Thursday, 22 August 2013

በቄሣራውያን መዳፍ ሥር ያለ አስኬማ(ክፍል-1)

በታደሰ ወርቁ ከፌስ ቡክ ገጹ ላይ የተወሰደ


ይህ ጹሑፍ በእነ ተመስገን ደሳለኝ -ፋክት መጽሔት ላይ በሁለት ተከታታይ ክፍል የወጣ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛ ፓትርያርክ የነበሩት እና በአዛጋቢነታቸው የሚታወቁት ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ ጳውሎስ ቅጥ በአጣው አምባገነናዊነታቸው የተነሣ በቅጡ ሳይዘከሩና አስክሬናቸውም ያረፈበት ስፍራም ለመዓርጋቸውም ሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብር በማይመጥን መልክ በቆርቆሮ እንደታጠረ  እነሆ የሙት ዓመት መታሰቢያቸው ዋዜማ ላይ እንገኛለን፡፡                                                                                                ቅዱስነታቸው የሙት ዓመት መታሰቢያ ዋዜማ ላይ መሆናችንን ከተገነዘብን ሦስት መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሳታችን አይቀርም፡፡ የመጀመሪያው ተሰያሚው ፓትርያርክም ሆኑ ጳጳሳቱ ከአምስተኛው አወዛጋቢ ፓትርያርክና ከዘመነ ፕትርክናቸው ውድቀት ምን ተምረው ምን አደረጉ ? የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ  የቅዱስነታቸውን ሞት እንደ አንድ  ምቹ አጋጣሚ በመቁጠር በቀኖና ተጥሷል-አልተጣሰም ጭቅጭ የተነሣ የተከፈለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅራዊ አሐቲነት ለማከም ምንድ ተደርጉነው ውጤቱ እንዲህ የከፋው? የሚለው ነው፡፡  ሦስተኛው  ከአምስተኛው ፓትርያርክ ሞት በኃላ በእውንነታቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን  ወደ ቅድመ ግራኝ ክብሯና ልዕልናዋ  ይመልሷታል ተብለው ተስፋ  የተሰነቀባቸው የተቋማዊ ለውጥ  እንቕስቃሴዎች እና የፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊነት  ከየት ተነስተው በምን መልኩ ተደመደሙ  ? የሚለው ነው፡፡        
  ከእነዘህ ሦስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በመነሳት  ስንገመግምና አሁን እየሆነና እየተደረገ ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ተቀጥፋ ያልደረቀች  አበባን መስላለች፡፡ያውም አጥር ቅጥር የሌላትን፡፡የሚቀጥፏት ወጪዎቹና ወራጆቹ ጆቢራዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ወርቋን እንጂ የወርቁ መገኛ መሆኗን የዘነጉ ጳጳሳት መሆናቸው ደግሞ ነገሩን ግራ ያደርገዋል፡፡            
             ተቀጥፋ  እንዳትደርቅ  ተጨማሪ  አጥር ቅጥር ያበጃጁላታል ተብለው የተሾሙት  አበው ጳጳሳት አጥር ቅጥር መዝለላቸው ሳያንስ  ቀደምት አበው የሠሩትን  የእርቀ ሠላም ፣ዘመንን  የዋጀ ተቋማዊ  ለውጥና ሢመተ ፕትርክና  የሚመራበትን አጥር ቅጥር  አፍራሽ ኀይለ ግብር ሆነው ከመገለጣቸው በላይ ምን ግራ ያጋባል? ፡፡ 
ይህም ሆኖ አለመድረቋና በወርኃ ጽጌ እንደ አሉ አበባዎች ልምላሜ ሃይማኖትና መዐዛ ምግባር ከምዕመኑ አለመጥፋቱ እጅግ ይደንቃል፡፡ይህ የሆነው ግን    የሐዋርያት ውሳኔ በሆነው  በመጽሐፈ ዲድስቅልያለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ኤጴስ ቆጶስ ሆኖ  የሚሾመውየምዕመናን ጠባቂ፣ነውረ የሌለበት፣ንጹሕና ቸር፤ የዚህንም ዓለም ጭንቀት የማያስብ ፣፶ ዓመት የሞላው፣ የጉልማሳነትኀይልን ያለፈ፣ ነገር  የማይሠራ፣ በወንድሞች መካከል ሐሰትን  የማይናገር  ይሆን ዘንድ  እንደ ሚገባው በጌታችን ኢየሱስክርስቶስ ዘንድ ሰማን፡፡በሚለው አምላከዊ ድንጋጌ መሠረት የተሾሙ ወይም ሆነው የተገኙ ጳጳሳት  ሰላሉን  አይደለም፡፡ጌታ ሰለ ቃልኪዳኑ ሰለሚጠብቃትና የቀደምት አበውና እመት በረከተ ጥላ ከለላ ሰለሚሆናት ብቻ ነው፡፡/ዲድስቅልያ4 1 /                                                                                                                         
           ቀድሞም አብዛኛቹ  በዚህ ውሳኔ  መሠረት ባለመሾማቸው እና በኃላም መለካውያን-ፈጻሚ ፈቃድ ቄሣር ሆነው መገኘታቸው  ጵጵስናቸውን አስኬማ  መላእክት አለመሆኑን ከማጋለጡም  በላይ አስኬማ ቄሣር አድርገን እንድንወስድ አድርጉናል ፡፡                                                                                                                                    
የቤተ ክህነቱ የችግር ሰኮፍ ከነአቶ ስብሐት ነጋ ቢመዘዝም  እዚህ ጋ ብቻ ከአቶ ስብሐት ነጋ  አሳብ ጋር እንድስማማ እገደዳለው፡፡ይኸውም  እነርሱ መጥተው ተጣበቁብን  እንጂ እኛ መች  ሔድንባቸውከሚለው  ጋር፡፡ የአብዛኛዎቹ  ጳጳሳት  የነገር ማንጸሪያ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረት እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮ፣ቀኖናና ትውፊት ሳይሆን  ፈቃደ ቄሣር መሆኑ የአቶ ስብሐትን አሳብ ትክክል ያደርገዋል፡፡ሕገ ቤተ ክርስቲያን ምን ይላል? ከሚለው ይልቅ ቄሣራውያን ምን ይላሉ?የሚለው ቀልባቸውን በሚገዛ  ጳጳሳት በተወረረች ቤተ ክርስቲያን ሰለ እርቀ ሠላም፣ስለተቋማዊ  ለውጥና ሰለፓትርያርክ ምርጫ ውጤታማነት በራሱ ማሰብ አሰብኩ ፣አሰብኩናደከመኝ” እንዳለው ልጅ ነው ነገሩ ፡፡                                                                                                                                          
               
 እናም አሁን ባለው  ሆኔታ   ከቅዱስነታቸው ሞት በኃላ ተስፋ ያደርግናቸው እርቀ ሠላምየፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊነትና ነጻናመሠረተ ጠንካራ ማዊ ለውጥ ሙሉ በሙሉ  የመከኑ  ይመስላሉ፡፡ እንዴት እና በማን እንደመከኑ እስቲ በተጨባጭ እንመልከት፡፡      
 አስተዳደራዊ  አሐቲነት       ǃ                 
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን  በወልድ ዋሕድ መሠረትነትናነቢያትና ሐዋርያት ሰለወልድ ዋሕድ  በአስተማሩት ትምህርት ላይ  የታነፀች አንዲት ናት፡፡ምንጯ በአካል ሦስት  የሆነው አንድ እግዚአብሔር ነውና ፡፡ቤተ ክርስቲያን አንዲት ናት፡፡መሥራቿ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመሠረተው አንድ እንጂ ብዙ አይደለምና ፡፡/ማቴ 16/ 18/ቤተክርስቲያንአንዲት ናት፡፡የአንዱ መንፈሰ ቅዱስ ቤተ መቅደስ ናትና፡፡
ሊቁ ጎርጎርዮስ ዘዳቴሽ ”why the church  is one ?“ በተባለው  ጹሑፉ  የአሐቲነትን  ምንነት  ሲገልጽ” ቤተ ክርስቲያንአሐቲ የምትባለው በአንድ ቦታ ስላለች  ሳይሆን በመሠረተ እምነቷ፣ በተጠራችበት ተስፋና በእናትነቷ አሐቲነት ፤እንዲሁምከአንድ የጥምቀት ፏፏቴ በመወለዷ፣ በአንድ መለኮታዊ  መጻሕፍት ምግብነት፣በሥጋወደሙ አዳኝነት፣ በአንድ ራስናዘውድ በምናጌጥበት ልብስ ነው፡፡እርሱም ክርስቶስ ነው ፡፡በማለት ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን የአሐቲነት ባሕርያዊ ትስስርየ ተረጋገጠው ከሐዋርያት በተቀበልነው የእምነት ድንጋጌ፣ በምንፈማቸው ምስጢራትና በምስጢረ ክህነት በኩል በሚገኘ የሐዋርያት ወራሽነት ነው፡፡በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ወንድማዊ ስምምነትን ማንበር  የተቻለው  በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሠሪያየሆነውን ፍቅር ልበሱት በሚለው እና በሠላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ ፡፡በሚለው አንድ ተስፋን በመጋራት ነው፡፡/ቁላ3/ 4 ፣ኤፌ 4/ 4 /
ምንም እንኳን ክርስቲያኖች በአያሌ አስቸጋሪ ሁኔታዎች  ተከፋፍለው ቢታዩም  ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባሕርያዊ አሐቲነቷን-አንድነቷን በጭራሽ አታጣም፡፡ ይህም ሆኖ ግን ክርስቲያንኖች  ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ ሁሉም  አንድ ይሆኑ ዘንድ፤እኛም አንድእንደሆንን አንድ  ይሆኑ ዘንድ፤ ብሎ ለጸለየው ጸሎት በብቃት ምላሽ ለመስጠት መትጋት ይገባል፡፡ የተበጠስውን ትስስር ለመጠገን በመካካላችን አሐቲነት ያስፈልጋል፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኤፌሶን መልእክቱ“ … በአንድ ተስፋ  እንደ ተጠራችሁ  አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤አንድጌታ፣አንድ ሃይማኖት፣አንዲት ጥምቀት…   ”እንዲል ቅድስት   ቤተክርስቲያን    በመሠረተ እምነትና በሥርዐተ አምልኮ  አንዲት ናት፡፡/ኤፌ 4/ 4-6/ ነገረ መለኮታዊ አስተሳሰቦችን በመተግበና በመኖር አንዲት ናት ፡፡ስለዚህ  በየትኛውም ደረጃ ያለ ሰው ከዚህ አንድእምነት  ካፈነገጠ ከአንዲቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ተከታይነቱ ይቆረጣል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ግን በአንድ እምነቷ እንደጸናች ትኖራለች፡፡ይኸም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን  በተለያዬ አዝማናት በኑፋቄ ላይ ያካሔደቻቸውን  ቅዱሳን ጉባኤያትን ልብ ይሏል፡፡
በሃይማኖት ጸሎት ውሳኔያችንም  “…በቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡፡”    ስንልየቤተክርስቲያንን  ክህነታዊ ሚናዋንም ጭምር መናገራችን ነው፡፡ይህ ደግሞ መሪዎቿን ይገልጣል፡፡ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ  ይህን ሲተረጉሙ በሃይማኖት ጸሎት ውሳኔላይ ‹ቤተ ክርስቲን ሲል መሪዎቻቸውን ማለቱ ነው፡፡ብለዋል፡፡  በዚህ  መነሻነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ለሁለት ተከፈለች ስንል  የመሪዎቿን ወይም የአመራር አሐቲነቷ አጣች ማለታችን ነው እንጂ የመሠረተ እምነት፣ የሥርዐተ አምልኮና የትውፊት አሐቲነቷን  አይደለም፡፡እኔ እስከሚገባኝ በኢትዮጵያና በውጭ ባሉ አባቶች  መካከል  ያለው“የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ” ተጥሷል- አልተጣሰም ጭቅጭቅ የመሠረተ እምነት ፣ የሥርዐተ አምልኮና ትውፊትአሐቲነት ጉዳይአይደለም፡፡የእርቀ ሠላም ድርድሩም ውጤት እንዲያመጣልን የተጋነውም ይህንኑ የአመራር መዋቅራዊ አሐቲነት  ነበር ፡፡          
ይሁንና እርቅ ሠላሙ ያመጣዋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት መዋቅራዊ አሐቲነት መክኗል፡፡ እንደውም  ከድጡ ወደ ማጡ  እንደሚባለው ሆኗል፡፡ ይኸውም በሦስት ምክንያት ነው፡፡
የመጀመሪያው  ያልተሳካው የሢመተ ፕትርክና  ሕልመኝነት  ነው፡፡የዚህ ደዌ ሰለባ የሆኖት  በዋነኝነት  በኢትዮጵያ  ከሚገኙ አባቶች መካከል ቄብ ጳጳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ጥቂት ጳጳሳት በሁለቱ  ወገኖች እርቀ ሠላም መውረዱን አንድም  ብፁዕወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበር በመመለስ የፕትርክና ሕልመኝነታቸውን ወደ ቅዥት ይቀይራ ከሚል ስጋት፤ አንድም እርቀ ሠላሙ ከወረደ ተጨማሪ ተፋካካሪ አበውን  ማምጣቱን እነዚሁቄብ ጳጳሳት ለሕልመኝነታቸው  እንደ ስጋት ተመልክተው ሰለነበረ በቅድመ ሁኔታ እርቀ ሠላሙ የሚፈርስበትን ሴራ በመጉንጉናቸው አፍርሰውታል፡፡እነርሱም ያለሙበት ሳይደርሱ መንገድ ላይ ቀሩ፡፡ቤተ ክርስቲያኒቱንም ለባሕር ተሻጋሪው አባት እና ዙሪያቸውን እንደቅንቅን ሊወሩ ለተዘጋጁት የአባ ጳውሎስ ደንገጡሮች አስረክበው ወደ ቤታቸው ገብተዋል፡፡
ሁለተኛው የሢመት ጵጵስና ቅቡልነት ስጋት ነው፡፡ስጋቱ በጉልህ  የሚታይባቸው በዚህ ሃያ ዓመታት ውስጥ  በብፁዕወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ ዕድ በተሾሙት ብፁዓን አበው ላይ ነው፡፡ የእርቀ ሠላሙ መፈጸም በተለይም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበር በመመለስ የሚፈጸም ከሆነ የአምስተኛውን ፓትርያርክ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ዘመነ ፕትርክና ሕገ ወጥነት ያረጋግጣል ብለውም ያምናሉ፡፡ይኸ ደግሞ  በእርቸው አንብሮተ ዕድ የተሾምነውን ጳጳሳት ሢመት ሕጋዊ ቅቡልነት  ያሳጣዋል ከሚል ስጋት እነዚህ አባቶች ለእርቀ ሠላሙ ይሁንታቸውን  አልሰጡም፡፡ይህ የቅቡልነት ስጋት ከስጋትነቱም በላይ ስጉዋን አበው ኀብረታቸውን አጠናክረው እርቀ ሠላሙ ውጤታማ እንዳይሆን  እንዲሠሩ የመንግሥትና የቄብ ጳጳሳቱ የቅስቀሳ የስበት ማእከል(point of gravity) በመሆን አገልግሏል፡፡ 
  ቄሣራውያኑም ሆኖ አስኬማቸውን በቄሣራውያን  መዳፍ ሥር ያስቀመጡት ቄብ ጳጳሳት  በጋራ ስምምነት በሚወርድ እርቀ ሠላም የቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ አሐቲነትን ከማምጣት ውጪ የሢመተ ጵጵስና ቅቡልነት ስጋት ሊሆን እንደማይችል ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ሆኖም ግን እርቀ ሠላሙን ለማፍረስ ተጠቀሙበት፡፡   ሦስተኛው የእርቀ ሠላም ድርድሩ የቆመባቸው ስንጥሮች  ክትያ ነው፡፡ስንጥሮቹም ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት፣ሒደት አክፋፊዎችና የእርቀ ሠላም ኮሚቴው ሥዕለ ሕሊና ናቸው፡፡
ፖለቲካ ጣልቃ ገብነቱ  በድዮስጶራ የፖለቲካ ኀይል እና በገዥው ፓርቲ መጠነ ክበብ የሚገለጽ ነው ፡፡በድዮስጶራነት  ያሉ አበው ጳጳሳትን ማእከለ ቅቡል አድርጉ የሚኖረው የድዮስጶራ የፖለቲካ  ኀይል እርቀ ሠላሙን የደገፈ መስሎ ቢታይም በተግባር ግን የእርቀ ሠላሙን እውንነት  አይደግፍም፡፡ምክንያቱም አብዛዎቹ በድዮስጶራነት ባሉ አባቶች ሥር ያሉት አብያተ ክርስቲያናት የእነዚህ ፖለቲከኞች የሕዝባዊ ንቅናቄ ማእከላት ናቸው፡፡ገዥውን ፓርቲ ለመቃዎም ሕዝብ የሚደራጅባቸው እና የሚቀሳቀስባቸውም ነጻ መሬቶች  ናቸው፡፡                                                                                        ከዚህ አኳያ የእርቀ ሠላሙ መፈጸምና እርሱን ተከትሎ የሚመጣው መዋቅራዊ አሐቲነት የድዮስጶራውን የፖለቲካ ኀይል  ሕዝባዊ  መሠረት  በድዮስጶራነት ባሉ አባቶች ሥር ካሉ አብያተ ክርሰቲያናት መንቀሉ አይቀርም፡፡በእነዚህ አባቶች ሥር ያሉት አብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ በሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ሰለሚጠቃለሉ ገዥው ፓርቲ  ከእርቀ ሠላም በኃላ ያለውን ውሕድ መዋቅር በመጠቀም የቁጥጥር ሰንሰለቱን በመዘርጋት የድዮስጶራውን የፖለቲካ ኀይል ከሕዝባዊ ንቅናቄ ማእከላቱ ማስወጣቱ አይቀርም ፡፡የድስጶራው ፖለቲካ ኀይል ይህን በመረዳት እርቀ ሠላሙ  እንዳይሳካ በድዮስጶራነት ባሉት አባቶች ላይ ስልታዊ ጫና አሳድሯል፡፡ለዚህም የእነዚህን አበው መግለጫ እና የድርደር ነጥቦቻቸውን ማጤን  አባባሌን ትክክል ያደርገዋል፡፡                                                                                                                                                   የእርቀ ሠላሙን ድርደር በማፍረስ ረገድ ከድዮስጶራው ፖለቲካ ኀይል ይበልጥ በአገር ቤት  ያለውን ቅዱስ ሲኖዶስ የሕዝባዊ መሠረቱ መካነ ቅቡል አድርጉ የሚመለከተው ገዥው ፓርቲ የወቅቱን የቤተ ክህነቱን ቱባና ገላግለት ሹማምንት እጅ አድርጉየተጫወተው አሉታዊ ሚና  ምንም ጊዜ አይረሳም፡፡ገዥው ፓርቲ ለፖለቲካ መድረክ ፍጆታና ሕዝባዊ ተቀባይነትን ላለማጣት እርቀ ሠላሙን የደገፈ መስሎ ለመታየት ቢውተረተርም የእርቀ ሠላሙ አፍራሽ ስለመሆኑ በኃላ ላይ በወሰዳቸው ርምጃዎች አረጋግጧ፡፡ይኸውም የእርቀ ሠላምና የአንድነት ኮሚቴው አባል ከአገር እንዲባረሩ መደረጉ፣አፍቃሬ እርቀ ሠላም የሆኑ አባቶችና ወንድሞች  በብሔራዊ ደኀንነትና መረጃ አባላት ነን ባዬች  መዋከብና ለእርቀ ሠላሙ መፍረስ አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ ዘገባዎች በመንግሥታዊ ብዙኃን መገናኛዎች ሽፋን  እንዲያገኙ መደረጉ ተጠቃሽ ናቸው፡፡                          
 የመንግሥት የአፍራሽነት ሚናው  ምንጩ ባሕርየ ጠቅላይነቱ የወለደው ስጋት ነው፡፡ገዥው ፓርቲ  ከጳጳሳቱ መካከል ጥቂት ዐቃቤ ሕዋስ ቢኖሩትም  አብዛኛዎቹ ጳጳሳት  የሥርዐቱ  ‹ሽንፍ›  አለመሆናቸውን ይረዳል፡፡በጫና አስኬማቸውን  በእርሱ መዳፍ ሥር ያስቀመጡ  ቢበዙም በቅሬታ እንደሚኖሩ  ጠንቅቆ ያውቃል፡፡እነዚህ ቅሬታን አርግዘው የተቀመጡ አበው ለአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ከድዮስጶራ የፖለቲካ ኀይል ጋር ተጋብተው ከኖሩት  የድዮስጶራ አበው ጋራ ሲዋሕዶ  ምን ዐይነት ፖለቲካዊ አቋም  ሊወስዱ እንደሚችሉ  ሰለማይገመት በሚል ገዥው ፓርቲ እርቀ ሠላሙ የሚያመጣውን መዋቅራዊ አሓቲነት  በስጋት አምክኖታል፡፡                                                                                              
ይሁንና በእርቀ ሠላሙ ውጤት አልባነት ከገዥው ፓርቲ ይልቅ የድዮስጶራ የፖለቲካ ኀይል ተጠቃሚ ሲሆን ፤ከድዮስጶራ የፖለቲካ ኀይል ደግሞ ገዥው ፓርቲ ተጉጂ ሆኗል፡፡መሬት ላይ ባለው እውነታ የእርቀ ሠላሙ ውጤታማነት የሚያመጣው  መዋቅራዊ አሐቲነት የድዮስጶራ የፖለቲካ ኀይልን ከሕዝባዊ መሠረቶቹ ሲነቅል፤ገዥው ፓርቲ ፖለቲካዊ  የቁጥጥር ሰንሰለቱን ለአለፉት ሃያ ሁለት ዓመታት ወደ አጣባቸው) እንዲዘረጋ ያስችለው ነበር፡፡ሆኖም ግን ከፖለቲካ ስልት አኳያ የእርቀ ሠላሙ ድርድር መፍረስ ከድዮስጶራው የፖለቲካ ኀይል ይልቅ ለገዥው ፓርቲ የዜሮ ድምር ፖለቲካ  ከመሆኑም በላይ በጥላቻ የተለወሰ ቂልነቱን ያረጋገጠበት ክስተት ነበር፡፡                                                                                                                                                        
  የእርቀ ሠላሙ ሒደት አክፋፊዎች የቆሙበት ማእዘነ እይታም ከሦስት አካላት አንጻር ሲታይ የስንጥሩን ጫፍ ስለታማነት እንመለከታለን፡፡እነዚህም አካላት በቤተ ክርስቲያኒቱ አገልግሎት ውስጥ ንቁ ተሳታፌ የሆኑ እና በመንበረ  ፓትርያርክ እና በሀገረ ስብከት ደረጃ የተቋቋሙ ማኀበራትአመራሮች፣የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አመራር ፣የተለያየ አደረጃጀት ያላቸው ቡድኖችና የማኀበራቱም ሆነ የቡድኖቹ የአንድ ወቅት ፈለግ አስዋቢግልስቦች ናቸው፡፡                        
 የማኀበራቱ ጥቂት አመራሮችም ሆኑ የእነዚህ ማኀበራት የአንድ ወቅት ፈለግ አስዋቢዎች የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጥሷል- አልተጣሰም ውዝግብና ክትያውን(ለምሳሌ የድዮስጶራ አባቶች የፈጸሙት የጳጳሳት ሾመት)ተከትሎ የወሰዷቸው አቋሞች በወቅታዊው የእርቀ ሠላም ድርድር ላይ የወሰዶትን አቋም ምንነት ወስኖታል፡፡ሒደቱን ከቀደመው አቋማቸውና ከድርደሩ ክትያ(ከመጡ ችግር ሊፈጥሩብንይችላሉ ከሚል ስጋት)ጋር በማዛመድ በወሰዱት አቋም ለእርቀ ሠላሙ ስኬታማነት በጉ ሚና  ሲጫወቱ አልታዬም ፡፡                                                                                                    እንደውም በአንድ በኩል  ለሕዝባዊ ተቀባይነት “እርቀ ሠላሙን እደግፋለው“ እያሉ በሌላ በኩል ደግሞ የእርቀ ሠላሙን ሒደት በውስጠ  እያክፋፉ ድርድሩንከድጡ ወደ ማጡ እንዲሆን አድርገውታል፡፡እንደ ማኀበር ያላቸውን ተቀባይነት ከእርቀ ሠላሙ ይልቅ ለደበጨው ምርጫ ሲያውሉ፤ እንደ  ፈለግ አስዋቢ ግለሰብ ደግሞ ተደማጭነታቸውን ተጠቅመው የእርቀ ሠላም ድርድር ሒደቱን ለማደናቀፍ  ሸፍጥ ፈጽመዋል፡፡ይህም ሆኖ ግን የቋመጡለትን የፓትርያርክ ምርጫ ከመደብጨት ሲታደጉት ግን አልታዬም፡፡
ከእነዚህ አካላት ባልተናነሰ  የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አመራርም እርቀ ሠላሙ ያረፈበት ስንጥር ነበር፡፡በአንድነቱ ሥር ከታቀፉ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አባላት ብዛት ፣የተሐድሶ መናፍቃንን ለማስወገዝ ከአደረገው የአደባባይ ሰልፍና በቀላሉ ሕዝባዊ መሠረት ከመፍጠር አቅሙ አኳያ በእርቀ ሠላሙ ድርድር ውጤታማነት መጫወት የሚገባውን በጎ ሚና እንዲጫወትተጠላፊው አመራር አላበቃውም፡፡ይብስኑ “እርቀ ሠላሙን እደግፋለው ”ከሚለው አቋሙ ተንሸራቱ የምርጫው ሕጋዊ ቅቡልነት ትእምርት በመሆን እርቅ ከገፉት አካላት አንዱ ሆኗል፡፡                                                            የአንድነቱ  አመራር እንዲ ሆኖ የመልመጥመጡ  ምስጢር ሦስት ነው፡፡አንደኛ የአስተሳሰብ  ሞግዚቱ  የሆነው ማኀበር እርቀ ሠላሙን ሲደግፍ ዐለማየቱ፤ ሁለተኛ ከቅዱስ ሲኖዶስ  አገኘዋለው ብሎ የሚያስበው ዕውቅና  በሚያራምደው  አቋም የተነሣ እንዳይደናቀፍበት  ከመሥጋት ፤ሦስተኛ በወቅቱ ካድሬያዊነት የወለደው ልዬነት  በአንድነቱ አመራር መካከል መፈጠሩ ናቸው፡፡
ከዚሁ ጋር አብሮ መታየት የሚገባው ሌላው ስንጥር የድዬስጶራ  የተሐድሶ መናፍቃን ሕዋስ ነው፡፡የዚህ ሕዋስ ተጠርናፊ አባላት በድዮስጶራነት ያሉትን አበው ጳጳሳት የቅቡልነት ማእከል አድርጉ እየተጠቀመ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡በኢትዮጵያ ያሉት አባቶች በሃይማኖትና በሥርዐት ዐቃቤነት ዳተኝነት የምንወቅሳቸውን ያህል በድዮስጶራነት ያሉትንም አባቶች በተሐድሶውያን ወደብነት እንወቀሳለን፡፡                                                                                                     
   አብረዋቸው ያሉት ተሐድሶውያን የእርቀ ሠላሙ ድርድር  ውጤታማነት የሚያመጣውን አሐቲነት የደገፉ መስለው ለመታየት ቢውረገረጉም ፤ከጀርባ በመሆን በድዮስጶራነት ያሉት አበው ወደ መንበራችን እንመለስ ” የሚለውን አቋማቸውን አጠንክረው እንዲዙና እንዲገፉበት በማድረግ የእርቀ ሠላም ድርድሩን አፍርሰዋል ፡፡                                                                     
 የዚህ ምክንያት ሁለት ነው፡፡የመጀመሪያው ተሐድሶአዊ ባሕርያቸው ነው፡፡ይኸውም ሐዋርያዊትና አንዲት የተጠናከረች ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ሰለማይፈልጉ እና ቤተ ክርስቲያንን ለመረከብ ለዐቀዱት የረጅም ጊዜ ዕቅድ እንቅፋት ሰለሚሆንባቸው እርቁን በተግባር አይደግፉም፡፡ሁለተኛው የቅቡልነት እና ተጠቃሚነት ቦታ ላለማጣት ነው፡፡እነዚህ በድዮስጶራነት ያሉትን አባቶች ወድብ አድርገው የሚኖሩት  የተሐድሶ መናፍቃን ሕዋስ ተጠርናፊ በኑፋቄያቸው ከአገር ወጥተው በድዮስጶራነት ያሉትን አበው የሕጋዊነትና የተጠቃሚነት ማእከል አድርገው እየኖሩ ነው፡፡ስለዚህ የቅቡልነትና ተጠቃሚነት ወደብ የሆነውን አካል ላለማጣት ሲሉ የእርቀ ሠላሙን ድርድር ስልታዊ በሆነ መንገድ እንዲፈርስ የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ስምና ፊርማ ለኢትዮጵያው ቅዱስ ሲኖዶስ ከተጻፈው ደብዳበቤ በስተጀርባ ያሉትን  ተሐድሶውያን ልብ ይሏል፡፡                                                                                   
 በአፍቃሬ ተሐድሶ መናፍቃን ብሎጉች እንደተመለከትነው የእርቀ ሠለም ድርድሩን በፕሮቴስታዊ  ተሐድሶ መስመራዊነት ሕዝቡን ለማሰለፍ ሲጠቀሙበት ታይተዋል ፡፡የእነርሱ ፈቃድ ተጻባይ የሆኑ አካላትን ለማስጠላት በአጀንዳነት ከመጠቀም ውጭ  ተጨባጭ ድጋፍ ሲያደርጉም አልታዬም፡፡                                                                                          
ሌላው የእርቀ ሠላም ድርድሩ ያረፈበት ስንጥር  የሠላምና አንድነት ኮሚቴው የታየበት ሥዕለ ሕሊናና የተመዘዘበት ሽክርክሮሽ ነው፡፡የታየበትም  ሥዕለ ሕሊና የተለያየ ነው፡፡ገዥው ፓርቲ የድዮስጶራው የፖለቲካ ኀይል ተላላኪ አድርጎ ሲመለከተው፤ የድዮስጶራ አንዳንድ የፖለቲካ ኀይሎች ደግሞ የአንዳንድ የኮሚቴውን አባላት ሀገረ ሙላድ እየተመለከቱ የሕ.ወ.ኣ.ት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሰላይ አድርገው  ይገምቷቸዋል ፡፡የሁለቱም ተደራዳሪ አባቶች አፈ ቀላጤ ነን ባዬች ለአንዱ ተደራደሪ አካል ወገንተኛ አድርገው ሲመለከቱት፤የአእምሮ ጡረተኛ አማሳዬቹ ደግሞ ለአቅመ ሽምግልና ያልደረሱ ወጠጤዎች  አድርገው ይወስዷቸዋል፡፡አንዳንዶቹ ቄብ ጳጳሳት ደግሞ ከአንደንድ የሠላምና አንድነት ኮሚቴው አባላት ጋር ባላቸው የግል ቅራኔ የተነሣ በጥቅመኝነት ሲከሷቸው፤አንዳንዶቹ ቄብ ጳጳሳት ደግሞ ፓትርያርክ የመሆን ሕልም በወለደው  ቅዥት የተነሣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ወደ መንበር ለመመለስ ራሱን ያደራጀ ቡድን አድርገው ይከሱታል፡፡
እነዚህ አካላት ከላይ በገለጽነው አግባብ የፈጠሩት የተዛባ ሥዕለ ሕሊና(Image) ከተመዘዙበት  ሽክርክሮሽ ጋር ሲዳበል የሠላምናአንድነት ከሚቴውን የአደራዳሪነት ምንነት(essence) እና የእሴት መልክ(form of value) ቅርቃር ውስጥ  ከቶታል፡፡በመጨረሻም በአደራዳሪነቱ እንዳይቀጥል በማድረግ የእቀር ሠላሙ ድርድር እዲፈርስተደረገ፡፡                                                                                                                                                                                   
   ከላይ በዝርዝር የተመለከትናቸው የእርቀ ሠላሙ ድርድር ያረፈባቸው ስንጥር ክትያዎች(consequences) የተደራዳሪ አባቶችንም ሆነ የወከሏቸውን ቅን የሲኖዶስ አባላትን ልቡና ወግተው አድምተዋል፡፡በተግብሮት ደረጃም የእኛን እንዲሁ፡፡የደማ ልብ መቁሰሉ አይቀርም ፤የቁሰለ ልብ ደግሞ ለእርቀ ሠላም ዝግጁ ይሆናል ተብሎ አይጠበቅም ፡፡ይኸው የመቁሳሰሉ መንገድ በመመረጡ የቤተ ክርስቲያናችንን መዋቅራዊ አሐቲነት  ያመጣል ብለን ተስፋ ያደረግነው የእርቀ ሠላም ድርድር ባዱ ተስፋ እንዲሆን ተደረገ፡፡ 
ይቀጥላል  

No comments:

Post a Comment