ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት?
ማውጫ፦ ምልከታ
- ቅዱስነታቸው ስለ ራሳቸው እና ስለ ፕትርክናው ሊናገሩ ይገባቸዋል።
(ደጀ ሰላም፤ ነሐሴ 25/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 31/ 2012/READ THIS ARTICLE IN PDF)፦ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስአርፈው መንበረ ፕትርክናው ባዶ ከሆነ እነሆ ቀናት ተቆጠሩ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ባለው ሥልጣን መሠረት ተተኪው ፓትርያርክ እስከሚሰየም ድረስ “አቃቤ መንበረ ፓትርያርክ” ይሆኑ ዘንድ ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሰይሟል። ቤተ ክርስቲያኒቱ 5ኛውን ፓትርያርኳን በሐዘን እያሰበች ባለችበት በአሁኑ ወቅት “ቀጣዩ ማን ነው?” የሚለው ጥያቄ በስፋት በመጠየቅ ላይ ይገኛል። ድምጻቸው ቀላል ያልሆኑ ኦርቶዶክሳውያንም “እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ሊሰጥ ዕድል ከፍቶልን ሳለ፣ የቀደሙትን አራተኛውን ፓትርያርክ ወደ መንበራቸው መመለስ ሲገባ የምን አዲስ ምርጫ ነው?” እያሉ ነው። ለደጀ ሰላም የደረሱ ብዙ መልእክቶችም ይህንን በማበከር ላይ ይገኛሉ። በዚህ አጋጣሚ “ደጀ ሰላም” አንድ ሁነኛ ጥያቄ ማቅረብ ትፈልጋለች። የቀድሞው ፓትርያርክ አቡነ መርቆርዮስ የት ነዎት? ድምጽዎትን ለምን አንሰማም? ሐሳብዎን ለምን አይገልጹም? ከምዕመኖችዎ ጋር በቱርጁማን፣ በስማ በለው፣ በተላላኪ፣ በሦስተኛ ወገን መነጋገር መቼ ነው የሚያበቃው ለማለት እንወዳለን። አንባብያንም ሐሳባችሁን እንድታካፍሉን እንጋብዛለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን፡፡
No comments:
Post a Comment