የተሃድሶያውያኑ ቀበሮ መነኩሴ
(አንድ አድርገን ሐምሌ 16 2004 ዓ.ም)፡- ትምህርተ ሃይማኖቷ እምነቷና ሥርዐቷ ምሉዕ የሆነውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ርትዕት ሃይማኖት «እናድሳለን» በሚል ስልት ወደ ውስጧ ሠርጐ በመግባት ልጆቿን እስከ ሕንፃ ቤተክርስቲያኗ እንረከባለን ይላሉ፡፡ የበግ ለምድ የለበሱ ተኩላዎቻቸውን በማሰማራት በጎቿን በኑፋቄያቸው እያሳሳቱ ከመንጠቅ፣ በተለያዩ ርዳታዎች ስም እየደለሉ ከማስኰብለል ጀምሮ፤ ትምህርተ ሃይማኖትና ሥርዐቷን በማጣጣል፣ ቅዱሳት መጻሕፍቷን በማራከስ፣ መልካም ስምና ገጽታዋን በማጠልሸት የሚያደርጉት የጥፋት ጥረታቸው ዛሬም እንደቀጠለ ነው፡፡ በእናትነት እቅፏ ውስጥ ጡቷን ጠብተው ማዕዷን ተሳትፈው አድገው፤ ነገር ግን ንጹሕ እናትነቷን ክደው በውስጧ ሆነው በኑፋቄያቸው የሚቦረቡሯት ብዙዎች ናቸው፡፡
መዝሙራትን ለማስረሳት ፤ ትውፊትን ለማቃለል ፤ የእኛነታችንን መገለጫዎች ለመሸረሽር የማያካሂዱትን የውስጥ ለውስጥ ሴራዎች ቀጥለውበታል ፤ ነገር ግን “የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።” የማቴዎስ ወንጌል 16፤18 በማለት በወንጌል የተነገረላት ቅድስት ቤተክርስትያን አሁንም አለች ወደፊትም ሳትናወጽ ትኖራለች፡፡
መዝሙራትን ለማስረሳት ፤ ትውፊትን ለማቃለል ፤ የእኛነታችንን መገለጫዎች ለመሸረሽር የማያካሂዱትን የውስጥ ለውስጥ ሴራዎች ቀጥለውበታል ፤ ነገር ግን “የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።” የማቴዎስ ወንጌል 16፤18 በማለት በወንጌል የተነገረላት ቅድስት ቤተክርስትያን አሁንም አለች ወደፊትም ሳትናወጽ ትኖራለች፡፡
ሃያ ዓመት ወደ ኋላ ሄደን ዛሬን ብንመለከት ደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ሰንበት ትምህር ቤቶች ውስጥ የነበረው የምንፍቅና እና የተሃድሶያውያን እንቅስቃሴዎች ከዛሬው እጅጉን የላቁ ነበሩ ፤ ያሬዳዊ ዜማ ተረስቶ የመናፍቃኑ መዝሙር ዜማዎች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎች አእምሯቸው ላይ የመቅረጽ ከፍተኛ ስራ የተሰራበት ጊዜ ነበር ፤ በገና ፤ ክራር ፤ ከበሮና ጸናጽል ተቀምጠው በጊታርና በፒያኖ የተተኩበት ወቅት ነበር ፤ በጊዜው ሁኔታው የተገነዘቡ ጥቂት ቤተሰቦች ልጆቻቸው ቤተክርስቲያን ሄደው የተማሩት መዝሙር አሳስቧቸው መልሰው ቤተክርስትያን ሰንበት ትምህርት ቤት ላለመላክ ለራሳቸው ቃል የገቡበት ደረጃም ደርሰው ነበር ፤ የቤተክርስቲያን ስርዓት ከስረ መሰረቱ ጠንቅቀው የሚያውቁ ቤተሰቦች ልጆቻቸው ሄደው የሚማሩት ነገር ያልጣማቸው ሰዎች ልጆቻችንን ለአውሬ በአደባባይ አንሰጥም በማለት የተናገሩበትና ሰንበት ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ የከለከሉበት ወቅት ነበር ፤ እነዚያ በዚያን ጊዜ የነበሩ እድሜያቸው ከ10 እስከ 15 የሚገመቱ የሰንበት ተማሪዎች 20 ዓመት አልፎ በጊዜው ቤተክርስትያንን ለማደስ የተሰማሩ ሰዎች ያስተማሯቸውን መዝሙሮች አሁን ላይ በ30ኛው ዓመታቸው መጀመሪያ ላይ ሙሉ ግጥሙንና ዜማውን ሲዘምሩልዎት ሲሰሙ ቤተክርስቲያን በጊዜው ምን አይነት አደጋ ላይ እንደነበረች የሚያሳይ ህያው ምስክር ከማግኝትዎ በተጨማሪ ዘመን ተሻግረው ችግሩን እንዲመለከቱ ያስችሎታል (ከቻልን ወደፊት በሰማኒያዎቹ ሲዘመሩ የነበሩ መዝሙሮች ግጥማቸውን ከነዜማዎቻቸው ለማቅረብ እንሞክራለን) ፤ በቅዱስ ሲኖዶስ ይህን ወረራ ለማስቆም በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች በጠቅላላ በወቅቱ እንዲዘጉ መታዘዙ ይታወቃል ፤ ይህ ቤተክርስቲያን የማደስ እንቅስቃሴ ከ10 ዓመት ያልበለጠ ታሪክ እንደሌለው አድርገው የሚያዩና የሚያስቡ ሰዎች አሉ ፤ እውነታው ግን ይሄ አይደለም ፤ በዚያን ሀገሪቷ ራሷ ባልተረጋጋችበት ጊዜ የተጀመረው የመበረዝ ሴራ አሁን እኛ አስከምንገኝበት ጊዜ ድረስ የሞተ በመምሰል ዳግም በመነሳት በሚመስል አካሄድ ቀጥሎ እናገኝዋለን ፤
ኦርጋንና መሰል የሙዚቃ መሳሪያዎች ሰንበት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ገብተው እግዚአብሔርን በመዝሙር ማገልገያ መሳሪያ ሆነው ነበር ፤ ይህ ኦርጋን በጊዜው አራት ኪሎ ቅድስ ስላሴ ቤተክርስትያ ውስጥም እንደነበር ይነገራል ፤ የዚያን ጊዜ ርዝራዦች አሁን ጠፉ ባይባሉም ጥቂት የማይባሉ ህዋሶች ግን በተለያዩ አድባራትና አብያተክርስቲያናት እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ፤ በዚያን ጊዜ አባ ዮናስ አዲስ አበባ ኢግዚቢሽን ማዕከል በአደባባይ ከመሰሎቹ ጋር ከመታየቱ በፊት የደብረ ብርሃንን አካባቢ የተሃድሶ እንቅስቃሴ የሚመራ የተሃድሶ ከፍተኛ ክንፍ አንቀሳቃሽና ፊት አውራሪ ሰው እነደነበረ ይታወቃል ፤
ይህን እንቅስቃሴ ጠፉ ሲባል ዳግም ብቅ በማለት የያዙትን አይዲዎሎጂ ሰዎች ዘንድ ለማስረጽና ለማስፋፋት በአሁኑ ወቅት በደብረ ብርሃን ከተማ አባ በረከት የሚባሉ ሰው ብቅ ብለዋል፡፡ አባ በረከት መጀመሪያ ጎንደር ይኖር የነበረ ከዚያም ደንጨት ዮሐንስ ገዳም ሲያገለግል የነበረ ሰው ሲሆን ከመንዝ አካባቢ እንደመጣ የጀርባ ታሪኩ ይናገራል ፤ የካቲት 2004 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረብርሐን ከተማ በደብረ ማዕዶት ቅድስት አርሴማ ገዳም በመግባት ሲያገለግል እንደነበር መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ገዳም የሚመጡ በርካታ እህቶችን በማታለል ዝሙት ለመፈጸም ሲንቀሳቀስ ስለተደረሰበት ይህን ድርጊቱን እንዲያቆም ከወንድሞች ምክር ተሰጥቶት ነበር ፤ በቤተመቅደስ ውስጥ ድፍረትና ክህደት የተሞላበት የአማኙን እምነት የሚቀንስና ለትልቅ ድፍረት የሚያደፋፍር እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ እንደነበር በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ገልጸዋል ፤ ገዳም ሲገባ አብራው የመጣች ወለተ መስቀል የምትባል መነኩሴ የነበረች ሲሆን ፤ በገዳሙ በነበረው ቆይታ ለገዳማውያን አገልጋይ ካህናት ከአንድ እናት ማህጸን የወጣን እህቴ ነች እያለ ሲያወራ ነበር ፤ ይህ ሰው አውደ ምህረት አግኝቶ የለሰለሰ የኦርቶዶክስ የሚመስል ውስጡ እሾህ የሆነ ትምህርት ባያስተምርም እንኳን ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፤ ስለ ቅዱሳን መላእክት ፤ ስለ ጻድቃን ሰማዕታት ያማልዳሉ? አያማልዱም? የሚል አርእስት በማንሳት በርካታ እህት እና ወንድሞችን ላይ ውስጥ ውስጡን ምንፍቅና ሲዘራ እንደነበር ከእሱ ጋር ከተወያዩ ጥቂት ምዕመና አማካኝነት ለማወቅ ተችሏል ፤
አባ በረከት ደብረ ብርሃን ከተማ ውስጥ በጃኬት ፤ በሱሪና በኮፍያ ከርቀት የተነሳው ፎቶ
ከዚህ በተጨማሪም ለዓመታት በሰላም በፍቅር ሲኖሩ የነበሩ መነኩሳት መሐል እሾህ ተክሎ ለመሄድ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውን ለማሻከር ያልተባለ እና ያልተደረገ ነገር እያወራ ወሬን ከአንድ ወገን ወደ ሌላ ወገን እያመላለሰ የውስጥ ሰላማቸውን ለማናጋት ስራ ሲሰራ እንደነበር አብረውት ከነበሩት ሰዎች ለማወቅ ተችሏል ፤ በስተመጨረሻም በመነኮሳት ይህ እኩይ ስራ እንደታወቀበት ቀድሞ እህቴ ነበረች ያላትን ወለተ መስቀል የተባለችውን መነኩሴ ነኝ ባይ በአደባባይ ባለቤቴ ናት በማለት በደብረ ብርሐን ከተማ አንዲት ክፍል ቤት በመከራየት አብረው ሲኖሩ እንደነበር ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ሰዎች ይስረዳሉ ፡፡ ይህ ሰው ከገዳሙ ከተባረረ በኋም ደስ ሲለው የአቡነ ተክለሃይማት ቆብና ቀሚስ በመልበስ ፤ የአባቶችን መስቀል በመያዝ የምንፍቅና ትምህርት በየጎጡ ሲሰጥ የነበረ ሲሆን ፤ አንዳንድ ጊዜ ቆብና ቀሚሱን በማውለቅ በጃኬት ፤ በሱሪና በኮት እየሆነ የተለያየ ገጽታን በመላበስ የምንፍቅና ትምህርቱን ሲያሰራጭ እንደነበር በቅርብ ሲከታተሉት ከነበሩ ሰዎች ታውቋል ፤ በአሁኑ ሰዓት ግን ቀሚሱንና ቆቡን በመጣል “በፊትም ቢሆን መነኩሴ አልነበርኩም ፤ ተሀድሶያውያን የሰጡኝን አጀንዳ ለማስፈጸም የምንቀሳቀስ ሰው ነኝ” በማለት የተሀድሶ ተቋም የሰጠውን ሴራ በማስፈጸም ላይ የሚገኝ ሰው እንደነበረ በግልጽ በራሱ አንደበት ተናግሯል ፤ እሱ ቀድሞ ባይናገር ኖሮ ገዳም ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ሲሰራ የነበረውን ስራ ኮቴውን ኮቴያቸው አድርገው የሚያደርገውን ፤ የሚሰራውን ፤ የሚያወራንና የሚያናፍሰውን ወሬ በቅርበት የሚከታተሉት ሰዎች ነበሩ ፤ ሰውየው የተከራየበትን ሰፈረ ፤ የተከራየው ቤት ቁጥር ፤ የቤት ኪራይ ክፍያ ድረስ መረጃ እንዳላቸው ለማወቅ ተችሏል ፤ ይህ መነኩሴ ነኝ ባይ ሰው ከምንጩ ለመበረዘ ገና በአስራዎቹ አድሜ ላይ በአንሳስ ማርያም የሚገኙ አብነት ተማሪዎች ጋር በመሄድ በቻለው እና ጊዜው በፈቀደለት መጠን ምንፍቅናውንና ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቱን ለማስተላለፍ መሞከሩን ካነጋገራቸው ፤ ካወያያቸው የአብነት ተማሪዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ሰው በዚህ ተግባሩ መናንያንን ከገዳም ማስወጣቱን ከመቻሉም በተጨማሪ ከ3 ቀናት በላይ በከተማዋ የሚገኙ መናፍቃን አዳራሽ ሲሰብክም ተደርሶበታል፡፡ ይህ ሁሉ ስው እንደተጋለጠበትና ሰዎች እንዳወቁበት የነቃው አቶ በረከት በአሁኑ ወቅት ከ10 ቀን በፊት ወደ ናዝሬት ማምራቱን ለማወቅ ችለናል፡፡
በየደብሮቻችን የሚመጡ ጸጉረ ልውጦችን ከቤተክርስትያኒቱ ሰበካ ጉባኤ በተጨማሪ እያንዳንዱ ምዕመን በግልጽም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሰዎቹ ትክክለኛ ቤተክርስቲያን የወከለቻቸው ወንጌልን ለማስፋት የሚጥሩ ምንፍቅና እና ኑፋቄ ያልደረሰባቸው መሆናቸውን በጊዜ ሂደት ማረጋገጥ ግድ ይለዋል ፤ ያለበለዚያ በትንሽነቷ ስትጸድቅ ዝም ያልናት ተክል አድጋ እና በቅታ ተነቀይ ብትባል ብዙዎችን ይዛ እንደምትነቀል መዘንጋት የለብንም ፤ ያለፈው ስህተታችን ለወደፊት ትምህርታችን ሊሆነን ይገባል ፤
ይህን የመሰሉ ሰዎች በቅዱስ ሲኖዶስ ቀርበው ቢወገዙም አባ ሰላማን የመሰሉ ብሎጎች ንጽህናቸውን ለመግለጽ ይታትራሉ ፤ የጻፏቸውን ማር የተቀቡ ውስጣቸው ሬት የሆኑ መጻህፍቶቻቸውን ለምን ? ብለው ሲጠይቁ እያየን ነው ፤ የቤተክርስትያኒቱ የበላይ አካል ሲኖዶስ ስራቸውን ሚዛን ላይ አስቀምጦ መለየት አለባቸው ያላቸው ሰዎችን ሲለይ ፤ የተወገዙት ሰዎች “እነ አሸናፊ ትክክል ናቸው ቅዱስ ሲኖዶስ ታሪካዊ ስህተት ሰርቷል” ይሉናል ፤ “ይህ የማህበረ ቅዱሳን ውንጀላ ነው” በማለት የዋሻ ከበሮ እየደለቁ ይገኛሉ ፤ እንደ እኛ በግንቦት ሲኖዶስ የተወገዙት ሰዎች ከቀረቡት መረጃዎች አኳያ ምንም ናቸው የሚል አስተያየት አለን ፤ ቅዱስ ሲኖዶስም ወደፊት የቀረበውን መረጃ ተምልክቶ ወደፊት ለሚነሱት ሰዎች ትምህርት የሚሰጥ ውሳኔ ያሳልፋል ብለን እንጠብቃለን ፤ በግንቦቱ ጉባኤ ከተወገዙት ይልቅ የራሳቸው ትምህር ለመወገዝ ሚዛን ላይ የሚያወጣቸውም አሉ ፤ እነዚህን የመሰሉ ሰዎች ራሳቸው ስተው ምእመኑን እንዲያስቱ መንገድ አንሰጥም ፤ እርምጃቸው እርምጃችን ሆኖ አቅማችን በፈቀደ መጠን እኩይ ስራቸውን ማድረስ ለምንችለው ምዕመን እናደርሳለን፡፡
ቤተክርስትያናችንንም እግዚአብሔር ይጠብቅልን
ለሐገራችን ሰላምን ይስጥልን
ቸር ሰንብቱ
No comments:
Post a Comment