Friday, 12 October 2012

መስኪድ የሚያሰሩት ሚኒስትር


  • አቶ ጁነዲን ሳዶ በእናታቸው ግቢ በአርሲ ሁሩታ አርብ ገበያ አካባቢ መስኪድ እያሰሩ ነበር
(አንድ አድርገን ጥቅምት 2 2004 ዓ.ም)፡- ከሳምንታት በፊት “ቀይ መብራት” በሚል  ጽሁፍ በአሁኑ ሰዓት ሃይማኖትን ተገን አድርገው ስለሚሰሩ ስራዎች ትንሽ ለማስዳሰስ መሞከራችን የሚታወቅ ነው ፤ ብዙዎች ህዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ስራቸውን በአግባ የሚሰሩ ብዙ ባለስልጣኖች እንዳሉ ሁሉ በርካቶች ደግሞ ህዝብና መንግስት የጣለባቸውን ሃላፊነት ወደ ኋላ በማለት ለሚከተሉት ሃይማኖታቸው ቅድሚያ በመስጠት በርካታ ስራዎች መስራታቸው ይታወቃል ፤ ከነዚህ ሰዎች አንዱ በአሁኑ ጊዜ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር ኃላፊ አቶ ጁነዲን ሳዶ አንዱ ናቸው ፤ አቶ ጁነዲን ሳዶ ተወልደው ያደጉበት ቀዬ በአርሲ ክፍለ ሀገር ሁሩታ አርብ ገበያ  የገጠር አካባቢ መሆኑ ይታወቃል ፤ እኝህ ሰው በስልጣን በነበሩበት በርካታ ዓመታት በአካባቢያቸው ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ጥቂት መስኪዶችን አስገንብተዋል ፤ በቅርቡ በእናትና በአባታቸው የመኖሪያ ግቢ ውስጥ ትልቅ መስኪድ እያስገነቡ መሆናቸው ይታወቃል ፤ ይህ መስኪድ በሚሰራበት ወቅት ከዋናው የገጠር መንገድ ወደ መስኪዱ ልዩ መንገድ እንዲሰራ ከፍተኛ ግፊት ያደርጉ እንደነበር የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ ፤ በኦህዴድ ውስጥ ስራ አስፈጻሚ በመሆን እያገለገሉ የነበሩት አቶ ጁነዲን ስልጣናቸውን ያለአግባብ በመጠቀም በቅርቡ መንግስት እርምጃ ወስዶባቸዋል ፤ ከ2 ወር በፊት የመንግስት ልዩ ሃይል እኚህ ሰው ላይና በዙሪያቸው የሚገኙ ሰዎች ላይ ባደረገው ልዩ ክትትል ወንጀል አግኝቶባቸዋል፡፡ 



በተገኝው መረጃ መሰረት አቶ ጁነዲን በእናታቸው  ቃል መሠረት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ መስጅድ ለማስገንባት፣በሚኒስትርነታቸው ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ለመስጅዱ ማስጨረሻ ከሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ ዕርዳታበመጠየቃቸው፣ የመስጅዱ የመጀመሪያ ደረጃ ምርቃት ሲደረግ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ተገኝተው500 ቅዱስ ቁርአንና 50 ሺሕ ብር ዕርዳታ መስጠታቸውን ራሳቸው አቶ ጁነዲን በጻፉት ደብዳቤ መንግስት ሊያረጋግጥ ችሏል፡፡
ከሳምንታት በፊት የአቶ ጁነዲን ባለቤት ከአንድ የአረብ ኢምባሲ በሚገቡበት ወቅት የፌደራል ፖሊስ ልዩ ኃይል ከመግቢያው በር ላይ ተበታትነው ይጠብቋው ነበር ፤ እኝህ ወ/ሮ ኢምባሲው ውስጥ ገብተው ሲወጡ በእጃቸው የተገኝው ነገር ቢኖር በርካታ የእስልምና እምነት መጽሐፍቶች ፤ በ50 ሺህ ብር እና መሰል ለሌላ አላማ የሚጠቀሙባቸው ሰነዶች ይዘው ሲወጡ በፌደራል ፖሊስ አማካኝነት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፤ባለቤታቸው አምባሳደሩ የሰጡትን 50 ሺሕ ብር ለመቀበል ኤምባሲ ሄደው ተቀብለው ሲወጡ፣ ለሽብር ተግባርየሚውል ገንዘብ ተቀብለዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው እና ወደ እስር መውረዳቸውይታወሳል፡፡ አቶ ጁነዲን የሚስታቸውን መታሰር በማስመልከት የተቀበሉት ብር እናት አባቶቻው መንደር ለሚሰራው መስኪድ ማስጨረሻ መሆኑን በግልጽ ተናግረዋል ፤ ይህ ማለት አቶ ጁነዲንን እና መሰል በስልጣን ላይ የተቀመጡ መንግሥትና ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነታቸውን መወጣት ያቃታቸው ባለስልጣናት በእንደዚህ አይነት ተግባር ላይ ለመሰማራታቸው አብይ ምሳሌ ሆኖ ተመልክተናል ፤ ይህ መስኪድ በእምነቱ ሰዎች ቢሰራ ማንም ምንም ላይመስለው ይችል ይሆናል ፤ ነገር ግን ህዝብን እንዲያገለግል በመንግስትና በህዝብ የተመረጠ ባለስልጣን አማካኝነት መሰራት መቻል ግን አግባብ አይደለም ፤ አሁንም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ስልጣናቸውን ተገን አድርገው ይህን መሰል ስራ የሚሰሩ ባለስልጣናት እንደሚኖሩ ይገመታል፡፡
መንግስት አክራሪነትን እዋጋለሁ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የማይመለከታቸውን ማኅበራት ላይ እጁን ከሚጠቁምና የውሃ ወቀጣ ስራ ከሚሰራ ይልቅ ውስጡን ከእደነዚህ አይነት መሰሪ ሰዎች ቢያጸዳ መልካም ይመስለናል ፤የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ከመስከረም 21 ቀን እስከ መስከረም 24 ቀን 2005 .ባካሄደው ዓመታዊጉባዔው ላይ፣ በሟች እናታቸው መኖሪያ ላይ እያሠሩት ካለው መስጅድ ጋር በተያያዘ የተገመገሙት ሚኒስትርጁነዲን፣ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈጸማቸውንና ካሉበት ኃላፊነትና ሥልጣን አኳያ ተገቢ ያልሆነ ሥራመሥራታቸው በዋናነት እንደተገመገሙበት ታውቋ፤ በድርጅቱ ውሳኔ መሰረት ወደ ተራ አባል እንዲወርሱና እንዲያገለግሉ ተደርገዋል፡:
አቶ አሊ አብዶን የመሰለ የቀድሞ የአዲስ አበባ መስተዳደር ባለስልጣን ከተማ ከተማውን መስኪድ ሲሰሩ አቶ ጁነዲን ሳዶን የመሰሉ ባለስልጣናት ደግሞ ገጠር ገጠሩም መስኪድ በመስራት የረዥም ዓመት እቅዳቸውን ለማሳካት ሁሉም አማኝ በተቀመጠበት ወንበር የራሱን አስተዋጽኦ እያደረገ ሲያልፍ እየተመለከትን እንገኛለን፡፡  



ስድስት ኪሎ የሚገኝው የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ ሀሰን ባለቸው ሃላፊነት ምን ያህል የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ታሪክ  እየበረዙ  እንደሆነ ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን 



ቸር ሰንብቱ  

No comments:

Post a Comment