Tuesday, 23 October 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጀመረ


የሊቀ ማእምራን አበባው ይግዛው የቀብር ሥነ ሥርዐት ተፈጸመ:: 

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 12/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 22/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ የ2005 ዓ.ም ጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት ትናንት ተሲዓት በኋላ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡ በፍትሕ መንፈሳዊ አምስተኛው አንቀጽ ቁጥር 164 በታዘዘው መሠረት በዓመት ሁለት ጊዜ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ፣ ጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም የሚጀምረው ምልአተ ጉባኤው ከአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ኅልፈተ ሕይወት በኋላ የመጀመሪያው ነው፡፡ ምልአተ ጉባኤው በሥራ ላይ በሚቆይባቸው ቀናት የዕርቀ ሰላሙ ሂደት አስቸኳይ ፍጻሜ ስለሚያገኝበት ኹኔታ፣ በፓትርያርክ አመራረጥ ሕግ ረቂቅ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ካለፈው ምልአተ ጉባኤ በተላለፉ አጀንዳዎች አፈጻጸም ላይ በመወያየት ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ 31ው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለስድስት ቀናት በቆየበትና በአጠቃላይ ጉባኤው ታሪክ የተለየ ገጽታ በታየበት የስብሰባ ዝግጅት የተመከረባቸው የመዋቅር፣ የአደረጃጀት እና አሠራር ለውጥ ውሳኔ ሐሳቦች ላይም እንደሚመክር ተመልክቷል፡፡ ምልአተ ጉባኤ እንዲያጸድቀውና የሥራ መመሪያ አድርጎ እንዲያስተላልፈው አጠቃላይ ጉባኤው የውሳኔ ሐሳቡንና የአቋም መግለጫውን ለቅዱስ ሲኖዶሱ ያቀረበበት ቃለ ጉባኤ 33 ነጥቦችን እንደያዘ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የአጠቃላይ ጉባኤው የውሳኔ ሐሳብና የአቋም መግለጫ ትኩረት የሰጣቸው ነጥቦች፦

ላያቸው ተዋህዶ ፤ ውስጣቸው ተሐድሶ የሆኑ መጻህፍት



(አንድ አድርገን ጥቅምት 13 2005 ዓ.ም)፡- ባሳለፍነው ዓመት በወርሀ ግንቦት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ አንድ ወሳኝ ውሳኔ መወሰኑን ይታወቃል ፤ በውሳኔውም በርካቶች የተወገዙበት ቀሪዎቹ ደግሞ መዝገባቸው በይደር እንደቆየ የምናስታውሰው ነው ፤ በጊዜው  በፕሮቴስታንቶች እየተደገፉ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ሥርዐተ እምነት፣ ክርስቲያናዊ ትውፊትና ታሪክ በኅቡእና በገሃድ ተደራጅተው ለማፍረስና ለማፋለስ እየተንቀሳቀሱ  ድርጅቶች ፍጹም ውግዘት የሚገባቸውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ማኅበራትና ግለሰቦች በመለየት ማኅበረ ሰላማ፣ ማኅበረ በኵር፣ የምሥራች አገልግሎት፣ አንቀጸ ብርሃን፣ የቅድስት ልደታ ለማርያም መንፈሳዊ ማኅበር፣ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ ተሐድሶ ኅብረት፣ አሸናፊ መኰንን፣ አግዛቸው ተፈራ፣ ጽጌ ስጦታው እና ግርማ በቀለ የመሰሉት ሰዎችና ላያቸው ማር የተቀቡ ውስጣቸው ግን ነጣቂ የሆኑ ተቋማት ተለይተው መለየታቸው ይታወቃል፡፡

Friday, 19 October 2012

የቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት ዕውቅና እንዲያገኝ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ


በታምሩ ጽጌ(reporter)


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት መንፈሳዊ ጉዳዮችን የምትከታተልበት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት፣ ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና የሚያገኝበት ሁኔታ መመቻቸቱንና ለተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ እየተመረመረ መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ያለው ግንኙነትና እንዴት ማጣጣም እንደሚቻል ረቂቅ ሕጉ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ በትናንትናው ዕለት የተጀመረውን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ 31ኛ መደበኛ ስብሰባን አስመልክቶ የቤተክህነቱ የሕዝብ ግንኙነት መምርያ ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ፣ ‹‹ቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አላት፡፡ መንፈሳዊ ቦታ በመሆኗ ግን እስር ቤት የላትም፡፡ ፖሊስም የላትም፡፡ ፍርድ ቤቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚሠራው መንፈሳዊ ተግባራትን ነው፤›› ብለው፣ የተጋጩ ሰዎችን በእርቅና በስምምነት እንዲፈቱ ማድረግ ነው፣ ከመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ውጭ የሆነ ጉዳይ ካጋጠመ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

Thursday, 18 October 2012

‹‹የድንግሊቱ ስም››


በዲያቆን ህብረት የሺጥላ

በዚህ አጠር ያለ ጽሑፍ ውስጥ የእመቤታችንን ስም አጠራሯን ብቻ የሚመለከቱ በአጠቃላይ ሦስት መሠረታዊ ነጥቦችን እንዳስሳለን፡፡

እመቤታችን በብሉይ ኪዳን አበው ሁሉ ዘንድ በብዙ ትንቢቶችና በብዙ ኅብረ አምሳል ትነገር ነበር፡፡ በአዲስ ኪዳን ግልጥ ባለ መልኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰችው ቅዱስ ሉቃስ ስለ ብሥራተ መልአክ በተረከበት አንቀጽ ነበር፡፡ መተዋወቅ ከስም የሚጀምር በመሆኑ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ‹‹የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበረ›› ሲል የእመቤታችንን ስመ ተጸውዖ በመግለጥ ለዓለም ሁሉ ያስተዋውቃታል፡፡ (ሉቃ1.27)

1ኛ. ስሟ የተለየ ስለመሆኑ

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብሉይና በአዲስ ኪዳን ማርያም በሚለው ስም የተጠሩ ከስምንት የማያንሡ ሴቶች አሉ፡፡ የሙሴ እኅት ማርያም፣ ባለሽቱዋ ማርያም፣ መግደላዊት ማርያም፣ የቀለዮጳ ሚስት ማርያም፣ …እያሉ የሁሉንም መጠቀስ ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንዳቸውም ከድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክነት በኋላ የተሰየሙ አይደሉም፡፡ ማርያም በሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ሴቶች ሁሉ በእርሷ ዘመንና ከእርሷ በፊት የተሰየሙ ናቸው፡፡ ነገር ግን የእቤታችን ክብርና ማዕርግ /ደረጃ/ ይፋ ከሆነ በኋላ ማለትም የአምላክ እናትነቷ ከተገለጠ በኋላ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዚህ ስም የተጠራች አንዲትም ሴት የለችም፡፡ 




ቂል የያዘው ሰይፍ

(ፕሮፌሰር መስፍን ጥቅምት 2005 ዓ.ም)
በቅርቡ አቶ ስብሐት በአደረገው ቃለ መጠይቅ አዲሱጠቅላይ ሚኒስትር የተሾመው ወያኔ ዱሮምአስቦበት ወንበሩን ከአማርኛ ተናጋሪዎችናከኦርቶዶክስ አማኞች ለማጽዳት በተዘጋጀበት እቅድነበር ብሎአል፤ ልብ ላለው አነጋገሩ በሁለት በኩል ስለትያለው ቂል የያዘው ሰይፍ ነው፤ ከፊት ለፊት የተሰነዘረውአማርኛ ተናጋሪውንና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንአማኙን ለመምተር ነው፤ ቂል የሚያደርገው አማራ የሚባል ጎሣ ቢኖርም የኦርቶዶክስ ሃይማኖት በአማርኛተናጋሪዎች ታጥሮ ትግሬንና ኦሮሞን፣ ወላይታንና ጉራጌን፣ ሌሎችንም የማይነካ መስሎት ከባድ ስሕትት ላይመውደቁ ነው፤ ከሁሉም በላይ እሱን የሚያህል ሰው የተክለ ሃይማኖትን ታሪክ አለማወቁ ያሳዝናል፡፡

የቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት ዕውቅና እንዲያገኝ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ


Posted by አንድ አድርገን

በታምሩ ጽጌ(reporter)


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት መንፈሳዊ ጉዳዮችን የምትከታተልበት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት፣ ሕገ መንግሥታዊ ዕውቅና የሚያገኝበት ሁኔታ መመቻቸቱንና ለተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተመርቶ እየተመረመረ መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈሳዊ ፍርድ ቤቱ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ያለው ግንኙነትና እንዴት ማጣጣም እንደሚቻል ረቂቅ ሕጉ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ በትናንትናው ዕለት የተጀመረውን የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባዔ 31ኛ መደበኛ ስብሰባን አስመልክቶ የቤተክህነቱ የሕዝብ ግንኙነት መምርያ ኃላፊ አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ፣ ‹‹ቤተክህነት መንፈሳዊ ፍርድ ቤት አላት፡፡ መንፈሳዊ ቦታ በመሆኗ ግን እስር ቤት የላትም፡፡ ፖሊስም የላትም፡፡ ፍርድ ቤቱ አብዛኛውን ጊዜ የሚሠራው መንፈሳዊ ተግባራትን ነው፤›› ብለው፣ የተጋጩ ሰዎችን በእርቅና በስምምነት እንዲፈቱ ማድረግ ነው፣ ከመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ውጭ የሆነ ጉዳይ ካጋጠመ ወደ መደበኛ ፍርድ ቤት እንደሚወሰድ አስታውቀዋል፡፡

31ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እየተካሄደ ነው


  • ብፁዓን አባቶችን በጎጥ በመከፋፈል ቀጣዩን ፓትርያርክ በብሔር ማንነት ለማስመረጥ በየሆቴሉ፣ በየመናፈሻው እና በየግለሰቡ ቤት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ የሚገደዱበት አቋም እንዲወሰድ ለአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ ቀርቧል
  • በሪፖርት የተካተተው የዋልድባ ጉዳይ በንባብ መዘለሉ ጥያቄ አሥነስቷል
(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 7/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 17/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 31ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ ትናንት፣ ጥቅምት 6 ቀን 2005 ዓ.ም ረፋድ ላይ በመንበረ ፓትርያርኩ ጠቅላይ ጽ/ቤት አዳራሽ እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅትከአራረ ቤተ ክርስቲያን ቀጥተኛ አመራር በሚሰጣቸው የተሐድሶ መናፍቃን ግንባር ቀደም መሪዎች የተደራጁ ጥቅመኛ ቡድኖች የሽግግር ወቅት አጋጣሚውን ተጠቅመው ብፁዓን አባቶችን በጎጥ በመከፋፈል ቀጣዩን ፓትርያርክ በብሔር ማንነት ለማስመረጥ በየሆቴሉ፣ በየመናፈሻው እና በየግለሰቡ ቤት ከሚያደርጉት እንቅስቃሴ እንዲቆጠቡ የሚገደዱበት አቋም እንዲወሰድ ለአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች ጥሪ ቀርቧል፡፡

Tuesday, 16 October 2012

የየራሳቸውን “ፓትርያርክ ለመሾም” ሙከራ የሚያደርጉ …

(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 6/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 16/2012/ READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ የቤተ ክርስቲያን አባቶች አንድነት አስፈላጊነት ከምንም በላይ በሁሉም ዘንድ ትልቅ ትኩረት እየተሰጠው ነው። በአገር ውስጥም ከአገር ውጪም “አንድነት፣ እርቅ” የሚሉት ቃላት ተደጋግመው በመሰማት ላይ ናቸው። የቀጣዩ ፓትርያርኩ ጉዳይ ከእርቅ እና ከአንድነት በኋላ እንጂ በችኮላ አሁን መሆን እንደሌለበት አጽንዖት እየተሰጠው ባለው በአሁኑ ወቅት የየራሳቸውን ወገን “ፓትርያርክ” አድርገው ለማስሾም ፍላጎት አላቸው የተለያዩ አካላት፣ ቡድኖች፣ ግለሰቦች እና ስብስቦች በይፋ ብቅ ማለት ጀምረዋል። ከመንግሥት እንጀምር።

Monday, 15 October 2012

ዐቃቤ መንበሩ ከአቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት አደረጉ


(ደጀ ሰላም፤ ጥቅምት 5/2005 ዓ.ም፤ ኦክቶበር 15/2012/ READ THIS NEWS IN PDF)፦ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ከአራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተሰማ፡፡ የውይይት መሥመሩን ያመቻቸው በውግዘት በተለያዩት አባቶች መካከል ዕርቀ ሰላም ወርዶ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ አንድነት ይጠበቅ ዘንድ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው “የሰላምና አንድነት ጉባኤ” ነው፡፡ በሁለቱ አባቶች የስልክ ውይይት÷ ከዐቃቤ መንበረ ፓትርያርኩ ጋራ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፤ ከአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጋራ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ አብረው መሳተፋቸው ተነግሯል፡፡

ከተሀድሶያውያን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት አባ ናትናኤል በወንጀል ተከሰሱ






(አንድ አድርገን ጥቅምት 5 2005 ዓ.ም)፡- ባለፈው ዓመት  የሀዋሳን  ህዝብ  ሲያስለቅሱት  የነበሩት ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስትያን   አስተዳዳሪ ለአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን  አስተዳዳሪ ተደርገው  ከቤተክህነት  ተሾሙው እንደነበር በጊዜው ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል ፤ነገር ግን ህዝቡ እኝን አባት አስተዳዳሪ አድርገን አንቀበልም ብሎ እሳቸው በእግራቸው ቢመጡም በኮንትራት ታክሲ ከቤተክርስቲያን አባሯቸው ነበር ፤    በፊት በተሐድሶ እና ከፕሮቴስታንት  አራማጆች (ተስፋኪዳነምህረት ማህበር እና ከመሰሎቻቸው ) ጋር  በመሆን የእግዚአብሔርን  አውደ ምህረት  እንዲፈነጩበት ካደረጉ ሰዎች መካከል ግንባር ቀደሙን የሚይዙ ሰው ናቸው ፡፡ በጊዜው  ገንዘብ አይናቸውን አሳውሯቸው ፤  ለአውደምህረት  የማይመጥኑ ፤ ትምህርቱ  የሌላቸው  ሰዎችን በመጋበዝ ህዝቡን እዚህ  ደረጃ እንዲደርስ  ካደረኩ  ሰዎች መካከል  አንዱ ናቸው፡፡