- የደቀመዛሙርቱ አካዳሚክ፣ አስተዳደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄ ወደ ግለሰቦች ኃላፊነት ማስነሳት በሚል ቅድመ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡
- “ተቃውሞውን አስተባብረሃል” በሚል ታስሮ የነበረው ደቀመዝሙር ከእስር ትናንት ተፈትቷል፡፡
- የተሃድሶ ኑፋቄ አራማጅ የሆኑ ተማሪዎች ተቃውሞውን ኦርቶዶክሳውያንን ከኮሌጆ ቁልፍ ቦታ በማስወገድ በመናፍቃን ለመተካት በኅቡዕ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
(አንድ አድርገን መጋቢት 19 2005 ዓ.ም)፡- የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በኮሌጁ ስላለው የአስተዳደር ጉድለት ፣ የትምህርት ጥራት ማነስና የምግብ አቅርቦት ጥራት መጓደል ተቃውሟቸውን በትምህርት ማቆምና የረሃብ አድማ በማድረግ እየገለጹ ነው፡፡ በርካታ መገፋት ቤተክህነቱ እያደረሰባቸው የሚገኙት የነገረ መለኮት ምሩቃንና ደቀ መዛሙርት ያቀረቡት ተቃውሞ የቤተክህነቱን አስተዳደረዊና መንፈሳዊ ድቀት ርቀት እንደ ማሳያ ተደርጎ ተወስዶአል፡፡