በታደሰ ወርቁ ከፌስ ቡክ ገጹ ላይ የተወሰደ
ቋማዊ ለውጥ (Institutional Reform) የተቋማዊ ቀውስ መድኀን የመሆኑን ያህል ፤ውጤታማ ያለመሆኑም ተግብሮት የተቋማዊ ውድቀት አመክንዮም ነው፡፡የተቋማዊ ውድቀቱ አመክንዮም ተቋሙ ከቆመለት መሠረታዊ ግብ-ዓላማ-ተልእኮ ጋራ ሰለሚቆራኝ ክትያው ተቋማዊ ቁመናን አሳጥቶ የታሪክ ሽታ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ እንይኖረው ያደርጋል ፡፡ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ሞት በኃላ በተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች ላይ ተስፋ ያደርግነው በአንድ ጀንበር የቤ ተክህነቱ ተቋማዊ የሞራል ዝቅጠት ፈውስ ያገኛል በሚል ሳይሆን የተቋማዊ ውድቀትን አመክንዮ ተግብሮት ቀድሞ ከመረዳት ነው፡፡ከዚህ አኳያ በቤተ ክህነቱ ላዕላይና ታህታይ መዋቅር መምጣት ያለበት ተቋማዊ ለውጥ በሁለት ዳርቻዎች ሊጠቃለል ይችላል፡፡በመጠን ለውጥ (Quantitative Change)እና በዐይነት ለውጥ (Qualitative Change)፡፡
ባለፈው ዕትም በዚሁ ርዕስ ከአምስተኛው ፓትርያርከ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎሰ ሞት በኃላ ተስፋ ያደርግነው በድዩስጶራነት በሚኖሩ አባቶች እና በቅዱስ ሲኖዶስ መካከል ሲደረግ የነበረው የእርቀ ሰላም ድርድር እንዴት እና በምን መልክ እንደመከነ በዝርዝር ተመልክተናል፡፡በዚህ ዕትም የምንመለከታቸው ሁለት የመከኑ ተስፋዎችና ተግብሮታዊ ክትያዎቻቸውን እነሆ፡፡የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች!
የትኛውም ለውጥ በመጠን ለውጥ ላይ የተመሠረተ ወይም ከሱ እንደሚመነጭ የለውጥ ኀልዩት ያስረዳል፡፡ከቤተ ክህነቱ አኳያ የመጠን ለውጥ መምጣት አለበት ሲባል ቤተ ክርሰቲያኒቱ የመሠረተ እምነት ፣የሥርዐት አምልኮና ትውፊት ለውጥ ሳታደርግ ፤እነዚህኑ ተቋማዊ ዓምዶቿን ከኢትዮጵያውያን መጠነ ክበብ ወደ ቀረውም ዓለም ማስፋትየሚያስችሏትን ፖሊስዎች፣ስትራቴጂዎችና መዋቅራዊ አደረጃጀቶችን መፍጠር አለበት ማለት ነው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረትነት በመሠረተ እምነቷ፣በሥርዐተ አምልኮዋና በትውፊቷ ላይ ቅሰጣ የሚፈጽሙትን ቡድኖችና ግለሰቦች አውግዞ መለየት የሚያስችል ብቁና ፈጣን ድርጅታዊ ድርጁነት መፍጠር መቻልም የመጠን ለውጥ አንዱ ዘርፍ ነው፡፡
የዐይነት ለውጥ ( Qualitative change) በቤተ ክህነቱ በፊት ያልነበሩትን ዘመናዊ መዋቅራዊ አደረጃጀትና የሰው ኀይል ምደባ፤ግልጸኝነትና ተጠያቂነት ያለበትን የፋይናስ አሠራር ማስፈንን ያመለክታል፡፡በዚህ መሠረት ቤተ ክህነቱ በመዋቅሩ ውስጥ በሚገኙ ተቃራኒ ኀይላት ትግል የተነሣ የመጠን ለውጥ ሲያደርግ ቆይቶ በእምርታ አጠቃላይ ተቋማዊ ለውጥ ለማድረግ ወደ አዲስ ድርጅታዊ ዲዛይን መቀየርና ለዚህም የሚረዳ ከቤተ ክህነቱ ባሕርይ ጋር የተገናዘበ ስትራቴጂ ፣ፖሊሲና ዝርዝር የተግባርና የበጀት ዕቅድ ዝግጅት የሚመነጭ ሓላፊነትና ተጠያቂነት ያለበት የተቀላጠፈ አሠራር ማስፈንንም የሚገልጽ ነው የዐይነት ለውጥ፡፡እንዲህ ዐይነቱም ለውጥ ፈጽሞ ሊቀለበስ እንደማይችል ንድፈ አሰባዊ ትምህርቱ ያስረዳል፡፡ በቤተ ክህነቱ እንዲመጣ ተስፋ ያደርግነው የዐይነት ለውጥ የቤተ ክህነቱ የመጠን ለውጥ ሂደት ውጤት ሆኖ የሚፈጸመው በእምርታ ብቻ እንደሆነም አምነን ነበር፡፡ከመጠን ወደ ዐይነት የሚደረገው ሽግግር የቤተ ክህነቱ ዕድገት ሁለንተናዊ ባሕርይ አድርገን ወስደንም ነበር፡፡
ሆኖም ግን በእነዚህ ሁለት የለውጥ ወሰነ ክበብ የተመለክትነው ተቋማዊ ለውጥ የመምከኑን መንገድ የተያያዘው ይመስላል፡፡መገለጫውም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የተዘረጋው ጎጠኝነትናጥቅመኝነትን መሠረት ያደረገው የምዝበራ-ዝርፊያ-ብኩንነት ሰንሰለት፤የቤተ ክህነቱ የዘመናት ነቀዞች በአዲስ ኀይል ዳግም አንሰራርተው ስድስተኛውን ፓትርያርክ የአምስተኛው ፓትርያርክ የጥፋት ፈለግ አስቀጣይና አስዋቢ ለማድርግ ተደራጅተው መታየታቸው፤ በቀድሞ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ግዙፍ አምባገነናዊነት ተጋርደው የነበሩት ትናንሽ አምባገነን ቄብ ጳጳሳት በጥቂቱም ቢሆን በስድስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ እየተቀነቀኑ ያሉትን የተቋማዊ ለውጥ አስተሳሰቦችን የመድፈቅ አዝማሚያዎችን ማሳየታቸው፤የሰው ኀይል ምደባው አሁንም ዕውቀትን፣ክሂሎትንና መንፈሳዊነትን ሳይሆን ጎጠኝነትንና ጥቅመኝነትን መሠረት ማድረጉ ናቸው፡፡
የዚህም ምክንያቱ ሦስት ነው፡፡የመጀመርያው ገዥው ፓርቲ ነው፡፡ሥርዐቱ ከተጠናወተው የጠቅላይነት ባሕርይው የተነሣ ተቋማዊ ነጻነቷን ያረጋገጠችና መሠረተ ጽኑ ቤተ ክርስቲያን ማየት አይፈልግም፡፡በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚካሄዱትን የተቋማዊ ለውጥ ሥራዎችን ለሥርዐቱ እንደ ስጋት ሰለሚመለከተው ከደጋፍነቱ ይልቅ አደናቃፊነቱን በተግባር አረጋግጧ፡፡የ1990ዓ.ም እና የ2001ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ እንቅስቃሴና የሥርዐቱን ምላሽ ማስታወስ በቂ ነው፡የቤተ ክህነቱን“ መሶብ ተሳላሚ” ሹማምንትና የወሬ ምስለኒዎች ከፊት በመወደር ርእሷ ክርስቶስ የሆነችውን የእውነትና የፍትሕ ግምጃ ቤት-ቤተ ክርስቲያንን የሥርዐቱ ወንበር ተሳላሚ ያደረጋትን የበሰበሰ አሠራር እንዲቀጥል የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች አደናቃፊነቱን ከእርቀ ሠላሙም ይልቅ በስድስተኛው ፓትርያርክ ቅድመና ድኀረ ምርጫ አረጋግጧል፡፡
በተለይም የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮችን በማስቀጠል ረገድ ርእይውና ገቱ ሊኖራቸው ይችል የነበሩትን ተፉካካር አባቶች ከዕጩነት በተባባሪ የምርጫ አስፈጻሚዎቹ በኩል እንዲውገዱ በማድርግ በአመራር ዳተኝነታቸውና በሁሉም ይሁንነትየሚታወቁትን አባት ያለተወዳዳሪ ማለት በሚቻልበት ደረጃ እንዲሰየሙ ማድረጉን ስንረዳ ደግሞከፖለቲካዊ ፍላጉት ባሻገር ሃይማኖታዊ ፍላጉት መኖሩንም እናረጋግጣለን፡፡በማሳያነት ዘውትር በፖለቲካዊ ቁርጠኝነት ሽፋን ሃይማኖታዊ ፍላጉታቸውን በቤተ ክርስቲያናችን ለመጫን በመሞከር የሚታወቁትን የፌደራል ጉዳዬች ሚኒስቴር ሚንስትር የሆኑትን በአንዳንዶቹ ጳጳሳት “ፓስተር” የሚባሉትን ዶክተር ሽፈራው ተክለ ማርያምን ጠቅሰን እንለፍ፡፡
ሁለተኛው “የአሸናፊዎች ደንገጡር” የሆኑ ማኀበራት ናቸው ፡፡የማኀበራቱ መገለጫ ጠባይ የሆነው ቅናዐተ ቤተ ክርስቲያን የወለደው ሰማእትነት እየነጠፈ የፍርሃት ተገዥነት ፤የሠላም ጊዜ ወዳጅ በመሆን በትግል ወቅት የሚከዶ፤እንዲሁም የያዙትን አቋም የሚተው ብቻ ሳይሆኑ ወደፊት ይህን አቋም አራምደው ነበር ተብለው እንዳይጠረጠሩ የጊዜው አድኀሮት ኀይላት መሣሪያ ወደ መሆን ተሸጋግረዋል፡፡
የጽናት አልበኝነት(Philistinism) ተግብሮት በሆነው ተንበርካኪነት የተነሣ ለተቋማዊ ለውጡ‹ የሐሞት ጠጠር› የሆኑም ይመስላሉ፡፡በሚያሳዬት ለዘብተኛ አቋም እና ተልመጥማጭ መርሕ የተነሣ የተቋማዊ ለውጡ ደጋፊዎች ሆነው አልተገኙም ፡፡እንደውም የረዥምና የአጭር ጊዜ መሪ ዕቅድ ነድፈው እየወደቀ ያለውን ቤተ ክህነት ሊታደጉት ሲገባ ለሥርዐቱ ያላቸውን ታማኝነት ለማረጋገጥ በሚመስል አኳኃን ተቋማዊ ለውጡ በሥርዐቱ ችሮታና መጠነ ውሳኔ ብቻ እንዲመጣ ፈቅደው ተቀምጠዋል፡፡ከሥርዐቱ ይሁንታ ውጪ የሚደረጉ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን ለመደግፍ ዝግጁ አይደሉም፡፡ ለዚህም መጀመሪያ ተሳትፈውበት በኃላ የሥርዐቱ ፊት መገርጣት ሲጀምር ወደ ኃላ ያፈገፈጉበትን የ2001 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስን የለውጥ እንቅስቃሴ ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡በዚህም የተነሣ የብዙዎቹን የለውጥ አራማጆችን ቅስም በመስበር በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚኖሩ እንጂ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የማይኖሩ ይሆኑን ?እንድንልም አድርገውናል፡፡
የተቋማዊ ለውጡ ጅምሮች መምከን ሕመም የሚሰማን አንዳንዶቹ ማኀበራት በጥራትና በቅልጥፍና ተቋማዊ ለውጡን በመምራት ተዋናይ ሊሆኑ የሚችሉ አንጋፋና ወጣት ምሁራን ስብስብ መሆናቸውን ስናስብ ነው፡፡አንዳንዶቹ ማኀበራት ምእመኑን አንቀሳቅሰው ዕወቅና በአገኙባቸው አህጉረ ስብከት ሥር ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት በልማትም ሆነ በሐዋርያዊ ተልእኮ ውጤታማ አድርገው ማየታችንነው፡፡ እነዚህ ማኅበራት ገዳማትና አብነት ትምህርት ቤቶች ላይ ለውጠው ያሳዬን ብዙ ነገሮች አሉና፡፡እነዚያን አስቸጋር ችግሮች ለውጠው ያሳዬን ማኀበራት ተቋማዊ ለውጥ ላይ ሲንሸራተቱ እና የብዙዎች ተስፋ በእነዚህ ማኀበራት ላይ መሆኑን ስንመለከት ታሪካዊ ተጠያቂነታቸውን ከማጉላቱም በላይ የለውጡ ተስፋ እየመከነ መሆኑን እንረዳለን፡፡ምእመኑ እነርሱ አሉ በሚል ራሱን ችሎ የለውጡ ተዋናይ እንዳይሆን ግርዶሽ ሆነዋልና፡፡
ከዚሁ ጋራ በመሥራ ቤታቸው በሚሠሩት ሥራ ውጤታማነት ሳይሆን በየደረጃው በተቋቋሙ ማኀበራት ውስጥ የሥርዐቱን ፖለቲካዊ ጥቅሞች በማስጠበቅና በመከባከብ በሚኖራቸው ሚና የሚገመገሙት ጥቂት የየማኀበራቱ ጉምቱ ሹማምንት አድኀራዊ መስመራዊነት ሲደመርበት በጥቂት ዓመታት ውስጥ አይደለም በተግባር በአስተሳሰብ ደረጃ ለውጥን የሚያቀነቅን ትውልድ ከነዚህ ማኀበራት ማግኝት ዘበት ይሆናል፡፡
ሦስተኛው የቤተ ክህነቱ ላዕላይና ታህታይ መዋቅር ሹማምንት ናቸው፡፡የነቢዩ ዳንኤል በንጽሕና ፣በቅድስናና በታማኝነት በዳርዬስ ቤተ መንግሥት መኖር የሌሎቹን የዳርዬስን ሹማምንት ሥርዓት አልበኝነት ፣ሃይማኖት ቢስነት፣ቅጥፈት እንደገለጠው ሁሉ ፤በቤተ ክህነቱ የሚካሄደው ተቋማዊ ለውጥን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን ብቁና ታማኝ የሰው ኀይል ምደባ፣መልካም አስተዳደር፣ግልጸኝትናተጠያቂነት ያለበት አሠራር የቤተ ክህነቱን ላዕላይና ታህታይ መዋቅር ሹማምንትን ሥርዐት አልበኝነት፣አቅመ ቢስነት፣ቀጣፍነትና ኢ ሃማኖተኝነት በመግለጥ ቦታ ማሳጣቱ አይቀርም ፡፡
በዚህም የተነሣ የተቋማዊ ለውጡ እንቀፋት የመሆኑን መንገድ ተያይዘውታል፡፡በቅርቡ የሆነ አንድ ምሳሌ ላንሳ፡፡ስድስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያና የደርጅት ሓላፊዎችን ያነጋግራሉ፡፡ቅዱስነታቸው በንግግራቸው መሓል “ የቤተ ክህነቱን የሰው ኀይል ዘመናዊ ትምህርት በተማሩ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ማደራጀትያስፈልጋል፡፡ዘመኑን ዋጅቱ ቤተ ክርስቲያኒቱን በቅንነትና፣በታማኝነት ና በሃይማኖት በማገልገል አንድ ርምጃ ወደ ፊትማራመድ ያስፈልጋል፡፡ ”ይላሉ፡፡የሌሎች መምጣትና ይህን ተከትሉ የሚፈጠረው በሥርዐት መመራት ራስ ምታት የሆነባቸውና የዘውትር የተቋማዊ ለውጥ ተጻባይ የሆኑ ግለሰቦች ብድግ አሉና ለአለፉት ሃያ ዓመታት ቤተ ክርስቲያኒቱን እንዲደቁሱ ፈቀደውላቸው የነበሩትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን እየከሰሱ“ … ለዚህች ቤተ ክርስቲያን አደጋው የማኅበራት መብዛት ነው፡፡…ቅዱስነቱ ከውጭ ሌላ ሰው ማምጣት አያስፈልግም ፡፡እዚሁ ግቢ ውስጥ ባለድግሪዎች አሉ፡፡እነርሱ ይበቃሉ፡፡ …” በማለት በሐሰት የተለወሰ የተቋማዊ ለውጥ አደናቃፊነታቸውን ከወዲሁ አረጋገጡ፡፡
በርግጥ እነዚህ ሹማምንት ሓላፍነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ፤የሃይማኖት ነቀፋ ያለባቸው፤ጥረውና ግረው መኖር ሳይሆን ከሚመጣው ፓትርያርክ ጋር ተጣብቀው ቤተ ክርስቲያኒቱን መምጠጥን ሥራዬ ብለው የተያያዙ ናቸው፡፡እነዚሁ ሰዎች የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ ለውጥ ለመደፍጠጥ የራሰቸውን ፍላጉት በሥርዐቱ ፍላጉት በመቀንበብ በተለያዬ ጊዜያት የተሞከሩ የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮችን አደፍነዋል፡፡ለዚህም በቀድሞ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩት በአቶ ልዑል ሰገድ ግርማ እና በአስተዳደርና አቅም ግንባታ መምሪያ ሓለፊ በነበሩት በአቶ በድሉ አሰፋ የተቀነቀኑ የለውጥ አሳቡችን ከማዳፈናቸውም በላይ በእነዚህ ሰዎች ላይ ያሳደሞትን አድማ የምናስታውሰው ነው፡፡
ከአምስተኛው ፓትርያርክ ሞት በኃላ ተስፋ ያደርግነው ተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች ሥርዐቱ ለፈቃዱ መጫኛነት ስለማይመቸው፤ የአሸናፊዎቸ ደንገጡር ማኀበራት ከርደተ ልቡናና ከተልመጥመጭነታቸው የተነሣ፤የቤተ ክህነቱ ሹማምንት እበላ ባይነት በወለደው ግትርነት የተነሣ የለውጥ ተስፋችንን አምክነው በጨለማ እያዳከሩን ነው፡፡
የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊነት ?
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ትባላለቸ ፡፡ይኸውም ከጌታ ጀምሮ ለዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት፣ለስባ ሁለቱ አርድእት፣ለሰባቱ ዲያቆናት በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በአንብሮተ እድ ሲወርድ ሲዋረድ በውርስ የመጣውን ሐዋርያዊ ሥልጣንናተልእኮን ገንዘብ በማድረጓ ነው፡፡ቤተ ክርስቲያናችን ጥምቀትን ሐዋርያት ከሾሟቸው ከስባቱ ዲያቆናት አንዱ ከሆነው ከፊልጶስ አግኝታና በሐዋርያዊ ትውፊት ላይ የተመሠረተች፤በሐዋርያዊ መንበር ላይ የምትገኝ፤የክርስቶስን ትምህርትና የሐዋርያትን ሃይማኖት ሰይፋለስ በትክክል እንዳለ የምታስጠብቅ እውነተኛ ቤተክርስቲያን በመሆኗም ነው፡፡/ሐዋ 6 5 ፤8 26 ፤ኤፌ 2 20/
መዓረገ ጵጵስናውም በዚሁ ሐዋርያዊ ውርስ መሠረትነት ከሦስት መቶ ዐሥራ ስምንቱ ሊቃውንት ከእለ አስክንድሮስ ጋር በመሆን በመሪና አስተባባሪ ከነበረው ከቅዱስ አትናቴዎስ ከመንበረ ማርቆስ ወንጌላዊው ምንጭ የተቀዳ ነው፡፡በዚህም የተነሣ ከዚህ መዓረግ የደረስ መነኮስ በሐዋርያት መንበር ላይ የተቀመጠ ስለሆነ ሥልጣነ ክህነቱ ምሉዕ ነው፡፡አይከፈልበትም፡፡ሐዋርያዊ ትውፊት ያለው ፣ ሐዋርያትን መስሎ ፣ ሐዋርያትን አኸሎ የሚሠራና የክርስቶስ እንደ ራሴና ባለሙሉ ሥልጣን ሰለሆነ በቤተ ክርስቲያን ከፍተኛውን መዓረግ ይይዛል፡፡ ሥልጣነ ክህነትም ከእርሱ ብቻ በምልዓት ይገኛል፡፡
ፕትርክና ደግሞ በዚህ ሐዋርያዊ መንበር ላይ ተገኝቶ ሐዋርያትን መስሎና አኸሎ በሐዋርያት ትውፊት ያገለግል የነበረ ጳጳስ ወይም አልፉ አልፉ ለመነኮስ የሚሰጥ ርእሰ አበውነት ነው፡፡የዚህንም ሹመት ሐዋርያዊነት ከምርጫ ካርድ ይልቅ ዕጣ ያጎላዋል፡፡የሐዋርያት ትውፊትም ይኸው ነውና፡፡
የአንድ ፓትርያርክ ሢመት ቀኖናዊነት የሚመነጨው የኤጲስ ቆጶሳቱን ይሁንታ በማግኘቱ ብቻ ሳይሆን ተሿሚውም ሆነ ሿሚው ቅዱስ ሲኖዱስ የሹመቱን ሒደት ሐዋርያዊ ማድርጉም ጭምር ነው፡፡ከዚህ አኳያ የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊ ነው ወይስ አይደለም ስንል መነሻችን የመጨረሻ ውጤቱ ብቻ ሳይሆን ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ ያለው ሒደትም ቀኖናዊ መሆኑ ወይም አለመሆኑም ጭምር ነው፡፡
ከመጀመሪያው በተበላሸና በኢ ቀኖናዊ ሒደት ውስጥ ያለፈ ምርጫ ምንም ቢሆን የመጨረሻ ውጤቱም ቀኖናዊ ሊሆን አይችልም፡፡ቅዱስ ሲኖዶስ የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊነትን ለማረጋገጥ መጫወት ያለበትን ግንባር ቀደም ሚና አልተጫወትም ፡፡ከዝግጅቱ አንስቶ እስከ ምርጫው የመጨረሻ ውጤት ድረስ ያለው መላ ሒደት ቀኖናዊ ሆኖ እንዲዘልቅ ማድረግ ሲገባው አላደረግም፡፡ምርጫው ሐዋርያዊና ቀኖናዊ ሊሆን የሚችለው ለሁሉም ዕጩዎችእኩል እንዲያገለግል ሆኖ የተቀረጸ የምርጫ ሕገ ደንብ ሲከበርና ሥራ ላይ ሲውል ነው፡፡ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው የምርጫ ሕገ ደንብ ከተጣሰ ምርጫው ቀኖናዊ ሆኖ ሊካሔድ አይችልም፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በጋራም ሆነ በተናጠል እንዲሁም የአስማራጭ ኮሚቴ አባላት ሐዋርያዊ የምርጫ ሥርዐትና በቅዱስ ስኖዶስ ምልዐት ጉባኤ የተደነገገው የምርጫ ሕገ ደንብ በጥብቅ አክብረውና አስከበረው መንቀሳቀስ ይገባቸው ነበር፡፡የምርጫውን ቀኖናዊነት የሚያሳጡ ማናቸውንም አዝማሚያዎችና ተግባራትን መቃወምና ለተፈጸመው ግድፈት ተመጣጣኝ ተጠያቂነት እንዲኖር ማድረግ ነበረባቸው፡፡ይኸን ሲያደርጉ ግን አልታዬም፡፡
እንደውም የምርጫው ቀኖናዊነት ጥያቄ ውስጥ መግባት የጀመረው አስመራጭ ኮሚቴው የምርጫውን ሕገ ደንብ አክብሩ ባለመንቀሳቀሱ እና ቅዱስ ሲኖዶስም ያወጣውን የምርጫ ሕገ ደንብ አክብሩ ማስከበር ባለመቻሉ ነው፡፡የተጣሱትም የምርጫ ሕገ ደንብ አንቀጾች፤ በአንቀጽ አምስት በንዑስ ቁጥር አንድ የተመለከተው ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ የሚለው እና በአንቀጽ ስድስት ንዑስ ቁጥር 2| ሰላይ የተመለከተውን የዕጩዎች ስም ዝርዝር ከትምህርት ደረጃቸው፤ችሎታቸውውና ልምዳቸው ጋር ለዐሥራአምስት ቀናት ለሕዝብ ይፋ ይሆናል፡፡በእነዚህ ቀናት ውስጥም በዕጩዎቹ ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ካሉ ኮሚቴውይቀበላል የሚለው ነው፡፡
ከዚህ ሲቀጥልም ገዥው ፓርቲ አስመራጭ ኮሚቴውም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ሥራቸውን በገለልተኝነትና በነጻነት የሚሠሩበትን ሁኔታ እንደ መንግሥት ማመቻቸት ሲገባውና የእነዚህን አካላት ተቋማዊ ነጻነት የሚጋፉ ተግባራትን ማስወገድ ሲኖርበት የመጀመሪያው ተጋፊ በመሆን የስድሰተኛውን ፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊነት ፈተና ውስጥ ጨመረው፡፡
የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊነት እውን የሚሆነው ምርጫው ነጻና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ሲከናወንና አምስቱም ዕጩዎች እኩል የሚስተናገዱበትና የሚገለገሉበት አመቺ የውድድር ሁኔታ ሲፈጠር መሆኑ እየታወቀ በገዥው ፓርቲ ይህንን የሚጻረሩ ተግባራት ተፈጽመዋል፡፡ለመራጭነት የተመዘገበውን መራጭ ከመራጭነት እንዲወጣ በማድረግናሥርዐቱ የሚፈልገውን አባት እንዲመርጥ የተለያዩ አስተዳደራዊና ማኀበራዊ ተጽዕኖዎችን እንዲደርስበት አድርጓል፡፡መራጩ ወደ ምርጫው አዳራሽ ሲመጣ ማንን መምረጥ እንዳለበት ከእግዚ አብሔርና ከ ሕሊናው ጋር ወስኖ እንደ ሚመጣ እየታወቀ ሲቪል በለበሱ የደኀንነት ሰዎች የመራጩን ውሳኔ የሚያዛቡና መራጩ አስተያየቱን እንዲ ቀይር ለማድረ ግ የተለያዬ የወከባ ሥራዎችን እንዲ ሠሩ ተደርጓል መባሉ በራሱ ያማል፡፡በዚህም የተነሣ በፍትሕ መንፈሳዊ “ በዚህ ዓለም መኳንንት ቢረዳ ከነርሱም ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን ቢሾም ይሻር፡፡ እርሱና ግብረአበሮቹ ሁሉ ይለዩ ፡፡ ” ተብሎ የተደነገገው ቀኖና ተጥሷል፡፡/ፍ.መ 5 175/
በድምፅ አሰጣጥ ሒደት የመራጩን በነጻ የመምረጥ ቀኖናዊ መብት የሚጋፉ ተግባራት በየትኛውም አካል እንዳይፈጸም ጥበቃ ማድረግ የሚገባው መንግሥት አሁን የተሰየሙትን አባት አሸናፊነት ለማረጋገጥ ሲል ከአጥፊዎቹ ጋር ተሰልፉ ታይቷል፡፡ የቤተ ክህነቱ የጥፋት ግንባሮች በአምስተኛው ዘመነ ፕትርከና የነበራቸውን ተጠቃሚነት አሁንም በስድስተኛው ዘመነ ፕትርክና ለማስቀጠል ራሳቸውን በሥርዐቱ ፍላጉት ሸሽገው ከምርጫው ሕገ ደንብ ውጭ መንቀሳቀሳቸው ሳያንስ በተለያዩ ስሜቶች ተገፋፍተው ከእነርሱ ጋር የወገኑትን አካላት ለዚሁ ኢ ቀኖናዊ ድርጊት አሰልፈውም ነበር፡፡ ማንኛውም ነጻና ቀኖናዊ ምርጫን የሚያደናቅፍ ወይም የሚጉዳ ድርጊት ሁሉ የተመራጩን አባት የመንበረ ሐዋርያት ወራሽነትና ቀኖናዊ ቅቡልነት ያሳጣል፡፡መራጩ በነጻነት እንዳይመርጥና የምርጫ ሒደቱ በሕጉ መሠረት እንዳይጠናቀቅ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ እንቅፋት መፍጠር የሐዋርያትንና ሠልስቱ ምእትን ውሳኔ ከአለመቀበልም ባሻገር በመንፈስ ቅዱስ የሚመራውን የሐዋርያት መንበር ወራሽ የሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ይግባኝ የሌለውን ወሳኔ አለመቀበልነው፡፡
የትኛውም የቤተ ክርስቲያኒቱ አካልም ሆነ መንግሥት ምርጫው ቀኖናዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ነበረባቸው የምንለው ለምርጫው ሥነ ሥርዐት ጥሩ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ነጻ፣ቀኖናዊና ሐዋርያዊ ቅቡልነት የሚያመጣ እና ሐዋርያዊ መንበር ወራሽነት የቤተ ክርስቲያናችን የአሐቲነት የማዕዘን ድንጋይ በመሆኑም ጭምር ነው፡፡
ቀኖናዊ ምርጫና የምርጫ ሒደት የመንበረ ሐዋርያት ወራሽነት ትእምርት ሲሆን በኢ ቀኖናዊ አኳኃን የሚካሔድና የሚጠናቀቅ ምርጫ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽነትን የሚያሳጣ ነው፡፡ይህም ብቻ ሳይሆን በቤተ ክርስቲያናችን የተረጋጋና ሠላማዊ አሐቲነት እንዳይኖር እንቅፋት መሆኑም አይቀርም፡፡ከዚህ ቀኖናዊ አስተሳሰብ አኳያ የስድስተኛው ፓትርያርክ ምርጫና የምርጫ ሒደት ላይ ችግሮ እንዳይፈጠሩ ጥንቃቄ መደረግ ነበረበት፡፡ግን አልሆነም፡፡በዚህም ምክንያት ስድስተኛው ፓትርያርክ በኢ ቀኖናዊነት ሢመተ ፕትርክና ከምንፈርጃቸው አበው መካከል አንዱ ሆኑ፡፡የሚያሳዝን ዕድል ይሔ ነው፡፡ፍትሕ መንፈሳዊ“በሸፍጥ ምርጫ በመንበር ላይየሚቀመጥ ምቱር ነው፡፡”እንዲል፡፡ /ፍ.አ. 5/17
ክትያዊ ተግብሮቱ ወዴት ሊያመራ ይችላል ?
በተመለከትናቸው ምክንያቶች እርቀ ሠላም-ተቋማዊ ለውጥ-የፓትርያርክምርጫ መክነዋል፡፡የእርቀ ሠላሙ ድርድርበመምከኑ መዋቅራዊ አሐቲነትን አጣን፤የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች በመዳፈኑ ዘመኑን የዋጀ አሠራር አጣን፤የፓትርያርክ ምርጫው በመደበጨቱ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽነትን አጣን፡፡ችግሩን እነዚህን ብቻ በማጣት የምንወጣው አይደለም፡፡የየራሳቸው ክትያዎች አሏቸው፡፡
እርቀ ሠላሙ በውጤት ደረጃ የሚያመጣውን አሐቲነት ማጣታችን በኢትዮጵያ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ እና በድዮስጶራነት በሚኖሩ አባቶች መካከል ያለውን ቀኖና ተጥሷል -አልተጣስም ልዬነት ወደ ሃይማኖት ልዬነት እንዲመራ የሚያደርግ ይመስለኛል ፡፡የዚህም መነሻ በዋነኝነት ሦስት ነው ፡፡የመጀመሪያው በድዮስጶራነት ያሉት አባቶች ራሳቸውን እንደ አንድ ሉአላዊ አገር ሲኖዱስ በመውሰድ በዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት አባልነት ለመመዝገብ የሚያደርጉት ጥረት፤ሁለተኛው የተለያዬ ቤተ ክህነታዊ አደረጃጀቶችን በመፍጠር በየደረጃው በሓለፊነት የሚቀመጡ ጳጳሳትንና ጥቁር ራሶችን የመሾም ዕቅድ መያዛቸው፤ሦስተኛ እንዲ ዐይነቱን አጋጣሚ ጠልፉ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ተልእኮ ማስፈጸሚያነት መጠቀም በሚችሉ የተሐድሶ ሕዋስ ተጽዕኖ ሥር መውደቃቸው እና በሃይማኖት ሕጸጽ በሚታሙ አበው ጳጳሳት መወረራቸው ነው፡፡
የተቋማዊ ለውጥ ጅምር ተስፋዎች መዳፈን ቤተ ክህነቱን ለተቋማዊ ቀውስ ይዳርገዋል፡፡ይህ መሆኑ ደግሞ ቤተ ክርስቲያኒቱ መደበኛ ተልእኮዋን ለመወጣ እንቅፋት ሰለሚሆንባት ከምዕመናን መነጠል እንዲደርስባት ያደርጋል፡፡በዚህም የተነሣ ቤተ ክርስቲያናችን ማቆሚያ ወደሌላቸው እና ጎጠኝነትንና ጥቅመኝነትን መሠረት ወደ አደረጉ ካህን መር ወደ ሆኑ ብጥበጦችና አመጾች ልታመራ ትእላለች፡፡ በዚህ ወቅት የጳጳሳቱ ዕጣ ፋንታ የሚሆነው ከዛሬ መቶ ዓመት በፊት የግሪክና የራሻ ኦርቶ ዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ጳጳሳት የተጎነጩትን ውርደት መጉንጨት ይሆናል፡፡ ከጳጳሳቱ መካከል ደግሞ እንደ እነርሱ ችግሮችን በአግባቡ ተረድቶና ተግብሮታቸውን በበቂ ሁኔታ ተንትኖ መፍትሔ ላይ የሚያተኮር አባት ሰለማይገኝ ቤተ ክርስቲያኒቱ መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ እቢተኝነትን ልታስተናግድ ትችላለች፡፡የካህናቱንም ሆነ የምዕመናኑን እንቢተኝነት በተደራጀና ተፈለጊውን ለውጥ ማምጣት በሚያስችል አኳኃን የሚመራ ድርጁ ኀይል ሰለማይኖር ቤተ ክርስያኒቱ በመንግሥታዊ ፍላጉት ሃይማኖታዊ ፍላጉታቸውን በሚያስፈጽሙ ኀይላት መዳፍ ሥር ልትወድቅ ትችላለች፡፡የችግሩም አፈታት ከጎጠኝነትንና ጥቅመኝነትን ጋር ሰለሚለወስ በሌላው ደህና ናቸው የሚባሉ ጳጳሳትን ለሁለት ሰለሚከፍል የተሐድሶ መናፍቃኑ የረጅም ጊዜ ዕቅድ ግቡን እንዲመታ ያግዘዋል፡፡
ሥርዐቱም እንደ ሙስሊም ወጉኖቻችን ሁሉ ሕዝባዊ እቢተኝነቱን ለመቆጣጠር መነሣቱ አይቀርም፡፡በዚህን ወቅት ሕዝባዊ እቢተኝነቱ ወደ መንግሥታዊ ተቃውሞ ይሽጋገርና አገራዊ ቀወስን ሊቀሰቅስ ይችላል፡፡ለዚህ ደግሞ ምቹ የሚሆኑ ሕሊናዊ እና ነባራዊ ሁኔታዎች አሉ፡፡የመጀመሪያው ሕሊናዊ ሁኔታ በካህናቱም ሆነ በሕዝቡ ዘንድ ሥርዐቱ እንደ ፀረ ኦርቶዶክስ መታየቱ ሲሆን፤ሁለተኛው ደግሞ ሥርዐቱ የቤተ ክህነቱ ዋነኛ የለውጥ እንቅፋት ተደርጉ መወሰዱ ነው፡፡የኢትዮጵያውያን ሙስሊም ወገኖቻችን ተቃውሞ አርአያነት፤ ገዥው ፓርቲ በሃይማኖት ተቋማት የሚያካሄደው ጣልቃ ገብነት ለሕዝቡ ግልጽ መሆኑና ተቃዋሚ የፖለቲካ ቡድኖች ይህን አጀንዳ የማድረግ አዝማሚያዎችን ማሳየታቸው፤ሊንቀሳቀስ የሚችል ቅምጥ(potential) የጥምቀት ተመላሽ ወጣት ኀይል በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናቱ መኖር ደግሞ በነባራዊ ምቹ ሁኔታነት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ ይህ እየተካሄደው ካለው የሙስሊም ወገኖቻችን የተቃውሞ እንቅስቃሴላይ ሲታከል እና የሥርዐቱ አምባገነናዊ ምላሽ ሲጨመርበት ሁላችንም ወደ አልጠበቅነው ትርምስ ምናልባት ሊያመራ ይችላል፡፡ከዚህስ ይጠብቀን፡፡
የስድስተኛው ፓትርያርክ የምርጫ ሒደት ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው በመደብጨቱ የመንበረ ሐዋርያት ወራሽነትን ማጣታችን ከሐዋርያት ሥልጣነ ክህነት ወራሽነት እንድንነጠል ስለሚያደርገ የቤተ ክርስቲያናችን ክህነታዊ አገልግሎት አደጋ ላይ የመውደቁ ምልክቱ ነው፡፡እንደቀድሞዎቹ ዘመነ ፕትርክና ሁሉ የቀኖናዊ ውዝግብ መነሻ ሆኑ ከማገልገሉም በላይ በሒደት ከአኀት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያለንን ሐዋርያዊ ትስስርን ሊፈታው ይችላል፡፡ከዚህም በተጨማሪ ሢመተ ፕትርክና ከሐዋርያት ክህነት ምንጭ መቀዳቱ ይቀርና ከየሥርዐቱ ሹማምንት ወንበር ሥር በመደፋት የሚገኘ ምድራዊ ሥልጣን ያደርገዋል፡፡ይህ ደግሞ አስኬማ ጳጳሳትን በዘመናችን ቄሣራውያን መዳፍ ሥር የሚነትብ ተምኔት ከማድረጉ ጎን ለጎን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሥርዐቱ መለካዊ በማድረግ በጊዜ ሒደት እንዳያጠፋት ያሰጋል፡፡
መከተርያው ምን ይሆን ?
የችግሩን ተዛማችነት ማቆሚያው መንገድ መሠረቱ ኦርቶዶክሳዊ ብሔርተኝነት ሆኖ ዘርፉ አምስት ነው፡፡ የመጀመሪያው ለአለፉት ሃምሳ ዓመታት የተዳፈነው ኦርቶዶክሳዊ ብሔርተኝነት እንዲያሰራራ ማድረግ ነው፡፡የዚህ ጥቅሙ ሦስት ነው፡፡ጎጠኝነትንና ጥቅመኝነትን መሠረት ያደረጉ ልዬነቶችን በማክሰም ኦርቶዶክሳያዊ ትብብሮችነን ያጎለበታል፤በቤተ ክህነቱ እንደዋዘ የሚታዩትን የአድልዎ አሠራር-የአስተዳደር በደል-የገንዘብ ምዝበራ-አምባገነናዊ አመራር-የመንፈሳዊ እምነትና ግንኙነት መዳከምን ያርቃል፤ውጫዊ ተጽዕኖችንና ውስጣዊ ግፊቶችን ለመቋቋም ያስችላል፡፡ ሁለተኛው ያላንዳች ቅድመ ሁኔታ የምዕመናን ተወካዬችን ያካተተ የእርቀ ሠላም ድርደሩ እንዲጀመር ሕዝባዊ ንቅናቂዎች የሚጀመሩበትን ሁኔታዎችን ሊያመቻች የሚችል የተጠና አደረጃጀት መፈጠር፤ከተለያዬ ፍላጉታቸው በመነሣት እርቀ ሠላሙ እንዲፈርስ ያደረጉ አካላትን ያካተተ ውይይት አድርጉ በውይይቱ ፍጻሜ የሚደረስባቸውን ስምምነቶች ለእርቀ ሠላም ድርድሩ ውጤታማነት ግብዓት እንዲ ሆን ማስቻል፤
ሦስተኛው ሐምሌ 10 ቀን 1990 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲን ከተቋቋመ አጣሪ ኮሚሽን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባዔ የቀረበውን የተቋማዊ ለውጥ ማሻሻያ አሳቦችን፣የአቶ በድሉ አሰፋንና የአቶ ልዑል ሰገድ ግርማ የተቋማዊ ለውጥ ማሻሸያ ጥናቶችን ወቅታዊነትና ተገቢነት በባለሞያ ጥናት በማስደገፍ እና የተወሰኑ ማሻሸያዎችን በማድረግ በሥራ የሚውሉበትን ሆኔታ መፍጠር፤
አራተኛው ከተቻለ የስድስቱንም ፓትርያርኮች ካልሆነ ደግሞ የስድስተኛውን ፓትርያርክ የምርጫ አፈጻጸም ሒደት ቀኖናዊ ግድፈቶችን የሚያጣራ ገለልተኛ ኮሚሽን ተቋቁሞ ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሐዋርያዊ ሥልጣነ ክህነት የሚያረጋግጥ ውሳኔ መወሰን የሚያስችለውን የውሳኔ አሳብ እንዲያቀርብ ቢደረግ፤ አምስተኛው በአገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት ሃይማኖት በመንግሥት ጉዳዬች ያለመግባቱ የመረጋገጡን ያህል መንግሥት በሃይማኖታዊ ጉዳዬቻችን መግባት የማያስችለውን ተቋማ ነጻነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ርምጃዎችን መውሰድ ናቸው፡፡
የጨው ገደል …
አስቀድሚ ለመግለጽ እንደሞከርኩት ቤተ ክህነቱ እንደሆነ አሰኬማቸውን በቄሣራዉያን መዳፍ ሥር በጣሉ ጳጳሳት ታንቆ እያጣጣረ ይገኛል፡፡ግበዓተ መሬቱን ለማፋጠን ደግሞ የቄሣራውያኑ የጆሮ ምንደኞች ውሏቸው ሁሉ በፓትርያርኩ እና በጠቅላይ ጽ/ቤት ሆኗል፡፡ከዚህም አልፈው ለእገሌ ሹመት ሊሰጠው፤እገሌ ደግሞ ሊሻር ይገባዋል እስከማለት ደርሰዋል፡፡
እንደ እኔ እይታ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረታዊ ችግሮች ከአገሪቱ መሠረታዊ ችግሮች ተለይተው የሚታዬ አይደሉም፡፡አገሪቱ ላይ የምናየውን መዳሸቅና መጉሳቀል በጉልህ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ እናያለን፡፡የቤተ ክርስቲያኒቱን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት መጀመር ማለት የአገሪቱን ችግሮች መፍታት መጀመር ማለት ነው ብዬ አምናለው፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያሏት ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ለአገሪቱ ጸጋ የመሆናቸውን ያህል በቤተ ክህነቱ ተዘውትሮ የሚስተዋለው ብልሹ አሠራር፣ ምዝበራ፣ ጎጠኝነትንና ጥቅመኝነትን መሠረት ያደረጉ አድሏዊ አሠራሮቸና የቆብ አምባገነንነት አገሪቱን የሚፈቱ እርግማን ናቸው፡፡
ከዚህ አኳያ በቤተ ክርስቲያናችን በወቅታዊነት ያስተዋልናቸውን ችግሮች በተቀመጠው የመፍትሔ አቅጣጫ መሠረት ለመፍታት መጣር ከአገሪቱ የችግር ቁልል ከፍተኛውን መናድ ነውና ለተግባራዊነቱ ርብርብ እንድናደርግ ያስፈልጋል፡፡አለበለዚያ ግን“ የጨውገደል ሲናድ ሞኝ ይስቃል ”ዐይነት ይሆናል ነገራችን ሁሉ፡፡ከዚህ ይልቅ በያንስ እንኳ “ብልህ ያለቅሳል ” የሚለውን ሆነን እንድንገኝ አንድ ነገር ማድርግ አለብን፡፡

No comments:
Post a Comment