(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 10/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 17/ 2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ በሰሜን ምዕራብ አሜሪካ በዋሺንግተን ሲያትል በሚገኙት በደብረ ሰላም ቅ/ሚካኤል እና በደብረ መድኃኒት ቅ/አማኑኤል አብያተ ክርስቲያናት በድብቅ ሊመጡ ያሸመቁትን አቡነ ፋኑኤልን ሕዝቡ በይፋ ተቃወመ፡፡ እሑድ ከቅዳሴ በኋላ ምእመናን በይፋ ባቀረቡት ጥያቄ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሕገ ወጡ ሊቀ ጳጳስ አባ ፋኑኤል ወደ አብያተ ክርስቲያናቱ እንዳይመጡ በብርቱ ተቃውሞ ቀርቧል። በሌሎች አካባቢዎች የተጀመረው “ቤተ ክርስቲያንን ከነአባ ፋኑኤል እና ከፕሮቴስታንቱ አጋራቸው ከኃ/ጊዮርጊስ ጥላሁን የመታደግ” እንቅስቃሴ በሲያትልም ተጀምሯል። “ምንም አያውቅም” እየተባለ የሚናቀው ምእመን ለቤተ ክርስቲያኑ የክፉ ቀን ደራሽ መሆኑን እና በሐዋሳ ያለው ሕዝበ ክርስቲያን እንባውና በተጋድሎው ቅ/ሲኖዶስ ኡኡታውን ሰምቶ ያገኘውን ድል በአሜሪካ የሚገኘውም ምእመን እንደሚደግመው አረጋግጧል።
እሑድ ከቅዳሴ በኋላ ማንም አልነቃብኝም በሚል የዕለቱን መዝሙር አስዘምረው፣ ሕዝቡን ለመሸኘት እና በሳምንቱ አቡነ ፋኑኤልን አምጥተው “ሰርፕራይዝ” ማድረግ የፈለጉት የደ/ሰላም ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ሰላም ቆሞስ አባ ወ/ሰማያት ከሕዝቡ ድንገት የተወረወረው “ጥያቄ አለን” የሚለው ድምጽ አስገርሟቸውም አስደንግጧቸውም ነበር። “እናንተ ወጣቶች አትረብሹ” በሚል የንቀትም ከቁብ ያለመቁጠርም ጥያቄውን አጣጥለው ለማለፍ ቢሞክሩም ሌሎች ምእመናንም ጥያቄ በማንሣታቸው “እትዉ በሰላም፤ በሰላም ሒዱ” ከተባለ በኋላ ውይይቱ በአዳራሽ ሊቀጥል ችሏል።
ጉዳዩን በከፍተኛ ምሥጢር እንደያዙት በአደባባይ ያመኑት አስተዳዳሪው “ለሰበካ ጉባኤው እንኳን ያልነገርኩት ምሥጢር እንዴት ሊታወቅ ቻለ?” በሚል ቁጭታዊ ጥያቄ አቅርበዋል። ለጊዜው አስተዳዳሪ የሌለውና በሰበካ ጉባኤ ብቻ የሚመራው እና በአባ ወልደ ሰንበት ረዥም እጅ የሚዘወረው የቅ/አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን በድብቅ አቡነ ፋኑኤልን እንዲያስመጣ እና ከዚያ ቀጥሎ ግን በቅ/ሚካኤልም እንዲገኙ፣ ሕዝቡንም በሰላ ምላሳቸው እንዲለውጡ ቀጠሮ ተይዞላቸው የነበረው የአቡነ ፋኑኤል ሥውር ዕቅድ በቅ/አማኑልም በተመሳሳይ መልኩ በተነሣ ጥያቄ ከከሸፈ በኋላ ሊቀ ጳጳሱ እንዳይመጡ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
በሲያትል የሚገኙ ምእመናን ሊቀ ጳጳሱን ለምን እንደሚቃወሙ የገለጹበትን ጽሑፍ ከዚህ በታች አእንደሚከተለው አስፍረዋል። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን::
"ሐዋርያት በሰበሰቧት በአንዲት ክብርት ቤተክርስቲያን እናምናለን::"
ጸሎተ ሀይማኖት
ሃይማኖታችንን እና የቤተክርስቲያናችንን ሥርዓት የሚጎዳ ህልውናዋን እና ጥቅሟን አደጋ ላይ የሚጥልማንኛውንም አሰራርና አካሄድን በእግዚአብሔር ስም እንቃወማለን::
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ ሲያትል ሊመጡ እንደሆነ እና ለዚህምሶስቱም አጥቢያወች እንደሚሰሩ በተጨባጭ መረጃ አረጋግጠናል:: የአቡነ ፋኑኤልን ወደ እኛ አካባቢ መምጣትአጥብቀን እንቃወማለን:: የምንቃወምባቸው ምክንያቶችም የሚከተሉት ናቸው::
1. በሃይማኖት ጉዳይ
በጥቅምትና በግንቦት 2004 ዓ/ም በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ በቤተክርስቲያንችን እና በሀማኖታችንላይ አደጋ ለማድረስ ተነሳስተው የነበሩ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን አውግዞ መለየቱ ይታወቃል:: እነዚህ ቡድኖችእና ግለሰቦችም በቤተክርስቲያን ውስጥ ተመሳስለው በመግባት ብዙ ጥፋት በማድረስ ላይ ናቸው:: አቡነፋኑኤል ግን እነዚህን ግለሰቦችን እና ቡድኖች በህቡእም በግልጽም ያበረታታሉ ይደግፋሉ በቤተክርስቲያንመዋቅር ውስጥ ቦታ እንዲኖራቸው ያደርጋሉ:: ለዚህ ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ሀዋሳ ላይ የሰሩት ስራ ነው:: ሐዋሳተመደበው ከሄዱበት ጊዘ ጀምሮ በሀገረ ስብከት በሰበካ ጉባኤ እና በሰንበት ት/ቤት ውስጥ ሲያገለግሉ የነበሩየቤተክርስቲያንን ልጆችን በመግፋት የሀይማኖት ችግር ያለባቸውን ሰወች በመተካት በሐዋሳ ውስጥ ያሉአባቶች ካህናትን እና ምዕመናን ቅስም ሰብረዋል አንገት አስደፍተዋል:: ካህናት አባቶችን በተሀድሶ አራማጆችበአደባባይ ተዋርደዋል ተሰድበዋል :: በቤተክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ የቤተክርስቲያን ያልሆነ ትምህርትእንዲሰጥ ተደርጓል:: በዚህም የተነሳ የሐዋሳ ህዝበ ክርስቲያን ደም እንባ አንብቶ እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ ድረስባደረገው ተጋድሎ ከሐዋሳ ተነስተዋል::
ሌላው በሀይማኖት ጉዳይ ላይ አቡነ ፋኑኤልን የምንቃወምበት ምክንያት ደግሞ አሁንም ከእነዚህ የተሀድሶመናፍቃን ቡድኖች ጋር ያላቸውን የአላማ ኅብረት የሚያሳየው ስራ ነው:: ይሄም በተለያዩ ጊዘያትየሚያወጧቸውን ኦፊሴላው ደብዳቤወች ቅዱሳን በሚሰደቡባቸው እመቤታችን በምትሰደብባቸው እናቤተክርስቲያን በምትዋረደባቸው የመናፍቃን ድረ-ገጾች ላይ ሲወጡ መታየታቸው ነው:: ምናልባት እርሳቸውሳያውቁ የሚደረግ ነው ሊባል ይችላል:: እርሳቸው በተደጋጋሚ የቤተክርስቲያን ማህተም ያልበት እናየእርሳቸው ፊርማ ያለበት ደብዳቤ እንዚህ ድረ-ገጾች ላይ ሲወጣ አንድ ጊዘ እንኳ ማስተባበያ አልሰጡምስራውንም አላወገዙም:: ይሄም ያላቸው የአላማ ግንኙነት እንዳይጎዳባቸው ነው::
ሌላው በሥራ አስኪያጅነት የሾሙት ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን የተበለው ግለሰብ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሌለው : በሃይማኖቱ እንከን ያለበትና ከመናፍቃኑ ጋር እየሠራ ያለ ነው:: ታዲያ እኒህ አባት ሃይማኖት ጠብቀው ማስጠበቅ እንዴት ይችላሉ ?
2. ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በተመለከተ
እስካሁን ባለው ሥርዓተ ቤተክርስቲያን አንድ አባት ወደ አንድ ሀገረ ስብከት ተመድበው ሲሄዱ ማገልገልያለባቸው ከእርሳቸው በፊት ሲያገልግሉ የነበሩት አባት በመሰረቱት ሀገረ ስብከት ውስጥ ነው:: አቡነ ፋኑኤልግን ይሄንን ሥርአት በመጣስ ከእርሳቸው በፊት የነበረውን ሀገረ ስብከት በግልጽ በአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮአላውቀውም ሀገረ ስብከትም የለም የሚል መግለጫ በመስጠት ትልቅ ስህተት ፈጽመዋል:: ለዚህም የሰጡትምላሽ ወደ አሜሪካ ስመጣ አየር ማረፊያ ላይ መጠው አልተቀበሉኝም የሚል ነው:: ነገር ግን የዲሲ እናአካባቢው ሀገረ ስብከት ካህናት እና ምእመናን በተደጋጋሚ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን ጠብቀው መዋቅርጠብቀው እስከሄዱ ድረስ አብረን ለማገልገል ዝግጁ ነን በሚል ያቀረቡላቸውን ጥሪ አልተቀበሉትም::
ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ከዚህ በፊት ባደረጓቸው ተግባራት የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር አስከብሮ ለመሄድ የነበራቸው አስተዋጽዖ አነስተኛ መሆኑንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን በመተላለፍ በፈጸሙት ተግባር የብዙዎችን ኅሊና ጎድተዋል ለማስረጃም፦
ከዚህ በፊት ያገለገሉበትና አሁንም እየመጡ የሚያርፉበት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ማስገባት ሳይችሉ መቅረታቸውን፤ ከዚህ በፊት በአሜሪካን እንዲያገለግሉ ቢመደቡም በነበራቸው ችግር ምክንያት ከካህናትና ከምእመናን ባላቸው አለመግባባት የተነሳ በቅዱስ ውሳኔ መነሣታቸውን፤ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት በመተላለፍ በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በመገኘት የሀገረ ስብከቱን መዋቅር በመናቅ ክህነት መስጠታቸውንና ቤተ ክርስቲያንም መባረካቸውን፤ ከዚህ በፊት በሰሜን አሜሪካ በመዋቅር ሥር ባለ ቤተ ክርስቲያን እንዳላገለገሉ፣ ለእንግድነት ወደ አሜሪካም በመጡበት ጊዜ ሁሉ በሀገረ ስብከቱም ሆነ በሀገረ ስብከቱ ሥር ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ተገኝተው እንደማያውቁ መጥቀስ ይቻላል::
3. መዋቅርን በተመለከተ
አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ ተመድበው እንደመጡ ያደረጉት ከሀገር ቤት የላካቸው የቅዱስ ሲኖዶስን አሰራርእና መዋቅር ተቀብለው ከሚያገለግሉ አጥቢያወች ጋር አብሮ መስራት ሳይሆን የሀገር በቱን ቅዱስ ሲኖዶስአንቀበልም መዋቅሩንም አንቀበልም የቅዱስ ፓትርያርኩን ስምም አንጠራም ከሚሉ እና ራሳቸውን ገለልተኛ ነንከሚሉ አጥቢያወች ጋር አብሮ መስራትን ነው::ይሄም ከቤተክርስቲያን መዋቅር እና ትውፊታዊ አሰራር የራቁትንወደ ቤተክርስቲያን ከማምጣት ይልቅ መለየትን ማፈንገጥን የሚያበረታታ አደገኛ ተግባር ነው::
4. ትውልድን በተመለከተ
በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የሚቆም ትውልድ በማስነሳቱ ወጣቱ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግደፋ ቀና እያለ ይገኛል:: ይሄም እግዚአብሔር የለም ከሚለው አብዮታዊ መንግስት በኋላ በጣም ትልቅ ደስታነው:: ይህ ወጣት በቤተክርስቲያን ውስጥ ህጓ እና ሥርአቷ በሚፈቅደው መሰረት በብጹአን አበው መልካምፈቃድ ቡራኬ እና መመሪያ ተሰባስቦ እያገለገለ ይገኛል:: አቡነ ፋኑኤልም ከመጡ በኋላ በተለያየ መልኩየሚያገልግሉ የአገልግሎት ማኅበራት ያናግሩን እና አብረን እናገልግል በሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርቧል::እንዲያውም እርስወ ያሉበት ድረስ የአየር ቲኬት ቆርጠን እንምጣ እና ያናግሩን ብለው እስከ መለመንምደርሰዋል:: እርሳቸው ግን አሁን በመላው አሜሪካ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው የየአጥቢያወችአገልግሎት እንዲጠናከር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ ያለውን ወጣት አልቀበልም አላውቀውም አብሬምአልሰራም ብለዋል:: ይሄ ምናልባትም ታዲያ በቤተክርስቲያን ምን አይነት ወጣት ነው የሚፈልጉት አላማቸውስምንድን ነው? ቤተክርስቲያንንስ ትውልድ አልባ ማድረግ ነው የሚፈልጉት ማለት ነው? ብለን እንድንጠይቅአስገድዶናል ::
የተወደዳችሁ ምዕመናን እኛ ይሄንን ሁሉ የምናነሳው በአቡነ ፋኑኤል ወይንም በሌላ ማንም አካል ላይ ጥላቻወይንም ቂም በቀል ኖሮን አይደለም:: አቡነ ፋኑኤልን በግል አናውቃቸውም የምናውቃቸው በእናትቤተክርስቲያናችን አማካኝነት ብፁዕ አባት ተብለው ስለተሾሙ ነው:: ነገር ግን የሚሰሩት ስራ እናትቤተክርስቲያናችንን አደጋ ላይ የሚጥል የቤተክርስቲያንን አንድነት የሚያናጋ የቤተክርስቲያንን ሰላም የሚነሳቤተክርስቲያንንም ግለሰቦች በፈልጉት መንገድ እንዲጠቀሙባት የሚያደርግ ስለሆነ ነው:: ከዚህም ባለፈ ደግሞበወጣቱ ትውልድ ላይ ያላቸው አመለካከት በጣም አደገኛ ስለሆነ እና ቤተክርስቲያንንም ትውልድ አልባእንድትሆን የሚያደርጋት ስለሆነ ነው:: ስለዚህ እኒህን ብዙ ችግር ያለባቸውን እና በብዙ አቅጣጫ ጥያቄየሚነሳባቸው አባት በአጥቢያችን መጋበዝ እና ማስተናገድ ለሚሰሩት የጥፋት ስራ እውቅና መስጠት እና ተባባሪመሆን ስለሚሆን አጥብቀን እንቃወማለን:: የቤተክርስቲያን ቅናት የሚያቃጥለን ክርስቲያኖች ሁሉ በዚህ ጉዳይላይ አባቶችንን እና የሰበካ ጉባኤ አባላትን በአንድ ድምጽ እና በህብረት በፍጹም ክርስቲያናዊ ጨዋነት እናአክብሮት ልንጠይቃቸው ይገባል እንላለን::
እግዘአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!
12 comments:
ጉዳዩን በከፍተኛ ምሥጢር እንደያዙት በአደባባይ ያመኑት አስተዳዳሪው “ለሰበካ ጉባኤው እንኳን ያልነገርኩት ምሥጢር እንዴት ሊታወቅ ቻለ?” በሚል ቁጭታዊ ጥያቄ አቅርበዋል።
ምክንያቱም ስላላመኑ::
1. ለምዕመናን ደንታ የሌላቸው ለሚያዋጡት ገንዘብ እንጂ ፡ ለቤተ ክርስቲያን በማሰብ ሃሳብ ቢያቀርቡ ምንም የማይቀበሉ::
2. ምዕመናንን በቀናነት ከማገልገል ይልቅ በቀቢጸ ተስፋ ሲመተ ጵጵስና ቅዥት ውስጥ የሚኖሩ::
3. በሲያትል አድባራት “ሊቀ ካህናት” የሚል ሹመት በአቡነ ፋኑኤል በመሾማቸው ፡ የጳጳሱ ቀኝ እጅ በመሆን የአካባቢው ጉዳይ የሚያስፈጽሙ::
4. ከኃይማኖት ይልቅ ለገዢው ፓርቲ የዘረኝነት ፖለቲካ ታማኝነታቸውን በተለያየ ጊዜ ያንጸባረቁ እንደሆነ በቅርብ የሚያውቋቸው ይመሰክራሉ::
5. ከዚህ ቀደም ይነሱ ተብለው በ2001 ዓ.ም. በፓትርያርኩ ልኡካን የተላኩ ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት ባቀረቡት ሪፖርት ቅዱስ ሲኖዶሱ ይነሱ ቢልም ነገር ግን በፓትርያርኩ ከለላ እስካሁን ያሉ:: በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያንና ምዕመናን ለሁለት እንዲከፈል ያደረጉ::
6. በእርሳቸው ዙሪያ ከአዲስ አበባ ... ሱዳን ... ሲያትል ቅዱስ አማኑኤል ... ቅዱስ ሚካኤል ... ባደረጓቸውን ቤተ ክርስቲያንን የሚያውኩ ተግባራት ዙሪያ ብዙ ማለት ይቻላል... ወደፊት በሰፊው እንመለስበታለን ... ይቆየን...
ሊቀጳጳሱ አቡነ ፋኑኤል በማንአለብኝነት መጀመሪያ አማኑኤል ከዛ ደግሞ ሚካኤል ለመምጣት አቅደው ነበር:: የትም ይምጡ የት መዋረዳቸው ግን አይቀሬ ነው:: ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ሄደው በጀርባ በር ወጥተው እንዳመለጡት እዚህም አመልጣለው ብለው አስበው ከሆነ ሃሰት ነው:: የሚመጡበት መኪናም ቢሆን የቲማቲምና የድንች መጫወቻ መሆኑ አይቀርም ልክ እንደሳቸው አባባል "This is America."