ከብርሃን ብሂል
ከፌስቡክ ገጿ ላይ የተወሰደ
ሰሞኑን ከሀዋሳ ንፋስ ማዶ አንድ ወሬ ሰማን እነ……….ይቅርታ ጠየቁ አሉii
ማንም ሰው ስለበደሉ ይቅርታ መጠየቁ አጀብ የሚያሰኝ የሚያስመሰግንም ነው፡፡ ስንፀልይም “…..የበደሉንን ይቅር እንደምንል….. እንል የለ? ግን የሰዎቹ ጥፋት የሰው ነው ወይስ የሃይማኖት?(ሰዎቹ የበደሉት የሀዋሳን ምእመን ነው ወይስ ሃይማኖታችንን)? ታዲያ የሃይማኖት በደል በጉልበት(በሰዎች ፊት) በመንበርከክ ይቅርታ ይባላል እንዴ? የሰው በደልስ ቢሆን ልብ ካልተንበረከከ ጉልበት ቢንበረከክ ምን ዋጋ አለው፡፡ የሃይማኖት በደል ግን በኃያሉ በእግዚአብሔር ፊት እራስን አዋርዶ በንስሃ በመመለስ፣ በቀኖና ቤተክርስቲያን፣ በእግዚአብሔር ቃል…. ሂድና እራስህን ለካህን አሳይ…. እንጂ፡፡
የጠፋው፣ የተጣሰው እኮ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ሕገ እግዚአብሔር እንጂ ሕገ ሰብእ አይደለም፡፡ በእርግጥ ይቅርታው የእውነት ይቅርታ ከሆነ በአንድ ቤተክርስቲያን ጉባዔ ሳይሆን ቤተክርስቲያናችን ሥርዓት… ከዛም ምንፍቅናው እና ሕግ ጥሰቱ በተሰራጩባቸው መንገዶች ሁሉ(በሲዲ፣ በቪሲዲ፣ በመጽሐፍ፣ በቴሌቪዥ….) እንየው እንስማው፡፡
ሰውን የሰደበ በመንበርከክ ይቅርታ በእርግጥ ይቅር ይባላል፡፡ መንፈስ ቅዱስን የሰደበስ.........??????? ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናትና፡፡
ግን…… ያጠፋ ሰው ይቅር በሉኝ ይላል እንጂ ይቅር ብያችኋለሁ ይላል እንዴ???? ደፋር!!
ወደ ቤተክርስቲያን ልመለስ የሚለው ጥያቄ ዓላማው ምን ሊሆን ይችላል?? ምናልባት በመናፍቃን ጐራ ያሉትን አባላት ይዞ እና እንደገና ተመልሰን ከዚህ ቀደም ያላጠናቀቅነውን የተሀድሶ ኑፋቄ ሥራ እንቀጥላለን በማለት አድብተው የሚጠባበቁ አባላቱን ይዞ እንደሚመጣ መገመት አያስቸግርም፡፡
ምክንያቱም ቅድስት ቤተክርስቲያን ያፈነገጡ ያጠፉ ሰዎችን የምትመልስበት ሕግና ሥርዓት አላትና፡፡ ቀኖና በማይፈቅደው መሠረት ተመለስን የሚሉትና እርቅና ሰላም ሆነ እያሉ የሚነግሩንም የቤተክርስቲያንዋ አገልጋዮችም ሥርዓትዋን እንዲጠብቁና እንዲያስጠብቁ ሥልጣን ተሰጣቸው እንጂ…….
ቸር ወሬ ያሰማን፡፡
Erse berse mobochachik lemad argachiuet aydel ere nesha gebu lemen be video yetdegefe maserja atkerebum
ReplyDeleteእህታችን ሰላም፡ በቪዲዮ የተደገፈ ማስረጃ በተደጋጋሚ የቀረበበት ርዕሰ ጉዳይ ነበር። ምናልባት በጥልቀት ለመመልከት ስላልቻልሽ ይሆናል። ሌላው ይሄ የግለሰቦች ወይም የቡድኖች ጸብ ወይም "የመቦጫጨቅ" ጉዳይ አደለም። የነገሩን ጥልቀትና ክብደት ማስተዋል ከቻልሽ እጅግ ከባድ እና ታሪካዊ ስህተት የሚያሰራ ነው። ስለሆነም አንቺም ታሪካዊ ስህተት እንዳትሰሪ መጠንቀቅ ያለብሽ ይመስለኛል። ከልክ ያለፈ የዋህነት ንዝህላልነት እንጂ አስተዋይነት ሊሆን አይችልምና።
Deleteእህታችን ሰላም፡ በቪዲዮ የተደገፈ ማስረጃ በተደጋጋሚ የቀረበበት ርዕሰ ጉዳይ ነበር። ምናልባት በጥልቀት ለመመልከት ስላልቻልሽ ይሆናል። ሌላው ይሄ የግለሰቦች ወይም የቡድኖች ጸብ ወይም "የመቦጫጨቅ" ጉዳይ አደለም። የነገሩን ጥልቀትና ክብደት ማስተዋል ከቻልሽ እጅግ ከባድ እና ታሪካዊ ስህተት የሚያሰራ ነው። ስለሆነም አንቺም ታሪካዊ ስህተት እንዳትሰሪ መጠንቀቅ ያለብሽ ይመስለኛል። ከልክ ያለፈ የዋህነት ንዝህላልነት እንጂ አስተዋይነት ሊሆን አይችልምና።
ReplyDelete