Friday, 23 August 2013

በቄሣራውያን መዳፍ ሥር ያለ አስኬማ -ክፍል(2)

በታደሰ ወርቁ ከፌስ ቡክ ገጹ ላይ የተወሰደ


ቋማዊ ለውጥ (Institutional Reform) የተቋማዊ ቀውስ መድኀን የመሆኑን ያህል  ፤ውጤታማ ያለመሆኑም ተግብሮት የተቋማዊ ውድቀት አመክንዮም ነው፡፡የተቋማዊ ውድቀቱ አመክንዮም ተቋሙ ከቆመለት መሠረታዊ ግብ-ዓላማ-ተልእኮ ጋራ ሰለሚቆራኝ ክትያው ተቋማዊ ቁመናን አሳጥቶ የታሪክ ሽታ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ እንይኖረው ያደርጋል ፡፡ ከአምስተኛው ፓትርያርክ ሞት በኃላ በተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች ላይ ተስፋ ያደርግነው በአንድ ጀንበር የቤ ተክህነቱ ተቋማዊ የሞራል ዝቅጠት ፈውስ ያገኛል በሚል ሳይሆን የተቋማዊ ውድቀትን አመክንዮ ተግብሮት ቀድሞ ከመረዳት ነው፡፡ከዚህ አኳያ በቤተ ክህነቱ ላዕላይና ታህታይ መዋቅር መምጣት ያለበት ተቋማዊ ለውጥ በሁለት ዳርቻዎች ሊጠቃለል ይችላል፡፡በመጠን ለውጥ (Quantitative Change)እና በዐይነት ለውጥ (Qualitative Change)፡፡   

ባለፈው ዕትም  በዚሁ ርዕስ ከአምስተኛው ፓትርያርከ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎሰ ሞት በኃላ ተስፋ ያደርግነው በድዩስጶራነት በሚኖሩ አባቶች እና በቅዱስ ሲኖዶስ መካከል ሲደረግ የነበረው የእርቀ ሰላም ድርድር እንዴት እና በምን መልክ እንደመከነ በዝርዝር ተመልክተናል፡፡በዚህ ዕትም  የምንመለከታቸው ሁለት የመከኑ ተስፋዎችና ተግብሮታዊ ክትያዎቻቸውን እነሆ፡፡
የተቋማዊ ለውጥ ጅምሮች!                              

                                      

የትኛውም ለውጥ በመጠን  ለውጥ  ላይ የተመሠረተ  ወይም ከሱ እንደሚመነጭ የለውጥ ኀልዩት ያስረዳል፡፡ከቤተ ክህነቱ አኳያ የመጠን ለውጥ መምጣት አለበት ሲባል  ቤተ ክርሰቲያኒቱ የመሠረተ እምነት ፣የሥርዐት አምልኮና ትውፊት ለውጥ ሳታደርግ ፤እነዚህኑ ተቋማዊ ዓምዶቿን ከኢትዮጵያውያን መጠነ ክበብ ወደ ቀረውም ዓለም ማስፋትየሚያስችሏትን  ፖሊስዎች፣ስትራቴጂዎችና መዋቅራዊ አደረጃጀቶችን መፍጠር አለበት ማለት ነው፡፡                                                                       

 በሌላ በኩል ደግሞ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረትነት  በመሠረተ እምነቷ፣በሥርዐተ አምልኮዋና በትውፊቷ ላይ ቅሰጣ የሚፈጽሙትን ቡድኖችና ግለሰቦች አውግዞ መለየት የሚያስችል ብቁና ፈጣን ድርጅታዊ ድርጁነት መፍጠር መቻልም የመጠን ለውጥ አንዱ ዘርፍ ነው፡፡       
  

Thursday, 22 August 2013

በቄሣራውያን መዳፍ ሥር ያለ አስኬማ(ክፍል-1)

በታደሰ ወርቁ ከፌስ ቡክ ገጹ ላይ የተወሰደ


ይህ ጹሑፍ በእነ ተመስገን ደሳለኝ -ፋክት መጽሔት ላይ በሁለት ተከታታይ ክፍል የወጣ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አምስተኛ ፓትርያርክ የነበሩት እና በአዛጋቢነታቸው የሚታወቁት ብፁዕ ወቅዱስ  አቡነ ጳውሎስ ቅጥ በአጣው አምባገነናዊነታቸው የተነሣ በቅጡ ሳይዘከሩና አስክሬናቸውም ያረፈበት ስፍራም ለመዓርጋቸውም ሆነ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብር በማይመጥን መልክ በቆርቆሮ እንደታጠረ  እነሆ የሙት ዓመት መታሰቢያቸው ዋዜማ ላይ እንገኛለን፡፡                                                                                                ቅዱስነታቸው የሙት ዓመት መታሰቢያ ዋዜማ ላይ መሆናችንን ከተገነዘብን ሦስት መሠረታዊ ጥያቄዎችን ማንሳታችን አይቀርም፡፡ የመጀመሪያው ተሰያሚው ፓትርያርክም ሆኑ ጳጳሳቱ ከአምስተኛው አወዛጋቢ ፓትርያርክና ከዘመነ ፕትርክናቸው ውድቀት ምን ተምረው ምን አደረጉ ? የሚለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ  የቅዱስነታቸውን ሞት እንደ አንድ  ምቹ አጋጣሚ በመቁጠር በቀኖና ተጥሷል-አልተጣሰም ጭቅጭ የተነሣ የተከፈለውን የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅራዊ አሐቲነት ለማከም ምንድ ተደርጉነው ውጤቱ እንዲህ የከፋው? የሚለው ነው፡፡  ሦስተኛው  ከአምስተኛው ፓትርያርክ ሞት በኃላ በእውንነታቸው ቤተ ክርስቲያኒቱን  ወደ ቅድመ ግራኝ ክብሯና ልዕልናዋ  ይመልሷታል ተብለው ተስፋ  የተሰነቀባቸው የተቋማዊ ለውጥ  እንቕስቃሴዎች እና የፓትርያርክ ምርጫ ቀኖናዊነት  ከየት ተነስተው በምን መልኩ ተደመደሙ  ? የሚለው ነው፡፡        
  ከእነዘህ ሦስት መሠረታዊ ጥያቄዎች በመነሳት  ስንገመግምና አሁን እየሆነና እየተደረገ ባለው ሁኔታ የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ተቀጥፋ ያልደረቀች  አበባን መስላለች፡፡ያውም አጥር ቅጥር የሌላትን፡፡የሚቀጥፏት ወጪዎቹና ወራጆቹ ጆቢራዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ወርቋን እንጂ የወርቁ መገኛ መሆኗን የዘነጉ ጳጳሳት መሆናቸው ደግሞ ነገሩን ግራ ያደርገዋል፡፡            
             ተቀጥፋ  እንዳትደርቅ  ተጨማሪ  አጥር ቅጥር ያበጃጁላታል ተብለው የተሾሙት  አበው ጳጳሳት አጥር ቅጥር መዝለላቸው ሳያንስ  ቀደምት አበው የሠሩትን  የእርቀ ሠላም ፣ዘመንን  የዋጀ ተቋማዊ  ለውጥና ሢመተ ፕትርክና  የሚመራበትን አጥር ቅጥር  አፍራሽ ኀይለ ግብር ሆነው ከመገለጣቸው በላይ ምን ግራ ያጋባል? ፡፡ 
ይህም ሆኖ አለመድረቋና በወርኃ ጽጌ እንደ አሉ አበባዎች ልምላሜ ሃይማኖትና መዐዛ ምግባር ከምዕመኑ አለመጥፋቱ እጅግ ይደንቃል፡፡ይህ የሆነው ግን    የሐዋርያት ውሳኔ በሆነው  በመጽሐፈ ዲድስቅልያለአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ኤጴስ ቆጶስ ሆኖ  የሚሾመውየምዕመናን ጠባቂ፣ነውረ የሌለበት፣ንጹሕና ቸር፤ የዚህንም ዓለም ጭንቀት የማያስብ ፣፶ ዓመት የሞላው፣ የጉልማሳነትኀይልን ያለፈ፣ ነገር  የማይሠራ፣ በወንድሞች መካከል ሐሰትን  የማይናገር  ይሆን ዘንድ  እንደ ሚገባው በጌታችን ኢየሱስክርስቶስ ዘንድ ሰማን፡፡በሚለው አምላከዊ ድንጋጌ መሠረት የተሾሙ ወይም ሆነው የተገኙ ጳጳሳት  ሰላሉን  አይደለም፡፡ጌታ ሰለ ቃልኪዳኑ ሰለሚጠብቃትና የቀደምት አበውና እመት በረከተ ጥላ ከለላ ሰለሚሆናት ብቻ ነው፡፡/ዲድስቅልያ4 1 /                                                                                                                         
           ቀድሞም አብዛኛቹ  በዚህ ውሳኔ  መሠረት ባለመሾማቸው እና በኃላም መለካውያን-ፈጻሚ ፈቃድ ቄሣር ሆነው መገኘታቸው  ጵጵስናቸውን አስኬማ  መላእክት አለመሆኑን ከማጋለጡም  በላይ አስኬማ ቄሣር አድርገን እንድንወስድ አድርጉናል ፡፡                                                                                                                                    
የቤተ ክህነቱ የችግር ሰኮፍ ከነአቶ ስብሐት ነጋ ቢመዘዝም  እዚህ ጋ ብቻ ከአቶ ስብሐት ነጋ  አሳብ ጋር እንድስማማ እገደዳለው፡፡ይኸውም  እነርሱ መጥተው ተጣበቁብን  እንጂ እኛ መች  ሔድንባቸውከሚለው  ጋር፡፡ የአብዛኛዎቹ  ጳጳሳት  የነገር ማንጸሪያ የቤተ ክርስቲያኒቱ መሠረት እምነት፣ ሥርዐተ አምልኮ፣ቀኖናና ትውፊት ሳይሆን  ፈቃደ ቄሣር መሆኑ የአቶ ስብሐትን አሳብ ትክክል ያደርገዋል፡፡ሕገ ቤተ ክርስቲያን ምን ይላል? ከሚለው ይልቅ ቄሣራውያን ምን ይላሉ?የሚለው ቀልባቸውን በሚገዛ  ጳጳሳት በተወረረች ቤተ ክርስቲያን ሰለ እርቀ ሠላም፣ስለተቋማዊ  ለውጥና ሰለፓትርያርክ ምርጫ ውጤታማነት በራሱ ማሰብ አሰብኩ ፣አሰብኩናደከመኝ” እንዳለው ልጅ ነው ነገሩ ፡፡                                                                                                                                          

Wednesday, 14 August 2013

ሠለስቱ ደቂቅን ያዳናቸው ማን ነው ?

ሰኮናቸው ያልተሰነጠቀና የማያመሰኩ እንስሳት (የዘመናችን ተሐድሶዎች)(የመጨረሻ ክፍል)
 
ታዲያ ሠለስቱ ደቂቅን ያወጣቸው ማን ነው?ለሚለው የተሐድሶዎች ጥያቄ የቀረበ መልስ 


መጀመሪውንም መጽሐፍ ቅዱሱ ገብርኤል ነው አይልም፡፡ መጽሐፍ ቅዱሱ የሚለው የሚከተለውን ነው፤ ‹‹ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም፤ ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም፦ ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት። እርሱም፦ እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ ›› /ዳን 3 ፤ 24 -25/ ፡፡ በዚህ ገለጻ መሠረት አራተኛውን ያየው ንጉሡ ናቡከደነጾር ነው፡፡ እርሱም አየሁ ያለው አራተኛ ሰው ነው፡፡ የጨመረበት ቢኖር አራተኛው የአማልክትን ልጅ ይመስላል የሚለውን ነው፡፡ ለመሆኑ አራተኛውን ሰው እርሱ ብቻ ለምን አየ ? ሌሎቹ ለምን አላዩም ? አንደኛው የጥያቄው ቁልፍ ምስጢር ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ እውነቱን ለመናገር ይህ ሰው ጥንቱንም ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እሣት የጣለው ራሱን ምስል አቁሞ ለምስሉ ሕዝቡን በማሰገድ ራሱን አምላክ አድርጎ ሊያስመልክ ነበር፡፡ ታዲያ ራሱንና እርሱን የመሰሉትን አምላክ አድርጎ የሚቆጥር ከሆነ የሚያየውን አራተኛውን  ሰው ‹‹ የእኛን ልጅ ይመስላል ወይም እኛን ይመስላል›› ለምን አላለም? ከዚያ ይልቅ አርቆ ሌሎች አማልክትን የሚያመልክ አስመስሎ ‹‹ የአማልክትን ልጅ›› ይመስላል ያለበት ምስጢር ምንድን ነው ? ይህን ያለበት ምክንያቱ ያየው ነገር አራተኛው አካል ከህልውና ያለው በዘር በሩካቤ የተወለደ ሰው እነርሱ ሳያዩት እሳቱ ውስጥ ገብቶ ሳይሆን ነገሩ መገለጥ ስለሆነ ነው፡፡

ሰኮናቸው ያልተሰነጠቀና የማያመሰኩ እንስሳት (የዘመናችን ተሐድሶዎች)

ሠለስቱ ደቂቅን ያዳናቸው ማን ነው ለሚለው የተሐድሶዎች ጥያቄ የቀረበ መልስ

ሰሞኑን በተለይ በርከት ባሉት በመጽሐፈ ገጽ ወዳጆቼ በኩል  ‹‹ ሠለስቱ ደቂቅን ያዳናቸው ማን ነው? ›› የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ ቀርቦልኛል፡፡ በተሐድሶዎች በተሰራጨ አንድ የቪዲዮ ቁራጭ ላይ በሦስቱ ድርሳናት ማለትም በድርሳነ ገብርኤል ላይ ገብርኤል ፤ በድርሳነ ሚካኤል ላይ ሚካኤል ፤ በድርሳነ ራጉኤል ላይ ደግሞ ራጉኤል አዳናቸው ተብሎ ስለተገለጸ ትክክሉ የቱ ነው፤ በርግጥ ያዳናቸውስ ማን ነው የሚል ነው፡፡ በዚያም ጊዜ ሆነ ዛሬ ከአንዳንዶቹ መልእክት እንደተረዳሁት የድንጋጤ ስሜትም የተሰማቸው አሉ፡፡ ይህን ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶችንም ስመለከት ለጉዳዩ ቢያንስ አንዲት ትንሽ መጣጥፍ እንዳአቅሜ  እንኳ ለጊዜው መስጠት እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ጥያቄውን ለላካችሁልኝ ሁሉ ይህችን መቆያ እንካችሁ ብያለሁ፡፡ ዋናው ወይን ሁልጊዜም ወደ ኋላ መምጣቱ አይቀርምና እርሱን አብረን ከወይን አዳዩ እንጠብቃለን፡፡