Sunday, 28 October 2012

የፓትርያርክ ምርጫ ሕግን በሚመለከት ቅዱስ ሲኖዶሱ በኅዳር ወር መጨረሻ ልዩ ስብሰባ ይጠራል


አርእስተ ጉዳይ፡- 
  • READ THIS ARTICLE IN PDF
  • የግብጹ ፓትርያርክ ምርጫ ልኡክ ዛሬ ማምሻውን ወደ ካይሮ ያመራል፤ በምርጫው ይሳተፋል፤
  • የጠ/ቤ/ክህነቱ ‹የጨለማ ቡድን› የተቋማዊ ለውጡን አመራር ለመቀልበስ ያደረገው ሙከራ ከሸፈ፤
  • በወኅኒ ቤት የሚገኙ መነኰሳት ቁጥር መጨመር አሳሳቢ ኾኗል፤ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ብቻ በተለያዩ ወንጀሎች ተከሰው የተፈረደባቸው ከ70 ያላነሱ ‹መነኰሳት› ይገኛሉ፤
  • ገዳማት የመነኮሳታቸውን ቁጥር ጨምሮ ዝርዝር መረጃዎቻቸውን ለአህጉረ ስብከትያሳውቃሉ፤ መነኰሳት መታወቂያ እንዲኖራቸውና ከቦታ ወደ ቦታም ያለደብዳቤ እንዳይንቀሳቀሱ ይደረጋል፤
  • ከአብነት ት/ቤቶች ጋራ የተያያዘው የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን እንቅስቃሴ በልዩ ትኩረት ክትትል ይካሄድበታል፤ የአብነት ትምህርት መለኪያ ተበጅቶለትና በየቋንቋው መምህራን ተመድበው መምህራን በየጊዜው የሚስመርቋቸው ደቀ መዛሙርት በምደባ በየአህጉረ ስብከቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እንዲመደቡ ይደረጋል፤
  • ምልአተ ጉባኤው በድሬዳዋ ሀ/ስብከትና በድሬዳዋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጸመውን ሙስናና የመልካም አስተዳደር ችግር የሚያጣራው ልኡክ በአስቸኳይ ወደ ስፍራው እንዲያመራ አዘዘ፤ የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ አባ አረጋዊ ነሞምሳ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ስም በማጥፋት የኮሚቴውን ተልእኮ የሚያደናቅፉ ሕገ ወጥ ቡድኖችን እያደራጁ ነው፤
  • የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ዛሬ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፤

 (ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 17/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶ. 27/2012)፦ ከተጀመረ ስድስተኛ ቀኑን ያስቆጠረው የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ከቀትር በኋላ እንደሚጠናቀቅ እየተጠበቀ ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በትናንት፣ ጥቅምት 16 ቀን 2005 ዓ.ም ውሎው በፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ዝግጅት ዙሪያ በመወያየት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በውሳኔው መሠረት ቀደም ሲል የሕገ ቤተ ክርስቲያኑን ማሻሻያ እንዲሠራ የተሠየመው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና የሕግ ምሁራን ኮሚቴ የፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ረቂቅንም አዘጋጅቶ በኅዳር ወር መጨረሻ ያቀርባል፡፡ የስብሰባው ምንጮች እንደገለጹት ኅዳር 30 ቀን 2005 ዓ.ም በተሻሻለው የሕገ ቤተ ክርስቲያን ረቂቅ እና በፓትርያርክ ምርጫ ሕግ ረቂቅ ሰነዶች ላይ ተወያይቶ ሕግጋቱን የሚያጸድቅ ልዩ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ የሚጠራ ይኾናል፡፡

ምልአተ ጉባኤው ዛሬ ከቀትር በኋላ እንደተጠናቀቀ በግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን 118 ፖፕ ምርጫ ላይ ተገኝቶ በምርጫው በድምፅ እንዲሳተፍ የተሠየመው አምስት አባላት የሚገኙበት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ልኡክ ማምሻውን ወደ ካይሮ እንደሚያመራ ተነግሯል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባላት ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስን፣ ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘኢየሩሳሌም፣ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ በመንበረ ፕትርክና ራሷን በምትችልበት ዋዜማ የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስን የኤጲስ ቆጶስነት (ሐምሌ 18 ቀን 1940 ዓ.ም) እና የሊቀ ጵጵስና (ጥር 6 ቀን 1943 ዓ.ም) ማዕርጋት በሰጧቸው 115ው የግብጽ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዮሳብ በኋላም ሰኔ 21 ቀን 1951 ዓ.ም ወደ ፓትርያርክነት ማዕርግ ከፍ ባደረጓቸው በ116ው የግብጽ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ 6 ሹመት ላይ ኢትዮጵያውያን አባቶች በካይሮው ቅዱስ ሲኖዶስ በመራጭነት ተወክለው መገኘታቸው ይታወቃል፡፡

ተጨማሪ ዜናዎችን ይከታተሉ
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡

3 comments:

Anonymous said...
1. Since EOTC is a sister church to the Egyptian Orthodox Church, not a subsidiary, why is participating in the vote for the election of the Egyptian Pope?!

2. Thanks to the Almighty God that, finally, EOTC's bylaws will hava thorough review. I pray that, among the many burning issues, the following will be fully addressed by the drafters:
(a) The system of electing the Patriarch so that it will be much more participatory, transparent, accountable and even better than the excellent one being applied by the Coptic church;
(b) The need to improve EOTC's entire management system so that it would render its apostolic duties in a much more efficient and effective manner including the application of the church's policies and teachings in a strategic, planned and programmed manner; the achievement of full accountability and transparency or getting rid of corruption and nepotism; the focus on women and youth; the use of international languages suh as English, French, Spanish, Arabic, and the other languages used by the UN as well as, of course, Geez; the strengthening of the church's evangelization while maintaining its basic dogma; etc. The bylaws should, in essence, transform the church into a modern spiritiual with its roots to its very beginning i.e. the Acts, chapter 8 vs 26-39.
Anonymous said...
በአውሮፓና አሜሪካ እዲሁም ኤዢያና አፍሪካ እየወጡ ቤተክርቲያን ሳትልካቸው ሳታውቃቸው ገለልተኛ ምናምን እያሉ እሚያውኩ የተመደቡብበትን ቤተክርስቲያንና ምዕመናንን ጥለው የሚኮበልሉም
መነኮሳትስ?
Nolawi said...
እውነት እንዳትወጣ አስቀድሞ የአባቶችን ስም ማጉደፍ የተለመደች ናት፣ አይይ አባ ባይሆን እንደ ጴንጤ ነገር ያደርጋቸው ነበር ፍርሃቴ እንጂ እንደዚህ ዓይነት ሙስና ውስጥ እንኳን ይዘፈቃሉ ብዬ አላሰብኩም ነበር፣ እንግዲህ እውነት ታሸንፋለች The search for truth is more important than its possession.
ጎበዝ ማለም ብቻ ሳይሆን መምታትም ያስፈልጋል፣ ውይይ የመነኮሳቱ ህግስ ማሰሪያ ገመድም ቢጨመርበት፣ ለነገሩ በደህናዎቹ ስም ስለሚጠሩ ነው እንጂ ቃሊቲ ያሉት ቢመረመሩ ይሄኔ ያልመነኮሱ አጭበርባሪዎች ናቸው፣ ደህናዎቹ ፈረደባቸው፣
እውነትም ቸር ወሬ ያሰማን፥

No comments:

Post a Comment