገውን) ብቻ ነዉ፡፡ በርእሳችን እንደተቀመጠዉ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞን ከተለዩት በተለየዉ ቅኔያዊ መዝሙሩ በመኀልየ መኀልይ ላይ ግራዉ ከራሴ በታች ናት የሚለን ይህችን ኦሪት ነዉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን መጻሕፍተ ኦሪትን ዕቃ ቤት እንደተቀመጠ መታሰቢያ ብቻ ሳይሆን ተርጉማ አማነዊ በሆነ መንገድ የምትፈጽማት ስለሆነ ከራሴ በታች ናት አለቻት፡፡ እንዲህ የምትለዉ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ራሷ ደግሞ ክርስቶስ ነዉ፡፡ ስለዚህ ኦሪትን ‹‹ከራሴ በታች›› ስትል ሥጋዌን አስቀድማ በምሳሌ ያሳየች የትንሣኤ በዓላችንን በፋሲካ በዓሏ፣ ለመሥዋዕተ ሐዲስ ለክርስቶስ ሥጋና ደምም ምሳሌዉን ስታሳይ የቆየች ቀድማ የተላከች መመሪያና በዚያም መሠረት እንድንፈጽም እንደ ካርታ ሆና ያገለገለች ስለሆነ ከራሴ በታች ጉዝጓዜ ትራሴ ትላታለች፡፡ በሰሙነ ሕማማቱም ስትነበብ የምትሰነብተዉ ለዚህ ነዉ፡፡ መሠረትና መደላድልነቷን ትራስነቷን ልንረሳዉ አንችልምና፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ቤተ ክርስቲያን የሚያሰኛትም ይህ ሐዲስ ኪዳንን በብሉይ ኪዳን ላይ ብሉይን ከሥር ሐዲስን በላዩ ማነጽ መቻሏ ነዉ፡፡ሐዋርያዉ ቅዱስ ጳዉሎስም ‹‹በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤›› /ኤፌ 2፤ 20/ ሲል እንደገለጸዉ መሠረታችን የነቢያትም የሐዋርያትም ነዉ፡፡ ኦሪትና ነቢያትን ፈጽሞና ተርጉሞ ከሐዲስ ኪዳን ጋር ያገናኘ የማዕዘኑ ራስም እንደተባለዉ ጌታችን ነዉ፡፡ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሉቃስና ቀልዮጳ በእርሱ ትንሣኤ አላምን ብለው ከኢየሩሳሌም ወጥተዉ ወደ ኤማሁስ ሲጓዙ መንገደኛ መስሎ እየተከተለ ኦሪትንና ነቢያትን ተርጎሞላቸዋል፡፡ ወንጌላዊዉ ቅዱስ ሉቃስ ‹‹ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው›› /ሉቃ 24፤27/ ሲል እንደገለጸው በርግጥም  ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ግራው ኦሪትን አንተርሷታል፡፡ ቀኙ ወንጌልም አቅፋታለች፡፡ እውነተኛይቱና አንዲቱ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ተጠብቃ ጸንታ ትኖራለች፤ የሰሎሞን ልዩ የዝማሬ ቃልም የሚያስረዳዉ ቤተ ክርስቲያንን ግራው የተባለች አሪትን አንተርሶ ቀኙ በተባለች ወንጌል አቅፎ (በዕቅፉ ዉስጥ አድርጎ) ቤተ ክርስቲያንን የሚጠብቃት ክርስቶስ ነዉ ሲለን ነዉ፡፡ ስለዚህም በነፍስ የዕውቀት ገንዘብ የበለጸጉ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አካልነታቸዉን አውቀዉ በእንደዚህ ያለዉ በዓል ግራህ ከራሴ በታች… እያሉ አሪት የወንጌሉን ባለቤት ሙሽራውን ክርስቶስን ያመሰግኑታል፡፡ እነርሱም ራሳቸዉም የሚኖሩት በክርስቶስ የማዳን ዕቅፍ ዉስጥ ነውና፡፡ ነፍስ ኅርይት ሁሉ ለራሷም ግራ ሥጋዊነትን ከራሴ (ከሃሳቤ) በታች ጥለህልኛልና ቀኝ መንፋሳዊነትንም በትንሣኤህ አጎናጽፈኸኛልና እያለች ታመሰግነዋለች፡፡ መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞን ስለ ጥበብም ተገብቶ ግራ ሓሳርና ውርደት( በግራ መቆም) እና ቀኝ የተባለ ክብር ሽልማትም (ቁመተ የማን) ከአንተ ዘንድ ነዉና እያለም ያመሰግናል፡፡ስለዚህም በዓላችን ግራው ፋሲካን ተንተርሣ በቀኝ ትንሣኤ ክርስቶስ ታቅፋ የምትከበር የእውነተኛ ፍቅር በዓላችን ናት ማለት ነዉ፡፡

ክርስቲያኖች ሆይ በዓላችንን በዓለ ፋሲካም በዓለ ትንሣኤም የምንለዉ በእነዚህ በኦሪቱና በሐዲሱ፣ በምሳሌዉና በአማናዊዉ፣ በንባቡና በትረጓሜዉ በአጠቃላይ  በሁለቱም እጆች በግራና በቀኝ የታቀፈችና የተያዘች ስለሆነ ነዉ፡፡ በአይሁድ ፋሲካ የክርስቶስን ማዳን እንደተነገረንና በዚያ በብሉይ የነበሩት አበዉ ሁሉ ሲጠባበቁት እንደኖሩት በክርስቶስ ትንሣኤም ትንሣኤ ሙታንና (የክብርና የውርደት) ዘለለማዊ ሕይወት እንዳለ ተነግሮናል፡፡
ስለዚህም ለራሳችን የክብር ትንሣኤም እየተዘጋጀን በቀኝ ለመቆም እንዲያበቃን እየተማጸንን በደስታና በመንፈሳዊ ሐሴት እናከብረዉ ዘንድ የእርሱ ቸርነት የድንግል እናቱ አማላጂነት አይለየን፤ አሜን፡፡