Tuesday, 21 August 2012

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሞት ተከትሎ የከሚሴ የጦር መሳሪያ ግምዣ ቤት በውሀቢያ ሙስሊም አክራሪዎች ተዘረፈ


·        "We are very glad about Meles' death. Ethiopia is sure to collapse,"Sheikh Ali Mohamud Rage, the spokesman for Al Shabaab told Reuters.

(አንድ አድርገን ነሐሴ 15 2004 ዓ.ም)፡- ቀናት አልፈው ቀናት ሲተኩ የሚሰማው እና የሚታየው ነገር ማህበረሰቡን እያስገረመው መጥቷል ፤ አዲስ ቀን በመጣ ቁጥር አዲስ ነገር ጠባቂ ጆሮዎች ተበራክተዋል ፤  አሁን የሰማው ግን አስደንጋጭ  ነው ፤ ሀገሪቱ በአሁኑ ሰዓት መተንፈስ እስኪሳናት ድረስ ውጥረት ውስጥ ገብታለች ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት ፤ የፓትርያርኩ ዜና እረፍት እና ቀጣይ ከመንግስት እጅ ነጻ የሆነ የፓትርያርክ ምርጫ ፤ የተለያዩ ባለስልጣናት የጤና መታወክ ፤ በሙስሊም ማህበረሰቦች ዘንድ የተነሳው የመጅሊስ 



ይውረድ ጥያቄ ፤ ጥያቄውን መሰረት በማድረግ መንግስት ያሰራቸው የሙስሊም ተወካዮች ፤ ሞያሌ አካባቢ የተነሳው ከ30 ሺህ ሰዎች በላይ ወደ ጎረቤት ሃገር የተሰደዱበት የጎሳ ግጭት ፤ በአዲስ አበባ አንዋር መስኪድ ውስጥ በየጊዜው የሚነሳው ተቃውሞ ፤ በየቦታው ጊዜ የሚጠብቁ የታፈኑ የመብት ጥያቄዎች ፤ በይበልጥ በዋልድባ ገዳም ተፋጠው ያሉት የአካባቢው ምዕመናን እና የመንግስት ወታደሮች ሀገሪቱ ወደ የት እየሄደች መሆኑ  አመላካች ምልክቶች ናቸው ፡፡ 

በቅርቡ በአንዋር መስኪድ በተነሳው ተቃውሞ ምክንያት በእለተ ቅዳሜ ከ700 በላይ ሰዎች በአዲስ አበባ እና በፌደራል ፖሊስ አባላት አማካኝነት መታፈሳቸው እና የይቅርታ ሰነዱን ፈርመው መውጣታቸው ይታወቃል ፤ ይህ እንዲህ እያለ ሙስሊም ማህበረሰብን ወክለው ከመንግስት ጋር ሲነጋገሩ የነበሩ 18 የሚያህሉ መሪዎቻቸው በፖሊስ ተይዘው ፍርድ ቤት ከቀረቡ በኋላ የ28 ቀን የምርመራ ጊዜ ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቆ ዳግም ወደ እስር ቤት መልሷቸዋል፡፡ 

አሁን ግን ከወደ ከሚሴ የተሰማው ዜና በአካባቢው የሚገኝን የመንግስት የጦር መሳሪያ ግምዣ ቤት ሙሉ በሙሉ በአካባቢው አክረሪ ሙስሊም ማህበረሰብ በተለይ ውሀቢዝምን የሚያቀነቅኑ ወጣቶች እንደተዘረፈ መረጃው ደርሶናል ፤ እዚህ አካባቢ ያለ የአክራሪነት እንቅስቃሴ ጠንካራ መሰረት እንዳለው ይታወቃል ፤ ለዓመታት በፊት ወደ ጊሸን ማርያም ሲጓዙ የነበሩ ምዕመናን ላይ እነዚህው ወጣት ውሀቢያ እንቅስቃሴ አራማጆች የተኮስ እሩምታ ማውረዳቸው ይታወቃል ፤ ሲጀመር ከዓመት በፊት መንግስት ውሃቢዝምን በተመለከተ በርካታ መረጃዎች እጁ ውስጥ እያሉት በጊዜው እርምጃ መውሰድ ሳይችል ቀርቶ ጉዳዩን እዚህ ደረጃ እንዲደርስ የበኩሉን አስተዋጽዎ አድርጓል ፤ ይህ ማለት ሀገሪቱ ያለችበትን ያለመረጋጋት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከሳምንታት ወይም ከወራት በኋላ በአካባቢው ምን አይነት ነገር ሊፈጠር እንደሚችል አመላካች ምልክት ነው ፤ አክራሪዎቹ አሁን ያለውንም ክፍተት ለመጠቀም ያሰቡ ይመስላሉ ፤ አሁን መሳሪያ ያነገተ የተቃውሞ ኃይል አማካኝነት መብታችንን እናስከብራለን በማለት በቅርባቸው የሚገኝውን የጦር መሳሪያ ግምጃ ቤት ዘርፈዋል ፤ መሳሪያ የታጠቀ የውሀቢዝም ሰራዊት በመላ ሀገሪቱ ለመነሳት እያኮበኮበ የሚገኝበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ፤ በዚህ መሀል መጀመሪያ ተጎጂዎች ከደሙ ንጹህ የሆኑ ዜጎች መሆናቸው አይቀሬ ነው ፤ አንድ መሳሪያ 30 ጥይት የመጉረስ አቅም አለው ፤ በአንድ ሰው አማካኝነት የብዙዎችን ነፍስ ሊነጥቁ መሳሪያዎችን አንድም ሳይቀር ዘርፈው ወስደዋል ፤ ይህ ጉዳይ መንግስት አንደኛ ለራሱ ህልውና ሲል ሁለተኛ ደግሞ ለሰላማዊው ህዝብ ብሎ የተዘረፈውን መሳሪያ ለቅሞ መመለስ ካልቻለ አደጋው ወደፊት እየሰፋና ከቁጥጥሩ ውጪ ሊሆን ይችላል፡፡

 አሁንም ጊዜው አልረፈደም ከዓመታት በፊት ቤተክርስትያኖች ላይ ሲፈጸም የነበረው ጉዳት አሁን በመሳሪያ በታጠቁ ሰዎች አማካኝነት ዳግም እንደማይፈጸም ምንም ማረጋገጫ የለንም ፤ ይህ የተዘረፈው መሳሪያ ወደ ስራ ካስገቡት የበርካቶችን ደም የሚፈስበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል ፤ የሀገሪቷ ሰላም ሊያናጋ ይችላል ፤ ሰዎች በሰላም ወጥተው በሰላም እንዳይገቡ እንቅፋት ሊፈጥር ይችላል ፤ እንደ አልሻባብ አይነት ሃይማኖትን መሰረት ያደረጉ ቡድኖች እንዲያድጉ እና ወደ ተሻለ ጥቃት የመፈጸም አቅማቸውን ሊያሳድግላቸው ይችላል ፤ በዚህ መሀል የመጀመሪያ ተጎጂዎች ከመንግስት ተቋማት ቀጥሎ በየአካባቢው የሚገኙ አብያተክርስትያናት እና ክርስትና እምነት ተከታዮች መሆናቸው አይቀሬ ነው ፤ ይህ መሳሪያ መጀመሪያ መንግስትን ለመቃወም እንደ ግብአት ሊጠቀሙበት ይችላሉ ፤ የመጀመሪያ አላማቸው ከተሳካለቸው ሁለተኛ ዓላማቸውን ለመገመት አያዳግትም ፤ ከሁለት ዓመት በፊት በአንድ ለሊት “አላህ ዋክበር” እያሉ በአንድ መሳሪያ 38 ቤተክርስትያኖች የተቃጡበት በርካቶችን ያፈናቀሉበት ድርጊት ትዝ ሊለን ይገባል ፤ የዚህ ሁሉ ማስረጃ በእጁ እያለ ሰዎችን ለማስተማር መንግስት የሄደበት መንገድ አሁን አላስፈላጊ ዋጋ ሊያስከፍለው ይችላል ፤ በጅማ አካባቢ ጉዳት ያደረሱት አክራሪዎች የእያንዳንዳቸው መረጃ  ቀርቦ ሳለ ህጉን ከማስፈጸም ይልቅ ትምህርት በመስጠት ብቻ የተለቀቁ በርካቶች ናቸው ፤ ተምሮ የሚቀየር ሰው እንዳለ ሁላ የወንዝ ድንጋይ የሆነ እድሜ ልኩን ውሃ ቢፈስበት ወደ ውስጡ የማይዘልቅ ጭንቅላት ያላቸው ፍጹም ጨለምተኛ አመለካከት የተጠናወታቸው ሰዎች በውስጣቸው እንዳሉ መንግስት አላስተዋለም ፤ ሁሉም ሙስሊም አክራሪ ነው አንልም ነገር ግን እምነቱን ሽፋን በማድረግ ሌላ አላማ ለማሳካት የሚንቀሳሱ ቡድኖች መኖራቸው ግን የማይታበይ ሀቅ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ለሁሉም አደጋ ነው፡፡ መንግስት ያስብበት ፤ ሰላማችን በዋጋ የማንለውጠው ትልቁ ሀብታችን ነው፡፡

(ሁኔታውን ተከታትለን እናንተው ዘንድ እናቀርባለን)
ቸር ያሰማን    

MOGADISHU (Reuters) - Somali Islamist militants hailed on Tuesday the death of Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi as an "historic day" and said Ethiopia, which has troops inside Somalia, would now crumble.
"We are very glad about Meles' death. Ethiopia is sure to collapse," Sheikh Ali Mohamud Rage, the spokesman for Al Shabaab told Reuters.
Meles twice rolled his troops across the border to help crush Islamist insurgencies.
(Reporting by Feisal Omar; Editing by Richard Lough and Jon Hemming)

No comments:

Post a Comment