የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለቀጣይ ዘመናት የሚመራውን አባት የመምረጡ ታላቅ ሥራ ቅዱስ ሲኖዶሱን ከገጠሙት የዘመናችን ተግዳሮቶች ዋናው ነው፡፡ ይህንን ተልዕኮ ከተግዳሮቶቹ ሁሉ ዋናው የሚያደርጉት አራት ምክንያቶች ናቸው፡፡
የመጀመርያው በአራተኛውና በአምስተኛው ፓትርያርኮች መካከል በተደረገው ሽግግር በተፈጠሩ ወቅታዊና ቀኖናዊ ጉዳዮች ምክንያት ቤተ ክርስቲያኒቱ በታሪኳ ለመጀመርያ ጊዜ ሁለት ‹ሲኖዶሶችን› ያስተናገደችበት ዘመን ላይ የሚደረግ ምርጫ መሆኑ ነው፡፡ በሀገር ቤትና በውጭ ባሉት አባቶች መካከል እየተከናወነ ባለው የዕርቀ ሰላም ሂደት ውስጥ ዛሬም በሕይወት ያሉት የአራተኛው ፓትርያርክ ዕጣ ፈንታ ቀጣዩን የቤተ ክርስቲያኒቱን ሰላማዊና መንፈሳዊ ብሎም ቀኖናዊ ጉዞ የሚወስነው ይሆናል፡፡ ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድም አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበር ትመልሳለች፣ ያለበለዚያም አራተኛውን በጸሎት ወስና በእንደራሴ ትቀጥላለች፣ ያለበለዚያም ስድስተኛውን ትመርጣለች፡፡
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ኅብረተሰቡ የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ በንቃትና በቅርበት በሚከታተልበት ጊዜ የሚከናወን ሂደት መሆኑ ነው፡፡ ከዚህ በፊት የተደረጉት የፓትርያርክ ምርጫዎች የሕዝብን በቂ ክትትል ለማግኘት ዕድል አልነበራቸውም፡፡ በአንድ በኩል የመገናኛ አውታሮች እንደልባቸው ያለመሆን፣ በሌላም በኩል ሕዝባችን አስቀድሶ ከመሄድ ባለፈ የቤተ ክህነቱን ጉዳይ ለቤተ ክህነት ሰዎች ብቻ የተወበት ዘመን ስለነበር ምርጫዎቹ የሕዝብን በቂ ትኩረት አላገኙም ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ የስብከተ ወንጌል መስፋፋቱና የቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ የሚዘግቡ ሚዲያዎች መብዛት የፓትርያርክ ምርጫው ጉዳይ ትኩረት እንዲኖረው አድርጓል፡፡ በመረጃ መረብ እንኳን ስለ ቤተ ክርስቲያኒቱ የሚዘግቡ 26 ብሎጎችና ከስድስት በላይ ድረ ገጾች አሉ፡፡
ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ባለፉት ፓትርያርክ ዘመን የተሠሩና ከቤተ ክርስቲያኒቱ ማንነት፣ ትምህርትና ደረጃ ጋር የማይሄዱ ተግባራት ለሕዝብ ይፋ ሲሆኑ መቆየታቸውና ማኅበረሰቡ የስድስተኛው ፓትርያርክን ምርጫ ያለፉት ችግሮች የማይደገሙበት እንዲሆን መፈለጉ ነው፡፡ በጳጳሳት ምርጫ፣ በአስተዳዳሪዎች ሹመት፣ በገንዘብ ምዝበራ፣ የቤተ ክህነቱ በወይዛዝርት ተጽዕኖ ሥር መውደቅ፣ በስብከተ ወንጌል መድረኩ ላይ ይሰሙ የነበሩት ሌሎች ድምጾች፣ የሐውልት መሠራት፣ በየቦታው ይነሡ ለነበሩ ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት አለመፈለግ፣ የአንዳንድ አባቶች ባልተጠበቀና ባልታሰበ ሁኔታ ማለፍ፣ ወዘተ ሕዝቡ በቤተ ክህነቱ ላይ እንዲያመርር አድርጎታል፡፡ ቀጣዩ ፓትርያርክ እነዚህን ችግሮች የሚያርሙና የሕዝቡን የተሰበረ ልብ የሚጠግኑ እንዲሆኑ የመፈለግ ከፍተኛ ጉጉት አለ፡፡
አራተኛው ምክንያት ይህ ሂደት በተለያዩ አካላት ግፊትና ተጽዕኖ እየደረሰበት ያለ መሆኑ ነው፡፡ ከሰሞኑ እንደሚሰማው ራሳቸውን በየጎራው ያደራጁ አካላት እነርሱ የሚፈልጉትን አባት ለማስመረጥ በሲኖዶሱ ላይ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ፖለቲካን፣ ዘርንና ጥቅምን አንድ አድርገው የተቧደኑት እነዚህ አካላት ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅመውን ሳይሆን ለእነርሱ የሚጠቅማቸውን አባት ለማምጣት ያስኬዱናል ያሏቸውን ነገሮች ሁሉ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ በአንድ በኩል ተራው የኛ ነው የሚሉ፣ በሌላ በኩል ሙስናውና ዘረፋው እንዲቀጥል የሚፈልጉ፣ በሌላም በኩል ‹በስሜ ይመጣሉ› እንደተባለው በመንግሥት ስም የሚነግዱ ኃይሎች ምርጫውን በሚፈልጉት መንገድ ለመጠምዘዝ በመትጋት ላይ መሆናቸውን የቤተ ክህነቱ ምንጮች እያመለከቱ ነው፡፡
እነዚህ ሁሉ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ቀጣዩ የፓትርያርክ ‹ምርጫ› ሦስት ነገሮችን የሚያሟላ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት የሚያስጠበቅ፣ ያለፉትን ችግሮች ለመፍታት መንገድ የሚከፍት እና የሕዝቡን አመኔታ የሚያገኝ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ ሲያስብ የመጀመርያው ነገር ምርጫው የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት የሚያስጠብቅ እንዲሆን ማስቻል ነው፡፡ ችግሩ ከተፈጠረ ሃያ አንድ ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በዚህ መካከል ችግሮች ሲፈጠሩ በአካል የነበሩት፣ ጉዳዩን የሚያውቁትና የጉዳዩም ዋና ዋና ተዋንያን በሞት እየተነጠቁ በመሄድ ላይ ናቸው፡፡
ከሁለቱ ዋና ዋና አካላት መካከል አምስተኛው ፓትርያርክ ዐርፈዋል፣ አራተኛው ፓትርያርክም በጤና እክል ላይ ናቸው፡፡ ከችግሩ መፈጠር በኋላ ዐቃቤ መንበር የነበሩት አቡነ ዜና ማርቆስ ዐርፈዋል፤ ችግሩ ሲፈጠር ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ታምራት ላይኔ ሌላ መሥመር ውስጥ ገብተዋል፣ በዚያ ወቅት ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ መለስም (ነፍሳቸውን ይማርና) አርፈዋል፡፡ ከወዲህ ወገንም በዚያ ዘመን ከነበሩት አበው መካከል ቢያንስ ወደ ስምንት የሚጠጉት ዐርፈዋል፤ በወዲያ በኩልም አቡነ መልከ ጼዴቅና አቡነ ኤልያስ አርጅተዋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ ወቅት የተሻለ ችግሩን የመፍቻ ጊዜ አይኖርም፡፡ የኬልቄዶንን ጉባኤ ችግሮች ለመፍታት በዓለም ዐቀፍ ደረጅ ከሃምሳ በላይ ጉባኤያት በየዘመናቱ ተካሂደዋል፡፡ ችግሩን በመፍታት ረገድ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ፍላጎቱ ቢኖርም ሦስት ምክንያቶች ግን እንቅፋት ሆነዋል፡፡ የመጀመርያው ስለ ጉባኤው የተጻፉት መረጃዎች በየወገኑ የተጻፉ መሆናቸው፤ ሁለተኛው ችግሩ በ450 ዓም ከተፈጠረ በኋላ 1600 ዓመታት ማለፋቸውና ጉዳዩ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ታሪክ፣ ጸሎት፣ ሥዕል፣ ገድላትና ድርሳናት ውስጥ የገቡ በመሆናቸው እነዚያን ሁሉ ዶክመንቶች እንደገና መከለሱ ከባድ መሆኑ፣ ከዚያም በላይ ደግሞ ውግዘቱን ያወገዙት አበው ዛሬ በዐጸደ ነፍስ በመሆናቸው የእነርሱን ውግዘት ማንሣቱ አስቸጋሪ መሆኑ ናቸው፡፡
ነገሮች በጊዜያቸው ካልተፈቱና ባለቤቶቹ ዐልፈው መዛግብቶቹ ብቻ ከቀሩ ነገሮችን ወደ መጀመርያቸው ሁናቴ መመለስ በተለይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከባድ መሆኑን ጉባኤ ኬልቄዶን አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ለዚህም ነው በጉዳዩ የነበሩበት አካላት ፈጽመው ከመለየታቸው በፊት፣ ችግሩም ወደ ሁለተኛ ትውልድ ከመሻገሩ በፊት ሳይርቅ በቅርቡ፣ ሳይደርቅ በርጥቡ ችግሩን መፍታቱ ከምንም የተሻለ የሚሆነው፡፡
በርግጥ ይህ ሂደት ሁለት ነገሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በአንድ በኩል በሚደረገው የዕርቅና የአንድነት ሂደት የሚስማሙትንና በተከፈተው በር ለመግባት ፈቃደኛ የሆኑትን ተቀብሎ ለሁሉም በሚስማማ፣ ይበልጥም ቤተ ክርስቲያንን በሚጠቅም መንገድ ችግሩን መፍታት፤ በዚህ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍም ሆነ ከሂደቱ በተቃራኒው ለመጓዝ የሚሹትን አካላትም ‹እንደ አረማዊና ቀራጭ ይሁንልህ› በሚለው መሠረት በውግዘት መለየት ናቸው፡፡
ሲኖዶሱ የሚደርሱበትን ተጽዕኖዎች መቋቋም ካሉበት ምክንያቶች አንዱም ለዚህ ሀገራዊም፣ ታሪካዊም፣ ቀኖናዊም ነገር ሲል ነው፡፡ ዕርቅና ሰላም ሁለት ነገር ይጠይቃል፤ ጊዜና ቻይነት፡፡ ሲኖዶሱም ይህንን ታሪካዊ ሥራ ለመሥራት ጊዜና ቻይነት ያስፈልገዋል፡፡ ከየአቅጣጫው ተጽዕኖዎች ይኖራሉ፡፡ በዕርቁ ቤተ ክርስቲያን እንደ ምትጠቀመው ሁሉ በዕርቁ ጥቅማቸው የሚነካ አካላትም ይኖራሉ፡፡ ስለዚህም ትንንሾቹን ሥዕሎች ሳይሆን ትልቁን ሥዕል በማየት የሚከፈለውን መሥዋዕትነት ከፍሎ ችግሩን ለመፍታት መትጋት ይኖርበታል፡፡
በአንድ በኩል የተጽዕኖዎቹ መኖር መልካም ነው፡፡ ተጋድሎ ማሸነፍን፣ በአስጨናቂ ሁኔታዎች ውስጥ መሥራትንና ፈተናን ማለፍን እንማርበታለን፡፡ ችግሮች ላወቀባቸው አስተማሪዎች ናቸው፡፡ ማጠናከርያዎች ናቸው፣ የበረከት ምንጮችም ናቸው፡፡
የቀጣዩ ፓትርያርክ ምርጫ አንድን አባት ከአባቶች መካከል መምረጥ ብቻ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ የቤተ ክርስቲያን ያለፉት ችግሮችን የሚፈታ፣ በቀጣይም ለራሱና ለሀገር ዕድገት የሚሠራ ቤተ ክህነትን ለማየት የሚያስችለን መሆን አለበት፡፡ የቤተ ክህነቱ አሠራር ከሀገሪቱ አሠራሮች ሁሉ ወደ ኋላ የቀረ አሠራር ነው፡፡ ቀበሌዎች እንኳን ያገኙትን የመዋቅርና የሥራ ሂደት ማሻሻያዎችን ቤተ ክህነቱ አላገኘም፡፡ በመሆኑም ሲኖዶሱ ገለልተኛ በሆነ አማካሪ ድርጅት የቤተ ክህነቱን አጠቃላይ አሠራርና አወቃቀር ፣ የሰው ኃይልና የእዝ ሠንሠለት እንዲያጠና ቢደረግ አሁን ሀገሪቱ ለደረሰችበት ዕድገት የሚመጥን አወቃቀርና አሠራርን መዘርጋት ይገባል፡፡ የቤተ ክህነቱ አሠራር ካልተጠናና ካልተስተካከለ ምንም ዓይነት ብቁና ቅዱስ አባት መምረጥና ማስቀመጡ ‹በእሾህ መካከል የተዘራ ዘር› ይሆናል፡፡
ባለፉት ዘመናት የተደረጉት የፓትርያርክ ምርጫዎች ጉምጉምታ የሚሰማባቸው እንደነበሩ በየዘመናቱ የተጻፉ መዛግብትና በዘመኑ የታዘቡ ሰዎች ግምገማዎች ያሳያሉ፡፡ በቅዳሴያችን ላይ ‹እነዚህን ሁለቱን አባቶች በዘመናችን ተቀብለናቸዋል› ይላል፡፡ ይህንንም ብሎ የፓትርያርኩንና የሀገረ ስብከቱን ጳጳስ ስሞች ያነሣል፡፡ ይህ ነጥብ የሚያሳየን ነገር አለው፡፡ ሕዝቡ ‹ይደልዎ› ሊል እንደሚገባ፡፡
በሕዝብ ዘንድ ተአማኒነትና ተቀባይነት ያለው ምርጫ የሚከተሉትን ነገሮች የሚያሟላ ምርጫ ነው፡፡
- መንፈሳዊነትን የተላበሰ ምርጫ፡- መንፈሳዊ ምርጫ መንፈሳዊ ደረጃውን የጠበቀ ከሆነ ሕዝብ ይቀበለዋል፡፡ እኔን ምረጡኝ የሚል ፖለቲካ ያልገባበት፣ እገሌን ምረጡ የሚል ጫና ያልተቀላቀለበት፣ ከእገሌ ዘር ይመረጥ የሚል ሥጋ ያልተጨመረበት፣ በትኁት ሰብእናና ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅመውን ብቻ በመሥራት ላይ ከተመሠረተ ሕዝብ ይቀበለዋል፡ ሂደቱ በጸሎትና በጾም ከታጀበ፣ አባቶች ከእኔ ወንድሜ ይሻላል ካሉ፣ እግዚአብሔር እንዲመራ ቦታውን ከሰጡ ሕዝብ ይቀበለዋል፤
- ቀኖና የጠበቀ ከሆነ፡- በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የጳጳሳትንና የፓትርያርኮችን ምርጫ፣ መመዘኛና አሠራር የሚደነገጉ አያሌ ቀኖናት አሉ፡፡ እነዚህ ቀኖናት በመንፈስ ቅዱስ በተመሩ አባቶች የተሠሩ በመሆናቸው ችግን በመከላከልና ከተከሰተም በመፍታት ረገድ ወሳኝ ናቸው፡፡ በመሆኑም ሂደቱ በቤተ ክርስቲያን የተደነገጉትን እነዚህን ቀኖናት የጠበቀ ከሆነ የሕዝብን ታማኝነትና ተቀባይነት ያገኛል፤
- ግልጽ ከሆነ፡- እያንዳንዱ ሂደት ዝርዝር አሠራር የተቀመጠለት፣ መመዘኛዎቹ የሚታወቁ፣ አንድ ነገር ለምን እንደተደረገ የሚታወቅበት መንገድ ካለው፣ ከየት ተነሥቶ የት እንደሚደርስ መንገዱ ከተለየ ሕዝብ ሂደቱንም ውጤቱንም ይቀበለዋል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ወቅት ከሚጠበቁበት ነገሮች አንዱ ግልጽ ዕቅድ አውጥቶ ለሕዝብ ግልጽ ማድረግና ውጤቱንም በየጊዜው መግለጥ ነው፡፡ የሚሰጡ መግለጫዎች ሌላውን የሚገልጡ መሆን አለባቸው እንጂ እነርሱ ራሳቸው ሌላ መግለጫ የሚያስፈልጋቸው ቅኔዎች መሆን የለባቸውም፤
- አሳታፊ ከሆነ፡- የሚከናወነው ተግባር የቤተ ክርስቲያን ተግባር ነው፡፡ የሃምሳ አራት ጳጳሳት ተግባር ብቻ አይደለም፡፡ የሚመረጠው አባት ከ45 ሚሊዮን በላይ የሆነውን ምእመን የሚመራ እንጂ ጥቂት የቤተ ክህነት አካላትን ብቻ የሚያስተዳደር አይደለም፡፡ በመሆኑም ምእመናኑ በግልጽ መሳተፍ፣ ድምፃቸውን መስማት፣ ሃሳባቸውን መቀበልና ተረድቶ ማስረዳት ይገባል፡፡ እስካሁን ለምሳሌ ከአድባራት አስተዳዳሪዎች እንጂ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሂደት አስተዋጽዖ ከሚያደርጉ ምእመናንና ምእመናት ጋር ውይይት አልተደረገም፡፡ በዚህ ምክንያት ሐሜትና ወሬ የሕዝቡ የመረጃ ምንጮች እንዲሆኑ ተፈርዷል፡፡ ሲኖዶሱ ሲሆን ከየሀገረ ስብከቱ ተወክለው ከሚመጡ፣ ካልተቻለም በአዲስ አበባና በዙርያዋ ካሉ ታላላቅ ሽማግሌዎች ጋር ሂደቱን በተመለከተ መመካከር ይገባዋል፡፡ ‹ምእመን ለገንዘቡ ብቻ› የሚባልበት ዘመን ያለፈ ይመስለኛል፡፡
ለዚህ ነው ‹ሲኖዶሱ ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም› ያልኩት፡፡ እነዚያን ተግዳሮቶች ተቋቁሞ፣ እነዚህን ተግባራት ለማከናወን ‹ረዳት› ያስፈልገዋል፡፡ የሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ የምሁራን፣ የምእመናንና የሌሎችም በጎ አሳቢ አካላት ርዳታ ያስፈልገዋል፡፡ ሲኖዶሱም ብቻውን መሆኑ መልካም አለመሆኑን ዐውቆ የሚመለከታቸውን ባለ ድርሻዎች በመጋበዝ አብሮ መሥራት፣ ባለ ድርሻዎችም እስኪጋበዙ ሳይጠብቁ ቀርቦ ማገዝ ‹ከሚመጣው ቁጣ› ሁሉንም ያድናል፡፡
እነዚህ ሁሉ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ቀጣዩ የፓትርያርክ ‹ምርጫ› ሦስት ነገሮችን የሚያሟላ እንዲሆን ይጠበቃል፡፡
የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት የሚያስጠበቅ፣ ያለፉትን ችግሮች ለመፍታት መንገድ የሚከፍት እና የሕዝቡን አመኔታ የሚያገኝ፡፡
ሲኖዶሱ ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም›
i agree with ur idea dani . all of us should pray .God have a means for any obstacle .let us .........pray pray pray pls pls pls pls ....................
"ቤተ ክርስቲያኒቱ አንድም አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበር ትመልሳለች፣ ያለበለዚያም አራተኛውን በጸሎት ወስና በእንደራሴ ትቀጥላለች፣ ያለበለዚያም ስድስተኛውን ትመርጣለች፡፡"
The last option we have is chosing the 6th patriach. Here Daniels message, we have to conduct the election very carefully. I strongly agree with him. We should learn from history, we should seek for a best solution for the sake of the church.
To make history I believe you and me and others should have to buried our feelings and guide literatures, if we feel they are in wrong direction. But this literature in my opinion it is genuine. What we should not forget is that as a person dn daniel has the wright to appreciate the election. The home work to you and me is to debate with him on our ideas. Personally some scarification should be done to end the split.
God Bless Ur Life,
"ለፍቅርና ለመልካምም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በርሳችን እንተያይ፤
በአንዳንዶችም ዘንድ ልማድ እንደ ሆነው፥ መሰብሰባችንን አንተው እርስ በርሳችን እንመካከር እንጂ፤ ይልቁንም ቀኑ ሲቀርብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።" እብ 10፡24-25 so sinodos and the Christan people working together the day is this day ምእመን ለገንዘቡ ብቻ› this word is making dislike the church father and sinodos "እምነትና በጎ ሕሊና ይኑርህ፥ አንዳንዶች ሕሊናን ጥለው፥ መርከብ አለ መሪ እንደሚጠፋ፥ በእምነት ነገር ጠፍተዋልና፤" the sinodos and the church father must be give respect to the followers people "
I dont know how to win the hearts and minds of the people around the church.Something has to be done .Information is the first thing .We are divided on different issues.
"ሲኖዶሱ ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም"
God bless Ethiopia !!!
ግን ከአብሮት ጋር ፥ምዕመን ለገንዘብ ብቻ የሚባልበት ዘመን ያለፈ ይመስለኛል፥ የምትለዋ ሃረግ ትንሽ ትከብዳለች፡ ምክንያቱም በተለይ በውጪ ሃገር በምትገኘው ቤተ ክርስትያን ትልቅ ችግር የፈጠረው ይህ አይነት አባባል ነው፡ ደሞዝ የምንከፍላቸው እኛ ነን ካህኑ ተቀጣሪ ነው እኛ የምንፈልገው ነገር ብቻ ይሁንልን ያ ነገር የቤተ ክርስትያንን ስርዓት ጠበቀ አልጠበቀ ጉዳያቸው ያልሆነበት ቦታዎች በብዛት አሉ ለዛ ነው ትከብዳለች ያልኩት። ለቤተ ክርስትያን ስጦታ መስጠት፣ ስዕለት፤ መባእ፤ አስራት በኩራትን ማውጣት ክርስቲያናዊ ግዴታ ይመስለኛል፤ በወንጌሉም የታዘዘ ነውና። ከዛ ውጪ ከትምክህት በጸዳ መልኩ ቤተ ክርስትያኗን በሚያሳድግና በሚጠቅም መልኩ መሳተፉ ተገቢና መልካም ነው። ገንዘብ ስለሰጠ ሳይሆን የተዋህዶ ልጅ በመሆኑ። ይሄን ሁሉ ልል የወደድኩት ፥ ‹ምእመን ለገንዘቡ ብቻ የሚባልበት ዘመን ያለፈ ይመስለኛል። የምትለዋ ሃረግ እዚህ በውጪ ሃገር ትልቅ ችግር እየፈጠረች ስለሆነ ነው። እግዚአብሄር አምላክ ከአባቶቻችን ስብሰባ የእርቅና የሰላም ዜና እንድንሰማ ያብቃን። አሜን
ሁላችንም የቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳይ ሊመለከተንና ልንሳተፍበት ይገባል፡፡
"በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ። የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው።" 2ኛ ቆሮንቶስ ምዕራፍ 11:27-28
Any ways I would like to extend my heartfelt gratitude to the effort you are making towards the peaceful return of our church as it was in the very ancient times where real people of God leading it with full spirituality and the power of God bestowed to them to do so.
May the Grace of Jesus Christ, The Love of God and The Fellowship of His Holy Spirit be with you All, Amen?