READ IN PDF
አባ ሰላማ በማለት በቅዱሳን ስም እየተጠራ ቅዱሳን መላእክትን፣ እመቤታችንን እና ጻድቃንን የሚዘልፈው “አባ ሰላማ” የተሰኘው የተሐድሶ መናፍቃን ብሎግ፤ በማያፍር አንደበቱ ማኅበረ ቅዱሳንን በመሳደብ ላይ ይገኛል:: ማኅበረ ቅዱስንም “የቅዱሳኑ የስድብ በረከት ለእኔም ይድረሰኝ” በማለት ይመስለናል ለብሎጉ ምን ዓይነት መልስ ሰጥቶ አያውቅም::
“አባ ሰላማ” ብሎግ በ1992 ዓ/ም ከቤተ ክርስቲያ ተወግዘው የተለዩት የተሐድሶ መናፍቃን በድሬዳዋዎቹ ቡድን እንደሚመራ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ::
ይህ የመናፍቃኑ ብሎግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ማኅበረ ቅዱሳን ላይ በሬ ወለደ ዓይነት ወሬዎች ይዘግባል:: ሰሞኑን ከተዘገቡ የሐሰት ውንጀላዎች መካከል “ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ አባላቱን በግድ ወርሃ ጽጌ እንዲጾሙ ያዛል” የሚል ነው:: በእርግጥ ዲያቢሎስ ጾም መች ይወዳል፤ የግብር ልጆቹ ቢቃወሙም አይደንቅም:: ወርሃ ጽጌን ብዙዎች ምእመናን እና ካህናት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስደቷን በማሰብ በፈቃድ እንደሚጾሙት የሚታወቅ ነው:: እንግዲህ አንዳንድ የግቢ ጉባኤ ተማሪዎችም በፈቃድ ይጾሙታል የሚል እምነት አለን::
በአጽዋማት ወቅት በሚሰበሰበው የቁርስ ዳቦ አማካኝነት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሌለባቸው አካባቢዎች ቤተ ክርስቲያን እንደተሰሩ ሰምተናል አይተናልም:: የሰንበት ትምህርት ቤተ አዳራሽ በሌለባቸው አጥቢያዎች ደግሞ የመማርያ አዳራሾች እንደተሰሩ የአይን ምስክሮች ሲናገሩ እንሰማለን:: ታድያ ተሐድሶዎቹ ከቁርስ ዳቦ በመሸጥ የተሰበሰበው ገንዘብ “በእኛ ኪስ ለምን አልገባም” ለማለት ይመስላል “አባ ሰላማ” ብሎግ አምርሮ ተቃውሞታል::
ለመሆኑ “አባ ሰላም” ብሎግ እና ሌሎች መሰሎቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን ሚጠሉ ሰዎች እነ ማን ናቸው? ለምንስ ይጠሉታል? ብለን እንጠይቅ ይሆናል:: በአጠቃላይ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚጠሉ ሰዎች በሦስት ከፍለን እንያቸው::
፩. ማኅበረ ቅዱሳን በዓላማ እንዲጠፋ የሚፈልጉ:: እነዚህም:-
ተሐድሶ መናፍቃን ( ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ)
መናፍቃን የውጭ (“ጴንጤ”)
አክራሪ እስላሞች እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ቡድኖች የማኅበሩን አገግሎት በደንብ ጠንቅቀው ያውቁታል:: እንዲሁም ዓላማውም በሚገባ ተረድተውታል። አክራሪው እስላም በቤተ ክርስቲያን ላይ በተለያዩ ጊዜያት የሚያደርሱት ጥፋት እየተከታተለ መረጃ እየሰበሰበ እኩይ ተግባራቸውን እያጋለጣቸው ስለሆነ፤ የማኅበሩን መኖር የእግር ላይ እሳታቸው ነው። ወደፊትም ላቀዱት ጥፋት ይከታተለናል ብለው ስለደመደሙ ማኅበሩ እንዲጠፋ ደፋ ቀና ሲሉ ይታያሉ:: ማኅበረ ቅዱሳን “ኢትዮጵያን የማስለም ዓላማ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ሆኖብናል” ብለው በግልፅ በተለያዩ የእስልምና ፓል ቶክ ውይይት እየሰማናቸው ነው።
ሌሎቹ ሁለቱን የውስጥ(ተሐድሶ) እንዲሁም የውጭ መናፍቃን ግብራቸው እና ዓላማቸው ማኅበሩ በሚገባ አውቆት አጥብቆ እንደሚቃወማቸው ያውቃሉ:: ስለዚህ የተለያዩ አጋጣሚዎች በመጠቀም የማኅበረ ቅዱሳን ስም ሲያነሱት እናያቸዋለን:: ለዚሁም “አባ ሰላማ” ብሎግ ማየት በቂ ማስረጃ ነው:: ሁለቱንም የመናፍቃን ቡድን የተዋሕዶ እምነትን የማጥፋት ዘመቻቸው ማኅበረ ቅዱሳን እስካለ ድረስ ማስፈጸም አንችልም ብለው ስለወሰኑ፤ በማንኛውም መንገድ እንዲሁም ከአክራሪው እስላም ጋር በመተባበርም ቢሆን ማኅበሩን ሊያጠፉት ይፈልጋሉ።
፪. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተለያዩ ጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ሰዎች
ከአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እስከ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ድረስ በጥቅማ ጥቅም የተሳሰሩ ቡድኖች ማኅበረ ቅዱሳንን ይጠሉታል የሚል እምነት አለን:: እነዚህኞቹ በጊዜአዊ ጥቅምና ሥልጣን የሰከሩ ናችው።እነ ወይዘሮ እጅጋየሁ እና ቡድኖቻቸውም እዚህ ቡድን ላይ መድበናቸዋል:: ማኅበሩን የሚጠሉበት ዓላማቸው ደግሞ ተግባራቸውን ሥለሚቃወም ነው:: እንዲሁም ደግሞ ያጋልጠናል ብለውም ይሰጋሉ:: የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና ይከበር የሚለው ጥብቅ አቋሙ በተቃራኒው ይህን በማይፈልጉት ጥቅመኞ ማኅበሩን እንዲጠሉ አድርጓቸዋል:: ይኸው እነዚህ “ሆዳቸው አምላክ” የሆነባቸው ወገኖች ማኅበሩን ቢችሉ ለማፍረስ ነበረ፤ ነገር ግን ስላልቻሉ ስም የማጥፋት ዘመቻ ቀጥለውበታል::
፫. የማኅበሩን አገልግሎትና ዓላማ ያልተረዱ ወገኖች
እነዚህ ወገኖች ማኅበረ ቅዱሳንን በስም ብቻ ያውቁታል። የማኅበሩን ስም እንኳ የሰሙት ከተሐድሶ መናፍቃን፣ ከተለያዩ ሚድያዎች እንዲሁም ደግሞ ከአክራሪ እስላም ነው። እናም አንድ ጊዜ ብቻ የሰሙትን ወሬ ይዘው ማኅበረ ቅዱስንን ይጠሉታል። እንደው ማኅበረ ቅዱዳን ማን ነው?፤ ዓላማው ምንድ ነው? በቤተ ክርስቲያኒቱስ የትኛው መዋቅር ሥር ነው? ብሎ ለመጠየቅ ጆሮዋቸው የዘጉ አይጠፉም:: ነገር ግን ለመጠየቅ ተዘጋጅተው ምላሽ ለማግኘት አጋጣሚው ያላገኙ ወገኖች እንዳሉም እንገምታለን።
ማኅበረ ቅዱሳን አንዳንድ ለሚነሱ የስም ማጥፋት ዘመቻዎች ምላሽ ቢሰጥ መልካም ነው እንላለን:: ሐሰት ተደጋግሞ ሲነገር እውነት ይሆናል እንደሚባለው ማኅበሩ በተመለከተ የሚወጡ የሐሰት ውንጀላዎች በተቃራኒ ማሰተባበያ ቢሰጥባቸው የሚል እምነት አለን::
እግዚአብሔር ተዋሕዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን።
No comments:
Post a Comment